TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Tigray

የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዳሳወቀው በዚህ ሳምንት እስካሁን 16 የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ፣ መቐለ የደረሱ ሲሆን ሌላ ኮንቮይ 64 ተሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ ይገኛሉ ይህ በ2022 6ኛው ኮንቮይ ነው።

ድርጅቱ ፥ በሚያዚያ ወር በሸራሮ ወረዳ ለሚገኙ 45,000 ሰዎች ምግብ ማቅረቡን የገለፀ ሲሆን የተመጣጠነ የምግብ ችግር ያለባቸውን 11,000 ሴቶች እና ህፃናትን መድረስ መቻሉን ገልጿል።

በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ሁኔታን ምላሽ ለመስጠት በየዕለቱ ወደ ክልሉ 100 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መግባት ያለባቸው መሆኑን ከዚህ ቀደም የዓለም ምግብ ፕሮግራም መግለፁ ይታወሳል።

ከወራቶች በፊት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ በፊት ከነበረው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መሻሻሎች ቢታዩም አሁንም ካለው ፍላጎት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛና የተቸገሩ ወገኖችን ሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት ሰፊ ስራ እንደሚጠብቅ የሚገልፁ በርካቶች ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
' የትምህር ቤት ክፍያ ' የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር። በዚህም ፥ በ2014 ዓ/ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል። ነገር ግን ላለፉት 2 እና 3 አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች…
#ክፍያ

የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በቀጣይ የትምህርት ዘመን (2015 ዓ/ም) ክፍያ መጨመር የሚችሉት የግል ትምህርት ቤቶች መለየታቸውን እና ጭማሪውም ከወላጆች ጋር መክረው የሚያደርጉት መሆኑን አስታውቋል።

ጭማሪ ማድረግ የሚችሉ ት/ቤቶች በ2014 ዓ/ም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ያላደረጉ ናቸው።

የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ ጉዳዩን ከተመለከተ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል፥ " ጭማሪ ማድረግ የሚችሉት በ2014 ምንም አይነት ጭማሪ ያላደረጉ ብቻ ናቸው። ጭማር ማድረግ ይችላሉ ሲባል ደግሞ ቀጥታ ይጨምራሉ ማለት ሳይሆን ከወላጆች ጋር መክረው / ከወላጅ ኮሚቴ ጋር መክረው ሲተማመኑ ነው " ብለዋል።

ወ/ሮ ህይወት ጭማሪ የሚደረገው ክፍያ ተፈፃሚ የሚሆነው ወላጆች እና የወልጅ ኮሚቴ ያመነበት ብቻ እንደሆነም አክለዋል።

ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ባይስማሙ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጣልቃ ገብቶ ሁለቱን አካላት የማግባባት ስራ የሚሰራ ሲሆን መንግስት ያስቀመጠውን መመሪያ ሳይከተል ወላጆች ያልተስማሙበት ወርሃዊ ክፍያ እጨምራለሁ የሚል ትምህርት ቤት ካለ እውቅና ፍቃዱ ይሰረዛል ፤ ትምህርት ቤቱ ይታሸጋል ለዚህም የተዘጋጀ በቂ መመሪያ መኖሩን የአዲስ አበባ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከተማሪ ወላጆች ጋር ምክክር ለማድረግ ቀድመው ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ሁሉም ወላጆች በት/ቤት ተገኝተው የተማሪዎች መመዝገቢያ እና የወርሃዊ ክፍያ ላይ በንቃት ተሳትፈው የጋራ ውሰኔ እንዲያሳልፉ የከተማው ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጥሪ ማቅረቡን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት አምጥተው በየዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ምደባውን እና የተለያዩ ጉዳዮችን ተከትሎ ያላቸውን ቅሬታ በኦንላይን ሲቀበል መቆየቱን ገልጾ ለቀረቡት ቅሬታዎች በሙሉ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቶ መጨረሱን ዛሬ አሳውቋል።

ይህን ተከትሎ ወደ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲዎቹ በሚያደርጉት የጥሪ መርሃ-ግብር መሰረት በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው እንዲገኙ አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት የተማሪዎችን ምደባ ይፋ ማድረጉ ፤ ይህንን ተከትሎም ቅሬታ ያላቸው ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ ማቅርቡ ይታወሳል።

በሌላ በኩል እስካሁን የመግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርሲቲዎችን ዝርዝር በዚህ ማግኘት ይቻላል : https://yangx.top/TikvahUniversity/3708

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዋጋ ግሽበት📈 መቆሚያ ያልተገኘለት የዋጋ ግሽበት አሁንም ማሻቀቡን እንደቀጠለ ነው። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ እንደሚያሳየው የመጋቢት ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ34.7 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ የምግብ ዋጋ ግሽበት የመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ43.4…
የዋጋ ግሽበት📈

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የሚያዝያ ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 36.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ምግብና ምግብ-ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች በሁለት ትልልቅ የሃይማኖት በዓላት ምክንያት በያዝነው ወር ወቅታዊ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ42.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በያዝነው ወር በተደራራቢ የሃይማኖት በዓላት መከበር ምክንያት በእህሎች የዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን የአትክልት ዋጋም ላይ መጠነኛ ጭማሪ መታየቱን ካፒታል ጋዜጣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ESP2022

በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ለEducationUSA Scholars Program (ESP) 2022 ማመልከቻ ክፍት መደረጉን ዛሬ አሳውቋል።

ኤምባሲው ፤ ESP የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት በአካዳሚክ የላቁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በአሜሪካ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በማመልከት የሰለጠኑ እና በደንብ የተማሩ መሪዎችን ለማፍራት የሚረዳ የ4 ሳምንት የስልጠና ፕሮግራም መሆኑን አስታውሷል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃንና የማመልከቻ ቅፆችን በዚህ http://ow.ly/B6b750J0X7q ማግኘት ይቻላል።

ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለመስጠት እንዲሁም ስለ ፕሮግራሙ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የፊታችን ማክሰኞ ግንቦት 2/2014 ዓ/ም የኦንላይን መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

በዚሁ ላይ ለመሳተፍ የሚከተለውን ሊንክ http://ow.ly/6e4w50J0X7s 👉Meeting ID 160 083 5437 መጠቀም እንደሚቻል በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፥ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኦንላይን ላይ ቀጠሮ አስይዘው በተለያየ ምክንያት የቀጠሮ ጊዜ ያለፈባቸው ተገልጋዮች ከዚህን ቀደም በቅጣት በማንኛውም የስራ ቀን አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን ገልጾ ከፊታችን ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ግን በስራ ሰዓት አርብ አርብ ቀን ብቻ በቅጣት አገልገሎት የሚያገኙ መሆኑን አሳውቋል።

ተገልጋዮች ይህን አውቀው በዕለቱ ብቻ እንዲገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪም ፦ የቀጠሮ ጊዜያቸው ከ1 ወር በላይ ያለፈባቸው ተገልጋዮች #በኦንላይን ላይ ዳግም ማመልከት እንዳለባቸው ገልጿል።

#ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም " የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ " ይባል የነበረው ተቋም ስያሜው የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም መሠረት " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት / Immigration and citizenship service " በሚል ስያሜ ተቀይሯል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸም የሚገኝ ገንዘብን/ ንብረትን በተለያየ ዘዴ በህጋዊ መንገድ እንደተገኘ አስመስሎ ለመጠቀም መሞከር ነው፡፡

በሀገራችን ህገወጥ ገንዘብ/ንብረት ማመንጫ ወንጅሎች ተብለው ከተለዩት መካከል ፦
👉 ሙስና፣
👉 ግብርን ማጭበርበር፣
👉 ህገወጥ የውጪ ምንዛሬ፣
👉 ህገወጥ ሀዋላ፣
👉 ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ፣
👉 አደንዛዥ ዕጽ ዝውውር፣
👉 ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት ህትመት እና ሌሎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እነዚህን ወንጀሎች የፈጸመ አካል ወንጀሎቹን በመፈጸሙ ለእያንዳንዶቹ ወንጀሎች በህግ በተደነገገው መሰረት ቅጣት ይጣልበታል።

በተጨማሪ ወንጀሎቹን በመፈጸም ያገኘውን ሀብት/ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ለማቅረብ ወይም ለመጠቀም በመሞከሩ በአዋጅ 780/2005 መሰረት ንብረቱን ሙሉ ለሙሉ መውረስ እንደተጠበቀ ሆኖ የበርካታ አመታት እሰራት እንዲፈረድበት ይደነግጋል፡፡

ምንጭ፦ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
ጋዜጠኛው የት ነው ያለው ?

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቀናት በፊት ማንነታቸውን ባልገለጹ የመንግስት ሰዎች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ተይዞ መወሰዱንና የት እንዳለ አለመታወቁ መግለፁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጋዜጠኛው የት እና በምን ሁኔታ እንዳለ ግልፅ እንዲደረግ እየጠየቁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከልም የጋዜጠኛው የት እንዳለ አለመታወቅ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ማዕከሉ ፤ መንግስት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የት እንዳለ እንዲያሳውቅ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ፤ ከ2019 ጀምሮ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን የሚሟገቱ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኞችን አቅም በመገንባት፣ ከለላ በመስጠት እና በማስተዋወቅ ላይ የሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዋሪዎችን ያማረሩት ጫኝ እና አውራጆች ፦ ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦ " ... በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሁሉም ሰፈር ማለት ይቻላል በህገወጥ ጫኝና አውራጆች በሚጠየቅ የተጋነነ ክፍያ ምክንያት ዕቃ መኪና ላይ መጫንም ሆነ ማውረድ አዳጋች ሆኗል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህ ህገ ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ሊታደግ ይገባል። ሰው ተሰቃይቷል ፤ ህዝቡ ተበሳጭቷል ፤ ጉረቤትህ እና ልጆችህ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ጫኝና አውራጆች ያለአግባብ ገንዘብ በመጠየቅ ነዋሪዎችን እያማረሩ ነው።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመዲናዋ ከሚገኙ የጫኝና አውራጅ ማህበራት ጋር ምክክር አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ዳይሬክተር ኮማንደር ሰለሞን ፋንታሁን ህብረተሰቡ ንብረቱን ከቦታ ቦታ ሲያንቀሳቅስ በጫኝና አውራጅ ያለአግባብ ገንዘብ እየተጠየቀ በመሆኑ ነዋሪዎች ለምሬት ተዳርገዋል ብለዋል።

ንብረቱ ከሚገዛበት ዋጋ በላይ ህብረተሰቡ እንዲከፍል እየተጠየቀ መሆኑ ንብረታቸውን በለሊት ፈረቃ እንዲያጓጉዙ ተገደዋል ሲሉም ገልፀዋል።

ጫኝና አውራጆች ያልተደራጁበት ቦታ ላይ በመምጣት እናወርዳለን በማለት ግጭት የሚፈጠርበት ሁኔታ መኖሩን አክለዋል፡፡

አቅመ ደካሞች ገንዘብ የለንም ሲሉ ፍቃደኛ አለመሆን በጉልበት ለማስገደድ መሞከር፣ጠጥተው በመምጣት ከማህበረሰቡ ጋር መጋጨት፣ ገንዘብ አስገድዶ መቀበል የሚሉት ዋናነት የሚታዩ ችግሮች መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

በህጋዊ መንገድ የተደራጁ ጫኝና አውራጆች ደግሞ ከስራ አድል ፈጠራ ባሻገር #መብትና_ግዴታቸውን_ያለማወቅ ችግር እንዳለባቸዉ የጠቀሱት ኮማንደር ሰለሞን መሰል ሕገወጥ ድርጊቶችን መከላለል የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ ህብረተሰቡም ሊተባበር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ በተካሄደው መድረክ በከተማዋ 1072 ህጋዊና 577 ህገወጥ ጫኝና አውራጅ ማህበራት ይገኛሉ መባሉን አዲስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

#ማስታወሻ ፦ ያልተገባ ስራ የሚሰሩ ጫኝ እና ወራጆችን ወደ ህግ ከማቅረብ ይልቅ #ተስማሙ የሚሉ የፖሊስ አባላትን ህብረተሰቡ ሲመለከት በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና በ 0111110111 በመደወል ለፖሊስ መጠቆም ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 🪪 " ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ መስጠት አቁመናል " - የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ላልተወሰነ ጊዜ " አዲስ መታወቂያ " የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል። ኤጀንሲው የመታወቂያ ፣ የልደት ፣ የጋብቻና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል ፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡ በአገልግሎት አሰጣቱ…
#መታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተበራከተ የመጣዉን ሰነድ እና የነዋሪነት መታወቂያ አስመስሎ የመስራት /ፎርጀሪ/ ወንጀል ተጋላጭነትን ለመከላከል አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ከሚያዚያ 21፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እድሚያቸው 18 ዓመት ሞልቶ የነዋሪነት መታወቂያ ያላወጡ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ ተማሪዎች ፦

* በከተማዉ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ መሆኑን የሚያስረዳ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ እና

* ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለፉበትን ዉጤት በማቅረብ በነዋሪነት የቤተሰብ ቅጽ ዉሰጥ አስቀድሞ የተመዘገቡ መሆኑ ሲረጋገጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ተፈቅዷል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ወ/ኩ/ም/ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#ሌተናል_ኮሎኔል_ፍሥሐ_ደስታ

በድረግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያን በምክትል ፕሬዝዳንትነት የመሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ምክትል በመሆን የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ፣ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር ቆይተዋል።

ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን ለዚህም በአገር ውስጥና በውጪ ክትትል ሲያደርጉ ነበር።

ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩት ፍሰሐ ሕይወታቸው ያለፈው አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ. ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ከእስር ከወጡ በኋላ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ "አብዮቱና ትዝታዬ" የሚል መጽሐፍ ያበረከቱ ሲሆን፣ በዚህም "ደርግ በወሰዳቸው በጎ ዕርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለው ነበር።

ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ከመጀመሪያው መጽሐፋቸው በተጨማሪ 2ኛ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደነበሩ ቢቢሲ ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

ትግራይ አድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌፍተናንት ኮሎኔል ፍሰሐ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአደዋ ንግሥተ ሳባ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-05-07

@tikvahethiopia