TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፎቶ : የስቅለት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም።

ፎቶ :- በዲ.ን ሙሉዓለም ዐሥራት (EOTC TV)

@tikvahethiopia
ፎቶ : ዛሬ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን።

ፎቶ ፦ St. Joseph Catholic Church , St. Francis Parish , St. Gebriel Catholic Church , Bezawit Assefa

@tikvahethiopia
#IFTAR

ዛሬ እና ትላንት በተለያዩ ከተሞች ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ታካሂዷል።

የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች አንዷ መዲናችን አዲስ አበባ ስትሆን በቤተል አደባባይ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በደ/ወሎ ልጓማ ከተማ፣ ሶማሌ ክልል ቀብሪደሃር ከተማ ፣ በወራቤ ከተማ ፣ በአፋር ማንዳ ከተማ ፣ በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ፤ ኬራቴ ከተማ ፣ ሻሸመኔ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

ትላንት ደግሞ ፤ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ በጅማ ዞን ኦማንዳ ወረዳ ፣ በኢሊአባቦር ዞን አልጌ ሰቺ ወረዳ ፣ ሰንዳፋ በኬ ፣ ቡራዩ ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ፣ ጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ፣ በወልቃይት ሁመራ እና በወልቂጤ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

የሁሉንም የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፎቶዎች ይመልከቱ ፦ https://telegra.ph/Iftar-04-22

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform

ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።

የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።

http://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።
#LineAddis

የከፍተኛ ትምህርትዎን በተለያዩ ሀገራት ለመማር በሚያደርጉት ሂደት የአድቫንስድ እንግሊዝኛ ስልጠና ፣ የዶክመንቴሽን ዝግጅት እንዲሁም የቅድመ እና ድህረ በረራ አገልግሎቶችን ቢፈልጉ ላይን አዲስ ኮንሰልታንሲ #ያማክርዎታል። ለተጨማሪ ቴሌግራም ቻነል @lineaddisconsultancy ይጎብኙ።

ስልክ፦ 0116671693 / 0115580951

አድራሻ ቦሌ ራክሲም ፕላዛ 5ኛ ፍሎር ወይንም ለቡ ፎዝያና ሕንፃ 5ኛ ፍሎር
#ዋግኽምራ 📍

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ አመልክተዋል ተብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የሚስተዋለውን የግጭት ሁኔታ አንስተውም ሰላምን ማስፈን የሰላማዊ ወኪል ለመሆን ወስኖ በቁርጠኝነት የሰላም እሴቶችን መገንባትን ይጠይቃል ማለታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

ዋግኽምራ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ፣ እንግልት እና ስቃይ የደረሰበት አካባቢ ሲሆን አሁንም ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው ይገኘሉ።

@tikvahethiopia