TIKVAH-ETHIOPIA
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#UK
የሀገራችን ኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ የጎረቤታችን ኬንያ፣ ሶማሊያ ፣ ሱዳን መሪዎች ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መጓዛቸው ተሰምቷል።
ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ለንደን የገቡ ሲሆን ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፤ ዛሬ ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ለንደን በረዋል። ፕሬዜዳንቱ በስርዓተ ቀብሩ ላይ ከታደሙ በኃላ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚታደሙና ከዓለም መሪዎች ጋር እንደሚቀለቀሉ ገልፀዋል።
በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት #ኬንያ የ3 ቀን ብሄራዊ ሀዘን አውጃ እንደነበር ይታወሳል። በንግስቷ ሞት በኬንያ ሀዘን መታወጁ በቅኝ ግዛት ወቅት ከተፈፀሙ ግፎች ጋር በተያያዘ በርካቶች ሲቃወሙ ነበር።
በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ድርዓተ ቀብር ዛሬ ለንደን ገብተዋል። ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን እንደገለፁ ተሰምቷል።
የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንም ወደ ለንደን አቅንተዋል።
@tikvahethiopia @officialtikvahethiopiaBOT

#መልዕክት
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ፤ ከዚህ ቀደም ይህ @tikvahethiopiaBOT መልዕክት መቀበያ አስቻገረ እንደሆነ መልዕክት ልከንላችሁ ነበር።
ይህ ችግር እስኪስተካከልም መልክት ለመለዋወጥ አማራጭ ይህን @OfficialTikvahethiopiaBOT እንድትጠቀሙ ገልፀንላችሁ ነበር።
አንዳንድ ቤተሰቦቻችን በ @tikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክቶቻችን እየታዩ እና እየተመለሱ አይደለም የሚል ቅሬት አቅርበዋል ችግሩ እስኪስተካከል በ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክት እንድንለዋወጥ ከትልቅ ይቅርታ ጋር በድጋሚ እንገልፃለን።
ከዚህ ቀደም (ከሶስት ወር ወዲህ) ልካችሁ ያልታየም በድጋሚ መላክ ትችላላችሁ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቦቹ መልዕክት መለዋወጫ ነውና ከጥላቻ ንግግር፣ ከሀሰተኛ መረጃ፣ የሰዎችን እና የሀገርን ክብር ዝቅ ከሚያደርጉ መልዕክቶች ውጭ ማንኛውም ጥቆማ፣ ጠቃሚ መልዕክት ማጋራት እና መለዋወጥ ይቻላል።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia

G4 U1-3.pdf
#Update
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከተዘጋጀው ፤ የ4ኛ ክፍል የሒሳብ መፅሀፍ ጋር በተያያዘ አንድ በመፅሀፉ ስራ ላይ የተሳተፈና ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል በመፅሀፉ ውስጥ መነጋገሪያ የሆነው " የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ነው የተወሰዱ ናቸው። " የሚለው ሀሳብ በእርግጥም በሶፍት ኮፒ ላይ እንደነበር አረጋግጠዋል።
ነገር ግን ይሄ ሶፍት ኮፒ መፅሀፉ ከመታተሙ በፊት ኤዲት ሳይደረግ መምህራን ለዝግጅት እንዲሆናቸው ተብሎ በችኮላ የተላከ እንደነበር ፤ በኃላም ይሄንን ጨምሮ ሌሎች ያልታረሙ ሀሳቦች፣ ስሌቶች፣ የቃላት ግድፈቶች ታርመው አሁን ላይ የተስተካከለው መፅሀፍ መታትሙን አስረድተዋል።
አዘጋጆችና ገምጋሚዎች በመፅሀፉ ውስጥ የነበሩ ክፍተቶችንና ስህተቶችን የማስተካከል ስራ የተሰሩት ቀደም ብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከመውጣቱ በፊት ነው ብለዋል።
በዚህም አሁን ላይ የተስተካከል መፅሀፍ መታተሙን ገልፀዋል።
ሙሉ ቃላቸው ፦
" በመጀመሪያ ደረጃ መፅሀፉ አልታተመም (ከግሪክ በቀጥታ የተወሰደ ነው የሚለውን ሀሳብ የያዘው) ፤ የታተመው መፅሀፍ ይህ የለበትም።
ትምህርት እንዲጀምርና ስኬጁል እንዲያወጡ ተብሎ ይመስለኛል (ሁሉም ነገር ላይ ስለማልገባ ነው ይህን ያልኩት) ሶስት ቻፕተር ተቆርጦ እንዲላክ ጠይቀውን እኛም ቆርጠን ልከናል።
በአጋጣሚ ተቆርጦ የተላከው ኤዲት ያልተደረገው ነው። በኃላ ኤዲቶሪያሉ / ገምጋሚዎቹ ይሄ ይውጣ፣ ይሄ ይግባ ብለው ሚቀነሰውን ቀንሰው መስተካከል እና መታረም ያለበትን አስተካክለዋል።
መጃመሪያ ኤዲት ያልተደረገው ተቆርጦ በመውጣቱ ነው ነገሩ የተጋጋለው ነገር ግን ታትሞ የወጣው የታረመው እና በገምጋሚዎችም የተስተካከለ ነው።
መንግስትም ይሄን ግልፅ ቢያደርገው ኖሮ ጥሩ ነበር።
በአጭሩ ግን መጀመሪያ ላይ ተቆርጦ የተላከው፣ መምህራንም የደረሳቸው ያልተስተከከለው ነው። ይሄ ነገር በዚህ ደረጃ ከመሆኑ በፊት ሶፍት ኮፒው የደረሳቸው ሰዎች እራሳቸው ት/ት ቢሮውን ቢጠይቁ ጥሩ ነበር ፤ እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ከዛ ያልተስተካከለው እንደሆነ ግልፅ ይሆን ነበር።
በነገራችን ላይ ይሄ ብቻ ሳይሆን ብዙ የተስተከከሉ አሉ። ከዛ በኃላ እራሱ ብዙ ኤዲት ተደርጓል። በአጋጣሚ ይሄኛው ታየ እንጂ በዝግጅት ወቅት ብዙ ታርሟል።
አሁን መናጋገሪያ የሆነው ሀሳብ ከአዘጋጆቹ አንዱ መረጃውን በሚያሰፍርበት ጊዜ የተሳሳተው ነው። ከዛም ስህተቶች ሲገኙ ታርሟል። በአጋጣሚ መምህራን እንዲዘጋጁበት በፍጥነት ላኩ ስለተባለ ያልተስተካከለው ተቆርጦ ተላከ እንጂ ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሳሆን ቀደም ብሎ ነው የተስተካከለው። በዛም ነው አሁን የተስተካከለው የታተመው።
እኔ እስከማውቀው ግለሰቡም፤ ሌሎችም አዘጋጆች ምንም ሌላ አጀንዳ የላቸውም። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሃይማኖት እና ከብሄር ጋር እያገናኙ እንደሚያወሩትም አይደለም፤ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ ሲባል ስላየሁ ነው ገምጋሚዎቹም አዘጋጆቹም በሃይማኖት ሆነ በብሄር ምንም ችግር የሌለባቸው አንድ ላይ በጋራ በሀገራዊ መንፈስ በትብብር ያዘጋጁት ነው።
በዝግጅት ወቅትም እንዲህ አድርጉ፣ እንዲህ አታድርጉ የሚል የመንግስት ጣልቃ ገብነት አልነበረም። እንደዛ አይነት ነገር ቢኖር እኔም በግል አልሰራም ነበር።
መፅሀፉ በጣም ተደጋግሞ ነው የተገመገመው ፣ ከህትመት በፊትም ኤዲት የተደረገው። ይሄ የሀገር ጉዳይ እና የትውልድም መቅረጫ ስለሆነ በጣም በተደጋጋሚ ነው ያዩት አዘጋጆች እና ገምጋሚዎች።
እንዳጋጣሚ ኤዲት ያልተደረገው በመውጣቱ ነው እንጂ ሌሎች የቃላት ስህተቶች፣ የስሌት ስህተቶችም ነበሩ እነሱም ታርመዋል። የታረመው ደግሞ ቀደም ብሎ ነው፤ ለዛም ነው ተስተካክሎ የታተመው መፅሀፉ።
የመንግስትን መግለጫ በተመለከተ ግን ትክክለኛውን ነገር በግልፅ ማስረዳት ነበረበት ለሌላ ጊዜ እንደዛ መሆን የለበትም፤ መታረም አለበት። "

አራራይ የታክሲ ማህበር ፦
" እኛ ከ2 ዓመት ጊዜ ጀምሮ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት የሚያስፈልገውን ሂደት አሟልተን፣ የትራንስፖርት ቢሮ ድጋፍ ሰጥቶን አስፈላጊ መ/ቤቶችም የትራንስፖርት ሚኒስቴርም የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሰልጣንም ድጋፍ ደብዳቤ ፅፈው ገንዘብ ሚኒስቴር ደርሰን ነበር።
ገንዘብ ሚኒስቴር የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቶ የመመሪያና የማሻሻያ ደንብን አፀድቆ ከቀረጥ ነፃ መብት ለመስጠት በተቃረበበት ወቅት ላይ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እግድ ፅፎብናል።
የእግዱ ይዘት ሁለት ነገሮችን ይጠቅሳል፤ አንደኛው ነባር የታክሲ ማህበራት ተስተናግደው እስኪጠናቀቅ ድረስ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚል ነው ፤ ሁለተኛ ቢሮው የሚሰራቸድ የአሰራር እና ከመመሪያ ማሻሻያዎች ስላሉ እነዛን ሰርቼ እስካጠናቅቅ በጊዜያዊነት የሚል ነው።
ነገር ግን ገንዘብ ሚኒስቴር ያወጣው የመመሪያ ይዘት 72/13 ላይ የሰፈረው ሁለታችንም ነባር የታክሲ ማህብራት ነን እንደ አዲስ ወደ ዘርፉ የሚቀለቀሉ ማህበራትንም የሚያስተናግድበት ዝርዝር ሁኔታዎች አሉ።
...ዘመናዊ መኪኖቹን ገዝተን ወደ ስራ ለመግባት የ30% ቅድመ ክፍያ ስንከፍል አቅም ኖሮን ሳይሆን ከልጆቻችን ጎሮሮ ቀንሰን፣ እጃችን ላይ ያለውን ንብረት ሽጠን ፣ ከባንክ ተበድረን፣ አረብ ሀገር ሰርተው የመጡ አባሎችም ካለቸው ላይ ቀንሰው ነው የከፈሉት ነገር ግን 2 ዓመት ሙሉ ሰርተን ከድርጅቱ ጋር ያለን ውል በ6 ወር ውስጥ መኪኖችን ተረክበን ወደ ስራ ልንገባ ነው ነገር ግን ሂደቱ በፈጠረብን እክልና መስተጓጎል 2 ዓመት ሆነን በዚህ ጊዜ ውስጥ መኪኖቹን አግኝተን ወደ ስራ መግባት አልቻልንም።
አሁንም ፍትህ እናግኝ ፤ እንስተናገድ 900 አባላቶችን ነን የ900 አባላቶች ቤተሰብ ጨምሮ እንግልት ላይ ነው ያለነው። "

ኤርትራ ተጠባባቂ ጦሯን ጠርታለች ?
ኤርትራ ቢቢሲ (BBC)ን ጨምሮ ሌሎችም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ከሰሞኑን ያወጡትን መረጃዎች " ሀሰተኛ " ነው ብላለች።
በርካታ ዓለም ረቀፍ ሚዲያዎች ባለፈው ሳምንት ኤርትራ ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በታች የሆኑ ተጠባባቂ የጦር ኃይሉ አባላት በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንደተጠሩ ዘግበዋል።
ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በተጨማሪ የካናዳ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ተከትሎ የአካባቢ ባለሥልጣናት ለሠራዊቱ በአጠቃላይ የክተት ጥሪ አቅርበዋል ሲል አሳውቋል።
በኤርትራ የሚገኙ ዜጎቹን እንቅስቃሴያቸውን እንዲገድቡ መክሯል።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በኤርትራ መቀመጫውን ያደረገው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ነታባይን መልዕክት አጋርተዋል።
እሳቸው በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያጋሩት መልዕክት ቢቢሲ ያሰራጨው ሀሰተኛ ዜና መሆኑን ይገልጻል።
ቢቢሲ " ምንጮች ገለፁ " ብሎ ያሰራጨው መረጀ ሀሰተኛ መሆኑን የሚገልፀው ይኸው ሚኒስትሩ ያጋሩት ፅሁፍ ቢቢሲ በ2018 ከኢትዮጵያ ጋር በነበረው የድንበር የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተወሰደ አሮጌ ፎቶ ጋር ሀሰተኛ ዜናውን ለማጀብ ተጠቅሟል ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል " ኡልሪህ ከፕል " ለተባለ የጀርመን ድረ ገጽ በሰጡት ቃል የተሰራጨው ዜና ሆን ብሎ እውነታውን ያዛባ ፣ የተጋነነና ከእውነታው የራቀ ነው ብለውታል።
አቶ የማነ ኤርትራ አጠቃላዩን ሕዝቧን ወደ ሠራዊቷ እያስገባች እንዳልሆነም በመግለፅ መሬት ላይ ያለው እውነታ ሆን ተብሎ እንዲዛባ እና እንዲጋነን ተደርጓል ብለዋል።
የተወሰኑ የተጠባባቂ ኃይል አባላት የተጠሩ ቢሆንም ቁጥራቸው ግን በጣም ጥቂት መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

#Somalia
የጎረቤት ሶማሊያ መንግስት በ " አልሸባብ " ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን በዚህ ዘመቻ በርካታ የቡድኑን ታጣቂዎች መግደል ጨምሮ ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን ነፃ አድርጓል።
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ከጉሪኤል ከተማ በስተምስራቅ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የ " ጃው " መንደር በአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ ከአልሸባብ ነፃ ማድረጉ ተሰምቷል።
ጃው በጉሪኤል እና ኤልቡር መካከል ያለ ስልታዊ ቦታ መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጿል። ከዚህ አካባቢ በፊት ባለፈው አርብ በተሰራ ኦፕሬሽን ሳጋልጌድ፣ ያሶማን እና አቦሬይ የሚባሉ አካባቢዎች ከአልሸባብ ነፃ ማድረግ ተችሏል።
በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር በአካባቢው ማህበረስብ እገዛ በሂራን ክልል በያሶማን መንደር አቅራቢያ በትናንትናው እለት ባካሄደው ዘመቻ 75 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸው ተመላክቷል።
በአጠቃላይ በዚሁ ክልል እስካሁን በተካሄደ የፀረ ሽብር ዘመቻ ኦፕሬሽን 200 የቡድኑ ታጣቂዎች መገደላቸውና 30 መንደሮች ከአልሸባብ ነፃ መደረጋቸውን የሀገሪቱ ጦር አሳውቋል።
Photo Credit : SNTV

#ETHIOPIA በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል። በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል።…
#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር በአብዛኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በዛሬው እለት መጀመሩን አሳውቋል።
በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ በይፋ በተጀመረው የ2015 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትና መመሪያ ማስተላለፋቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ የትምህርት ዘመኑ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል።
የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ የሚከናወነው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውሷል።
ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ

#የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ምርጫ_ቦርድ @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ➡️ ኢትዮጵያ ሌበር ፓርቲ !
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ን ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለመመለስ የተሰባሰቡ አደራጆች የፓርቲውን መጠሪያ ወደ " የኢትዮጵያ ሌበር ፓርቲ " በመቀየር ለምርጫ ቦርድ በድጋሚ ማመልከቻ ማስገባታቸውን ኢትዮጵያ ኢንይደር አስነብቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን አደራጆች ማመልከቻ ባለፈው ሳምንት አርብ መቀበሉ ተረጋግጧል።
በደርግ ዘመነ መንግስት ገዢ ፓርቲ የነበረውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ዳግም ለማቋቋም የተሰባሰቡ አደራጆች ከዚህ ቀደም ለምርጫ ቦርድ ያቀረቡት የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ ጥያቄ ወድቅ ተደርጎ እንደበር ይታወሳል።
Credit : www.ethiopiainsider.com