TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፦
- በጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ወላይታ፣
- ጌዴኦ፣
- ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ደግሞ ፦
- በአሌ፣
- ቡርጂ፣
- አማሮ፣
- ባስኬቶ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች በምርጫ አስፈጻሚነት የነበሩ በቀጣይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ለሚካሄደው #ሕዝበ_ውሣኔ በምርጫ አስፈጻሚነት በድጋሚ ለመሣተፍ ፍቃደኛ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡለት ጠይቋል።

ፍቃደኛነታቸውን ለመግለፅም ከላይ የተጻፈው መልዕክት (text message) በእጅ ስልካቸው ሲደርሳቸው አንድን ተጭነው እንዲመልሱ መልዕክት ተላልፏል።

መልዕክቱ ከታች ከተያያዘው ማስፈንጠሪያ (Link) ጋር ከደረሳቸው የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ፍቃደኝነታቸውን ማሳየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

http://nebecertificate.org.et/recruitment 

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ካሉበት ሆነው  ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://yangx.top/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
#አዲስአበባ_እና_አካባቢዋ!

በአዲስ አበባና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ 511 ድንገተኛ አደጋዎች የ115 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ከ200 በላይ ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

👉 362 የእሳት አደጋ ፤ 149 የጎርፍ፣ የኮንስትራክሽን፣ የወንዝና የኩሬ አደጋዎች ደርሰዋል።

👉 የ115 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በ200 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

👉 ከ115 ሰዎች መካከል 14ቱ በእሳት አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን  ቀሪዎቹ 101 ሰዎች በተለያየ ድንገተኛ አደጋ ነው ሕይወታቸው ያለፈ ነው።

👉 577 ሚሊየን 780 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ፤ በአንጻሩ በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ 39 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ድኗል።

👉 የ137 አደጋዎች መንስኤ የታወቀ ሲሆን 63  በኤሌክትሪክ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ናቸው። አብዛኛዎቹ አደጋዎች ያጋጠሙት በጥንቃቄ ጉድለት ነው።

#ማሳሰቢያ

ሰሞኑን የበዓል ወቅት እንደመሆኑ ከፍተኛ የኃይል አጠቃቀም እንደሚኖር ስለሚኖር ህብረተሰቡ ከምግብ ማብሰል ጋር ተያይዘው ለሚሠሩ ሥራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#GambellaRegion

በጋምቤላ ክልል የ2014 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 79 ነጥብ 5 በመቶ ያህሉ ወደቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን ተገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ፦

👉 አማካይ ውጤት ለወንዶች 48 በመቶ እና ለወንድ አካል ጉዳተኞች 46 በመቶ / ለሴቶች 44 በመቶ እና ለሴት አካል ጉዳተኞች 42 በመቶ እንዲሆን ተወስኗል።

👉 ለፈተናው ከተቀመጡ አጠቃላይ 16 ሺህ 629 ተማሪዎች 7,395 ወንዶችና 5,843 ሴት ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል አልፈዋል።

👉 በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተማሪዎች ካርድ ይሰጣል።

@tikvahethiopia
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ድንበር ውስጥ መያዝ የሚቻለውን የውጭ ምንዛሪ መጠን የሚደነግገውን መመርያ በማሻሻል በአገሪቱ ድንበር ውስጥ በውጭ ምንዛሪ ምንም ዓይነት ግብይት እንዳይደረግ ክልከላ ማድረጉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በብሔራዊ ባንክ " ልዩ ፈቃድ " ካልሆነ በስተቀር የውጭ ምንዛሪ ይዞ መገኘት የተከለከለ ሲሆን፣ በስጦታና በረድዔት መልክ ለሦስተኛ ወገን በጥሬ ገንዘብ ማስተላለፍም ተከልክሏል፡፡

ከ6 ዓመታት በፊት በወጣው ነባሩ መመርያ ውስጥ እነዚህ ክልከላዎች አልነበሩም፡፡

በአዲሱ መመርያ " በልዩ ፈቃድ " የተባለው ምናልባት ለአስጎብኚ ድርጅቶች፣ ለሆቴሎችና ለቀረጥ ነፃ መደብሮች ይሆናል የሚል ግምት ቢኖርም በመመርያው ላይ ግን አልተገለጸም፡፡

በብሔራዊ ባንክ ገዥ በሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ ተፈርሞ የወጣውና ከሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው አዲሱ መመርያ መሠረት ፦

👉 ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ይዞ ከውጭ አገር የሚመጣ ሰው በብር መመንዘር እንዳለበት ተገልጾ፣ ይህም ከተፈቀደው መጠን በላይ ከሆነና የውጭ ዜጋ ከሆነ ገንዘቡ በከፈተው ሒሳብ (አካውንት) ውስጥ እንደሚቀመጥ ተገልጿል፡፡

👉 በአዲሱ መመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚመጡና ለአጭር ጊዜ ለሚቆዩ ዜጎች የሚፈቀደው የገንዘብ መጠን ግን ከፍ ተደርጓል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡና ለሚወጡ ሰዎች መያዝ የሚፈቀድላቸውን የገንዘብ መጠን የሚደነግገውን መመርያ ከ6 ዓመት በኋላ በማሻሻል፣ የገንዘቡን መጠን ከእጥፍ በላይ ከፍ አድርጓል፡፡

• ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ዜጎችም፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን 10 ሺሕ ዶላር ወይም በሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች ተመጣጣኝ ይዘው ሲመጡ፣ በኢትዮጵያ ብር መንዝረው መጠቀም ይችላሉ፡፡ ከ10 ሺሕ ዶላር የበለጠ ይዘው ከመጡ ግን፣ ለጉምሩክ በማሳወቅ በግላቸው የውጭ ምንዛሪ አካውንት ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በነባሩ መመርያ ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ ዜጎች መያዝ ይፈቀድ የነበረው 4 ሺሕ ዶላር ብቻ ነበር፡፡

• ነዋሪነታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሆኑ ሰዎች ከውጭ ሲመጡ እስከ 4 ሺሕ ዶላር ወይም በሌሎች የውጭ ምንዛሪዎች ተመጣጣኙን ይዘው መምጣት የተፈቀደላቸው ሲሆን፣ ይህ በነባሩ መመርያ አንድ ሺሕ ዶላር ብቻ ነበር፡፡

👉 የኤምባሲ ሠራተኞች፣ ጊዜያዊ ሠራተኞች፣ እንዲሁም ለስብሰባና ለተለያዩ ጊዜያዊ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ዜጎች የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ከቻሉ ከአሥር ሺሕ ዶላር በላይ ይዘው እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡

👉 ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣም ሆነ ከኢትዮጵያ የሚወጣ ሰው ከ3 ሺሕ በላይ መያዝ አይፈቀድለትም፡፡ ይህም በነባሩ መመርያ 1 ሺሕ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ጂቡቲ የሚሄዱ ሰዎች በተለየ ሁኔታ እስከ 10 ሺሕ ብር መያዝ የሚችሉ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት 4 ሺሕ ብር ብቻ ነበር፡፡

👉 በአዲሱ መመርያ ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ይዘው የሚመጡ ሰዎች በሕጋዊ የምንዛሪ ቢሮዎች ወደ ብር መቀየር ሲኖርባቸው፣ ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ከብር ውጪ ለመገበያያ ሌላ ገንዘብ መጠቀም ስለማይፈቀድ ነው። ምንዛሪ ማድረግ የሚችለውም ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መግባቱን የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ 30 ቀናት ውስጥ ነው፡፡

👉 በድንበር በኩል የሚገቡ ሰዎች 500 ዶላር ወይም በሌሎች ምንዛሪ ተመጣጣኙን ይዘው መግባት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በድንበር አካባቢ ለሚገኙ የኢትዮጵያ የጉምሩክ ጣቢያዎች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-09-07
#Ethiopia #Somalia

" የፕሮግራሙ ይዘት የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ #የማይወክል ነው " - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ትላንት በኢትዮጵያ ብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ (Etv World) በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰራጨ ፕሮግራም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ፕሮግራሙን ተመልክተው ቅሬታቸውን የገለፁ በርካቶች ሲሆኑ ፤ ፕሮግራሙን በተመለከተ የሶማሊያ ሚዲያዎች ሲቀባበሉት ውለዋል።

በEtv የእንግሊዝኛው የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ አሁን ድረስ ያለው ይኸው ፕሮግራም ስለ ሱማሊያ የተለያዩ የሚያነሳ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ አዲሱን ፕሬዜዳንት እና መንግስታቸውን የሚመለከት ነው።

ይህንን ፕሮግራም በተመለከተ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አጭር መግለጫን አውጥታለች።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት በ “Etv WORLD” ፕሮግራም ስለ ሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በሚመለከት በቀረበው ፕሮግራም ላይ ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ መመልከቱን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ የፕሮግራሙ ይዘት የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ የማይወክል እና ከሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጋር የማይጣጣም ነው ብሎታል።

@tikvahethiopia
#UNSC

አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ አይርላንድ፣ ኖርዌይ እና አልባኒያ በኢትዮጵያ ጉዳይ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባ እንዲያካሂድ ጠይቀው የነበር ቢሆንም በም/ቤቱ ባለው አመግባባት ሳቢያ መካሄዱ እንደሚዘገይ ተሰምቷል።

ከዲፕሎማቶች ሰማሁኝ ብላ የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ አማንዳ ፕራይስ እንደገለፀችው ፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ተጠይቆ የነበረው ለዛሬ ሀሙስ ቢሆንም እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ሊዘገይ ይችላል።

ይህ የሆነውም ስብሰባው በዝግ ወይስ ክፍት ሆኖ በግልፅ ይካሄድ በሚለው ላይ በምክር ቤቱ አባላት ውስጥ ባለው አለመግባባት መሆኑ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል ፤ ተመድ ያቋቋመው የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ኤክስፐርቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዳግም ያገረሸው ግጭት እንደሚያሳስበው ባወጣው  መግለጫ ገልጿል።

ኮሚሽኑ የኤርትራ ወታደሮችም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ይገኛሉ ያለ ሲሆን ይህም ግጭቱ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይዛመት ስጋት አለኝ ብሏል።

ኮሚሽኑ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙና ወደ ውይይት ሂደቱ እንዲመለሱ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ ብሏል።

በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ ላይ ካለው ስጋት አንፃርም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ሁኔታ መመልከቱን ኮሚሽኑ እንደሚቀበለው በመግለጫው አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ምክር ቤቱ የሲቪል ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና ቀጣናውን የበለጠ ሊያናጉ የሚችሉ ግጭቶችን ለመከላከል በወጣው ቻርተር መሰረት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታዎችን አጀንዳው አድርጎ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ " ኒውስ ሀወር " ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ " ኒውስ ሀወር " ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ! @tikvahethiopia
አምባሳደሩ ምን አሉ ?

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር፤ አሜሪካ ግጭቱን በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል " - አምባሳደር ተፈሪ መለሰ

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ ኒውስ ሀውር ጋር ቆይታ አድርገው የነበረ ሲሆን በዚህም ወቅት አሁን ስላለው ሁኔታ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ፤ የተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኃላ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ በየቀኑ ጥሩ በሚባል ሁኔታ እየሄዱ ነበር ብለዋል። በአየር በረራዎችም መድሃኒትን ጨምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ሲጓጓዙ እንደነበር ገልፀዋል። ይህ ሁሉ ወደ ሰላም ጥረቱ ለማምራት ሲሆን ለዚህ ጥረት ምላሹ ግን  ያ አልነበረም (ሰላም አልነበረም) ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ እንዳሉ እና ጉብኝታቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሰደሩ ...

" ከዚህ በፊትም እዚያው ነበሩ ፤ የአውሮፓ ህብረት እና የዩናይትድ ኪንግደም ልዩ ልዑካንም ኢትዮጵያ ነበሩ ህወሓት /TPLF ወደ ሰላም ጠረጴዛውን እንዲመጣ ለማበረታት። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ገና ከጅምሩም አቋሙ ገልጽ ነው በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ፤ ኤርትራ ወደ ግጭቱ ዳግም መግባቷን በመግለፅ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር መስራቷን እንድታቆም እና በኢትዮጵያ በኩል የሚፈፀሙ የአየር ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቃለች በሚል ለተነሳው ....

" ይህ በቀላሉ እውነት አይደለም። ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር ነች ፤ ከህወሀት ጋርም የራሳቸው ታሪክ አላቸው። እንደሚታወቀው ከኤርትራ ጋር ያለውን አለም አቀፍ ድንበር የሚቆጣጠሩት የህወሓት ሃይሎች ናቸው እንጂ የኢትዮጵያ ጦር አይደለም፤ ድንበሩ ለኛ ነው እኛ ግን እየተቆጣጠርነው አይደለም " ብለዋል።

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህወሓትን ለመደምሰስ እንደሚፈልግ ተናግሯል በዚህስ ላይ ...

" የኤርትራን መንግስት ወክለን ልንናገር አንችልም። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ግን እነሱም ህወሓት ወደ ዋና ከተማዋ አስመራ በተኮሳቸው ሚሳኤሎች እና ሮኬቶች ተተንኩሰዋል። (በህወሓት) "

የኢትዮጵያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ ሰፍረዋል ? በሚል ለቀረበ ጥያቄ ...

" አይ ፤ /No / ፤ ያ መረጃ የለኝም " ሲሉ መልሰዋል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች እዛ እንዳሉና ከፕሬዜዳንት ኢሳያስም ትዕዛዝ እንደሚቀበሉ የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ በሚል ለተነሳው ሀሳብ...

" ያን ለማመን ይከብዳል ምክንያቱም ጦራችን #ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሀገራት እንደነበረው ለሰላም አስከባሪ ሃይል #ካልተጠራን በስተቀር ወታደሮቻችን ኤርትራ የሚሄዱበት ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

የኤርትራስ ወታደሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ወይ  ? ለሚለው ጥያቄ ...

" አይ / no / " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ያለው ከበባ እንዲያበቃ በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ወታደሮች ይውጡ በሚለው ላይ ምላሹ " የሉም " የሚል ነው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄም ...

" ጥሩ ! እኛ እስከሚገባን ምንም አይነት እገዳ የለም። በዓለም አቀፍ ህግ የዓለም አቀፍ ድንበሮቻችንን የመከላከል ኃላፊነት አለብን (መንግስት ኃላፊነት አለበት) ነገር ግን አሁን ላይ ከኤርትራ ጋር ባለው ድንበር ላይ እየተፈጠረ ላለው ነገር ተጠያቂ አይደለንም " ብለዋል።

ለአዲስ የተኩስ አቁም እድል ይኖር እንደሆነ ተጠየቀው ...

" መንግስት እስካሁን በመከላከል አኳኋን ላይ ነው ያለው። በትግራይ ውስጥ ጥቃት እየፈፀምን አይደለም ፤ እስካሁን በመከላከል ላይ ነን ፤ እንዲሁም ህወሓት ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመጣ ጥሪ እያደረግን ነው፤  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን እንዲያደርግ እናበረታታለን ምክንያቱም በጦርነት ምንም መፍትሄ የለም። " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ ኤርትራ ዳግም ወደ ግጭት ገብታለች በሚል ከማውገዟ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ባሉት የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ምን መልዕክት ደረሰ በሚል ለተነሳ ጥያቄም ...

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር። አሜሪካ ይየሶስተኛውን ዙር ግጭት / ጦርነት በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል። " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
አቶ አብይ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አብይ ኤፍሬም በድንገተኛ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምራን ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ነገ ሀሙስ " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ይካሂዳሉ። በዚህም ወቅት ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞቶ የሚተላለፍበት እንዲሁም ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ የሚጠየቅበት መርሀግብር ይኖረናል ተብሏል። የእግር ጉዞው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ በካዛንቺ ሴቶች አደባባይ ጀምሮ መስቀል አደባባይ…
ፎቶ ፦ ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ዛሬ ሀሙስ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የእግር ጉዞ ተሳያፊዎቹ ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በሀገራችን ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ ጠይቀዋል።

በዕለቱ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል ፦

🪧 #በቃን መደፈር !
🪧 የሀገር ሰላም የሴቶችም ሰላም እና ደህንነት ነው !
🪧 የሴቶች ሰውነት የጦር ሜዳ አይደለም !
🪧 ጦርነት የሞት፣ የረሃብ፣ የስደት እና የጥፋት መንስኤ እንጂ የልማት መሳሪያ አይደለም !
🪧 በጦርነት የትኛውም አይነት አለመግባባት መፍትሄ አግኝቶ አያውቅም። እኛ የኢትዮጵያ ሴቶች ሰላማዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን እንደግፋለን የሚሉት ይገኙበታል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ ሴት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት

@tikvahethiopia