TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#HawassaUniversity ዛሬ ጠዋት መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ሚኒስቴሩ በደረሰው ጉዳት አዝናለሁ ብሏል። ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና…
#Update

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድዩ የፈረሰው መሸከም ከሚችለው በላይ ተማሪ ወጥቶበት መሆኑን ገልጿል።

ዩንቨርስቲው ይህ የገለፀው ባወጣው መግለጫ ነው።

" ዛሬ ጥዋት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲሸጋገሩ ሁለቱን ግቢዎች የሚያገናኘው ድልድይ ላይ ድልድዩ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ ተማሪዎች ሲወጡበት በመውደቁ አደጋ አጋጥሟል " ብሏል ዩኒቨርስቲው።

" በዚህ አደጋ ምክንያት ጥቂት ተማሪዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል " ያለው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጿል።

የዛሬውን ፈተናው መፈተን ያልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዕድል ከት/ት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ጋር በመነጋገር እንደሚመቻችላቸውም አሳውቋል።

ፎቶ ፦ ክብሩ ግዛቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድልድዩ የፈረሰው መሸከም ከሚችለው በላይ ተማሪ ወጥቶበት መሆኑን ገልጿል። ዩንቨርስቲው ይህ የገለፀው ባወጣው መግለጫ ነው። " ዛሬ ጥዋት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከዋናው ግቢ ወደ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሲሸጋገሩ ሁለቱን ግቢዎች የሚያገናኘው ድልድይ ላይ ድልድዩ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ ተማሪዎች ሲወጡበት በመውደቁ አደጋ አጋጥሟል " ብሏል ዩኒቨርስቲው። "…
#Hawassa

" የተማሪ ወላጆች ተረጋጉ " - የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ ጥሪ አቀረበ።

ዛሬ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ ምክንያት የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ያለው ከተማ አስተዳደሩ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በጤና ተቋማት በልዩ ሁኔታ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብሏል።

በመሆኑንም የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ የከተማው አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከነገ መስከረም 30 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል። ነገ ፈተናቸውን የሚፈተኑት በመጀመሪያ ዙር ወደ መፈተኛ ማዕከላት / ዩኒቨርሲቲ የገቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው። ተማሪዎቹ ስለፈተናው አጠቃላይ (ኦረንቴሽን) ገለፃ ተደርጎላቸዋል። በፈተና ወቅት መከተል ስላለባቸው የስነምግባር መርሆች፣ የሰዓት አከባበርን በተመለከተ ፣ የተብራራላቸው…
ብሔራዊ ፈተናው መሰጠት ተጀመረ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መስከረም 30 መሰጠት ተጀምሯል።

ዛሬ ፈተናውን መውሰድ የጀመሩት የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር ሀገሪቱንና ትውልዱን ከፍተኛ አደጋ ላይ እየጣለ ነው ያለውን የፈተና ስርቆት እና ኩረጃን ለመከላከል ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ወደ ፌዴራል ተቋማት / ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ማስፈተን ጀምሯል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ ላለው ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ወጪ የወጣተበት፣ 8 ሺህ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የተማሪዎችን እና የፈተናውን ደህንነት ለማረጋገጥ የተሰማሩበት ፣ ከ35 ሺህ በላይ ፈታኞች የተሰማሩበት፣ በርካታ የምግብ አብሳይ ሰራተኞችም የተካፈሉበት ነው።

ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈተናን እንመኛለን።

ፎቶ ፦ ENA & EPA

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ እና ሁለት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህን የገለፀው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ነው።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል " ብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#SRTA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሲዳማ ክልል የትምህርት ቢሮ ፤ ከዋናው ግቢ በስተቀር በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ5 ካምፓሶች ፈተና እየተሰጠና ሌሎች የፈተና ጣቢያዎች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት ፈተና እየሰጡ መሆኑን አስታወቀ።

በዋናው ግቢ በደረሰው አደጋ በፈተናው ጣቢያው የተመደቡ ተማሪዎች መፈተን ያልቻሉ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር አማራጭ ይፈለጋል ሲል አሳውቋል።

ተማሪዎች ዛሬ ከሰዓት በተረጋጋ መንፈሰ ወደ መፈተኛ ጣቢዎች በመመለስ በቀጣይ የሚሰጡ ፈተናዎችን እንዲወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለደ/ሬ/ቴ/ድ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

በሌላ በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ልጆቻቸውን ለብሔራዊ ፈተና የላኩ ወላጆችን መልዕክት እየተቀበለ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ጥዋት በተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ መደናገጣቸውን ገልፀዋል።

ተማሪዎች ከፈተና ማዕከሉ መውጣታቸውንም ጠቁመዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን የሚውስዱበት አማራጮች እንዲፈለግና በግቢው የነበሩ ክፍተቶች በተለይም ከምግብ ጋር በተያያዘ እንዲስተካከሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መግለጫ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ምን አሉ ? - በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው። - በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት "…
#Update

የጥዋቱ የፈተና መርሀ ግብር ተጠናቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / በዩኒቨርሲቲዎች / ውስጥ መስጠት የጀመረው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዛሬ ጥዋት መርሃግብር መጠናቀቁን አሳውቋል።

ከሰዓት ብሔራዊ ፈተናው በተያዘለት መርሃግብር  የሚቀጥል ይሆናል ብሏል።

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ በዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ #በመደርመሱ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ በተመለከተ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ፦

- አራት መቶ አስራ አምስት (415) ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ ተደርምሷል።

- የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው አልፏል።

- በድልድዩ መደርመስ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ተጎጂዎች  በሪፌራል፣ ያኔት፣ አላትዮን፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

የተማሪ ወላጆችም ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች በጥዋቱ ያልተጠበቀ አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻሉ ገልጾ ፤ በሁኔታው ተደናግጠው ከግቢ የወጡም ሆኑ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደነበሩበት እንዲመለሱና ለነገ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስቧል።

@tikvahethiopia