TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#የጀግኖቹ_ወላጆች ❤️

የኢትዮጵያን ስም በዓለም ላይ ከፍ እያደረጉ ካሉት አትሌቶቻችን መካከል ቤተሰቦቻቸው የግንኙነት መስመር ከዓመት በላይ በተቋረጠበት ትግራይ ክልል ውስጥ ይኖራሉ።

እነሱን ጨምሮ ሁሉም የትግራይ ህዝብ የኢንተርኔት ግንኙነት ባለመኖሩ ስሜቱን እንደኛ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለማጋራት አልታደለም።

ከከተሞች ወጣ ባሉ የትግራይ ክልል ክፍል የሚኖሩ የአትሌቶች ቤተሰቦችም የልጆቻቸውን ድል የሰሙት ሌላው የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው።

የለተሰንበት ግደይ ወላጆች ፦

" ነገ መንጋቱ አይቀርምና ጠንክረሽ ስሪ ፣ ይሄ ግዜ አልፎ ከትግራይ ህዝብ ጋር የምትገናኝበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ በሰላም ያገናኘን "

የጎተይቶም ገ/ስላሴ እናት ፦

" ድሉን ቢሰሙ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ወላጆቼ ይደሰቱ ነበር ስትል እኔም ከእሷ ጋር አለቀስኩኝ።

በጣም ተደስቻለሁ ግን ደስታዬ ግማሽ ነው።

ከዚህ በፊት በነበረው ውድድር ላይ ስታሸንፍ ቀጥታ ስትደውል ነበር። በስልክ ነበር የምንገናኘው። አሁን ከ2 ዓመት ወዲህ ግን ስትወዳደር በቴሌቪዥን ነው የምንሰውማው እንጂ በስልክ አንሰማም።

ሁሉን ተሸክማ ናፍቆትም ፣ ሁሉን ነገር ተሸክማ እዚህ መድረሷ በጣም ነው የተደሰትኩባት እዚህ መድረሷ በጣም ደስ ያለኝ። የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው እንጂ ቤተሰቧን ሳታገኝ እዚህ መድረሷ በጣም ነው ደስ ያሰኘኝ።

ጎተይቶም ልጄ ከህፃንነትሽ ጀምሮ ነው የኔን ክብር የምታሳይኝ ልጄ ያንቺን ልጅ ለመሳም ነው የምመኘው አይዞሽ ደስ ይበልሽ ለመገናኘት ያብቃን ነገ ይነጋል ሰው ለሰው ይገናኛል ይነጋልና አይዞሽ በርቺ "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-23
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ተጠባቂው የሴቶች 5,000 ሜትር ፍፃሜ ዛሬ ይካሄዳል።

የዓለም ሻምፒዮና ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ሀገራችን ሜዳሊያ እንደምታመጣ የምትጠበቅበት የ5,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ሌሊት ይካሄዳል።

🏟️ 5,000 ሜትር ሴቶች #ፍፃሜ

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ዳዊት ስዩም

(ሰዓት - ሌሊት 10:25)

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 !

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ (ኢንፓ) ሚያዝያ 02 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በተመለከተ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት ፦ " ... የጉባኤው ምልዓተ ጉባኤ በቁጥር ደረጃ የተሟላ ቢሆንም የቦርዱ ተወካዮች ከታዘቡት እና የጉባኤው ማገባደጃ አካባቢ ከተፈጠረው ግርግር መረዳት እንደቻሉት አብዛኛው የጉባኤ ተሳታፊዎች የፓርቲ አባል ስለሆኑ የተገኙ ሳይሆን በልመና…
ሁለቱ ፓርቲዎች ይለያያሉ !

ትላንት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲን (ኢነፓ) ማገዱ ይታወቃል።

ነገር ግን አንዳንዶች የታገደው ፓርቲ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) እንደሆነ አድርገው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲያሸራሽሩ ተስተውኗል።

ነገር ግን ሁለቱ ፓርቲዎች የተለያዩ ፓርቲዎች ናቸው።

የታገደው ፓርቲ የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ (ኢነፓ) እንጂ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) አይደለም።

@tikvahethiopia
#ሰበር

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ዛሬ አወጀ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅታቸው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ማወጁን አሳውቀዋል።

#AFP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ 100 የሚጠጉ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት ተገድለዋል " ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ጥቃት የሰነዘረው የአልሻባብ የሽብር ቡድን በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። ይሄ የሽብር ቡድን በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከመታቱ በፊት በንብረት እና ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተነግሯል። አልሸባብ ፤ ከሶማሊያ ጋር ወደ ሚዋሰነው ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን በመግባት ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ በሶማሌ ልዩ ኃይል…
#ይፋዊ_መግለጫ !

" የአልሸባብ የሽብር ቡድን ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል " - የሶማሌ ክልል ፀጥታ ም/ቤት

ዛሬ ምሽት የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ከ4 ቀናት በፊት "አቶ" በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን አልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂ መግባቱን አመልክቷል።

የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች " ሁልሁል " በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበቡ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሰዋል ሲል አሳውቋል።

የፀጥታ ም/ቤቱ አልሸባብ በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት በኢትዮጵያ የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው " ሸኔ " ቡድን ጋር ለመገናኘት አልሞ እንደነበር ገልጿል።

አልሸባብ ወዳሰበው ቦታ ሳይደርስ የያዛቸውን 13 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ያለው የክልሉ ፀጥታ ም/ቤት " ይዞት የገባው ትጥቅ እና ስንቅ ተማርኳል " ብሏል።

ለ3 ቀናት ያህል በተካሄደው ኦፕሬሽን ከ100 በላይ የአሸባሪው አልሸባብ ቡድን አባላት መገደላቸውን የክልሉ ፀጥታ ም/ቤት አሳውቋል።

ለኦፕሬሽኑ መሳካት የሶማሌ ክልል ህዝብ ለጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የተለያዩ ምግቦች፣ በርካታ የቁም እንስሳቶች፣ መጠጦች ፣አልሰባሳት እንዲሁም ደም በመለገስ ከልዩ ሀይሉ ጎን መቆማቸው የተገለፀ ሲሆን የክልሉ ህዝብ ላደረገው ድጋፍና እገዛ የፀጥታ ምክር ቤቱ ምስጋና ማቅረቡን ከክልሉ ኮሚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሰላም ፤ ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ እንዴት ቆያችሁ ?

ፍጥነትን ከጥንካሬ ጋር አዳምሮ የሚጠይቀው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ዳዊት ስዩም

ውድድሩን DSTV በልዩ ቻናል (240) እንዲሁም በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በመዝናኛው ቻናል መከታተል ትችላላችሁ።

ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹❤️ !
ድል ለሀገራችን ልጆች 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia
የመጨረሻ ዙር !

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ዳዊት ስዩም

ድል ለሀገራችን !!

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ !! ዳዊት ስዩም ነሀስ !! @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

ኢትዮጵያውያን የበላይ ሆነው አጠናቀዋል !

እጅግ በጣም የሚደንቅ የቡድን ስራ በታየበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር በጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት ወርቁ 🥇 ወደ ኢትዮጵያ ገቢ ተደርጓል።

ነሀስም 🥉 በዳዊት ስዩም ተገኝቷል።

ከፍተኛውን የቡድን ስራ የሰራችው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ባለድሏ ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ኬንያ ብር አግኝታለች።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !!

@tikvahethiopia