TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Russia

ሩስያ ተጨማሪ አሜሪካውያንን ' ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳይሉ ስትል " እገዳ ጣለች።

ሩስያ በዛሬው ዕለት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የፌስቡክ (Facebook) መስራች ማርክ ዙከርበርግን ጨምሮ 29 የአሜሪካ ባለስልጣናት ፣ የንግድ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ወደ ሀገሯ እንዳይደርሱ እገዳ ጥላባቸዋለች።

በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው የማዕቀብ ዝርዝር ከምክትል ፕሬዜዳንት ካማላ ሃሪስ እና ከፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በተጨማሪ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ካትሊን ሂክስ እና የፔንታጎን ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ይገኙበታል።

ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ላይ ፤ " እነዚህ ግለሰቦች ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሩሲያ ፌዴሬሽን እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 313 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እየሰጠች መሆኑ አስታውቃለች።

አሜሪካ ፤ በ #USAID በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ወደ 313 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ እርዳታ እየሰጠች መሆኑን ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአፋር ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች እየተካሄድ ያለው ግጭት ወደ 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋላጠቸው ሲሆን ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ ማድረጉንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ብቻ 90 % የሚሆነው የክልሉ ህዝብ እርዳታ የሚሻ ነው ያለው መግለጫው በ3ቱም ክልሎች ወደ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በሚቀጥለው ሰኔ ከፍተኛ ረሀብ ለመሰለ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ብሏል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው አዲሱ እርዳታ ወደ 7 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያደርግ ሲሆን የማህበረሰባዊ ጤና ተቋማትን ለማጠናከር የሚውል መሆኑም ድርጅቱ መግለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform

ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።

የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።

http://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።
" ስቅለት "

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡

በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

11 ሰዓት

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።

@tikvahethiopia
#በዓላትና_ትራንስፖርት

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሮታን እያስነሳ መፍትሔ ያላገኘው የበዓል ሰሞን የትራንስፖርት አገልግሎት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

መጪው የትንሳኤ በዓልን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ትራንስፖርት የለም በማለት በደላላ ትኬት የመሸጥ እና ከመደበኛ ዋጋ እጥፍ ወይም ከፍ አድርገው እየሸጡ ይገኛሉ።

በተላይ ሰሞኑን በርካታ ሰዎች ከአዲስአበባ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በዓል ለማክበር ወደ ቤተሰብ ጋር ለመሄድ በዚህ የትራንስፖርት ዘርፍ ብልሹ አሰራር ምክንያት እየተጉላሉ እና ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ ይገኛሉ።

በዚህ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ በሚታየው ብልሹ አሰራር በስምሪት ላይ የሚሰሩ የተለያዩ አካላት ፣ አንድ አንድ ብልሹ ስነምግባር ያላቸው የትራፊክ ፖሊሶች እና ደላሎች በተጨማሪም የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ችግሩን መፍትሔ አልባ አድርጎታል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ለመፍታት የመፍትሔ ስራ በመስራት ለማስተካከል ቢሰሩ መልካም ነው ብለዋል ትራንስፖርት ለመጠቀም በመጠበቅ ላይ ያሉ ተሳፋሪዎች።

#ጋዜጠኛ_ነፃነት_ጌታቸው

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስቴርና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ! ከብሄራዊ ፈተና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮች ለመቅረፍ ከፈተና ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ማሳወቅ ያሉትን ተግባራት በጥቃቄ እንዲከናወኑ ፦ 1ኛ. ፈተናዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፎ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፤ ይህ እውን እስኪሆን ድረስ የሚሰጡ…
#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡ 3,628 ተማሪዎች ተለይተው የ2014 ፈተናን (በድጋሚ) እንዲወስዱ እድል እንደተሰጣቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር ውስጥ በመሆን የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ባሳለፈው የድጋሚ ፈተና ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ብሏል።

በሰባት ዞኖች ማለትም ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ እንዲሁም ምዕራብ ሸዋ ውጤት ያልመጣላቸው በሙሉ ከዘንድሮ ተፈታኞች ጋር ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን 7 ወረዳዎች፣ በጅማ ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ምዕራብ ሀረርጌ ሁለት ሁለት ወረዳዎች እንዲሁም በቦረና 3 ወረዳዎች ፣ በምስራቅ ሀገርጌ 1 ወረዳም የድጋሜ ፈተና ከተፈቀደላቸው መካከል ይገኙበታል።

የድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱት አጠቃላይ 3,628 ተማሪዎች መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

እንደ ኦሮሚያ ክልል ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 253 ሺህ ተማሪዎች መካከል 134 ሺህ ተማሪዎች ለከፍተኛ ትምህርት አልፈዋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና ዕድል እንዲሰጣቸው በተለዩ አካባቢዎች ቀጣዩን ፈተና ለመውሰድ የሚያስችል የፀጥታ እና የደህንነት ሁኔታ መኖሩ በተመለከተ በዚህ ላይ " የክልሉ መንግስት እና የፀጥታ አካላት እየሰራ ነው " ያለ ሲሆን ቢሮው በፈተና ወቅት ሰላማዊ ሁኔታ ይፈጠራል ብሎ እንደሚጠብቅ መግለፁን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኋላ መግለጫ  አውጥቷል።

ም/ቤቱ ፤ ከሰላምና ከሀገር ደኅንነት  በተቃራኒው ተሰልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ፣ አካል እና ቡድን ላይ ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢውን ሕግና ጸጥታ የማስከበር ሥራ ይሰራል ሲል አሳስቧል።

የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኙ የገለፀው መግለጫው " አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ ተመጣጣኝ ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ አንልም " ብሏል።

በተጨማሪ የደህንነት ምክር ቤቱ የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥ መንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ፎቶ : የስቅለት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም።

ፎቶ :- በዲ.ን ሙሉዓለም ዐሥራት (EOTC TV)

@tikvahethiopia