TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ደግም ያገረሸው ግጭት በመኃል ለቀናት ጋብ እያለ የመጣ ቢሆንም ከመጋቢት 15 ወዲህ ግን ለተከታታይ 4 ቀናት ያለመቋረጥ በቀጠለ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን፤ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸዋል። በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር በኩል " ዲማያ " የሚባል አካባቢ…
#Update
ዳግም ባገረሸው የኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ ግጭት የሁለቱ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታው መዋቅር፣ ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል አመራሮች በተገኙበት የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት የሁለትዮሽ ዉይይት ዛሬ አካሂደዋል።
ዛሬ በነበረው ውይይት ላይ ሰው ሰራሽ ችግሮች ሲከሰቱ እንደመንግስት እና አጎራባች ህዝቦች ትክክለኛ መረጃ አለመናበብ ፣ በሀሰት የመፈራረጅ አዝማሚያዎች እና ህዝብን ለግጭት የሚዳርጉ ትንኮሳ እና ኡሉባልታዎች መኖራቸው ተገምግሟል።
በውይይቱ በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ህዝቦች መካከል ለሠላም ግንባታና ቀጠናውን ለመረጋጋት የሁለትዮሽ የውሳኔ ሀሳብን መተላለፉ ታውቋል።
በዚህም ፦
👉 ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ድምፅ እንዳይሰማ ፤
👉 በኮልሜና ኧሌ ህዝቦች መካከል ሠላምና ደህንነት የሚከታተሉ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ቡድን አቋቁሞ ስለ ሠላም እንዲሰሩ ወደ ተግባር ማስገባት፣
👉 የፖለቲካ አመራሩ በሁለቱም መዋቅሮች ህዝባዊ ዉይይቶችን እንዲያደርጉ፣
👉 በክልሉ በኩል የተጀመሩ ስለ ሠላም እና አንድነት ሥራዎችን ማስቀጠልና የህዝቡን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም እንዲረባረብ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተደርሷል።
የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሰራዊት ቲቶ ለቲክቫህ ፤ " ቡድኑ ከልዩ ኃይሉ ጋር የሚተባበርና በትኩረት ሊሰራ የሚችል ከአሌ ልዩ ወረዳ የተወጣጣ ከኮንሶ ዞንም የተወጣጣ የፖሊስ ሰራዊትና የሚሊሻ ሰራዊት በሁሉም ቀጠናዎች በመናበብ ከልዩ ኃይሉም ጋር በመናበብ ውስጥ ለውስጥ የሚከሰቱ ጥቃቅን ችግሮች ጨምሮ በይበልጥ እንዲከታተል ለማድረግ የታሰበ ነው " ብለዋል።
@tikvahethiopia

#Tigray የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆመ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ከመንግስት ውሳኔ በኃላም ከትግራይ ክልል በኩል በጎ ምላሽ መኖሩ ለበርካታ ወራት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እና ከክልሉ ውጭ ላሉ ቤተሰቦች በጎ ተስፋን ያጫረ እንደሆነ ይታመናል። ነገር ግን ከዚህ በፊት የመከላከያ ኃይል ባለበት ፀንቶ ይቆያል ከሚለው ውሳኔ በምን ይለያል የሚል ጥያቄ የሚነሳ ሲሆን የመንግስት…
#Update
የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አስገነዘበ።
መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል መንግስት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል።
ነገር ግን ውሳኔ ከተላላለፈበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ እንዳልቻለ የክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
ክልሉን ወክለው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ወደግጭት ማቆም እንዲደረስ ብዙ ጥረት አድርጓል፤ የባለፈው ሳምንት ስምምነት ዝም ብሎ የመጣ ስምምነት አይደለም ብዙ ጊዜ የተሰራበት ስምምነት ነው ብለዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ለምን እንዳልገባ የተጠየቁት ፕ/ር ክንደያ ፤ ኃይላቸው በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የእርዳታ መኪናዎች ስላልደረሱ ማወቅ እንዳልቻሉ ፤ ለምን እንዳልተላኩ መላክና ማሳለፍ የሚገባቸው አካላት ማብራሪ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
ከባለፈው ሃምሌ ወር በየዕለቱ 100 የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደነበረባቸው የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ይገልፃሉ አሁን ያለው ችግር ሲታይ ፍላጎቱ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን ያለው ግጭት ለማቆም እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ የሚለው ውሳኔ ካልተሳካ ለረጅም ጊዜ ተዘጋግቶ መጠበቅ ስለማይቻል ሌላ አማራጭ እናያለን ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤
" ... እነሱ ግጭት እናቆማለን ብለው አልነበር እንዴ ? ቀደም ብሎ መንግስት የትኛውም አይነት ትንኮሳ እንደማይፈፅም እና የትኛውም አይነት ግጭት ውስጥ እንደማይገባ አስቀምጧል።
በአንፃሩ እነሱ እርዳታው በቀላሉ ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ በጉልበት ከያዟቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች መውጣት አለባቸው ብሎ አስቀምጧል። እስከዛሬ ድረስ ከ5 ወይም 6 ወረዳዎች አልወጡም።
እንደውም ትላንትና 'ኮኖባ' በሚባል ቦታ ከአፋር ሚሊሻ ጋር ጦርነት ነበር።
ለህዝቡ ካሰቡ ከያዙት ቦታ መውጣት እና መንገዱን ክፍት ማድረግ አለባቸው። ይሄን ሳያደርጉ መንግስት ሆን ብሎ ነው የሚለው ትክክል አይደለም "
👉 መጋሌ ፣
👉 ኤሬብቲ ፣
👉 በርሃሌ፣
👉 አብዓላ የተባሉ የአፋር ቦታዎችን የ " ህወሓት ኃይሎች " ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
" ... ይሄ በዋናነት እርዳታው የሚሄድበት የአስፓልት መንገድ ላይ ነው ያለው። ይሄንን መልቀቅ አለባቸው ይሄንን ሳይለቁ ' መንግስት እርዳታ አላቀረበም ' ብለው ቅሬታ ማቅረብ ሚችሉበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። ስለዚህ እርዳታው ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ ለህብረተሰቡ የሚያስቡ ከሆነ በጉልበት ከያዟቸው አካባቢዎች መልቀቅ ነው ያለባቸው፤ አካባቢውን ከግጭት ነፃ ነው ማድረግ ያለባቸው ። " ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ፤ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ዝግጅቱነት በመተመለከተ 3 የነዳጅ እና 20 የእርዳታ እህል የጫኑ 23 መኪናዎች ቆመዋል (ከዚህ በፊት ሄደው በፀጥታ ችግር የተመለሱ) ፤ በተጨማሪ ሰመራ ላይ ከመጋዘን ለመጫን የሚጠባበቁ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችም አሉ በአጠቃላይ 43 ተሽከርካሪዎች ናቸው መንገዱ ካልተከፈተ እና ግጭት ካልቆመ እርዳታ ሊሄድ አይችልም ብለዋል።
መንግስት የወሰነው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ እስከመቼ እንደሚቆየ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " በመንግስት በኩል የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም። ህብረተሰቡ ወደ ተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመጣ ነው መንግስት የሚፈልገው ፤ አካባቢውም ተረጋግቶ መጪውም ክረምት ስለሆነ እርሻውን እንዲያርስ መንግስት የሚፈልገው ከዛ ውጭ የሚደረግ ነገር ካለ እሱን በሂደት ይታያል። " ብለዋል።

🌧 ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ - ዝናብ ጥሏል 🌧 በታሪኳ እጅግ አስከፊ በሆነ ድርቅ ላይ የምትገኘው እና 4.5 ሚሊዮን ህዝቧ ለረሃብ የተጋለጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ዝናብ አግኝታለች። በሀገሪቱ ብዙ ክፍሎች ላይ ዝናብ መጣሉን የሚገልፁ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። አሁንም ከፍተኛ ደመና በተለያዩ ቦታዎች የሚታይ ሲሆን ብዙ ቦታዎች ተጨማሪ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል። ዝናቡ ሲጠፋ የድርቅ አደጋ ፤ ዝናቡ ሲገኝ…
#KENYA
በመጨረሻም በጎረቤታችን ኬንያ የዘገየው የዝናብ ወቅት ጀመረ።
በኬንያ አብዛኛው ክፍል የዘገየው የዝናብ ወቅት አሁን መጀመሩን የኬንያ ሚቲዎሮሎጂ ዲፓርትመንት ማሳወቁን ካፒታል ኒውስ ኬንያ አስነብቧል።
ይህ ሁኔታ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ለነበሩ ኬንያውያን እና ለተጨማሪ የሰብል እና የግጦሽ ሳር መጥፋት አደጋ ላይ ለነበሩ አርሶ እና አርብቶ አደሮች እፎይታን ፈጥሯል።
የኬንያ ሚቲዎሮሎጂ ዲፓርትመንት በሳምንታዊ ትንበያው አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች አማካይ እና ከአማካይ ጋር የሚቀራረብ ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል።
ኬንያ በአፍሪካ ቀንድ በድርቅ ከተጠቁ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በሀገሪቱ 3.5 ሚሊዮን ሰዎች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
ከሰሞኑን በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም ድርቅ ባጠቃቸው አካባቢዎች እንዲሁም አስከፊ ድርቅ ባጋጠማት ጎረቤታችን ሶማሊያ ዝናብ እየጣለ መሆኑን መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።
እንደ ተመድ መረጃ በኢትዮጵያ ፣ በሶማሊያ ፣ በኬንያ በተከሰተው ድርቅ 13 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ችግር ተጋልጧል።

ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሶሴትድ ፕሬስ (AP) ዘጋቢ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኞቹ ከአገር እንዳይወጡ የጉዞ እገዳም አስተላልፎባቸዋል።
ጋዜጠኞቹ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለ የተፈረጀውን "ሸኔ" ን በዓለም አቀፍ ደረጃ አስተዋውቃችኃል ተብለው ተጠርጥረው መያዛቸው ይታወሳል።
የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ከታሰሩ ወዲህ ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው።
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የጋዜጠኞቹ የትዳር አጋሮችን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባላቶቻቸው በአካል ተገኝተው ሂደቱን መከታተላቸው ethiopiainsider.com ዘግቧል።

#ETHIOPIA
ከነገ ጀምሮ ዜጎቻችንን የመመለስ ስራ ይጀመራል ተብሏል።
ለረጅም ጊዜያት ሲጠበቅ የነበረው በሳዑዲ አረቢያ በከፋ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ሥራ እንደሚጀመር አስታውቋል።
ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከ7 እስከ 11 ባሉት ወራት ውስጥ ለመመለስ እንደታቀደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

#Bichena📍
2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን በቀን 19/07/2014 ዓ/ም ወደ ብቸና ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ቀርበው የማያውቁት ሰው ስልክ እየደወለ " ልጅሽን አግተነዋልና ዛሬውኑ 400,000 ብር ካላመጣሽ እንገለዋለን " እያለኝ ነው የሚል መረጃ ለፖሊስ ይሰጣሉ።
የብቸና ፖሊስም አባላቱን ስምሪት ውስጥ በማስገባት በተጠርጣሪወች ላይ ክትትል ማድረግ ይጀምራል።
ፖሊስ በ " ስልክ ልውውጡ " መሰረት አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማድረግ ሲጀምር እድሜያቸው 12 ዓመት እና 14 አመት የሆኑ 2 ወንድ ታዳጊዎች ታግተው የሚገኙበትን ቦታ መረጃ ያገኛል።
ፖሊስ ባገኘው መረጃ መሰረት ጥቆማ የሰጠውን ተጠርጣሪ እንዲመራ በማድረግ ታዳጊዎቹ ታግተዋል ተብሎ ወደተጠረጠረበት ቦታ ይጓዛል።
በዚህም አጎራባች ከሆነው " እነማይ ወረዳ " ውስጥ እድገት በአንድነት ቀበሌ ሁለቱ ታዳጊወች ሰው ከማይኖርበት ባዶ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው በ2ኛ ተጠርጣሪ እየተጠበቁ እንዳለ እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የታገቱት ታዳጊዎች ወደ ፖሊስ ከቀረቡ በኋላ ሁኔታውን ፥ በመጫወት ላይ እንዳሉ ሁለት የማያውቋቸው ሰዎች ጠርተው " ወንጀል ፈፅማችኋልና ትፈለጋላችሁ " በሚል በባጃጅ አስገብተው ወደማያውቁት ቦታ በመውሰድ ባዶ ቤት ውስጥ እንደዘጉባቸው አስረድተዋል።
የብቸና ፖሊስ በእገታ ወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት 2 ግለሰቦች ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ገልጿል።
መረጃው የብቸና ከተማ አስ/ፖሊስ ነው።

#NEBE
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል።
በዚህም ምክክር ወቅት ይፋ ያደረገው ለፓርቲዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ መጠን ከላይ ተቀምጧል።
የገንዘብ ድጋፉ ከዚህ ቀደም በፀደቀው መመሪያ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

" የነዳጅ እጥረት ለስራችን እንቅፋት እየሆነ ነው " -የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጓጎለ መሆኑን አመልክተዋል። ለአብነት ከቡሌሆራ፣ ሀዋሳ፣ ወልቂጤ፣ አሶሳ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ ፣ አሳስ፣ አዶላወዮ፣ ሻኪሶ፣ አሳሳ ከሚገኙ አሽከርካሪዎች የመጡ መልዕክቶች ነዳጅ ለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ…
" የቤኒዚን አቅርቦት ችግርን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየተሰራ ነው " - የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን
በአዲስ አበባ የተፈጠረውን የቤንዚን አቅርቦት ችግር በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
የኢትየጵያ ነዳጅ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለችግሩ መከሰት የተለያዩ ምክንያቶችን አንስቷል ፦
1ኛ. የዩክሬን – ሩስያ ጦርነትን ተከትሎ የተፈጠረውን ዓለማቀፋዊ ችግር ፤
2ኛ. የጅቡቲ መንገድ መበላሸቱና ከጅቡቲ አዲስ አበባ ከ2 ቀን እስከ 2 ቀን ተኩል ይወስድ የነበረው መንገድ አሁን 4 ቀን ድረስ በመውሰዱ መዘግየት መፈጠሩ ነው።
የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ከሎጂስቲክስና ከዓለማቀፋዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አሳውቋል።
ከባለፈው አርብ ጀምሮ 6 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን ከጅቡቲ በመጓጓዝ ላይ ነው ያለው ባለስልጣኑ እስከመጭው #አርብ ድረድ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ይፈታል ብሏል።
በጊዜያዊነት ችግሩን ለመቅረፍ ከመንግስት ቋት ቤንዚን እየቀረበ ነው ሲልም አሳውቋል።
ችግሩ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች ከተሞችም እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ለሁሉም ከተሞች መፍትሄ ይሰጣል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሀዋሳ ፣ ቡሌሆራ ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ አሶሳ ... በሌሎችም በርካታ ከተሞች የነዳጅ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ተፅእኖ እሳያደረ መሆኑን በተለይም ነዳጅ ለማግኘት ከለሊት ጀምሮ ተሰልፎ መጠበቅ ግድ እንደሚል መጠቆሙ ይታወሳል።
ሁኔታ በርካቶችን ከስራ እዲስተጓጎሉና ቀናቸውን ነዳጅ ለመቅዳት በመሰለፍ እንዲያሳልፉ እያደረጋቸው መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

" ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን ያቁም " -የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት
የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚጣደፈው ምዕራቡ ዓለም ወደ ድሀ አገራት የሚልከውን እርዳታ ወደ አውሮፓ ማዞሩን እንዲያቆም የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ጠየቀ።
የኖርዌይ የስደተኞች ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ያን ኢግላንድ " ዩክሬንን እርዱ ነገር ግን በሌላው የዓለም ክፍል ያለውን ቀውስም አትዘንጉ " ሲሉ ጠይቀዋል።
ሃላፊው ምዕራባውያን በጎ ፈቃደኞችና ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የዩክሬን ስደተኞችን ለመርዳት የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ለዩክሬን የተጠየቀው 1.7 ቢሊዮን ዶላር በቀናት ውስጥ ሲደርስ ለየመንም እንዲሰጥ የጠየቅነው ገንዘብ እንዲህ በፍጥነት ቢደረሰ ምንኛ ደስ ባለን ነበር ብለዋል።
ኢግላንድ እንዳሉት ፤ ለየመን እርዳታ ከተጠየቀው 4.2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው ለዩክሬን ከተፈቀደው ያነሰ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር ብለዋል።
የዩክሬን ጦርነት ሳህል አካባቢ ለሚኖሩ ሀገራት መጥፎ ዜና መሆኑን የገለጹት ኢገላንድ ዛሬ በነዚህ አካባቢዎች የምግብ እና የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ማድረጉንም ተናግረዋል።
አንዳንድ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለድሀ ሀገራት ይለግሱ የነበረውን እርዳታ ወደአውሮፓ ማዞራቸው ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጓል ብለዋል።
ኢግላንድ በአውሮጳ በተለይም በዩክሬን የሚፈለገውን እርዳታ ከመስጠት ጎን ለጎን የሌሎች ሀገራትን የእርዳታ ጥያቄዎችንም በእኩል ሁኔታ ማስተናገድ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን AFPን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

#Oxfam " ኦክስፋም " ከአፍሪካ ቀንድ አስከፊ ድርቅ ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ኦክስፋም ፥ በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠው ሕዝብ መርጃ የሚዉል ገንዘብ ካልተገኘ ከፍተኛ ሰብአዊ ድቀት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል። 👉ኢትዮጵያን፣ 👉 ሶማሊያን 👉 ኬንያን በመታዉ ድርቅ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡን WFP ካስታወቀ 2 ወር ሊሞላ ነው። ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ…
ለማስታወስ ...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፦
👉 በኢትዮጵያ 🇪🇹
👉 በሶማሊያ 🇸🇴
👉 በኬንያ 🇰🇪 ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 13 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን ከገለፀ ሁለት ወር ሊሞላው ነው።
ተመድ ለረሃብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል የምግብ እህል መግዢያ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ዓለም አቀፉን ማህብረሰብ ተማፅኖ ነበር።
ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በ ' ዩክሬን ' ጦርነት ላይ ሙሉ ትኩረቱን ስላደረገ ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ መልስ አላገኘም።
ከቀናት በፊት በወጣው መረጃ ማግኘት የቻለው 3 በመቶ ብቻ ነው።
በተለይም ደግሞ በጎረቤታችን ሶማሊያ ለረሃብ ለተጋለጠው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ መርጃ ይሆን ዘንድ የተጠየቀው 1.46 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን እስካሁን የተገኘው 3 በመቶ ብቻ ነው።

#Update ዛሬ የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ኢትዮጵያን በሚመለከተዉ S.3199 በተባለዉ ረቂቅ ሕግ ላይ ይነጋገራል። በ2021 ላይ የተረቀቀዉ ሕግ የኢትዮጵያን ሠላም እና ዴሞክራሲን ለመደገፍ (ለማበረታት) ያለመ እንደሆነ አርቃቂዎቹ አስታዉቀዋል። ይህ S.3199 ረቂቅ ሕግ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ከቀረበዉና H.R.6600 በሚል መለያ ከሚታወቀዉ…
#Update
በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው S.3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል።
ኮሚቴው ፤ "በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ " በሚል ርዕስ የቀረበው S.3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው።
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው S.3199 ረቂቅ ህግ በጠቅላላ የምክር ቤቱ አባላት እንዲፀድቅ የሚመራ ሲሆን ህግ ሆኖ ለመውጣት የህግ አውጪው ምክር ቤት ድምፅ እና የፕሬዜዳንቱን ፊርማ ማግኘት አለበት።
S.3199 ረቂቅ ህግ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚህ ረቂቅ ጎን ለጎንም HR.6600 የተሰኘ " በኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን " በሚል ርዕስ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ በህግ አውጪው ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እንዲያየው መላኩን ቪኦኤ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ሊፀድቁ በመንገድ ላይ ናቸው የተባሉት S.3199 እና HR.6600 ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠል እና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር የሚያደርጋት በመሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ህጎቹ እንዳይፀድቁ ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#Sport ግብፅ እና ሴኔጋል ዳግም ተገናኝተዋል። ግብፅ እና ሴኔጋል ለኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በግብፅ መዲና ካይሮ እያደረጉ ይገኛሉ። በደርሶ መልስ (መጋቢት 15 እና 19) ከሚደረገው ጨዋታ በኃላ ግብፅ ወይም ሴኔጋል / ሞሀመድ ሳላህ ወይም ሳድዮ ማኔን በ2022 ዓለም ዋንጫው የምንመለከታቸው ይሆናል። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ እልህ አስጨራሽ…
ሴኔጋል ለ2022 ዓለም ዋንጫ አለፈች።
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድሏ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር።
ዛሬ በሀገሯ ላይ በተካሄደው የመልስ ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥራ በመደበኛው እና ተጨማሪው ሰላሳ ደቂቃ በድምር ውጤት 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው በመለያያ የፍፁም ቅጣት ምት በሴኔጋል 3-1 ውጤት ተጠናቋል።
ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ በዓለም ዋንጫው ላይ የሚታይ ሲሆን ግብፃዊው ኮከብ ሳላህ በዓለም ዋንጫው ድንቅ ብቃቱን የሚያሳይበት ዕድሉ መክኗል።
@tikvahethsport