TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ የኬንያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እስካሁን ድረስ ይፋ አልሆነም። ከሰዓታት በፊት ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት ሊያሳውቅ አልቻልም። ውጤት በሚገለፅበት ቦማስ የድምፅ ቆጠራ ማዕከልም እስከ መደባደብ የደረሰ አለመግባባት ተፈጥሯል። በጎረቤታችን ኬንያ እየሆነ ስላለው ጉዳይ ተከታትለን እናሳውቃለን። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኬንያ

በኬንያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ አለመግባባት እና ውዝግብ ተፈጥሯል።

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ያሳውቃሉ ተብለው በሚጠበቁት የኮሚሽኑ ባለሥልጣንት መካከል ክፍፍል መፈጠሩ ነው የተነገረው።

በዚህም 4 የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በይፋ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ከሚነገርበት ማዕከል ውጪ መሃል ናይሮቢ በሚገኘው ሴሬና ሆቴል ውስጥ ሂደቱን ጥያቄ ላይ በሚጥል ሁኔታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ከ6ቱ ኮሚሽነሮች አራቱ በሰጡት መግለጫ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት አያያዝ “ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ፣ ውጤቱን በኃላፊነት ለመውሰድ አንችልም” በማለት ገልጸዋል።

ውጤት በኮሚሽነሩ ዋፉላ ቺቡካቲ አማካይነት ይፋ ይደረግበታል በተባለው የቦማስ ማዕከል ውዝግብና ግብግብ ተፈጥሮ ታይቷል።

ለደቂቃዎች በአዳራሹ የነበረ ውጥረት ረግቦ በአሁን ሰዓት በአዳራሹ መርሀግብሩ ቀጥሏል። በአዳራሹ ውስጥ ሩቶ ቢገኙም ዋነኛ ተፎካካሪው ራይላ ኦዲንጋ የሉም።

በተለያዩ የኬንያ አካባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱም ተነግሯል።

Via BBC
Video Credit : CitizenTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ በኬንያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ አለመግባባት እና ውዝግብ ተፈጥሯል። የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ያሳውቃሉ ተብለው በሚጠበቁት የኮሚሽኑ ባለሥልጣንት መካከል ክፍፍል መፈጠሩ ነው የተነገረው። በዚህም 4 የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በይፋ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ከሚነገርበት ማዕከል ውጪ መሃል ናይሮቢ በሚገኘው ሴሬና…
#BREAKING

ዊሊያም ሩቶ የኬንያን ምርጫ ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ።

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን በቦማስ ማዕከል ዊልያም ሩቶ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ይፋ አድርጓል።

ዊልያም ሩቶ እና ራይላ ኦዲንጋ በተቀራራቢ ውጤት አንገት ለአንገት ተናንቀው እስከ አሁኗ የውጤት መግለጫ ሰዓት የደረሱ ሲሆን በመጨረሻም የፕሬዜደንታዊ ምርጫው አሸናፊ ዊሊያም ሩቶ መሆናቸውን በቦማስ ማዕከል ባለው ኮሚሽን ተገልጿል።

ሩቶ ያሸነፉት ከተሰጠው ጠቅላላ ድምፅ 50.49% በማግኘት ሲሆን ራይላ ኦዲንጋ 48.8% ድምፅ አግኝተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ዊሊያም ሩቶ የኬንያን ምርጫ ማሸነፋቸው ይፋ ሆነ። የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን በቦማስ ማዕከል ዊልያም ሩቶ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ይፋ አድርጓል። ዊልያም ሩቶ እና ራይላ ኦዲንጋ በተቀራራቢ ውጤት አንገት ለአንገት ተናንቀው እስከ አሁኗ የውጤት መግለጫ ሰዓት የደረሱ ሲሆን በመጨረሻም የፕሬዜደንታዊ ምርጫው አሸናፊ ዊሊያም ሩቶ መሆናቸውን በቦማስ ማዕከል ባለው ኮሚሽን ተገልጿል። …
ተቃውሞ እና ደስታ በጎረቤት ኬንያ !

ዛሬ በኬንያ የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ውጤቱን እንደማይቀበሉ የገለፁ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸው ፤ በአንዳንድ ቦታዎችም አመፅ መቀስቀሳቸው ተሰምቷል።

ከዚህ በተቃራኒው በጠባብ ውጤት እንዳሸነፉ የተነገረላቸው የዊሊያም ሩቶ ደጋፊዎች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እየጨፈሩ በመግለፅ ላይ ናቸው።

የራይላ ደጋፊዎች በተለይም በኪሱሙ መንገድ በመዝጋት ፣ ጎማዎችን በማቃጠል የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ገልፀዋል። ደጋፊዎቹ ሰዎች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩም እንደነበር ታይቷል።

የፀጥታ ኃይሎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ እስከመተኮስ መድረሳቸውም ተሰምቷል።

ኪሱሙ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች በብዛት ያሉበት ነው።

በሌላ በኩል በኪቤራ የራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎች " ራይላ ከሌለ ሰላም የለም " እያሉ ጎማ በማቃጠል የምርጫው ውጤት መጭበርበሩን በመግለፅ እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

ከዚህ በተቃራኒ በተለያዩ ከተሞች የዊሊያም ሩቶ ደጋፊዎች በውጤቱ ደስታቸውን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፍሪካ ቀንድ 🇸🇴🇪🇹🇰🇪

እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ በአፍሪካ ቀንድ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች #በድርቅ#በግጭት እና #በምግብ_ውድነት ምክንያት አስከፊ ለሆነ ረሃብ ተጋልጠዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ላሉ ቤተሰቦች እገዛ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

#ShareTheMeal (በUN | WFP ስር ያለ) በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ቤተሰቦች የድንገተኛ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ለዚሁ ስራ የሚውልን ገንዘብ ከለጋሾች በመተግበሪያው እንዲሁም በድረገፁ በኩል እያሰባሰበ ይገኛል። https://t.co/rjY1JlrJTl

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት #ነፃ እና #አስገዳጅ እንደሚሆን አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ይደረጋል " ብለዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን ገልፀው መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/MoE-08-16 (ኢቢሲ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲሱ ስርዓተ ትምህርት " የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ…
#HappeningNow #AddisAbaba

በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ በሚግባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዙሪያ ውይይት ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ስልጠና እና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባውን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ ከግል እና መንግስታዊ ካልሆኑ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ መካሄድ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደተገኘው መረጃ ፤ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የ2ኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

@tikvahethiopia
#Scotland

ስኮትላንድ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን የሚያስከብር ሕግን ማፅደቋን ቢቢሲ አስነብቧል።

ወዲያው ተግባራዊ እንዲሆን የተደረገው ሕግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ የማግኘት መብትን ለመጠበቅ አዲስ ሕግ ያወጣች የዓለማችን የመጀመሪያዋ አገር በመሆን እንድትመዘገብ አድርጓታል።

በዚህ ሕግም ሕዝብ የሚገለገልባቸው ህንጻዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች እና ሌሎች ተቋማት የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን #በነጻ_ለማቅረብ ይገደዳሉ።

የየአካባቢው ባለሥልጣናት ማንኛውም ምርቶችን የሚፈልግ ሰው በነጻ እንዲያገኝ የማመቻቸት ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#Amhara

አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህም ፦

አቶ ደጀኔ ልመንህ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሲሾሙ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ም/ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኀላፊ አድርገው ሾመዋል።

በተጨማሪም ረ/ኮሚሽነር ሠይድ አህመድ ም/ኮሚሽነር እና የአስተዳደር ልማት ድጋፍ ዘርፍ ኀላፊ እንዲሁም ረ/ኮሚሽነር እንዬው ዘዉዴ ም/ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኀላፊ አድርገው ሾመዋቸዋል።

መረጃው ከአማራ ፖሊስ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ #YALI2023

የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎ ሺፕ ፕሮግራም የ2023 (Mandela Washington Fellowship) ማመልከቻ ዛሬ ክፍት ተደርጓል።

በአህጉሪቱ ያሉ ወጣቶች ተወዳድረው #በአሜሪካ ሀገር በሚደረግ ሥልጠና ላይ እንዲሳተፉ እድሉ ተመቻችቶላቸዋል።

ከዚህ ቀደም በርካታ #ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እድሉን ተጠቅመው ይህንን ሥልጠና ወስደዋል።

በሥልጠናው ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶችን ለማየትና ለማመልከት ይህን ይጫኑ👇
https://www.mandelawashingtonfellowship.org/apply/

👉 Application Timeline :

• August 16, 2022 | Application opens

• September 13, 2022 | Application deadline

• November 2022 – January 2023 | Semi-finalists interviewed by local U.S. embassies and consulates

• March 2023 | Applicants are notified of their status

• May 2023 | Visa processing and Pre-Departure Orientations for Finalists

June 2023 | Fellowship begins in the United States

Via @tikvahethmagazine
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተነሳበት ተቃውሞ ምንድነው ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ስራ ሊጀምር በዝግጅት ላይ በሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።

የዘመቻው ምክንያት ቅጥር የሚፈፀመው እና ውክልና የሚሰጠው አግላይ በሆነ መንገድ ነው በሚል ነው።

#በተለይ ደግሞ በድርጅቱ የሰራተኞች አቀጣጠር እና ውክልና አሰጣጥ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተወላጆች ድርጅቱ ከአድሎ እንዲታቀብ ፣ ኢትዮጵያን እንዲመስል፣ ሁሉንም እንዲያቅፍ ካልሆነ በኦሮሚያ ክልል ያለው ህዝብ የድርጅቱ ደንበኛ እንዳይሆንና አገልግሎቱን እንዳይጠቀም ዘመቻ እንደሚያካሂዱ አስጠንቅቀዋል።

ከተነሱ ቅሬታዎችና ፍትሃዊ የሆነ አሰራር ተጓድሏል ከተባሉ ጉዳዮች መካከል የሲም ካርድና ሞባይል ካርድ አከፋፋዮች ላይ አድሎ አለ፣ የህትመት የማስታወቂያ የፕሮዳክሸን ስራዎች በአድሎ ተሰጥተዋል፤ እየተፈፀመ ያለው ቅጥር በቂ ልምድ ያላቸውን የኦሮሚያ ተወላጆችን ባገለለ መልኩ ነው፤ በድርጅቱ በየእርከኑ የተመደቡ ኃላፊዎች በአድሎ የተመደቡ ናቸው፤ ድርጅቱ ኦሮሚያ ክልል ላይ አፋን ኦሮሞ ላለመጠቀም ሲያንገራግር ነበር የሚሉ ናቸው።

ጉዳዩን በተመለከተ በቀጥታ ከድርጅቱ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ፤ ነገር ግን ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ ዘመቻውን እየመሩ ናቸው ካላቸው ተወካዮች ጋር መነጋገሩን አሳውቋል።

ሳፋሪኮም በውይይቱ የተወካዮቹን ስጋት በጥሞና ማዳመጡን ገልጿል። " ሁሉንም ኢትዮጵያ ሚወክል ድርጅት ያለአንዳች ወገንተኝነትና አድሎ እየገነባን እንደሆንን አረጋግጠንላቸዋል " ብሏል።

" በማንኛውም ጊዜ ለውይይት ዝግጁ ነን " ያለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፤ " ሁሉንም ቋንቋዎች እና ባህሎች ባከበረ መንገድ ሁሉንም ኢትዮጵያ ለማገልገል ቁርጠኞች ነን " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia