TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት የ " መስቀል ደመራ በዓል " አከባበርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት ፦ - ሁከት ቀስሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ይዞ መገኘት በፍፁም አይፈቀድም። - በበዓሉ ላይ ህገ መንግስቱ የደነገገውን የኢትዮጵያን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ #ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የፀደቀውን የቤተክርስቲያን…
ፎቶ / ቪድዮ : የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (አዲስ አበባ - መስቀል አደባባይ)
ፎቶ / ቪድዮ - የቲክቫህ አዲስ አበባ አባላት
በተለያዩ ከተሞች የነበረውን የበዓሉን አከባበር ፎቶዎች በ @tikvahethmagazine ላይ ያገኛሉ።
@tikvahethiopia

ፎቶ ፦ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጽዮን ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን
ፎቶ : ጽዮን ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
ፎቶ : ጽዮን ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ / ቪድዮ : የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን (አዲስ አበባ - መስቀል አደባባይ) ፎቶ / ቪድዮ - የቲክቫህ አዲስ አበባ አባላት በተለያዩ ከተሞች የነበረውን የበዓሉን አከባበር ፎቶዎች በ @tikvahethmagazine ላይ ያገኛሉ። @tikvahethiopia
" በዓሉ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል "
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ፣ ትውፊቱንና እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለአዲስ አበባ ህዝብ ፣ ለእምነት አባቶች ፣ ምእመናን ፣ ወጣቶች፣ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ ለከተማው የሰላም ሰራዊት አባላት እና የደንብ ማስከበር አገልግሎት ምስጋና አቅርቧል።
Video : Hena (Tikvah Family)

ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?
" አለመግባባትን በዕርቅ ዘግቶ በፍቅርና በሰላም ከመኖር የተሻለ ሌላ አማራጭ የለም። " ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ገለጹ፡፡
ቅዱስነታቸው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተከበረበት ወቅት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት " የምናከናውነው ተግባር በሙሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድና የመስቀሉን ምሥጢር የጠበቀ ሊሆን ይገባል " ብለዋል።
ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ፍጥረታት በሙሉ እርስ በእርስ ሲጣሉና ሲተረማመሱ ማየት ቀዋሚ ትዕይንት ሆኖ እንደሚገኝ የገለጹት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳ ችግሩ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ሰፍኖ ቢገኝም መፍትሔ የሌለው ችግር ግን አይደለም ብለዋል።
" በየጊዜው በተግባር የተፈተነ ጠንካራና የማያወላውል መፍትሔው ይቅርታና ዕርቅ ነው " ያሉት ቅዱስ ፓትርፓርኩ " የሰው ልጅ አለመግባባትን በዕርቅ ዘግቶ ሰላምንና አንድነትን መሥርቶ በመከባበርና በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና በመተጋገዝ፣ በመረዳዳትና በመቻቻል፣ በፍቅርና በሰላም ከመኖር የተሻለ ሌላ አማራጭ የለውም ብለዋል። "
ይህም እውን ሊሆን የሚችለው፥ ለወንድሜና ለእኅቴ የሚል ቅን ሀሳብና ለሁላችንም የሚል የጋራ አስተሳሰብ በሰዎች ልቡና የበላይነት ሲያገኝ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ " እግዚአብሔር ግጭቱን አስወግዶ ሰላሙን ፍቅሩን፣ አንድነቱንና ስምምነቱን እንዲያመጣልን፤ እኛም የዕርቅና የይቅርታ ሰዎች ሆነን እንገኝ ዘንድ በርትተን እንፀልይ " ሲሉ አባታዊና መንፈሳዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ፦ telegra.ph/EOTC-09-26

#DrAlQaradawi
የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን መስራችና ፌዴሬሽኑን ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት እውቁ የእስልምና ምሁር ግብፃዊ ዶክተር ሼክ ዩሱፍ አል ቃራዳዊ በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ህልፈታቸውን ልጃቸው አብዱል ራህማን ዩሱፍ አል ቃራዳዊ አረጋግጠዋል።
ዶ/ር አልቃራዳዊ ህይወታቸው ያለፈው ኳታር፤ ዶሃ ውስጥ ነው።
እኤአ 2004 የተቋቋመውን (እሳቸው መስራች ነበሩ) ዓለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ፌዴሬሽን ከተቋቋመበተ ጊዜ አንስቶ ለ14 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።
ዶ/ር አልቃራዳዊ ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የኳታር ዜግነት ተሰጥቷቸው ህይወታቸው እስክታለፍ ድረስ ኑሯቸውን በኳታር፣ዶሃ አድርገው ነበር።
አልቃራዳዊ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ወቅት በግብፅ በ1926 ነበር የተወለዱት።
ገና በለጋ እድሜያቸው እስላማዊ ትምህርትን መከታተል የጀመሩት አልቃራዳዊ በፀረ ቅኝ አገዛዛ ላይ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። በ1950 ዎቹ ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴና ከሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ብዙ ጊዜ ለእስር ተዳርገው ነበር።
ከ120 በላይ መፅሀፍትን ያሳተሙት ዶ/ር አል ቃራዳዊ ለእስልምና ባበረከቱት አስተዋፆ 8 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን መሸለም እንደቻሉ ተገልጿል።
ዶ/ር አል ቃራዳዊ በክፈለ ዘመኑ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ እንደነበሩ ተዘግቧል።
በህይወት በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አመለካከታቸውን ሲያጋሩ የነበረ ሲሆን በሚያነሷቸው ሀሳቦች የሚደግፏቸው እንዳሉ ሁሉ ሀሳባቸውን የሚቃወሙም ነበሩ።
የዶ/ር አልቃራዳዊን ህልፈት ተከትሎ ፤ የተርክዬ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለልጃቸው አብዱል ራህማን በመደወል የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው አፅናንተዋል።

Photo
#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሥጋቶች በመኖራቸው በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰቡን ይታወሳል።
ኢሰመኮ በአካባቢው ሲቪል ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች አሁንም ተሰፋፍተው መቀጠላቸው ገልጾ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አስገንዝቧል።
በዞኑ በአሙሩ፣ በሆሮ ቡልቅ እና በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሽኔ)፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና ግለሰቦች በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ታወቋል ሲል ኢስመኮ ገልጿል።
እንዲሁም የግል ንበረት እና የቁም ከብቶች መዘረፋቸውን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያለበቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአካባቢው የፍትሕና የአስተዳደር አካላት እንዲሁም በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ድርጅቶች ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች እና ማስረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ " የክልሉ አና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸመው ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል" ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል።

#ETHIOPIA
የ2015 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።
መልካም በዓል!
#TikvahFamily
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
የ2015 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።
መልካም በዓል!
#TikvahFamily
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
#እንድታውቁት
የኢፌዲሪ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የቪዛ ማራዘም እና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት መጀመሩን አሳውቋል።
አገልግሎቱ ከሐምሌ 18/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ቪዛቸዉ እና የመኖሪያ ፈቃዳቸው የሚፀናበት ጊዜ ከአንድ ወር በላይ ላለፈባቸው ግለሰቦች የቪዛ ማራዘምና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሷል።
ነገር ግን ፤ ከመስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎቱን መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

#MadingoAfework
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

#MadingoAfework ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። @tikvahethiopia
" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ
ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።
ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።
የድምፃዊው ወዳጆች በበኩላቸው ፤ ማዲንጎ ህመም ተሰምቶት እራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ህክምና ስፍራ መሄዱን ከዛ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈ ጠቁመዋል።