TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#US

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት በሀገራቸው ለሚታየው የዋጋ ግሽበት የሩስያን መሪ ቭላድሚር ፑቲንና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተጠያቂ አደረጉ።

ትላንት ጆ ባይደን ለሀገራቸው ህዝብ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ማብራሪያቸው ለዋጋ ግሽበት የኮቪድ-19 ወረርሽኝንና ሩስያን ተጠያቂ አድርገዋል።

"ዛሬ እያየን ያለነው የዋጋ ንረት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ" ያሉት ባይደን አንደኛው አስከፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሆኑን አስተዋል።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ "ፑቲን በዩክሬን ላይ የከፈተው ጦርነት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል፤ ባይደን በመጋቢት ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 60% የሚሆነው ከነዳጅ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባይደን ዩክሬንና ሩስያ በስንዴና በቆሎ ምርታቸው ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ በማስረዳት "የፑቲን ጦርነት የምግብ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል" ሲሉ የሩስያውን መሪያ ተጠያቂ አድርገዋል።

ከሪፖርተሮች በአሜሪካ ለሚታየው የዋጋ ግሽበት አስተዳደራቸው ኃላፊነት ይወስድ እንደሆነ ሲጠየቁ "ፖሊሲዎቻችን የሚያግዙ እንጂ የሚጎዱ አይመስለኝም" ሲሉ መልሰዋል።

ባይደን በሀገራቸው የሚታየው የዋጋ ግሽበት ሊፍታ የሚገበው ከፍተኛ ችግር መሆኑን በማንሳት ችግሩን ለመፍታት ልዩ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትላንት ማብራሪያቸው "በእርግጥ የተወሳሰበ ነው። የአሜሪካ ዜጎች ሊረዱት እንደማይችሉ ግን እየጠቆምኩ አይደለም። እነሱ ይረዱታል፤ ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ እንዲኖር ለማድረግ በቀን 8፣ 10 ሰዓታት እየሰሩ ነው" ብለዋል።

መቼ የምርቶች ዋጋ ይቀንሳል ለሚለው ባይደን ለመተንበይ ፍቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ሲሆን የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ምን መስራት እንዳለብን እናውቃለን ብለዋል telegra.ph/US-05-11-2

@tikvahethiopia
#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 147 ካምፓሶቻቸው ላይ ሚያዚያ 10 እና 11/2014 ዓ.ም ድንገተኛ ፍተሻ ማካሄዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ ተወስዷል፡፡

በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ በቀጣይ የተገኝባቸው ክፍተቶች በማስተካከል በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

(የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸው 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

እስካሁን ድረስ #አስተማማኝ የሆነና #ዘላቂ መፍትሄ ያልተገኘለት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ዳግም ሌላ የከፋ እልቂት እንዳያስከትል ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል።

ከጥቂት ወራት በፊት ተደርሶ የነበረው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ መላ ህዝብ በተስፋ ሲጠብቅ የነበረውን ጥቂት የሰላም ጭላንጭል አሁን እየታየ ያለው የዳግም ጦርነትና ግጭት ሁኔታ የታየውን ተስፋ እንዳያጨልመው ስጋት ደቅኗል።

በእርግጥ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ተብሎ በታወጀበት ወቅት እንኳን በየአቅጣጫው ያሉትና ለዚህ ወገን እንወግናለን የሚሉ ሚዲያዎች ፣ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች የጦርነት እና ግጭት ቅስቀሳዎች፣ ጥላቻንና የሰዎችን አእምሮ ለዳግም ጦርነት የማዘጋጀት ድርጊትና እቅስቀሳ አላቆሙም ነበር።

እስካሁን ባለው ጊዜ አቀራራቢ እና ሰላም ላይ ትኩረት ያደረጉ ስራዎች በአግባቡ አልተሰሩም ፤ ግጭት ቆመ ይባል እንጂ በተለይ በሚዲያ የሚሰራው ስራ ሰዎች ከጦርነት ስነልቦና እንዳይወጡ የሚያደርግ ነበር።

በተለያዩ አካላት እየተሞከሩ ነው ስለሚባሉት የሰላም ጥረቶች መላው ህዝብ ይሄ ነው የሚባል ዝርዝር መረጃ የለውም ፤ ይህንን ጥረት የሚያደርጉ አካላትም ለስራው እንቅፋት እንዳይሆነ መረጃውን ለመስጠት ባለመፈለጋቸው ከኃላ ለሰላም እና ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ስለሚደረገው ጥረት እና እንቅፋት ስለሆኑ ጉዳዮች በትክክል ማወቅም አልተቻለም።

ከሰሞኑ ግን ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅቶችና ቅስቀሳዎች ፣ የሚዲያ ዘመቻዎች ከየአቅጣጫው ተጧጡፈው በመቀጠለቸው ለሰላም የነበረውን ተስፋ ዳግም እያደበዘዘው ይገኛል።

ሌላው በትግራይ ክልል ላለው በብዙ ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂ ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተደረሰ በኃላ በየቀኑ መግባት የነበረበት 100 ተሽከርካሪ ለምን እየገባ እንዳልሆነ ለዚህ ደግሞ ማን ? ምን ? እንቅፋት እንደሆነ በግልፅ የሚያብራራ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅትም ብቅ አላለም።

የሆነው ሆኖ ግን አሁን ላይ በየአቅጣጫው የሚታየው የግጭት እና የጦርነት ቅስቀሳ ፣ ጥላቻን የመዝራት ዘመቻ ዳግም የከፋ እልቂት እንዳይመጣ የሚያሰጋ ሲሆን፤ ከግጭት እና ጦርነት ቀጠና ራቅ ያሉ አካላት ገና ከወዲሁ በሁኔታው የዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰቢያ ፣ የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ማድረግ ጀምረዋል።

ከዚህ በፊት በነበረ ጦርነት ሳቢያ እጅግ የተዳከመው ኢኮኖሚ፤ አሁን በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም ያለው ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚያዊ መናጋት በሀገር ውስጥ ዳግም ጦርነት ተደርጎ ኢኮኖሚው እንዳያንሰራራ ሆኖ እንዳይወድቅ ያስፈራል ፤ ይህ ደግሞ ይዞት የሚመጣው መዘዝ እጅግ የከፋ ነው።

@tikvahethiopia
#Google

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል #አፋን_ኦሮሞ እና #ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚናገራቸውን 24 አዳዲስ ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካቷቸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አስሩ ቋንቋዎች በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ትግርኛን ይናገራሉ።

" ለዓመታት ጉግል መተርጎሚያ የቋንቋ ልዩነቶችን በማጥበብ በመላው ዓለም የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ረድቷል " ሲል የአሜሪካው ኩባንያ ገልጿል።

አክሎም አሁን ቋንቋቸው በአብዛኛው ቴክኖሎጂ ውክልና ያልተሰጣቸው ሰዎችን መርዳት ይፈልጋል ብሏል።

አሁን የተካተቱትን ቋንቋዎች ጨምሮ በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ደርሷል።

አዲሶቹ የተካተቱት ቋንቋዎች የቴክኖሎጂ ምዕራፍን እንደሚወክሉ ገልጾም ምሳሌ ሳይኖር የሚተረጉም የማሽን መማሪያ ሞዴል እንደሚጠቀሙ አስፍሯል።

ይህ ኮምፒውተርን ለማሰልጠንና ትርጉሞቹን በማሰባሰብ የመረጃ ቋቱን ለማካበት የሚያገለግሉ በርካታ ሰዎች ለሌሏቸው ቋንቋዎች ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ነገር ግን ኩባንያው ቴክኖሎጂው ፍጹም እንዳልሆነ አምኗል።

https://telegra.ph/Google-05-12-3

#BBC/#Google

@tikvahethiopia
" በቦምባስ ከተማ በአኪሾ ጎሳ አባላት ባሕላዊ ሥነ ሥርዓት ላይ በክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት የተወሰደ መጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና የአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ጉርሱም ወረዳ ቦምባስ ከተማ መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በባሕላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ (ሱልጣን) ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ግድያ እና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መነሻነት ከሚያዝያ 7 እስከ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት  ምርመራ አድርጓል።

በዚህ መሰረት በአጠቃላይ በ2ቱ ቀናት በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች 11 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣  ይኸውም  በታጠቁ ሰዎች የተፈጸመ ግድያ እና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም (excessive use of lethal force) የደረሰ የሕይወት መጥፋት መሆኑን፤ በተጨማሪም ቢያንስ በ33 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ እንዳገኘድ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ምርመራውን ለማከናወን የአይን ምስክሮችን ፣ ተጎጂዎችን ፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በግል እና በቡድን በማነጋገር፣ ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ስለጉዳዩ ማብራሪያና ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር ነው ምርመራውን ማካሄዱን የገለፀው።

ኢሰመኮ የክልሉ መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ካሳ የከፈለ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ለተሟላ ፍትሕ የወንጀል ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#Sudan

ሱዳን ፤ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ከሰላ ከተማ የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሰዓት እላፊ ጣለች፡፡

ሰዓት እላፊው በኑባ እና ቤኒ ዓምር ጎሳዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ትናንት ረቡዕ ምሽት ጀምሮ የተጣለ ሲሆን ለ24 ሰዓታት ይቆያል ተብሏል፡፡

ሌላ አዲስ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ሰዓት እላፊው እንዲከበርም የከተማዋ ባለስልጣናት አሳስበዋል፡፡

ደም አፋሳሽ ነበር የተባለለትን ግጭት የሃገሪቱ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ገብተው እስኪያስቆሙት ድረስ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና ጉዳቶች መድረሳቸው አል ዐይን ኒውስ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ICRC #Oromia #Afar

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ ኩምቢ ለሚገኙ 5000 አባወራዎች የእንስሳት መኖ እያከፋፈለ ይገኛል።

ስርጭቱ በአካባቢው ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ሲሆን በዚህ ኦፕሬሽን እስከ 150,000 እንስሳት ይመገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ድርጅቱ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በአፋር ክልል ሲልሳ ለሚገኙ 9,000 የተፈናቀሉ ሰዎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም ሶላር የእጅ ባትሪዎችን፣ ጀሪካኖችን፣ የማዕድ ቤት እቃዎችን፣ ምንጣፍ እና መጠለያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በአውሮፕላን አብራሪነት እና በቴክኒሽያንነት ሙያ ፍላጎት ያላቸውንና የምልመላ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

ለዚሁ የተለያዩ መስፈርቶች የወጡ ሲሆን ከነዚህ መካከል የትምህርት መመዘኛ #ለአብራሪዎች፦ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ሆና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ወስዶ/ወስዳ አጠቃላይ ውጤት 350 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ የትምህርት አይነት አማካኝ ውጤት 70% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት መሆን አለበት / አለባት።

እንዲሁም የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደበትን/የወሰደችበትን የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል መሆን አለበት / አለባት።

ከሌሎች መመዘኛዎች መካከል ቁመት 1.65 ሜ እና ከዛ በላይ የሆነ/የሆነች፣ ክብደት ከ50-60 ኪ.ግ የሆነ/የሆነች፣ የአየር ኃይል አካዳሚን የመግቢያ ፈተና ወስዶ/ዳ ማለፍ የሚችል/የምትችል መሆን አለበት/አለባት።

#የቴክኒሽያኖች መመልመያ፦ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ/ዳ አማካይ ውጤት 300 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ ትምህርት አማካኝ ውጤት 60% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት መሆን አለበት / አለባት።

ሌሎች መመዘኛዎች ከላይ የተገለፀው ጋር ተመሳሳይ ነው።

የምዝገባ ቦታ ከላይ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን የምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 10 ጀምሮ እስከ ግንቦት 20/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት መሆኑን ተገልጿል።

NB. እድሜ ከ18-24

(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ ኢ-ኮሜርስ የክፍያ አማራጭ የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለሆቴል ፣ ለግብይት ፣ ለጉብኝት ክፍያ ይፈጽሙ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ አስቤዛ ያድርጉ ፣ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ ያግኙ! የሁሉም_ምርጫ !

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ! https://yangx.top/BoAEth