TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ፓሊስ በመምሰል የአንድን ግለሰብ ቤት ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች ሙከራቸው በህብረተሰቡ እና በፀጥታ ኃይሎች ትብብር መክሸፉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው " ቀጠና አንድ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን 4 የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱና 2 ሲቪሎች ሆኖው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመግባትና ሀሰተኛ የፌዴራል ፖሊስ መታወቂያ በማሳየት በር እንዲከፈትላቸው ካደረጉ በኃላ ሰራተኛዋን አግተው ዝርፊያ ሊፈፅሙ ሲሉ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ሀይሎች እና ህዝባዊ ሰራዊቶች የዝርፊያ ሙከራቸው መክሸፉን አስተሳደሩ ገልጿል።

የፀጥታ ሀይሎች ቀድሞም በነበራቸው  ጥርጥሬ ዘራፊዎቹን ሲከታተሏቸው እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን ዘራፊዎች ከውጭ ባስቀመጧቸው ግብር አበሮቻቸው ቀድሞ አዘጋጅተውት በነበረው " ኮድ 3 ኦሮ " በሆነ ተሽከርካሪ ሊያመልጡ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ቢያመልጡም በአካባቢው  የደህንነት ካሜራ ስለነበረ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞት ክትትል እያደረገበት ይገኛል ተብሏል።

ማህበረሰቡ እራሱን ከመሰል አጭበርባሪዎች ሊጠብቅ ይገባል፤ አጠራጣሪ ነገሮችንም ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ሊያሳውቅ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ኢትዮጵያን የማይመጥኑ ያሏቸው ኩባንያዎች ላይ መስሪያ ቤታቸው እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል ገለፁ።

ኢ/ር ታከለ ኡማ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው " ኢትዮጵያን የማይመጥኑ የስራ አቅም የሌላቸው (ድኩማን) ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ማዕድን ኃብታት ለዘመናት አክሳሪ ጨዋታ ተጫውተዋል " ብለዋል።

" እነዚህ ጨዋታዎች ከዚህ በላይ እንዳይቀጥሉ ተገቢ እርምጃዎችን መውሰዳችንን እንቀጥላለን " ሲሉም አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ " የስራ አቅም የሌላቸው (ድኩማን) " ሲሉ የጠሯቸውን ኩባንያዎች በግልፅ ከመጥራት ተቆጥበዋል።

ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ከቆየው ፖሊ-ጂሲ.ኤል ጋር የነበራትን ውል ከረጅም ጊዜ ትእግስትና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ማቋረጧን ኢ/ር ታከለ ኡማ አሳውቀው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶክተር ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለክብር ዶክተር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሰጥቷል። ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር የሚኖሩ፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ፤ ታላቅ አባት ናቸው። ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም…
#Update

የክብር ዶክተር ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ።

ከሀገር ውጭ የነበሩት ብፁዕ ኡቡነ ኤርምያስ ዛሬ ረፋዱን ወደ ባሕርዳር ሲገቡ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንት፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በባሕር ዳር ዓለም አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተውም በዩኒቨርሲቲው የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።

ባለፈው ዓመት ነሀሴ 21 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶ/ር ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለክብር ዶ/ር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መስጠቱ የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : AMC

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ የመለኮስ ስነ-ስርአት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም  ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ  ኡራኤል አደባባይ

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ

• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ  ለገሃር  ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ

• ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር የሚሄዱ ጠማማ ፎቅ አካባቢ

•  ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር  የሚወስደው ሚክሲኮ አደባባይ

• ከተከለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ  ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚኒዬም አካባቢ

• ከጌጃ ሰፈር ፣ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ

• ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ

• ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

• ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል

• ከፒያሳ በቸርችር ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ

• በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት

• ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል

• ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ 6ኛ ፖሊስ መታጠፊያ ላይ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ ይህን አውቆ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፏል።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

የመተሐራ ቲክቫህ ቤተሰቦች በሚኖሩበት የመተሀራ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ በላኳቸው መልዕክቶች አስገንዝበዋል።

ከዚህ ቀደም ወደ መተሀራ አካባቢ በርካታ ወጣቶች በመዝናኛ ቦታ እያሉ መገደላቸው በሚዲያዎችም ጭምር መገለፁ ይታወሳል።

እዛው " መተሐራ " አካባቢ ከአምስት ቀናቶች በፊት አንድ የቀበሌ ሊቀመንበር ተገድሎ ነበር ፤ ከዚህ ግድያ በኃላም የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የመተሐራ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

ከሚፈፀሙ ግድያዎች በተጨማሪ ደግሞ ታጣቂዎች ሰዎችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ (እስከ 2 ሚሊዮን ብር) ድረስ የመጠየቅ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመሆኑ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነውና ከመቼውም በላይ ልዩ ትኩረት ይፈጋል ሲሉ አስገዝበዋል።

በተጨማሪ ከአዳማ ከ50 እስከ 100 ኪ/ሜ ባለው ርቀት ውስጥ ባሉት አቦምሳ / አፐር አዋሽ አካባቢም ትኩረትን እንደሚሻ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ አንድ የቅርብ ቤተሰቡ በታጣቂዎች የተገደሉበት የቤተሰባችን አባልም በተመሳሳይ መልዕክት በመላክ የአካባቢው ደህንነት ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አስገንዝቧል።

ከአዳማ ወደ መተሀራ በሚወስደው መንገድ ላይ " ኑራሄራ " አካባቢ የሰዎች ግድያ እና እገታ እንዳለ የገለፀው ቤተሰባችን ከቀናት በፊት ዘመዱ መገደሉን አመልክቷል።

" የእናቴ አጎት ነው ለባለቤቱ ደውለው መጀመሪያ ብር አምጪ ነው የተባለችው። ብር ማምጣት አንችልም አለች ፤ ከዘመድም ቢሆን ጠይቂና አምጪ አሏት ፤ ብር ሊሰጥ የሚችል ዘመድ የለም የራሳችሁን የምትወስኑትን ውሳኔ ወስኑ ስትል ነው የመቱት " ሲል አስረድቷል።

" እኔም ለለቅሶ ወደዛ ሄጄ ነበር " ያለው ቤተሰባችን በአካባቢው የሚሰማው ሁሉ የደህንነት ስሜትን የሚነሳ ነው እና በተለይ ፌዴራል መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የአካባቢውን ድህንነት ማረጋገጥና አጥፊዎችን መቆጣጠር አለበት ሲል አጥብቆ አስገንዝቧል።

በተጨማሪም ይኸው ቤተሰባችን በቦሌ ወደ አዳማ በሶደሬ በኩል በሚወስደው መንገድ ቦፋ እና አውራ ጎዳና በሚባለው ቦታ የህዝብ ተሽከርካሪ ሳይቀር የማገት ድርጊት ተፈፅሞም እንደነበር በመጠቆም አጠቃላይ ለደህንነት ስጋት በሆኑ ቦታዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መንግስት የተጠናከረ ስራ እንዲሰራ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሊያ

በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ለ13 ዓመታት አልሸባብ ሲቆጣጠረው የነበረው ዋና መንገድ ነፃ መደረጉ ተገለፀ።

ለ13 አመታት በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረው በሂራን ክልል ቡልቡርዴ እና በለድዌይን ወረዳዎች መካከል ያለው ዋና መንገድ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር በአካባቢው ነዋሪዎች እገዛ ነፃ ማድረጉን አሳውቋል።

የፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ አስተዳደር በአልሸባብ ይዞታዎች ላይ እያካሄደ ያለውን እጅግ መጠነ ሰፊ ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን በተለይም በሂራን ክልል በርካታ ቦታዎችን ከአልሸባብ ነፃ ማድረግ ተችሏል።

በዚህ የፀረ ሽብር ዘመቻ ላይ አሜሪካም በአየር የአልሸባብ ይዞታዎችን በመደብደብ እገዛ እያደረገች መሆኑን ከሀገሪቱ መንግስት የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

የአፍሪካ ህብረት ኃይልም ለፀረ ሽብር ዘመቻው የአየር ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#UNGA

የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት #በአፍሪካ_ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

አቶ ደመቀ ፤ ይህንን የገለፁት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ነው ያሉ ሲሆን " ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት አይኖረውም። " ሲሉ ተናገረዋል።

በሌላ በኩል በንግግራቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ #በአፍሪካ_ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሶስትዮሽ ድርድር ጉልህ ተፅዕኖ በማያደርስ እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም አላት ሲሉ ለጉባኤው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በንግግራቸው አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠይቀዋል።

" እኛ አፍሪካውያን ይህ ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ይህን ጥያቄ መጠየቃችንን እንቀጥላለን። " ብለዋል።

ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው ፤ የሚሰጠውም ጭምር በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ምሽት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ያሰሙት ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል (40 MB)።

@tikvahethiopia
" የቀድሞ የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 በኃላ አገልግሎት አይሰጥም " - የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመንግስት ግዥ ለሚሳተፉ አቅራቢዎች ባሰራጨው ደብዳቤ የቀድሞው የአቅራቢነት ምዝገባ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኋላ አገልግሎት እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን (e-GP) ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑና በአሁን ወቅት 73 የፌዴራል ተቋማት በሲስተሙ ተጠቅመው ግዥ መፈፀም መጀመራቸው ገልጿል።

በአጭር ጊዜ ውስጥም የተቀሩት የፌዴራል ተቋማት ሙሉ በሙሉ የሲስተሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው ብሏል።

በሥራ ላይ የዋለው የመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሲስተም ለመንግስት ተቋማት አመታዊ የግዥ ዕቅድን ከማዘጋጀት ጀምሮ፣ ጨረታን የማውጣት ፣ የመገምገምና አሸናፊ የመለየትና ውል የማስተዳደር ሥራዎችን እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን አመልክቷል።

በተጨማሪ ሲስተሙ ለአቅራቢው ማህበረሰብ በአቅራቢነት እንዲመዘገቡና ለጨረታ የመወዳደር ሂደታቸው ሙሉ ለሙሉ በሲስተም የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል ሲል አስረድቷል።

በዚህም ፤ ከዚህ በፊት በባለስልጣን መ/ቤቱ ድረ-ገጽ (https://www.ppa.gov.et/) ላይ የተመዘገቡ አቅራቢዎች ምዝገባቸው ተቀባይነት የሚኖረው የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን (e-GP) መጠቀም ባልጀመሩ ተቋማት ብቻ እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አስገንዝቧል።

በመሆኑም በ https://egp.ppa.gov.et/ ላይ በመግባት ተገቢውን ምዝገባ በማከናወን በመንግስት ግዥ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ ከዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም ማታ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት የሞተር እንቅስቃሴ በከተማዋ የተከለከለ ሲሆን  ይሄንን ተላልፈው በሚገኙ ሞተረኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ #የፖለቲካ_ሥራ እንደሚውል በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠና ጥናት ላይ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ኮሚሽኑ ጥናቱን ያከናወነው በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የጥናቱ ትኩረት ሙስናና ብልሹ አሠራር በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርሰውን የሙስና ሥጋት ለመለየት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከምንጮቼ አገኘሁት ያለውና ኮሚሽኑ በተመረጡ 61 ተቋማት ላይ ያደረገው የጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው ፦

- በተቋማቱ፤ ከመምህራን ልማት እና ከአሠልጣኞች ምልመላ ጋር በተገናኘ፣ የዘመድና የፓርቲ አሠራር፣ እንዲሁም አድልኦና ጉቦ የመቀበል አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል።

- በመምህራንና ሠራተኞች አስተዳደር ክፍል ሕገወጥ ቅጥርና ዝውውር መኖር፣ መምህራን ተማሪዎችን ለይቶ ለመጥቀም የሚደረግ ዝንባሌ መኖር፣ ለመምህራን ቅጥር ውድድር ተፈልጎ እኩል ውጤት ሲመጣ፣ አንዱን በትውውቅ ብቻ የመምረጥ አሠራር እንደሚስተዋል ተገልጿል፡፡

- ከሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ ጋር በተያያዘ የብቃት ማረጋገጥና ፈቃድ አሰጣጥ ላይ መሥፈርት ሳያሟሉ፣ ለተቋማት ፈቃድ መስጠት እና የፈቃድ ዕድሳት እንደሚከናወን ተግልጿል።

- መምህራንና በትምህርት አስተዳደር አመራር ላይ ያሉ ሠራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች እንደተገኘባቸው ፤ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት ሲሞከር ደግሞ ሠራተኞች ከሥራ ቀድመው የመልቀቅ እንቅስቃሴ እንዳለ ተገልጿል።

- በግል ኮሌጆች የሲኦሲ ምዘና ሳያልፉና ትምህርት አጠናቀው ሳይጨርሱ፣ እንዲሁም ፈጽሞ ያልተማሩ ሰዎች የትምህርት ማስረጃ አትሞ መስጠትና በኮሌጆች ሽያጭ የመፈጸም ድርጊት መኖሩን ሪፖርቱ ገልጿል።

- በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች ሬጅስትራሮች ውስጥ የተማሪዎችን ውጤት የማሳሳትና የማጭበርበር ድርጊት እንዳለ ተጠቅሷሳ።

- በግል ትምህርት ተቋማት ውሳኔዎች የሚተላለፉት ለተቋማቸው መልካም ስም ቅድሚያ በመስጠት እንደሆነ፣ በመንግሥት ተቋማት ደግሞ ሰነድ ማዘጋጀት እንጂ ትግበራ ላይ እምብዛም እንደሌሉበት ተገልጿል።

- በተደረገው ጥናት በተቋማቸው ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ ወይ ተብለው ከተጠየቁት ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት " አዎ " የሚል መልስ መስጠታቸውን፣ 35 በመቶ የሚሆኑት " የለም " የሚል መልስ ሲሰጡ፣ በተመሳሳይ የሙስና ችግሮች መኖራቸውን 66 በመቶ መናገራቸውና 47 በመቶ ደግሞ ለሚቀርቡ ጥቆማዎች ከተቋማቱ መልስ እንደማይሰጥ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

- በትምህርት ተቋማቱ የመምህራን በተደጋጋሚ ወደ ክፍል አለመግባት፣ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መስጠት፣ በአመራር የሚከናወን ስርቆት፣ ሕገወጥ ዝውውርና የደረጃ ዕድገት፣ ሕግና ደንብን ተከትሎ የማይከናወን ግዥ፣ የመረጃና ማስረጃ ማጭበርበር፣ ግልጽነት የሌለው አሠራር መብዛት፣ በሬጅስትራር የሚፈጸም ብልሹ አሠራር ተቋማቱን ለከባድ ሙስና አደጋ ጥሏቸዋል፡፡

- በግዥ ወቅት ለተቋም የማያስፈልግ ንብረት እንዲገዛ ተጨማሪ በጀት ማስያዝ፣ በጨረታ ወቅት የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ እንዲጋብዝ አድርጎ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ወቅቱንና ጥራቱን ያልጠበቀ ግንባታ እንዲከናወን ማድረግ፣ በሕንፃ ርክክብ ጥራቱን ያልጠበቀ ሕንፃ እንዲገነባ ማድረግና ያልተጠናቀቀ ሕንፃ መረከብ ተቋማቱን ለከባድ ሙስና እንዳጋለጣቸው ሪፖርቱ ያሳያል።

እንደ ምክንያት የተጠቀሱት ችግሮች ምንድናቸው ?

• የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ፣
• የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት አለመኖር፣
• የሞራል መላሸቅ፣
• የተጠያቂነት ማነስ፣
• የላላ የአመራር ቁጥጥርና ከፍተኛ የሆነ የበጀት ምደባ የሚሉት ይገኙበታል።

ጥናቱ በሚደረግበት ወቅት ምን ችግሮች አጋጠሙ ?

➤ የተቋማት አመራሮች በቦታው ላይ አለመገኘት፣
➤ ተቋማት መረጃ ለመሥጠት ፈቃደኛ አለመሆን፣
➤ የተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች መረጃዎችን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመሥርቶ አለመስጠት ... መሰል ዓይነት ችግሮች ነበሩ።

ሪፖርተር 👇
https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-09-25

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ #የፖለቲካ_ሥራ እንደሚውል በፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠና ጥናት ላይ መገለፁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ኮሚሽኑ ጥናቱን ያከናወነው በፌዴራል ደረጃ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የጥናቱ ትኩረት ሙስናና ብልሹ አሠራር በትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርሰውን…
" ዘገባው ታርሞ እና ተስተካክሎ ይውጣ " - የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ታርሞና ተስተካክሎ እንዲወጣ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ጠይቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ሪፖርተር ጋዜጣ መስከረም 14/2015 ዓ.ም በእንግሊዘኛ እና መስከረም 15/2015 ዓ.ም በአማርኛ እትሙ " የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ስራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሣይ ሪፖርት ቀረበ " በሚል ርዕስ ያወጣው ዘገባ የፌደራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በትምህርት ዘርፍ ካስጠናው ጥናት ሪፖርት ጋር የማይጣጣም ነው ሲል አሳውቋል።

" ሙስናን ለመከላከል የሚዲያ ሚና የጎላ ነው " ያለው ኮሚሽኑ " ሪፖርተር ጋዜጣ ትክክለኛውን መረጃና ጥናት ከኮሚሽናችን በማግኘት የማስተካከያ ዘገባ እንዲሰራ እንጠይቃለን " ብሏል።

ምንም እንኳን ኮሚሽኑ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ጥናት በትምህርት ዘርፉ ላይ በኮሚሽኑ ከተደረገው ጥናት ጋር የማይጣጣም መሆኑን ቢገልፅም አድርጌዋለሁ ያለውን ጥናት (ትክክለኛውን ማለት ነው) በይፋ አላሰራጨውም።

@tikvahethiopia