TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ የተመረቀው የሳርቤት – ጎፋ ማዞርያ – የፑሽኪን -ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት።

• ግንባታው የተጀመረው ፦ በ2012 ዓ.ም

• ርዝመት እና ስፋት ፦ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ30 እስከ 45 ሜትር የጎን ስፋት

• ፕሮጀክቱ ፈጣን የአውቶብስ መንገድን ጨምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ሊያስተናግድ የሚያስችል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ እና ከመሬት ከፍ ብሎ የተገነባ ረጅም መሳለጫ ድልድይ ያካተተ ነው፡፡

• ከቂርቆስ፣ ከጎተራ፣ ከጎፋ ፣ ከሳር ቤት ፣ ከሜክሲኮ እና ከቄራ የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ያሳልጣል።

• የወጣበት ገንዘብ እና ምንጩ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አማካኝነት ከቻይና መንግሥት በተገኘ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር የተገነባ ነው፡፡

#ኤፍቢሲ

Photo Credit : Mayor Office AA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US #SOMALIA አሜሪካ ትላንትና ማክሰኞ ፤ ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመተባበር በፈፀመችው የአየር ድብደባ 4 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላትን መግደሏን አሳውቃለች። የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ ጦር ላይ በቤልድዌይኔ ጥቃት የከፈቱ ሲሆን ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር በአየር በፈፀመው ድብደባ 4 የቡድኑን አባላት መግደሉ ተገልጿል። አሜሪካ እርምጃው በሶማሊያ መንግስት በኩል ፍቃድ ኖሮት መፈፀሙን…
#Somalia

የጎረቤት ሶማሊያ ብሄራዊ ጦር በሂራን ክልል እያካሄደ ባለው የፀረ ሽብር ዘመቻ ትላንት በማሃስ አውራጃ መሀመድ ወህሊዬ ዋሱጌን የተባለ የአልሸባብ ቡድን ቀደኛ ሰው ጨምሮ 14 ታጣቂዎችን መግደሉን የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

በተጨማሪ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በጦሩ ተይዘዋል።

አሜሪካ ደግሞ የአየር ላይ ጥቃት በመፈፀም የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችን መደበቂያ ማውደሟ ተገልጿል።

አሜሪካ የአየር ድብደባ የፈፀመችው የፀረሽብር ኦፕሬሽን እያካሄደ የሚገኘውን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦርን ለመደገፍ ነው።

ከቀናት በፊት አሜሪካ በሶማሊያ መንግስት ጥያቄ የአየር ጥቃት መፈፀም መጀመሯን መነገሩ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል። የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል። የ2014…
#MoE

" የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Kenya🇰🇪

በጎረቤት ኬንያ ዛሬ ልዩ ቀን ነው ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ከቀናት በፊት የተካሄደው ምርጫ ውጤት የሚገለፅበት በመሆኑ ነው። ህዝቡ ባለፉት ቀናት የምርጫውን ውጤት በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር።

በኬንያ ምን እየሆነ ነው ያለው ?

- የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ ከደቂቃዎች በኃላ ገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።

- ውጤት በሚገለጽበት ቦማስ በሚባለው የድምጽ ቆጠራ ማዕከል ጠንካራ ጥበቃ እየተካሄደ ነው።

- ዲፕሎማቶች የምርጫ ውጤት ለመስማት ተሰይመዋል።

- ገና ውጤት ሳይወቅ ኬንያውያን የሚደግፏቸው ዕጩዎች ምርጫውን ያሸንፋሉ ብለው ወደ ጎዳና በመውጣት ደስታቸውን መግለጽ ጀምረዋል።

- ራይላ ኦዲንጋ ከፍተኛ ድጋፍ አላቸው በሚባለው የምዕራብ ኬንያ ግዛት በሆነችው ኪሱሙ ደጋፊዎቻቸው አደባባይ ወጥተዋል። በኤልዶሬት ከተማ ደግሞ ነዋሪዎች ሩቶ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ ብለው ወደ አደባባይ ወጥተዋል።

- ዛሬ የምርጫ ውጤት ይገለፃል መባሉ ተከትሎ የተለያዩ የንግድ ተቋማት የተዘጉ ሲሆን አብዛኛው መስሪያ ቤቶችም ዛሬ ከሰዓት ሰራተኞቻቸውን ወደ ቤት ሸኝተዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ እና ካፒታል ኤፍ ኤም ኬንያ

@tikvahethiopia
#ውብ_አረቢያን_መጅሊስ

ከአውሮፓና ከእስያ በሚመረቱ ጥሬ እቃ በብቁ ባለሞያ በዘመነ ማሽን ውብ አረቢያን መጅሊስ የሚያመርታቸውን ውብ እና ማራኪ የሆኑ መጅሊሶቻችን እና ሶፋዎችን እንካቹ ስንል 👉 በ9 ቅርጫፎቻችን ስንጠበቅዎ በታላቅ ደስታ ነው 0910222244 / 0954111133 / 0954111100
ተጨማሪ ፎቶ ለመምረጥ ሊንኩን የጫኑት https://yangx.top/wubeare
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕ/ት አቶ እስክንድር ነጋ ፤ በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው አሳወቁ። አቶ እስክንድር ሀምሌ 16/2014 ዓ/ም ካሉበት ቦታ ሆነው ፃፉት በተባለውና በፓርቲው የፌስቡክ ገፅ ላይ…
#BALDERAS

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከፕሬዝደንትነታቸው የለቀቁት አቶ እስክንድር ነጋ አሁንም የት እንዳሉ እንደማያውቅ ገልጿል።

የፓርቲው ኃላፊዎች ዛሬ ሰኞ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ጀምሮ አቶ እስክንድር ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጽህፈት ቤት እና ከሥራ አስፈጻሚው ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ገልጸዋል።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምኃ ዳኘው ከተናገሩት ፦

" አቶ እስክንድር ምንም የነገረን ነገር ባለመኖሩ፤ የት እንደሔደ እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ባልታወቀበት ሁኔታ አድማጭን የሚያረካ መልስ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አልነበረም።

በአሜሪካ ሀገር የሚገኙት የአቶ እስክንድር ባለቤት አልደነገጡም ፤ ከፓርቲው ሆነ በውጭ አገር ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ ማብራሪያ አልጠየቁም። በዚህ ምክንያት የመታፈን አደጋ እንዳልደረሰበት ገምተናል።

አቶ እስክንድር ያሉበትን ሁኔታ ያሳውቁናል ብለን በመጠባበቅ ላይ ሳለን ነው በአሜሪካ ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ በኩል የመልቀቂያ ደብዳቤው ይፋ የሆነው። "

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ቀለብ ሥዩም ፦

" ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ወዲህ አቶ እስክንድርን በስልክም ይሁን በአካል አግኝተናቸው አናውቅም።

መንግሥት አቶ እስክንድርን እንዳላፈናቸው እና እንዳላሰራቸው ፓርቲው ያምናል።

ከቤተሰቦቻቸው ደህና መሆናቸው ተገልጾልናል።

ይሁንና አቶ እስክንድር ከአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ የተለያዩ የደህንነት መኪናዎች እና የተለያዩ ሰዎች ይከታተሏቸው ነበር። በዚህም ውጥረት እና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ለመሆናቸው ምልክቶች እንደነበሩ እናውቃለን። "

(ከጀርመኝ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የትምህርት_እድል ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል። የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ። ሀ/ የውድድር መስፈርቶች 1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ…
#የተሻሻለ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ላለፉ ተማሪዎች አውጥቶ የነበረውን የትምህርት ዕድል ማስታወቂያ አሻሻለ።

ተቋሙ ማሻሻያውን ያደረገው የትምህርት ቢሮ ለምዝገባ የመቁረጫ ነጥብ በአዲስ መልኩ ስላሳወቀው መሆኑን ገልጿል።

በዚህም መሰረት የምዝገባ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 80 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ10/12/14 - 16/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• አንድ ክላሰር

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30

ት/ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች በማፍራት በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎችም እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈራ ት/ቤት ነው።

ለአብነት በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና 78 ተማሪዎችን አስፈትኖ 42 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት የመጣውም 659 ከዚሁ ት/ቤት ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኬንያ

የኬንያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እስካሁን ድረስ ይፋ አልሆነም።

ከሰዓታት በፊት ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት ሊያሳውቅ አልቻልም።

ውጤት በሚገለፅበት ቦማስ የድምፅ ቆጠራ ማዕከልም እስከ መደባደብ የደረሰ አለመግባባት ተፈጥሯል።

በጎረቤታችን ኬንያ እየሆነ ስላለው ጉዳይ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#Sport

ተጋጣሚውን 9 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ክለብ !

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው በ #CECAFA ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያው ንግድ ባንክ ቡድን ተጋጣሚውን ዋሪየርስ ኩዊን በሰፊ የግብ ልዩነት 9 ለ 0 አሸንፏል።

መዲና አዎል 4 ግቦችን እንዲሁም ሎዛ አበራ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ።

More : @tikvahethsport