TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
" እንወጣም " - ተቃዋሚዎች የስሪላንካ ጉዳይ ዓለምን ማነጋገሩ ቀጥሏል። የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ከስልጣን ወርዳለሁ ቢሉም ተቃዋሚዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀን አንወጣም ብለዋል። የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት ተቃዋሚዎች ዛሬም ፕሬዝዳንታዊ መኖሪያውን እንደማይለቁ ገልፀዋል። ተቃዋሚዎቹ የፕሬዜዳንቱን መኖሪያን ከተቆጣጠሩ በኃላና ፕሬዝዳንቱ በባህር ኃይል ታግዘው ከሸሹ…
#SeriLanka

• ፕሬዜዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ሀገር ለቀው ወደ ማልዴቪስ ሄደዋል።

• " ፕሬዜዳንቱ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋዊ ደብዳቤ ካላሳወቁ / ወጥተው ካልተናገሩ ከቤታቸው አንወጣም " - ተቃዋሚዎች

ዓለምን እያነጋገረ ያለው የሲሪላንካ ጉዳይ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ፕሬዜዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ሀገር ለቀው መሄዳቸው ተሰምቷል።

ፕሬዜዳንቱ ከሚስት እና 2 የግል ጠባቂዎቻቸው ጋር በሀገሪቱ የአየር ኃይል ፕሌን ወደ ማልዴቪስ፣ ማሌ ሄደዋል።

አሁንም ተቃዋሚዎች የፕሬዜዳንቱን መኖሪያ እንደተቆጣጠሩ ሲሆን ፤ " ፕሬዜዳንቱ ሀገር ጥለው መጥፋታቸው ምንም ሊያስደስተን አይችልም ፤ በአሁን ሰዓት በዚህች ሀገር ምንም ነገር የለንም " ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በይፋ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን እንዲያሳውቁ አሳስበዋል።

የሀገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ፕሬዝዳንቱ ስልጣን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ይደርሳቸዋል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን ደብዳቤው ሲደርሳቸው ለህዝቡ ይፋ ያደርጋሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቁ ተቃዋሚዎች ማሳሰቢያ እየሰጡ ሲሆን የእሳቸው ቢሮ በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። በኮሎምቦም የሰዓት እላፊ ተጥሏል።

የህግ ባለሞያዎች ግን የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህግ መሰረት የሌለው ነው ያሉ ሲሆን " በሀገሪቱ ህገመንግስት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የማድረግ ስልጣን የላቸውም ማድረግ የሚችሉት ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሾሙ ነው እስካሁን ደግሞ ያ አልሆነም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ። 

ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፥ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው። 

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በእንጅባራ በመሳሰሉ አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ ማብራራታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ !

ከነገ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ የሚኒባስ ታክሲ እና የሚድ ባስ (ሃይገርና ቅጥቅጥ) የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚመለከት ነው።

በሚኒባስ ታክሲ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ድርስ የጨመረ ሲሆን በሚድ-ባስ ላይ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 2 ብር ድርስ ጨምሯል።

የሸገር እና አንበሳ ከተማ አውቶብስ ታሪፍ በዚህ ወር መጨረሻ ይስተካከላል ተብሏል።

ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል #ያንብቡ !

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
ካሉበት ሆነው ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://yangx.top/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማብራሪያ የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ 👆 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦ " ... ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል። በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም…
" የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ ተደርጓል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ዕጣው የተሰረዘው የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡

በእጣው የሚካተቱት 79 ሺህ ቆጣቢዎች መሆን ሲገባው ምርመራ ሲደረግ ግን በእጣው ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ቁጥር 172 ሺህ መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

ይህ ማለትም 93 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በተጭበረበረ መንገድ ዕጣ በሚያወጣባት የቴክኖሎጂ ሲስተም ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)

@tikvahethiopia
የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ !

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ ከኢንሳ የአጣሪ ቡድን መሪ በጋራ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች ፦

👉 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት ተፈፅሟል።

👉 በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን።

👉 ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል።

👉 የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፤ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል።

👉 የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው።

👉 በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡

👉 ህብረተሰቡ መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ረድቶናል፡፡ እኛም ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፡፡

👉 የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነበር፡፡ ይህንንም ለማመን ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፡፡

👉 ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፡፡

👉 ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበርም በወቅቱ ተገልፆ ነበር ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ኢንሳ ያረጋገጠው እንዳለሆነ ታይቷል፡፡

👉 ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ ነበር። ነገር ግን የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ ታውቋል። በሂደቱ እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል።

👉 የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ ነው የጀመረው።

👉 ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ 4 ባለሙያዎች መወከሉንና ከዚህ በተጨማሪም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ በኢንሳ አስተባባሪነት ስራውን ሲሰራ ቆይቷል።

👉 ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን።

👉 በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ #ከእውነቱ_የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል፡፡

👉 ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡ ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

👉 የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ የህዝቡን መብት ማስከበር ነው። ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት ለሟሟላት ተሰርቷል።

👉 በፍትሃዊነት ህዝብን ሃብት ለማድረስና የኋላ የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡

👉 አሁንም ተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

👉 በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን አድርገናል፡፡

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ ከኢንሳ የአጣሪ ቡድን መሪ በጋራ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና…
#Update

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ።

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነታቸው የተነሱ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦ ዳይሬክተር

3ኛ. ሀብታሙ ከበደ፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

4ኛ. ዬሴፍ ሙላት፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

5ኛ. ጌታቸው በሪሁን፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

6ኛ. ቃሲም ከድር፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

7ኛ. ስጦታው ግዛቸው፦ ሶፍትዌሩን ያለማ

8.ኛ. ባየልኝ ረታ፦ ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፦ የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

10ኛ .ኩምሳ ቶላ፦ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)

@tikvahethiopia
ሶስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ገለፀ።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት በገላና ሸጥ እና ከምዕራብ ጉጂ ጋር በሚያዋስኑን አከባቢዎች የአከባቢውን ሠላም የማይፈልጉ ሀይሎች የንፁሐንን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብሏል።

" ምንም እንኳን የፀጥታ ሥጋት ብኖርም መተዳደሪያቸው የሆነውን የእርሻ ሥራ በማካሄድና ጤፍ በማጨድ ላይ የነበሩ ንፁሐን አርሶ አደሮች በገዛ መሬታቸው እና አከባቢያቸው ሲገደሉ ቁጥራቸው በርከት እያለ ያለ ነው " ብሏል።

ትላንትና በተመሳሳይ መልኩ #በዋሌያ ቀበሌ የዕለት ተግባራቸውን ለመከወን የወጡ ሶስት አርሶ አደረሮች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል ሲል አሳውቋል።

ልዩ ወረዳው የቡርጂ ማሕበረሰብ እና የሟች ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ሀዘኑን ገልጾ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ አንዳሳዘነውና ቁጭት እንደፈጠረበት ገልጿል።

" ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የእጃቸውን እንዲያገኙ በጥብቅ እየሠራን ነው " ያለው የቡርጂ ልዩ ወረዳ " " የክልል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን እንዳለ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይም ይህን ብለዋል (ከኢፕድ የተወሰደ) ፦ - ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ 4ኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት 8 ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል። - ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት…
#Update

ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንዲሁም አባቱ አቶ ኢሳያስ ገ/ወልድ እንዲሁም የቤተሰቡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ውሳኔ እንደማይቀበለቱ ገለፁ።

ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን እንዲቀለብስ እና ተማሪ ቢንያምን ከ4 ዓመት በላይ ወደለፋበት የትምህርት ገበታው እንዲመልሰው ጠይቀዋል።

ይህንን የጠየቁት " ሸገር ኢንፎ " በሚሰኝ የዩትዩብ ገፅ ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።

የተማሪ ወላጅ አባት አቶ ኢሳያስ " ውሳኔው ተቀባይነት አለው ብዬ አላስብም ፤ በውሳኔውም አዝኛለሁ አልቀበለውም፤ ውሳኔውን ተመልሰው እንዲያጤኑት " ሲሉ ጠይቀዋል።

" በሌላ ዓለም እንክብካቤ እየተደረገ እውቀት ያለው ጭንቅላት ያለውን ኡፍኡፍ እያሉ ነው የሚይዙት እዚህ ሳየው ተቃራኒ ሆኖብኛል " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ኢሳያስ ልጃቸው ወደፊት ትልቅ ደረጃ ደርሶ የህዝቡ አገልጋይ ሆኖ እንደሚመጣ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ተማሪ ቢንያም በበኩሉ ፤ ውሳኔው ከዚህ በፊት ከነበረው ያልተለየ መሆኑን ገልጾ " በእነሱ ምክንያት ሀገሪቱ እየከሰረች ነው " ሲል ገልጿል።

" እኔ ፕሮሰሱን ጠብቄ ነው የገባሁት እኔ ባላጠፋሁት ምን አይነት ኃላፊነት እንደወሰዱ አልገባኝም ፤ እኔን ማብቃት ነው የሚገባቸው እንጂ ቴክኒካል ጉዳዮችን ጠቅሰው መናገራቸው ሲሉት የነበሩትን ነው የደገሙት ለእኔ የተለየ ውሳኔ አይደለም፤ የተለየ ውሳኔም አልጠበኩም " ብሏል።

ተማሪ ቢንያም ዩኒቨርሲቲው የለፋበትን ትምህርት ሊያስጨርሰው እንደሚገባ ገልጾ በሌላ ዓለም ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን መውሰድ ይቻላል ብሏል።

ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ፤ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን ድጋሚ እንዲያጤነው ካልሆነ ወደ ክስ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Binyam-Esayas-07-14

@tikvahethiopia