TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
" ነዳጅ ማደያዎች በኃላፊነት እና በስነ ምግባር ሊሰሩ ይገባል "

ዜጎች ነዳጅ ፍለጋ በየቀኑ ረጅም ሰዓታት በሰልፍ እያሳለፉ ይገኛሉ ችግሩ በአዲስ አበባ ከተማ እና በሌሌችም ከተሞች ይታያል ፤ ላለፉት ወራትም ሲታይ ቆይቷል።

ነዳጅ ለመቅዳት ሰዉ አምስት ወይም ከዚያ በላይ ሰዓታት ወረፋ እየጠበቀ በጎን ሌሎች ስራዎች በትውውቅ እና በገንዘብ እንደሚሰሩ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ይህ እጅግ ያልተገባ እና እርስ በእርስ መተዛዘንና መተሳሰብን እየጎዳ ያለ ድርጊት ከመሆኑም በላይ ሰዎችን ክፉኛ እየተስተጓጎለ በስራቸውም ላይም ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

ነዳጅ ማደያዎች እና ነዳጅ ማደያ ቦታዎች የሚሰሩ ሁሉ ስራቸውን በአግባቡ ኃላፊነት እና ስነምግባር በተሞላበት መልኩ ሊያከናውኑ እንደሚገባ ችግሩን የተመለከቱ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBOT
#ጥቆማ

ለሰሜን ወሎ ዞንና አጎራባች ማህበረሰብ ክፍሎች ፦

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀረር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር እንዲሁም ከአንገት በላይ እባጭ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች #በነፃ_የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል።

በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0333311680 / 0920218203 በመደወል ከ1/09/2014 ዓ/ም ጀምሮ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።

(ላልሰሙትም አሰሙ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Shell ሼል ከሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ አልገዛም አለ። ሼል በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ከሩስያ በርካሽ ድፍድፍ ነዳጅ ገዝቶ የነበረ ሲሆን ለዚህም ይቅርታ በመጠየቅ ፤ ከሩሲያ ነዳጅ እና ጋዝ መግዛቱን ለማቆም ቃል ገብቷል ተብሏል። በተጨማሪ ሼል በሀገሪቱ ያሉትን ሁሉንም የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚዘጋና በሀገሪቱ ውስጥ አሁን ላይ እየሰራ ያላቸውን ሁሉንም ስራዎች እንደሚያቆም አሳውቋል። ሼል በሳምንቱ…
#የሼል_ትርፍ

በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።

ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9.13 ቢሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ካገኘው 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በሦስት እጥፍ ገደማ ያደገ ነው።

ነገር ግን ድርጅቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ገበያ መውጣቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንዲያጣ እንዳደረገው አሳውቋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተዳክሞ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ማንሰራራት ሲጀምር የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ እየጨመረ ቢመጣም የቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጣራ እንዲነካ አድርጎታል።

የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ መጨመር ለኢነርጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል " በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል። መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው። ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን…
#Konso #Ale #Amaro

2023 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ።

በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ከ2014 ተፈታኞች ጋር ድጋሚ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

ትላንትና የኮንሶ ዞን 773 ተማሪዎች ከ5 ትምህርት ቤቶች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ መወሰኑን መግለፁን የሚመለከት መረጃ ልከንላችሁ ነበር።

ከኮንሶ ዞን ባለፈ በአማሮ ልዩ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች 1171 ተማሪዎች በኧሌ ልዩ ወረዳ በ3 ትምህርት ቤቶች 79 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

በአጠቃላይ በአንድ ዞን እና ሁለት ልዩ ወረዳዎች የድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱት 2,023 ተማሪዎች ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች በአካባቢያቸው ላይ የፀጥታ ችግር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ከፍተኛ በሆነ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ሆነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተፈተኑ ሲሆን ነገር ግን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊያስገባቸው የሚችል ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም።

@tikvahethiopia
#Huawei #AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ሁዋዌ ሃንድሼኪንግ ፎረም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትናንት ተከፍቷል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያዘጋጀው የምርምርና ፌር ሳምንት Research and Fairs Week በትናትናው ዕለት ተጀምሯል።

በዚህ። የተለያዩ ኤግዚቢሽኖች ተከፍተው ፤ በአዲስ ዩኒቨርስቲ በምርምር ዘርፍ የተሰሩ የምርምር ስራዎች ለእይታ ቀርበው ተጎብኝተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአይሲቲ መሰረተልማት እና ስማርት መጠቀሚያዎችን በማምረት ቀዳሚ የሆነው ሁዋዌ በዩኒቨርስቲው በመገኘት የ Handshaking Forum ጆብ ፌር ከፍቷል ፥ ይህ ዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሁዋዌ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር Handshaking Forum በሚል የተመራቂ ተማሪዎችን ሲቪ ሲያሰባስብ ለ2ኛ ጊዜው ሲሆን በዚህ ፎረም አቅም ያላቸው ተመራቂ ተማሪዎችን ከአሰሪዎች ጋር ለማገናኘት ይሰራል።

ከሁዋዌ ባገኘነው መረጃ መሰረት ሁዋዌ አዲስ ለተመረቁ ምሩቃን ያዘጋጀው የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ሲኖረው በዚህም ለ3 ወራት በሁዋዌ ኢትዮጵያ ቢሮ እንዲሰለጥኑ ካደረገ በኃላ የተሻለ አፈጻጸም ያሰስመዘገቡትን ይቀጥራል።

ባለፈው ዓመት ለ250 ተማሪዎች የኢንተርንሺፕ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚያም መካከል 200 ያህሉ በድርጅቱ ተቀጥረዋል። በዚህ ዓመት 300 ያህል የመቀበል እቅድ ሲኖረው እስካሁን ከ90 በላይ ተቀብሏል።

@tikvahethiopia
#FDRE_Defense_Force

" በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ከ3 ዓመታት በላይ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ1 ሺ በላይ አመራሮችና አባላት በጉሙዝ ብሔረሰብ ዕርቀ ሰላም ባህል "ማንገማ" መሠረት #ትጥቃቸውን_አስረክበው_እርቅ_አካሂደዋል

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ " በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " ብለዋል።

ለፈፀሙት ቃለ-መሃላም ሁሉም ተገዥ በመሆን ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ቁርጠኝነቱን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ ህገወጥ ታጣቂዎችም የአፍራሽ ኃይሎችን ተልዕኮ ከማስፈፀም ተቆጥበው ቅድሚያ #ለሰላም ዕድል መስጠት እንደሚገባቸው ጥሪ አስተላልፏል።

#FDRE_Defense_Force

@tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( #ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 / 2014 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል በዚህም ፓርቲውን በመሪነት እና በሊቀመንበርነት የሚመሩ አመራሮችን እንደሚመርጥ አስታውቋል።

ፓርቲው ይህን ያሳውቀው ዛሬ በዋና ፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።

ዕጩ አመራሮቹ ከጠቅላላ ጉባኤው መዳረሻ በፊት ለ19 ቀናት የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ፓርቲው ገልጿል።

ኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ የጠራው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚደነግገው መሰረት በሶስት ዓመት አንዴ መደበኛ ጉባኤ ማከናወን ስለሚገባው መሆኑን አመልክቷል።

በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው የኢዜማ መሪ፣ ምክትል መሪ፣ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና የፓርቲው የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ እንደሚመረጡ ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

በግንቦት 2011 የተመሰረተው ኢዜማን ላለፉት ሶስት ዓመታት በመሪነት እያገለገሉ የሚገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሲሆኑ የምክትል መሪነት ስልጣን ያላቸው ደግሞ አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው።

የኢዜማን የዕለት ተዕለት ስራ በሙሉ ጊዜ የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው ለፓርቲው ሊቀመንበር ነው።

አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ ሊቀመንበርነት ኃላፊነትን ተረክበው ፓርቲውን እየመሩ የሚገኙ ሲሆን ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው የምክትል ሊቀመንበርነት ቦታውን ይዘው ቆይተዋል።

ኢዜማን በአሁኑ ወቅት በዋና ጸሐፊነት በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#Inflation

የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እያስመዘገቡ ነው።

ሀገራቱ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ውስጥ አይተውት የማያውቁት የዋጋ ግሽበት ነው እያስመዘገቡ ያሉት።

ለዚህ የዋጋ ግሽበት መባባስ ዛሬም ድረስ መፍትሄ ያልተገኘለትና ዓለም በጠቅላላ ያናጋው የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት እንደሆነ ይገለፃል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዩሮዞን ሀገራት በ30 እና 40 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት መመዝገቡን መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ይፋ በሆነ መረጃ ደግሞ፥ በቼክ በሚያዝያ ወር ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት 14.2% ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከ1993 ወዲህ (ከ29 ዓመታት በኃላ የተመዘገበ) ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው።

እንዲሁ በዴንማርክ አመታዊ የዋጋ ግሽበት በሚያዝያ ወር ወደ 6.7 % የጨመረ ሲሆን ይህም ከ1984 ወዲህ (ከ38 ዓመታት ወዲህ የተመዘገበ) ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት ነው።

በግሪክ (የዩሮዞን ሀገር ናት) በሚያዝያ ወር 10.2 በመቶ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቧል፤ ይህም ከ1995 ወዲህ (ከ28 ዓመታት በኃላ) ከፍተኛው ነው።

በሀገራቱ የምግብ ፣ የኃይል (ነዳጅ) ፣ የትራንስፖርት ፣ የቤት ውስጥ መገልገያዎች ዋጋ ማሻቀቡ ነው የተጠቆመው።

" ጦርነት መቼ እንደሚጀመር እንጂ መቼና እንዴት እንደሚጠናቀቅ አይታወቅም " ይባላል ፤ በሩስያ እና ዩክሬን መካከል የሚካሄደው ጦርነት ፤ ጦርነቱን ተከትሎ ምዕራባውያን በሩስያ ላይ የማዕቀብ ናዳ ማውረዳቸውና አሁንም ሌሎች ማዕቀቦችን ለመጫን እያቀዱ መሆናቸው ቀጣዩን ጊዜ ለዓለም ህዝብ እና ኢኮኖሚ እጅግ ፈታኝ እና አስቸጋሪ ያደርገዋል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ በአፍሪካ እና ሌሎች አህጉራት ያሉ ታዳጊ ሀገራት የሚደርስባቸው ጫና ከሚታሰበውም በላይ ነው።

@tikvahethiopia
* ዳንግላ

በዳንግላ ከተማ የሰዓት እላፊን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላለፉ።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ተገልጿል።

እነዚህም ፦

1. ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3:00 ስዓት እስከ ንጋቱ 12:00 መንቀሳቀስ አይችልም፤ ለባለ ሶስት እግር ባጃጅ ፣ ሞተር፣ ዳማስ፣ የህዝብ ማመላለሻ፣ የጭነት መኪኖች ከምሽቱ 3:00 ስዓት እስከ ንጋቱ 12:00 ስዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

2. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኋይል ውጭ የተመዘገበ ሆነ ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ የወገብም ሆነ የተከሻ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

3. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ፣ገጀራ፣አንካሴ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ያስጠይቃል ድርጊቱም የተከለከለ ነው።

5. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ የተከለከለ ነው።

6. የሠራዊቱን ሚሊታሪ(አልባሳት)
- የልዩ ኋይል
- የፓሊስ
- የመከላከያ ሠራዊት
- የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።

7. ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ነው።

8. ማንኛውም ግለሰብ የፀጥታ ኋይል ለሚፈለገው የስራ ትብብር ያለ ቅድመ ሁኔታ የመተባበር ግዴታ አለበት ፤ ከሚሉት ናቸው።

በቀጣይ በፀጥታው ም/ቤት እየታዩ የሚጨመሩ ክልከላዎች የሚኖሩ ይሆናልም ተብሏል።

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ም/ቤት ትላንት ያሳለፈው ውሳኔ በምን ምክንያት እንደሆነ በግልፅ የተብራራ ነገር የለም።

@tikvhahethiopia