TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል። የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል። መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች…
#MoE

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን አልተወሰነም።

@tikvahuniversity ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች በየዕለቱ ከተማሪዎች እና ወላጆች እየደረሱት ይገኛል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላትን የጠየቅን ሲሆን " የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን አሁንም አለመወሰኑን " ተገልጾልናል።

ምደባው ይፋ እስከሚሆን ተማሪዎች እና ወላጆች ለትንሽ ጊዜ በትግዕስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።

ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይሸበሩም መልዕክት ተላልፏል።

ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ የምናገኘውን አዲስ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

@tikvahuniversity
#FINTEX2022

3ኛው የፈርኒቸር፣ ቤተ-ውበት እና ግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ እና ጉባዔ (FINTEX 2022) ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 01 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።

በፈርኒቸር፣ ቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች የገበያ ሰንሰለት ላይ የተዘጋጀው ኤክስፖ በእንጨት ስራ፣ በቤት በቢሮ እና በኢንዱስትሪ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የውስጥ እና የውጪ ማስዋቢያ ምርቶች፣ መብራቶች፣ መጋረጃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች በአንድ መድረክ አሰባስቦ ይጠብቅዎታል፡፡

ለመጎብኘት ቀድመው በድረገፃችን ይመዝገቡ : https://bit.ly/3IWUnMm
TIKVAH-ETHIOPIA
Amnesty International & HRW .pdf
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ይፋ በሆነው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ በርቀት የሚደረግ ምርመራ ውስንነቶች እና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አንዳንድ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም ፦

👉 ከማይካድራ አንፃር በትግራይ ሚሊሻና ፖሊስ ድጋፍ በሳምሪ ቡድን በአማራ ሲቪሎች ላይ የተፈጸመው ግድያና ማፈናቀል፤

👉 በአፀፋ/በቀል የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ እና የፋኖ ቡድን የትግራይ ተወላጆች ላይ ያደረሱት ጥቃት እና ህገወጥ መጠነ ሰፊ ማፈናቀል ፤ የሚገልፁ የሪፖርቱ ግኝንቶች ከኢሰመኮ ጋር እንዲሁም በትግራይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (JIT) ጋር ከተሰራው የጣምራ ምርመራ ጋር ተመሳሳይ ናቸው ብለዋል።

በሁሉም ወገኖች የተፈፀሙ የግድያና መጠነ ሰፊ በኃይል የማፈናቀል ተግባራት የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋል።

ራኬብ ፥ የጣምራ ምርመራ ሪፖርት (JIT) ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲደረጉ ፤ ሁሉም ተዋናይ ወገኖች ተጨማሪ መፈናቀልን ሊያስከትሉ የሚችሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ፤ ሁሉም የውስጥ ተፈናቃዮች በፍቃደኝነት እንዲመለሱ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታን እንዲፈጥሩ፤ ለወልቃይት-ፀገዴ የተራዘመ የመሬት ውዝግብ በዘላቂነት እልባት እንዲገኝ አሳስበዋል።

የትላንቱን ሪፖርት ካዘጋጁት አንዱ ሂውማን ራይስት ዎች ከዚህ ቀደም በኢሰመኮና OHCHR ስለተሰራው የጣምራ ሪፖርት አስተያየት የሰጠ ሲሆን በግኝቶቻችን ውስጥ በርካታ ቁልፍ ልዩነቶች አሉ ብሏል። በጣምራ ሪፖርቱ ላይ በትግራይ ተወላጆች ላይ ስለተፈፀኑት ግፍፎችና የማሸብር ድርጊቶች ብዙም አልተጠቀሰም ሲል ገልጿል: telegra.ph/HRW-04-07

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ትላንትና በባቲ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በሀገራችን የጎዳና ላይ ኢፍጧር በማሰናዳት ፈር ቀዳኝ በሆነው በአቢ-ዘር የማህበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት አማካኝነት የተዘጋጀው ይኸው የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርኣት እጅግ በርካታ ወገኖች የተገኙበት ነበር።

የልማት ድርጅቱ መሰል ስነስርዓቶችን ከማዘጋጀት ባለፈ የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ በጎ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን አቅም ላነሳቸው ወገኖቻችንም የተለያዩ አይነት እገዛዎችን የሚያደርግ ነው።

Photo Credit : Mohammed Ebnu Seid (Tikvah - Family Bati)

@tikvahethiopia
#HoPR

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ም/ቤቱ እያካሄደ ባለው ሰብሰባ የም/ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ አፅድቋል።

በተጨማሪ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት ፦

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሰብሳቢ
2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ም/ሰብሳቢ
3. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል፤ አባል
4. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
5. ዶ/ር በድሉ ዋቅጀራ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
6. ዶ/ር መሣይ ገ/ማሪያም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ አባል
7. ዶ/ር ወዳጀነህ ማዕረነ አማካሪ፤ አባል
8. ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል
9. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል ሆነው ሹመተቸው በተቃውሞ በ11 እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በአሁን ሰዓት ም/ቤቱ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማድመጥ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ም/ቤቱ እያካሄደ ባለው ሰብሰባ የም/ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ አፅድቋል። በተጨማሪ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል። በዚህም መሰረት ፦ 1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፤…
#MoE

መንግስት ከ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከባድ ፈተናዎች ገጥሞት እንደነበር እና የፀጥታ ኃይሎችም ተሰውተው እንደነበረ ገለፀ።

ይህ የተሰማው ትምህርት ሚኒስቴር የ9ወር የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት ካቀረበ በኃላ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማብራሪያ በፈተና ስርጭት ወቅት እጅግ ከባድ የሚባል ፈተና እንደነበር ገልጿል።

" ስርጭት ሲባል ፈተናውን ማድረስ እና የፈተናውን የመልስ ወረቀት መመለስ ጭምር ያካታታል ያሉት " የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ፥ " በስርጭቱ ሂደት ከዚህ በፊታ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ 3000 የሚጠጉ የፈተና ጣቢያዎች (ንዑስ ወረዳ ድረሥ) ላይ ፈተና የደረሰ ሲሆን ከባለፉት ዓመታት በ3 እጥፍ ያደገ ነው " ብለዋል።

" ፈተና መፈተን እራሱ ፈተና ነው የሚያስብል ነገር ያጋጠመን ስርጭት ላይ ነው " ያሉት ም/ ዋና ዳይሬክተሩ ፥ " በብዙ ቦታዎች ላይ የክልል መንግስታት ፣ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ዋጋ እየከፈሉ እየተሰው ያደረሱበት ቦታ አለ። " ብለዋል።

የፌዴራል ፖሊስ አባላትም የተሰውቡት ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል።

" አንድ፣ ሁለት ፈተና ጣቢያዎች ላይ ማድረስም አቅቶን እስከመጨረሻ ድረስ ፈተናው ላይ እርምጃ የተወሰደበት ሁኔታ ነው የነበረው። " ሲሉም አስረድተዋል። እርምጃውን ግን በግልፅ አላብራሩም።

ከዚህ ባለፈ የፈተናው የመልስ ወረቀት በሚመለስበት ጊዜ ከባድ ፈተናዎችም እንደነበሩ ተጠቁሟል።

" ከዚህ በፊት የተማሪዎች መልስ የሚመጣው በአውቶብስ ነው ፤ ዘንድሮ ግን የተማሪዎችን የመልስ ወረቀት ለማውጣት የፌዴራል ፖሊሶች የተሰውቡት ሁኔታ ነበር የነበረው " ብለዋል።

የተማሪዎችን የፈተና መልስ ወረቀት ይዘው ለመውጣት በነበረ ሂደት 3 የፌዴራል ፖሊስ መሰዋታቸውን ተገልጿል። [ ቦታው የት እንደሆነ በግልፅ አልተብራራም ]

በ3 ጣቢያዎች ላይ ደግሞ አንድ ሳምንት ሙሉ የፈተናውን ወረቀት ማውጣት ያልተቻለበት በኃላ በሀገር ሽማግሌ የወጣትበት ሁኔታ ነበር ተብሏል። [ ቦታው የት እንደሆነ በግልፅ አልንተብራራም ]

ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ፥ " ስርጭቱ ከባድ ፈተና ነበር ፤ በፈተና ክዘና ላይ፣ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ይዞ መገኘት ፣ ለሰው መፈተን ፣ ፈታኞችን Abuse የማድረግ በጣም ብዙ ቦታዎች ችግሮች ነበሩ። ይህ ችግር አንድ ክልል ብቻ ተብሎ የሚወሰድ ሳይሆን ሁሉም አካባቢ ነበር " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE መንግስት ከ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከባድ ፈተናዎች ገጥሞት እንደነበር እና የፀጥታ ኃይሎችም ተሰውተው እንደነበረ ገለፀ። ይህ የተሰማው ትምህርት ሚኒስቴር የ9ወር የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት ካቀረበ በኃላ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማብራሪያ በፈተና ስርጭት ወቅት እጅግ ከባድ…
የመምህራን ጥራት ጉዳይ !

" ... በመምህራን ጥራት ላይ ያለውን ችግር ታውቁታላችሁ። #በሚያስተምሩበት ትምህርት ፈተና ተሰጥቷቸው ምዘናውን ያለፉ ከ50% በላይ ያገኙ መምህሮቻችን ከ30% በታች ናቸው፤ በሚያስተምሩት ትምህርት ነው የምላችሁ። አስቡት ባዛ እውቀት ላይ ያለ ልጆች አስተምሮ ምን ያህል ያበቃል ?

አስተማሪዎች ጥራት ላይ በከፍተኛ ደረጃ ለመስራት አሁን የኮተቤን መምህራን ትምህርት ቤት ካሪኩለሙን በሙሉ ፤ ሌላ ትምህርት የሚያስተምረውን አቁሞ የዚህ ሀገር ጥሩ መምህራን የሚወጡበት ቦታ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ እየሰራን ነው ፤ ኳሊቲውን እና የቅበላ አቅሙን ለማሻገር " - የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ረመዷን ከሪም ! አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ 25 የአገራችን ከተሞች ላይ ለፆም መያዣ (ሱሁር) እና ማፍጠሪያ የሚያገለግል የ 2014 ዓ.ም. የጊዜ ሰሌዳ ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ቻነል ሊንክ በመጠቀም ያግኙ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል መቀላቀልዎንም አይርሱ ! https://yangx.top/BoAEth
አቢሲንያ አሚን! ዕሴትዎን ያከበረ!
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ " ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 % ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን እኤአ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA #EHRC

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እና ከምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር ውይይት አደረጉ።

ውይይቱ ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰቱት ግጭቶች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በተመለከተ መሆኑን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ኬላ

የጉምሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ህገ ወጥ ናቸው ተብሏል።

ከትላንት በስቲያ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት አንድ ጥያቄ ተጠይቆ ነበር።

ይኸውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተከፈቱት የቁጥጥር ኬላዎች አሁንም አዋጅ ከተነሳ በኃላ ገመድ በመዘርጋት እያስቆሙ የትራንስፖርት ሁኔታውን እያጓተቱ ነው በእዚህ ላይ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ነበር።

ይህንን በተመለከተ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገ/መስቀል ጫላ የጉምሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ህገ ወጥ ናቸው ብለዋል።

አቶ ገ/መስቀል ጫላ ፦

" ከስምንት ወራት በኃላ በሁሉም ክልሎች በሚባልበት ደረጃ ጉሙሩክ የሚያውቃቸው ኬላዎች ካልሆኑ በስተቀር ኬላዎች እንዲነሱ ተደርጓል።

የጉሙሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ኬላ ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ካሉ ህገወጥ ናቸው። ይሄ በግልፅ መታወቅ አለበት። ህገወጥ ናቸው ግን እኛ ባለን መረጃ አብዛኛዎቹ ክልሎች ይሄንን ኬላ አንስተው የጉሙሩክ ኬላዎች ብቻ ገቢ እና ወጪ እቃዎችን የሚቆጣጠሩበት ሁኔታ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia