TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" እኔ የትራፊክ አደጋ አልደረሰብኝም " - አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ

አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የትራፊክ አደጋ #እንዳልደረሰበት ተናገረ።

አትሌት ኃይሌ " የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት " ሚዲያዎች እየዘገቡ ሲሆን አትሌቱ ለአል ዓይን አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል " መረጃው ሀሰት ነው እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ አልደረሰም " ብሏል።

ኃይሌ ፤ " ያለንበት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፣ ሌላም ነገር ቢሆን እንዲህ ነው የውሸት መረጃ የሚሰራጨው " ብሏል።

ዛሬ ጠዋት " ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 " በተሰኘው ሬድዮ ጣቢያ ከሚሰራጨው " አውቶሞቲቭ " የሬድዮ ፕሮግራም ጋር በስልክ ተደውሎልኝ ስለፍጥነት መገደቢያ ወይም ስፒድ ብሬከር ችግር መሆኑን አስተያየት ሰጥቼ ነበር ያለው ኃይሌ ፤ " ይህ ማለት ግን ዛሬ በእኔ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶብኛል ማለት አይደለም " ሲል ተናግሯል።

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ ምክንያት ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ አሳስቧቸው እጅግ ብዙ የስልክ ጥሪዎች እያደረሱኝ ነው ሲል ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጠው ቃል ተናግሯል።

#አልዓይንኒውስ

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች ፦
- በመምህርነት፣
- በተመራማሪነት እና በረዳት መምህርነት መቅጠር እንደሚፈልግ አሳውቋል።

መወዳደር የምትፈልጉ መስፈርቱን የምታሟሉ በተጠቀሱት አድራሻዎች ማመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግጭት አካባቢዎች ተቋርጦ የከረመውን የባንክ አገልግሎት በፍጥነት ለማስቀጠል በከፍተኛ ርብርብ እንደሚሰራ ማምሻውን አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ ለበርካታ ወራት የትግራይ ክልል አካባቢዎች የባንክ አገልግሎት ማግኘት ሳይችሉ እንደቀሩ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከ300 በላይ ነጋዴዎች የሚሳተፉበት ባዛር በ " ኤግዚቢሽን ማዕከል " እየተካሄደ ይገኛል።

ይኸው ባዛር በDct ኢንተርቴይመንትና ኢቨንትስ  " አሲና ገና " በሚል መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ከታህሳስ 8/2015 - ታህሳስ 28/2015 ይቆያል ተብሏል።

አዘጋጆቹ በላኩት መልዕክት በባዛሩ ከ300 በላይ የአገር ውስጥ እና የባህር ማዶ አምራቾች አክፋፋዮች ነጋዴዎች የተሳተፉበት መሆን ገልፀው ፤ " ጎብኝዎች በእውነተኛ ቅናሽ ነው የሚገበዩት " ብለዋል።

ባዛሩ በሚቆይባቸው ቀናት ታላላቅ እና ታዋቂ  ድምፃውያን ስራቸውን ለታዳሚ እንደሚያቅርቡም አዘጋጆቹ አክለዋል።

Credit : ዋልተንጉስ ዘ ሸገር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል። ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል። በሰሜን…
#Lion #Wegagen

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሽረ እንደስላሴና አካባቢው የሚገኙት ቅርንጫፎቹ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በአላማጣና በራያ ጥሙጋ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

ባንኩ ሰቲት ሁመራ፣ አዲ ረመፅ ፣ ዳንሻ  እና ተከዜ ቅርንጫፎች ቀደም ብለው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውሷል።

በቅርቡም ፤ #በመቐለ እና #በሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የህዝብ እና ቤት ቆጠራ #የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል " ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ይህን ያሳወቀው ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

ቃላቸውን ለመረጃ ማጣሪያው የሰጡት የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳፊ ገመዲ " የህዝብና ቤት ቆጠራ የፊታችን መጋቢት 29 ይካሄዳል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ ነው " ብለዋል።

የህዝብና ቤት ቆጠራ የሚካሄድበትን የጊዜ ሠሌዳ በፌዴሬሽንና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች እንደሚወስን ገልጸው ምክር ቤቶቹ ምንም አይነት ውሳኔ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

ም/ቤቶቹ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ  እንዲራዘም በተደጋጋሚ መወሰናቸው ይታወሳል።

#ኢትዮጵያቼክ

@tikvahethiopia
#USA #NorthKorea

አሜሪካ #ኑውክሌር_የመሸከም አቅም ያላቸውን " B-52 " ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ዛሬ በደቡብ ኮሪያ አቅራቢያ ለልምምድ ማብረሯን ቪኦኤ ዘግቧል።

በረራው ከሰሜን ኮሪያ ሊመጣ የሚችልን ስጋት የመመከት አቅሟን ለማሳየት ነው ተብሏል። በተጨማሪም F-22 የተባሉትን ስቲልዝ ተዋጊ ጄትችንም ማብረሯ ተሰምቷል።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ F-35A እና F-15K ይተሰኙ ተዋጊ ጄቶቿን በልምምዱ ማሳተፏን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሀገራቱን ልምምዱን ያደረጉት በዚህ ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚሳዬል ሙከራ ላደረገችውና በአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ላይ ዛቻዋ እየጨመረ ለመጣው ሰሜን ኮሪያ ጡንቻቸውን ለማሳየት እንደሆነ ነው የቪኦኤ ዘገባ የሚያስረዳው።

2ቱ አገሮች ወታደራዊ ልምምዳቸውን ለማጠናከርና በአሜሪካ በኩል የሚቀርቡትን የመሣሪያና ጄቶችን ቁጥር ለመጨመር፣ እንዲሁም አሜሪካ ደቡብ ኮሪያን ለመከላከል የገባቸውን ቃል በተግባር እንድታጠናክር ባለፈው ወር ተስማምተው ነበር።

የደቡብ ኮሪያው የመከላከያ ሚኒስቴር ፤ ያንን ስምምነት በመጥቀስ፣ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌርና የሚሳዬል ዛቻ መልስ ለመስጠት ሁለቱ አጋሮች የመከላከያ ብቃታቸውን ማሳየታቸውን ይቀጥላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ብቻ እጅግ ተደጋጋሚ ሚሳኤል ስታስወነጭፍ የነበር ሲሆን ከቀናት በፊትም መካከለኛ ርቀት ያላቸውን ባሊስቲክ ሁለት ሚሳዬሎች አስወንጭፋለች።

ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የስለላ ሳተላይት ለመላክ ወሳኝና የመጨረሻ ሙከራ ነው ማለቷን ዘግባው ያሳያል።

@tikvahethiopia