#TikvahFamily
ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦
• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።
• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)
• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።
• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።
ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦
- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።
- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።
- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።
- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።
- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።
#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።
#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።
#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube ፣ #TikTok ፣ #Facebook አካውንት የለም።
መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT
@tikvahethiopia

#Monkeypox
ጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያ በዝርጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ሳይያዝ አልቀረም ተብሎ የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃለች።
ሀገሪቱ የተጠርጣሪውን ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል እንዲላክ አድርጋለች።
የኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሀገሪቱ የመመርመር አቅሟ ውስን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ናሙናው ወደ ሴኔጋል እንዲላክ መደረጉን አሳውቋል።
ናሙናው በትክክል ቫይረሱ መኖሩን የሚያረጋግጥ ከሆነ ሀገሪቱ በጀት መድባ ለምርመራ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በማሟላት ምርመራው በሀገር ውስጥ እንዲደረግ ለማድረግ መሰራት አለበትም ብሏል።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ በአፍሪካ የዝንጀሮ የፈንጣጣ በሽታ በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቫይረሱ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

#EHRDC
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ቡድን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በሚገኙበት ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ መመልከቱን አሳውቋል።
ቡድኑ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ ፣ ጋዜጠኛ መስከረም አበራን መጠየቁን አመልክቷል።
ጉዳያቸውንም በንቃት እየተከታተለው መሆኑንም ማዕከሉ አሳውቋል።

#RUSSIA #AFRICA
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ አሳውቀዋል።
ፑቲን የስንዴ ምርቶች ወደ አፍሪካ መላካቸውን ለማረጋገጥ ሃገራቸው እንደምትሰራም ገልጸዋል፡፡
ይህን የገለፁት ከወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና ከሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጋር ከጦርነቱ ጋር በተያያዙ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሶቺ ከተማ በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይቱ ወቅት ማኪ ሳል አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖራትም በጦርነቱ ምክንያት ሰለባ መሆኗን ገልፀዋል።
በተለይ ከዩክሬንና ሩሲያ ይገቡ የነበሩ የግብርና ምርቶች እና ግብዓቶች ጉዳይ አፍሪካን ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር እንደዳረጋት አስረድተዋል።
ሩሲያን ጨምሮ የአፍሪካ አጋር የሆኑ ሁሉም ሃገራት የጣሏቸውንና በስንዴ እና በማዳበሪያ ላይ ያነጣጠሩ ማዕቀቦቻቸውን እንዲያነሱም ጠይቀዋል፡፡
የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ሩድያ የምግዜም የአፍሪካ አጋር መሆኗን ገልፀው ከዩክሬን ወደ አፍሪካ ለሚገቡ የስንዴ ምርቶች በወደብ ላይ ለቀሩትም ጭምር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ገልጸዋል፡፡
ፕሬዜዳንት ፑቲን ሰው ሰራሽ #የአፈር_ማዳበሪያ ምርቶች አፍሪካ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ዝግጁ ስለመሆናቸውም አሳውቀዋል።
ከ40 በመቶ የሚልቀው የአፍሪካ የስንዴ ፍጆታ በዩክሬን እና በሩሲያ የስንዴ ምርቶች የሚሸፈን ነው፡፡
መረጃው የአል አይን ኒውስ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa " በሲሚንቶ ላይ በሚታየው ከከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ቤት መገንባት እስከማቆም ደርሷል ፥ አንዳንድ ፕሮጀክቶችም እየዘገዩ ነው " - አቶ ከድር ጁሃር በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በየጊዜው በተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶች ፣ የምግብ ፍጆታዎች እንዲሁም በኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ላይ ሲሚንቶን ጨምሮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ይታወቃል። ድሬድዋ…
#ድሬ
ትላንት ድሬዳዋ ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ሲሚንቶ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተነግሯል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከናሽናል ሲሚንት አክሲዮን ማህበር እህት ኩባንያ ከሆነው ኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በድሬዳዋ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት ፍትሀዊ ለማድረግ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፋብሪካው ለኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ490 ከ36 ሳንቲም እያስረከበ ኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ደግሞ አስተዳደሩ ላደራጃቸው 200 ለሚጠጉ ቸርቻሪዎች አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ520 ብር ከ36 ሳንቲም እያስረከበ ይገኛል።
በዚህም በድሬዳዋ ከተማ ትስስር ከተፈጠረላቸው ቸርቻሪዎች ውስጥ ከኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ520 ብር ከ36 ሳንቲም ተረክበው 60 ብር ጭማሪ ተደርጎበት ለህብረተሰቡ በ580 ብር ከ36 ሳንቲም እንዲቀርብ ተብሎ ከፋብሪካው ሲሚንቶ የጫኑ መኪኖች ቢወጡም ሲሚንቶውን ለነዋሪው ህብረተሰብ ባለማድረሳቸው ምክንያት በተደረገው ክትትል 600 ኩንታል የሚሆን ሲሚንቶ የጫኑ 5 መኪናዎች ትላንት ምሽት በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
መረጃውን የከተማውን ንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢኒቨስትመንት ቢሮ ዋቢ አድርጎ ያሰራጨው የከተማው ኮሚኒኬሽን ነው።

Photo
" እስካሁን ከታፈኑ 4 አመራሮቻችን ሁለቱ የተለቀቁ ሲሆን ቀሪ ሁለቱ የገቡበትን ለማወቅ አልቻልንም " - እናት ፓርቲ
ከቀናት በፊት እናት ፓርቲ አራት አመራሮቹ በአማራ እና በደቡብ ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጾልን እንደነበር ይታወሳል።
ከአራቱ አንዱ አመራር (ሞጣ አካባቢ) ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉን ፓርቲድ እንደገለፀልን አይዘነጋም።
ትላንት ደግሞ የወላይታ ዞን የፓርቲው አመራርና ዕጩ የነበረችው ስመኝ ታደመ ከእስር መፈታቷን መረጋገጥ ተችሏል።
ፓርቲድ አመራሯ የጤናዋ ሁኔታ ከዕለት ወደዕለት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱና ሕክምና እንዳታገኝ በመከልከሏ ስጋት አድሮበት እንደነበር ነገር ግን በመጨረሻም #ከወንጀል_ነጻ ተብላ ከቤተሰብ ጋር መቀላቀል መቻሏልን አመልክቷል።
እናት ፓርቲ እስካሁን ከታፈኑ 4 አመራሮቹ ሁለቱ መለቀቃቸውን ቀሪ ሁለቱ የገቡበትን ለማወቅ ያደረግው ጥረት አለመሳካቱን ገልጿል።
በሌላ በኩል ሞጣ ላይ ከሚሰራበት ባንክ ታፍኖ ተወስዶ የነበረው አመራር አቶ ምግባሩ አስማረ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት እና እስካሁን ዐይኑ ላይ የደረሰበት ጉዳት እንዳልዳነ የፓርቲው መረጃ ያሳያል።

#AddisAbaba | የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ አንድ ተጨማሪ ዘመናዊ ሆቴል አግኝታለች።
በዛሬው ዕለት ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ የተገነባ " ኬና /KENA " የተሰኘ ሆቴል ተመርቋል።
ሆቴሉ ከ400 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ እንደወጣበት የተገለፀ ሲሆን ዘመናዊ ቁሳቁሶች፣ የተሟሉ የማረፊያ ክፍሎች፣ የምግብ አዳራሾች፣ ዘመናዊ የጂም ቤት፣ የስብሰባ አዳራሽ ፣ በሆቴሉ አናት ላይ የድምፅ ብክለትን የሚከላከል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መዝናኛ እንዲሆም ሌሎች የዘመኑ ሆቴሎች ሊያሟሉት የሚገቡ መስፈርቶች ሁሉ እንደተሟሉለት ተነግሯል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የግንባታ እቃዎች ዋጋ ንረት፣ የግንባታ ቁሳቁስ ለማስገባት ኮንቴነር ችግር ማጋጠሙ አጠቃላይ ያሆቴሉን ግንባታ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ መውሰዱ በምረቃው ወቅት ተገልጿል።
አዲስ አበባ በርከታ እጅግ የዘመኑ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች መገኛ ስትሆን ዛሬ የተመረቀው ሆቴልም በሆቴል አገልግሎት መስክ ተጨማሪ ግብዓት መሆኑ ተገልጿል።

የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ዋጋ አልቀመስ እያለ ነው።
የሞዴስ ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ ለበርካታ ዜጎች ፈተና ሆኗል።
ከዚሁ ከንፅህና መጠበቂያ ዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ በሚያዚያ ወር 2014 ታትሞ በወጣው የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ኤልሻዳይ ገበየሁ የተናገሩትን ያንብቡ ፦
" ሴቶች በወር አበባ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች (ሞዴስ፣ ፓድ) ለማስገባት መንግሥት ድጎማ (Subsidize) እንደሚያደርግ መግለጹን አስታውሳለሁ።
በወቅቱ ይህ ለእኛ ትልቅ እፎይታ የሚያመጣና አንድ እርምጃ ለመራመድ የሚያስችል ነው ብለን ነበር።
ሆኖም አሁን ገበያ ላይ ያለው ነገር ግን፣ መንግሥት ካለው ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ወይ ወደ ተግባር አልገባም አልያም ደግሞ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች ድጎማውን ተጠቅመውና ከዚያም በላይ አስፍተው አላግባብ ትርፍ እያገኙበት ነው።
የወጣው መመሪያ አፈጻጸም ምን ያህል እንደሆነና ክፍተቱ የቱ ጋር እንደሆነ አላውቅም ፤ ከላይ የሚነገረውና መሬት ላይ ያለው ተቃራኒ ሆኖ ከተገኘ ትልቅ የአፈጻጸም ክፍተት መኖሩን ያሳያል።
ብዙ ጊዜ ማሻሻያዎች ሲኖሩ ጉዳዩ #የአንድ_ሰሞን_አጀንዳ ይሆንና ይረሳል፤ ሲጀመርም ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ማግኘት የመብት ጉዳይም ነው።
ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን መጠቀም ካልቻሉ ጫናው በጣም ሰፊ ነው። ከትምህርት ቤትና ከሥራ ይቀራሉ፣ ከቤት ወጥተውም ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ እንዳይሳተፉ ይከለክላቸዋል። በሴቶች ላይ ካለው ጫና አንጻር ይህ ሲጨመርም ማነቆው ይበዛል።
...በሴቶች ላይ የሚሠሩና የሴቶች መብት ያገባናል የሚሉ አካላት በመንግሥት የተነገረው ለምን ተፈጻሚ እንዳልሆነና ማን ተጠያቂ እንደሚሆንም መጠየቅና መሠራት ይገባል "

#ሃጅ | ከኢንዶኔዥያ የተነሱ የሃጅ ተጓዦች መዲና ገብተዋል ። ወደ ቅድስት ከተማ መካ እንደሚጓዙ ይጠበቃል።
የሃጅ ተጓዦቹ ቡድን ከ2 ዓመታት በኋላ ከሳዑዲ አረቢያ ግዛት ውጭ የተጓዘ መጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ይሆናል።
ሳውዲ አረቢያ ባለፈው ወር የሃጅ መንፈሳዊ ተጓዦችን ከግዛቷ ውጭ እና ከግዛቷ ውስጥ ወደ አንድ ሚሊዮን ከፍ ማድረጓ ይታወሳል።
የሃጅና ዑምራ ሚኒስትር መሀመድ አል-ቢጃዊ " ዛሬ የመጀመሪያውን ቡድን ከኢንዶኔዥያ የተቀበልን ሲሆን በረራዎቹ ከማሌዢያ እና ህንድ ይቀጥላሉ " ብለዋል።
" በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከሳዑዲ አረቢያ ግዛት ውጭ የሚደረገው ጉዞ ለሁለት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ዛሬ ተጓዦችን በመቀበላችን ደስተኞች ነን " ሲሉም ገልፀዋል።
ሳውዲ አረቢያ የአላህ እንግዶችን ለማስተናገድ " ሙሉ በሙሉ ዝግጁ " መሆኗን አሳውቀዋል።
በእስልምና እምነት ከ5ቱ የሃይማኖቱ መሠረቶች አንዱ አቅም ያለው ሰው በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሃጅ ሥነ ሥርዓት እንዲያደርግ ይጠበቅበታል፡፡