#STEMPower #TikvahEthiopia
ስቴም ፖወር ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ግቢ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ላለፉት 7 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የወጣቶች የመጀመሪያ ደረጃ የአቅም ግንባታ ሥልጠና የምርቃትና የማበረታቻ መርሐግብር በትላንትናው ዕለት ተከናውኗል።
ሥልጠናውን ለመውሰድ 2,289 ወጣቶች የተመዘገቡ ሲሆን 578 ወጣቶች በስልጠናው ተካፍለዋል (ቢያንስ የስልጠናውን አንዱን ክፍል ወስደዋል።
ከሰልጣኞቹ 60% የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 40% የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
በዕለቱ ከ5 ቀናት በላይ የተሰጡ ስልጠናዎችን የተከታተሉ ሰልጣኞች ከስቴም ፖወርና ከቲክቫህ የተዘጋጀላቸውን ሰርተፊኬት የወሰዱ ሲሆን ሌሎች ሰልጣኞች ዲጂታል ሰርተፊኬት የሚደርሳቸው ይሆናል።
በመርሐግብሩ ላይ በስቴም ፖወር፣ ቪዛና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትብብር በተሰጡ ስልጠናዎች አልፈው የራሳቸውን ድርጅት የመሰረቱትና በፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩት ውጆ አፕ (Wujo App) ለተመራቂዎች ሥራቸውን አስተዋውቀው አስመርቀዋል።
በቀጣይ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሥልጠናዎችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
@tikvahethiopia

January 1,2023
የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠርን የሚከተሉት እጅግ በርካታ የዓለማችን ሀገራት አዲሱን 2023 ዓመት ተቀብለዋል።
አዲሱን ዓመት 2023 ከተቀበሉ ሀገራት መካከል ጎረቤት ሀገር ኬንያ ፣ ግብፅ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም ፣ ህንድ ፣ ፓኪስታን ፣ አይቮሪ ኮስት እጅግ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
ከዓለማችን ሀገራት መካከል የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ያላት #ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሲሆን ሀገራችን የአውሮፓውያን ቀን አቆጣጠርን አትጠቀምም።
የ13 ወራት ፀጋ ባለቤቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት የዘመን አቆጣጠሯ መለየቱ ብቻ ሳይሆን የራሷ የሆኑ ባህሎች፣ ቋንቋዎች ፣ ፊደል፣ ጥበብ ያለባት ሀገር ናት።

#ETHIOPIA
ከሰሞኑን የፌዴራሉ መንግስት የ #ሰላም_ስምምነቱን በተመለከተ ከ50 በላይ ለማሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።
ማብራሪያውን ከሰጡት መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ነበሩ።
በወቅቱ ፤ የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን አቅርበው ነበር።
ምን ተጠየቀ ? ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?
- ስለወልቃይት ባለቤትነት፣
- ስለኤርትራ ወታደሮች፣
- ስለሰላም ስምምነቱ ግልጽነትና የመረጃ አሰጣጥ፣
- ስለሰላም ስምምነቱ ተደራዳሪዎች ጥያቄዎች ቀርበው ነበር።
የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (የኢሶዴፓ) ምክትል ፕሬዚዳንት ራሔል ባፌ (ዶ/ር) ፦
" ከወልቃይት ጋር እየተነሳ ያለው ጉዳይ፣ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የባህር በር ስታጣ በሌላ በኩል ደግሞ ወልቃይትን በመቀማት አገሪቱ ከሌላ አገር ጋር እንዳትገናኝ ለመዝጋት የተደረገ እንቅስቃሴ በመሆኑ መንግሥት ጉዳዩን እንዴት እየተከታተለው ነው ? "
የኢዜማ ተወካይ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) ፦
" በሰላም ስምምነቱ ትግራይ ክልል ከአማራና ከአፋር ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ስምምነቱ ምን ይላል ? በዚህ የተዳፈነ እሳት ላይ የታሰበ ነገር ካለ ቢነገረን ? "
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አመራር አባል አቶ ሙላቱ ገመቹ ፦
" የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል አልፎ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው። መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ ? "
የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሰይፈ ሥላሴ አያሌው (ዶ/ር) ፦
" የሰላም ስምምነት ለአገር ተሰፋ የፈነጠቀ ቢሆንም፣ ድርድሩ ሲካሄድ የተሳተፉ የብልፅግና እና የሕወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ቅሬታ ፈጥሮብናል።
በጦርነቱ ውስጥ ዋነኛ ሰለባና ገፈት ቀማሽ የነበሩት የአማራና የአፋር ክልሎች ሕዝቦች ለምን እንዲሳተፉ አልተደረገም ?
በተጨማሪም እየተከናወኑ ያሉ ውይይቶችና ድርድሮች ለሕዝብ እየተነገሩ አይደለም።
ሲዋጋ፣ ሲሞትና ሲቆስል የነበረው ሕዝብ በመጨረሻ ስለተደረሰበት ስምምነት መንግሥት መረጃ ሊሰጠው የገባል።
ከአራት ዓመት በፊት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከነበረበት ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ሲደረግ መንግሥት ፈጸምኳቸው ያላቸውን ስምምነቶች በርካታ ቢሆኑም፣ ለሕዝብ ግልጽ ሳይደረጉ አሁን የሚታየው ጥፋት ተከስቷል። "
የጠ/ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን ምላሽ ሰጡ ?
አምባደር ሬድዋን ሁሴን ፦
ወልቃይት ...
" የወልቃይት ጉዳይ በ #ሕገ_መንግሥቱ መሠረት ይፈታል።
ከጅምሩ የጦርነቱ ዓላማ ወልቃይትን ማስመለስ እና ሕወሓትን ማጥፋት አልነበረም።
የጦርነቱ ዋና ዓላማ የነበረው የአገሪቱን ሉዓላዊነት ማስከበርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ማስፈን ነው
ሕወሓትን እንደ ፖለቲካ ኃይል የማጥፋት ዓላማ ያለው ሰው ይኖራል፣ ነገር ግን የፌዴራል መንግሥቱ ዓላማ አይደለም።
ወልቃይት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል ያለ ፀብ ነው፣ በሁለት ክልሎች መካከል ያለው ፀብ ደግሞ የሚፈታው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚመራው ሥርዓት።
የፌዴራል መንግሥት አቋም ተራ በተራ ጡንቻ እየተፈታተን አንዳችን ሌላችንን ማንበርከክ ይቁም የሚል ነው።
ወልቃይትን ከዚህ ቀደም ሕወሓት ጡንቻ ስለነበረው በጉልበት ወስዷል፣ አሁን ደግሞ ሕወሓት ሸብረክ ሲል ጡንቻ ያለው አካል ይውሰድ ካልን መጪው ትውልድ 20 ዓመታትን ጠብቆ ድንገት ጡንቻ ካገኘ ይወስደዋል ፤ ስለዚህም ዘላቂው መፍትሔ ጡንቻ ሳይሆን ሕግና ሥርዓት ነው።
አንድ ሰው ትግራይን ሲወድ ካርታውን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ነው፣ ነገር ግን ካርታውን ወዶ ሕዝቡን መጥላት አይቻልም።
ቲፎዞና ደም መርጠን መለቃቀስ ይቅር፣ የትም ቦታ ሰው ሲሞት ሁላችንም ሊሰማን ይገባል። "
ኤትራን በተመለከተ ...
" የእኛ ወገን ናቸው የምንላቸው የሕወሓት ሰዎች ለ30 ዓመታት ታገልኩለት ያሉትን ሕዝብ ለ30 ዓመታት እየቀለበ፣ እየጠበቀ፣ አብሮ እየሠራና እያረሰ የኖረውን ሠራዊት ከጀርባው አርደው ሜዳ ላይ ሲጥሉት የታደጉት እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ውለታን መርሳት ነውር ነው።
በሦስተኛው ዙር አገሪቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለማፍረስ በተካሄደው ጦርነት የፌዴራል መንግሥት በቆቦ በኩል ባለው ዳገት ወደ ላይ መውጣት ላዳገተው፣ ሕወሓት ያለውን መልክዓ ምድራዊ ጠቀሜታ ተጠቅሞ ቆቦን ተቆጣጥሮ ነበር።
ወቅቱ ክረምት ስለነበር በምዕራብ በኩል ተከዜን ሠራዊቱ ማቋረጥ ባለመቻሉ ፣ #በዛላምበሳ እና #በአዲግራት ለመምጣት ተከዜን መሻገር የኤርትራ መንግሥት በመፍቀዱ ጦርነቱ ሊቀለበስ ችሏል።
ለአጭር ጊዜም ቢሆን በራቸውን ባይፈቅዱልን ኖሮ ይኼንን ጦርነት መቀልበስ አይቻልም ነበር፡፡ እንደ አገር ከባድ ፈተና ውስጥ እንወድቅ ነበር።
የኤርትራ መንግሥት ይኼን ያደረገው ሕወሓት በዚያ ጊዜ የጋራ ጠላታችን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሕወሓት የጋራ ጠላት የሚሆነው ትጥቁን እስኪፈታ ነው። ትጥቁ ከሌለ አደጋ አይሆንም።
በፖለቲካ መጠላላት እና መለያየት ሲኖር ያለ ሦስተኛ ወገን በራችንን ዘግተን መነጋገር እንችላለን። "
የኤርትራ ሰራዊት ጉዳይ ...
" ' የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ይውጣ ' የሚሉት አካላት ለኢትዮጵያ አዝነው አይደለም። ኤርትራ ይውጣ የሚሉ አካላት ሱዳን 50 ኪሎ ሜትር አልፎ ድንበር ወሮ በነበረበት ወቅት አፋቸውን ዘግተው ነበር።
በተመሳሳይ #ግብፅ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ መድባ ወደ ኢትዮጵያ መሣሪያ እያስገባች በጋምቤላ ለኦነግ ሸኔና ለሕወሓት ጭምር በአየር እና መሬት ላይ ስታስታጥቅ፣ እነዚህ ምንም አላሉም ፤ ይህ የሚያሳየው መንግሥትን የሚያዳክም ሲሆን ዝምታ፣ መንግሥትን የሚያግዝ ሲሆን ደግሞ ጩኸት ማብዛት የሚወዱ በመኖራቸው ነው።
በመሆኑም ኤርትራ እኛን አስቸገረን ካላልን ምን አሳሰባቸው ? ኤርትራ ባስቸገረን ጊዜ እኛ ራሳችን በቃን እንላለን፡፡
የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ካሳሰባችሁ ሱዳን ትውጣ ብላችሁ መግለጫ አውጡ፡፡ ከዚያ ኤርትራ ትውጣ ብትሉ እኛ መረዳት እችላለን።
በሌላ በኩል በእኛ አስታኮ የኤርትራ መንግሥትን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም፡፡ ቢያንስ ከተፈጠረው የሰላም ስምምነት አንፃር እኛ እንዳንፈርስ አግዘውናል፡፡
የጋራ ጠላት የነበረን ቢሆንም ትጥቁን የፈታ የሕወሓት ታጣቂ ግን ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ አቅማችን ባለበት እስኪጠናከር ሕወሓት መጀመሪያ ትጥቁን መፍታት ይጀምርና እንደማንወጋ ስናረጋግጥ፣ ከጀርባችን ያለው አካል ማንም ይሁን ማን ይውጣልን ማለት እንችላለን። "
ምንጭ፦ www.ethiopiareporter.com

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጤና ሚኒስቴር፤ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ለመደበኛ አገልግሎት #በኮንትራት ተቀጥረው የነበሩ የጤና ባለሙያዎችን በተመከለተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ከመግለጫው የተወሰደ፦ " የባለሙያዎቹ ኮንትራት ለ6 ዙር (በአጠቃላይ ለሶስት አመት) በየ6 ወሩ በተደጋጋሚ እየታደሰ እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን ካለዉ የሀብት ዉስንነትና የወረርሽኙ ትርጉም ባለዉ ደረጃ መቀነስ ጋር ተያይዞ በዚህ ወረርሽኝ…
የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ማህበር የኮቪድ-19 ኮንትራት ተቀጣሪዎችን በተመለከተ ካወጣው መግለጫ ፦
" በቅርቡ ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ 19 የኮንትራት ተቀጣሪዎች ላይ የወሰደዉ አላግባብ ከስራ የማሰናበት እርምጃ ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባር መሆኑን ማህበሩ ያምናል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አለምን በአስጨነቀበት በዛ ወቅት ለአንድ ህይወታቸዉ ሳይሳሱ ፣ እጅግ አስቸጋሪዉን የስራ ሁኔታ ተቋቁመዉ ወረርሽኙን ግንባር ቀደም ሁነዉ የተፋለሙ ጤና ባለሙያዎች የጀግና ሽልማት መሸለም ሲገባቸዉ ሃላፊነት በጎደለዉ መልኩ ከስራ ገበታቸዉ መባረራቸዉን የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በፅኑ ይቃወማል።
ድርጊቱ በድጋሚ ታይቶ የእርምት እርምጃ እንዲሰጠዉ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ይጠይቃል።
ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የኮቪድ 19 የሶስት አመት ያህል የኮንትራት ተቀጣሪዎችን በሚመለከት የሰጠዉ መግለጫም የጤና ባለሙያዎችን አሁናዊ ሁኔታ ያላገናዘበና ጤና ባለሙያዎችን በበላይነት ከሚያስተዳድር ተቋም የማይጠበቅ ተግባር ነው። "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

በተጋጋሚ የታረመው /edit/ የተደረገው የመንግስት ሰራተኛው ህልፈተ ህይወት !
የአብክመ መሬት ቢሮ ባልደረባ የሆነ ወጣት ባየ በዛ ትናንት ምሸት ታህሳስ 22/2015 ባህር ዳር ውስጥ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የሰራተኛውን ህልፈት በተመለከተ ግን የሚሰራበት ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያሰራጨው መረጃ አወዛጋቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ቢሮው በቅድሚያ ባልደረባው " ባልታወቀ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ብሎ የገለፀ ሲሆን በኃላ ቆየት ብሎ " ባልታወቁ አካላት ጥቃት በደረሰበት ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ሲል አስተካክሏል።
ቆየት ብሎ ቢሮው ባልደረባው "በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " ብሏል። ከዚህ ማስተካከያ በኃላም " የትራፊክ አድራሹ መሰወሩን ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ባህር ዳር 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብሏል።
በ45 ደቂቃዎች በፊት ደግሞ በአስተያት መስጫው ላይ ቢሮው ባልደረባው በትራፊክ አደጋ መሞቱን አረጋግጣለሁ ሲል ፅፏል።
በመጨረሻም ቢሮው መረጃውን ከገፁ ላይ ሙሉ በሙሉ አጥፍቶታል።
እንዴት አንድ ተቋም የራሱ የባልደረባውን ህልፈት በተመለከት አጠራጣሪ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ለህዝብ ያሰራጫል ?

#TikvahFamily በትላንትናው ዕለት የ2ኛው ዙር የመማሪያ መፅሀፍትና ቁሳቁስ የማሰባሰብ ዘመቻ መካሄድ ጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር በጥቂት ቀናት 7 ሺህ በላይ መፅሀፍትና 3 ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር መሰብሰቡና በአማራ ክልልና በደቡብ ክልል ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ በአዲስ አበባ ላለ የህዝብ ቤተመፅሀፍ መከፋፈሉ ይታወሳል። በዚህኛው ዙር በመፅሀፍት ደረጃ ከ30 ሺህ በላይ ለመሰብሰብ ታስቧል። በዚህ ዙር…
#ምስጋና
በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም)
ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል።
የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው።
ስራው ከመፅሀፍ ባለፈ የትምህርት መሳሪያዎችን ያካተተ ሲሆን ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ #ከየቤተሰቦቻችን መኖሪያ አካባቢ በመሄድ የተሰበሰቡ ፦
ትላንት ቅዳሜ ፦
- አቶ ዳንኤል ቦጋለ ከልጃቸው ነብዩ ዳንኤልና ከመላ ቤተሰባቸው ጋር መደበኛ መፅሀፍት 58 ፣ አጋዥ 2 ፣ የህፃናት 2 ፣ ልብወለደ 1 ፣ የግል ት/ቤት 11 መፅሀፍት አበርክተዋል።
- ወ/ሮ ኑሪያ አደም ከልጆቻቸው ሲያ አህመዝ ፣ ሀናን አህመድ፣ ረምላ አህመድ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 9 አጋዥ መፅሀፍት ፣ መዝገበ ቃላት 3 ፣ መደበኛ 19 መፅሀፍት እና አንድ ሞኒተር አበርክተዋል።
- ወ/ሮ ሰብለ ተሾመ ከልጆቻቸው በረከት ፍስሃ፣ በእምነት ፍስሃ፣ በፍቅር ፍስሃ ከመላው ቤተሰባቸው ጋር 38 መደበኛ መፅሀፍ 5 አጋዥ መፅሀፍ አበርክተዋል።
- አንድ የቤተሰባችን አባል ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የ5 ሺህ ብር 106 መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።
- ዶ/ር አለማየሁ ሀብተገብርኤል ከልጆቻቸው ቤተልሄም ፣ መክሊት፣ ዳግማዊት እና በመላው ቤተሰባቸው ስም አንድ #ከለር_ፕሪንተር እና #ሞኒተር አበርክተዋል።
#ይቀጥላል

#ምስጋና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም) ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል። የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው። ስራው ከመፅሀፍ…
#የቀጠለ
ዛሬ እሁድ፦
- ካሌብ ጌትነት 10 መደበኛ መፅሀፍት አበርክቷል።
- ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘሚል ሀሰን እና አቶ አብድላዚዝ አህመድ ከልጃቸው ነሂማ አብድላዚዝ መሀመድ ጋር 31 መደበኛ መፅሀፍ ፣ 2 የግል ት/ቤት መፅሀፍ አበርክተዋል።
- መቅደስ ደረጀ መደበኛ 55 መፅሀፍ አበርክታለች።
- ናታን ደመቀ 8 አዲስ አጋዥ መፅሀፍት አበርክቷል።
- ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬ ከልጆቻቸው ፀጋ ተመስገን፣ ሜሎና ተመስገን፣ ናርዶስ ተመስገን ጋር በመላው ቤተሰባቸው ስም 7060 ብር ወጪ አድርገው 45 መፅሀፍ ገዝተው አስረክበዋል።
- ወ/ሮ ህይወት እንድርያስ ከልጃቸው ቤዛዊት ነጋሽ ጋር 10 አጋዥ ፣ 3 መደበኛ መፅሀፍ አስረክበዋል።
- ሀዊ ጨምዴሳ 20 አጋዥ መፅሀፍት፣ 34 መደበኛ መፅሀፍት አስረክባለች።
- ወ/ሮ ፀጋ ለማ፣ ከልጆቻቸው በእምነት ወንደሰን፣ ያሬድ ወንደሰን እና እድላዊት ወንደሰን 25 መደበኛ እና 5 አጋዥ መፀሀፍት አበርክተዋል።
- አሚር መኑር 48 አጋዥ ፣ 14 መደበኛ መፅሀፍ አበርክቷል።
- አንድ የቤተሰባችን አባል ከለቡ 28 መደበኛ መፅሀፍት ፣ 29 አጋዥ መፅሀፍት፣ 4 ልብወለድ መፅሀፍት አበርክቷል።
- ኤግዞም የፋርማሲ እቃዎች አከፋፋይ 3000 ብር ወጪ የሆነባቸው መፅሀፍት አስረክቧል።
- አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል የ2000 ብር መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።
ሁላችሁንም ቤተሰቦቻችንን እናመሰግናለን።
በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።
የትላንት ቅዳሜ እና የዛሬ እሁድ #ድምር ብቻ ፦
👉 1,089 መፅሀፍት
👉 2 ላፕቶፕ
👉 2 ሞኒተር
👉 1 ፕሪንተር
#አዲስ_አበባ