TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት ያከናውኑትን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኦነግ አመራር አባላት (በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ቡድን) የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት የለውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ በጉባኤው የተመረጡት አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችል አሳውቋል።…
#OLF

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኦነግን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ።

ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የቀረቡለትን አቤቱታዎች በማየት ውሳኔ መስጠቱን አስታውሷል።

በውሳኔው ቅር የተሰኙት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር እነ አራርሶ ቢቂላ ጉዳዮን ወደፍርድ ቤት በመውሰዳቸው ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ የሰበር ሰሚ ችሎት የሁለቱንም ወገኖች የመሰማት መብት በመጠበቅ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ወደቦርዱ መመለሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ተከትሎ ውሳኔ አሳልፏል።

ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚገባው ቦርዱ የገለፀ ሲሆን ፓርቲው እስካሁን ካለበት የአመራር ችግር አንጻር፣ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት የጉባኤው አጠራር ደንብ እና የምርጫ ህጉን የተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ማስፈለጉን አስታውቋል።

በዚህም የጉባኤ አጠራር ዝርዝር ዕቅድ፣ የጉባኤውን አጠራር በተመለከተ በተገቢው የፓርቲው አካል የተሰጠ ውሳኔ እና የውሳኔው ቃለጉባኤዎች እስከ ሚያዚያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስኗል።

(የቦርዱ ውሳኔ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ለቴሌብር ተጠቃሚዎች በሙሉ!

የቴሌብር ተጠቃሚ የሆናችሁ፣ በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የባንካችን ኤ.ቲ. ኤም ማሽኖች ገንዘብ ወጪ ማድረግ እንደምትችሉ ስናሳውቅ በደስታ ነው፡፡

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://yangx.top/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC ትላንት በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተመረጡት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባላት በጉባኤው ፊት ቃለመሃላ ፈፅመዋል። በሌላ በኩል ፤ የፓርቲው የኦዲት እና ኢንስፔክሽን አባል የሆነው የተመረጡ አባላትም ቃለመሃላ ፈፅመዋል። ትላንትና በነበረው የመጀመሪያው ቀን የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና - ሊቀመበር ፣ አቶ በቀለ ገርባ - ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ፣ አቶ…
#OFC

የኦሮሞ ፊዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህ መግለጫ ላይ ፤ ባለፉት 3 ዓመታት በሀገራችን የተከሰቱ ለአያሌ ንፁሃን ህይወት መቀጠፍ፣ ለከፍተኛ ንብረት ውድመትና ፣ ለዜጎች ክብር ውርደት የዳረጉ የርስ በርስ ጦርነቶች ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ከጥቂት ወራት ወዲህ ለእርስ በእርስ ጦርነቶቹ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ መንግስት ያደረገውን የአካሄድ ለውጥ በበጎ እንመለከታለን ብለዋል።

በቅርቡ የፌዴራሉ እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ጦርነት ለማቆም ያሳለፉት ውሳኔ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲለወጥ ፣ ያልተገደበ እርዳታ ለህዝቡ እንዲደርስ ፣ ግጭትም መልሶ እንዳይቀሰቀስ የሚደረጉ ስራዎች እንዲሰሩ በአፋጣኝ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ በሰሜን የሀገራችን ክፍል ያለውን ጦርነት ለማስታቆም እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ቢደነቁም ባለፉት 3 ዓመታት ኦሮሚያን እያመሰ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት የሚገባውን ትኩረት ያለማግኘቱ እንዳሳዘናቸው ጉባኤተኞች ገልፀዋል።

ስለዚህም የፌዴራል መንግስት የሰላም እጁን ለትግራይ ኬ እንደዘረጋ ሁሉ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም ላይ ሳይዘገይ እንዲደርስ አሳስበዋል።

ጉባኤተኞቹ በመግለጫቸው ፤ ሰላማዊ ኦሮሚያ ሳትኖር አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ያላትን ኢትዮጵያ ማሰብ አይቻልም ብለዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC የኦሮሞ ፊዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። በዚህ መግለጫ ላይ ፤ ባለፉት 3 ዓመታት በሀገራችን የተከሰቱ ለአያሌ ንፁሃን ህይወት መቀጠፍ፣ ለከፍተኛ ንብረት ውድመትና ፣ ለዜጎች ክብር ውርደት የዳረጉ የርስ በርስ ጦርነቶች ማዘናቸውን ገልፀዋል። ከጥቂት ወራት ወዲህ ለእርስ በእርስ ጦርነቶቹ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ መንግስት…
' ብሄራዊ ምክክር '

የኦሮሞ ፊዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያላካከተና ገልልተኛ እና ተዓማኒነት በሌላቸው አካላት የሚመራ ብሄራዊ ምክክር የሀገሪቱን ችግር ይፈታል ብለን አናምን ብለዋል።

ጉባኤተኞቹ የተሳካ የሆነ ብሄራዊ ምክክር እንዲደረግ ያስችላሉ ያሏቸውን ምክረ ሃሳቦችን በዝርዝር አቅርበዋል ፦

👉 በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም በማድረግ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ፤

👉 ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በተለይም ባአሁን ጊዜ በተለያዩ እስር ቤቶች ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉ የኦፌኮ እና ኦነግ አመራር አባላት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤

👉 መንግስት የእርስ በእርስ ጦርነቱ ላይ እየተሳተፉ ካሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር #ድርድር በመጀመር እና ግጭቶች እንዲቆሙ በማድረግ ፣ ያሉትን የህግ ማነቆዎችንም ሙሉ በሙሉ በማንሳት ብሄራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ሊጋብዛቸው ይገባል፤

👉 የብሄራዊ ምክክሩ አዋጅ ሊዘጋጅ የሚገባው በጋራ ስምምነት ሆኖ ኮሚሽነሮችም ምክክሩ ላይ በሚሳተፉ አካላት ሊመረጡ ይገባል ብለዋል።

(የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ)

@tikvahethiopia
#Gambella

ትናንት ምሽት ላይ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ መደረሱ ተገልጸ።

የክልሉ ፖሊስ ፤ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በክልል ፖሊስ እና በፌደራል ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል ሲል አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ሠላም ወደነበረበት ተመልሷል፤ ግጭት ፈጥረዋልም የተባሉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢው ማጣራት እየተካሄደ ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ የግጭቱን መንስኤ እያጣራ እንደሆነም አሳውቋል።

ከተማዋ ሰላም መሆኗን እና ህብረተሰቡም ወደ ተለመደው የሰላም ሁኔታ መመለሱንም ገልጿል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ነዋሪዎች ረብሻና ሁከት ከሚፈጥሩ አንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ገፆችና ያልተረጋገጠ መረጃ ከሚሰጡ ዘገባዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
#Harari

ለቀጣይ ሶስት ወራት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ማስወጣት ተከለከለ።

በዛሬው ዕለት የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ ቤት ባካሄደው ውይይት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ከተከራዩት ቤት ማስወጣትን የሚከለክለው ደንብ መርምሮ ማፅደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ደንቡን ያፀደቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብላል።

አዋጁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይና የ " ንግድ ቦታ ኪራይን " እንደማያካትት ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#EthiopianFederalPolice

ከዚህ ቀደም ወደ ሌላ ሀገራት ተልኮ ይደረግ የነበረው የዘረመል (DNA) ምርመራ ከ1 ወር በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል ( DNA ) ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር የገለፀው ፌዴራል ፖሊስ፤ በአስር ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ከአፍሪካ ምርጥ 5 የፖሊስ ተቋማት አንዱ ሊሆን አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን አስታውቋል።

ከቴክኖሎጂ ባለፈ ፖሊስ ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችለው ዘንድ አዳዲስ አደረጃጀቶች አዋቅሯል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች እያደገ የመጣውን የአየር እና የየብስ ትራንስፖርት ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ትኩረት አድርገው መዋቀራቸውን ተገልጿል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች ፦

👉 የአቪየሽን ፖሊስ፣
👉 የምድር ባቡር ፖሊስ፣
👉 የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች መሆናቸውን ኤፍ ቢስ ዘግቧል።

 @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ወያኔም አልቻለም፤ ብልፅግናም አልቻለም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ከወራት በፊት ከእስር ከተፈቱ በኃላ በአደባባይ ንግግር ሲየደርጉ/ ሃሳባቸውን ሲገልፁ/ለሚዲያ ቃላቸውን ሲሰጡ አልተስተዋለም።

ባለፉት ቀናት በነበረው የፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ ግን ንግግር አድርገዋል።

አቶ ጃዋር በንግግራቸው ሊበታትኗቸው የፈለጉ ኃይሎች ሁሉ ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ " ' ይሄን ካላደረጋችሁ እናፈርሳችኋለን " ይሄን ወያኔም አልቻለም፣ ብልፅግናም አልቻለም። ሊበታትኑን በፍፁም አይችሉም። ኦሮሞን በፍጹም ማስፈራራት አይቻልም በፍጹም " ብለዋል።

"እኔ በራሴ ከኦፌኮ ከወጣክ ይሄን እናደርግልሃለን ፣ ይሄንን ካላደረክ እንደዚህ አናደርግም ብለውኛል " ያሉት አቶ ጃዋር " ሞተን እንገኛለን እንጂ ካመንበት ነገር ወደኋላ አንመለስም " ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለው፥ " ብልፅግና ከግማሽ በላይ ኦነግን ወስዶት እንኳን ኦነግን ማፍረስ አልቻለም። ኦነግ ፈርሷል? አልፈረሰም " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር፥ " ከቦረና፣ ከጉጂ የሚነሳውን ቅሬታ እንሰማለን፣ እንመካከራለን፣ እናስተካክላለን " ያሉ ሲሆን " እኔ ያልኩትን ካልወሰዳችሁ አርሲን ከዚህ አወጣለሁ፣ ሸዋን አወጣለሁ፣ ወለጋን ከዚህ አወጣለሁ ካልክ አንተ ነህ የምትወጣው እንጂ ጉጂም አርሲም አይወጡም " ሲሉ ተናግረዋል።

"እኔ OMN በነበርኩበት ሰዓት እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ነበሩ " ያሉት አቶ ጃዋር " አንደዚህ ካላደረክ ከሀረርጌ የሚመጣውን ገንዘብ አንቆርጥብሃለን ከወለጋ የሚመጣውን ገንዘብ እንቆርጥብሃለን...ከቆረጣችሁ ትቆርጣላችሁ እንጂ የኦሮሞ አንድነት አይቆረጥም። ከተበታተንን እንበታተናለን እንጂ ወደኋላ አንመለስም" ብለዋል።

@tikvahethafaanoromoo
TIKVAH-ETHIOPIA
#Djibouti #Ethiopia የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ…
#Ethiopia #Djibouti

ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትላንት ኢትዮጵያ የገቡት የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና ልዑካቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ልዑካቸው ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ፦

👉 የንግድ፣
👉 የግብርና ሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣
👉 የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣
👉 ቱሪዝም፣
👉 ኢነርጂ እና ሌሎች ዘርፎችን ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ባማከለ መልኩ ማጠናከር ይገኙበታል።

መረጃውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

4 የኢትዮጵያ ዜጎች ድንበር ዘልቀው በገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች ተገደሉ።

የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ዳሰነች ወረዳ ባደረሱት ጥቃት የ 4 ዜጎቻችን ህይወት አልፏል።

የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳር ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፤ በቀን 18/07/2014 ዓ/ም የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የ4 ዜጎችን ህይወት ሲያጠፉ ፣ በ3 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሳቸውና የንብረት ዘረፋም መፈፀማቸውን ገልጿል።

በዚህም ወረዳው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

በኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች ጥቃት ህይወታቸውን ያጡት 4 ወንዶች ናቸው፤ በሦስት ወንዶች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

ህይወታቸውን ካጡት ዜጎች መካከል ፦

👉 አቶ ኘወይ ገልቴ ፦ የዳሰነች ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ሆነው ለ8 ወራት እንዲሁም እስከ እለተሞታቸው ድረስ የዳሰነች ወረዳ ም/ቤት ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።

👉 አቶ ሞሮኪን ኩያ ፦ በዳሰነች ወረዳ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ተቀጥረው ሲያገለግሉ ነበር።

👉 አቶ ኩቴ ታራትያንግ ፦ አቶ ኩቴ ታራትያንግ እስከ እለተሞታቸው ድረስ በመንግሥት መዋቅር የኤድኛንጋሉክ ቀበሌ ዋና ሊቀ-መንበር ነበሩ፡፡

የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረማሪያም አይመላ ፤ በሁለቱ ሀገራት የድንበር አከባቢዎች በሚከሰት ግጭት የሚደርስን ሞትና የንብረት ውድመትን ለመከላክለና እና ለመቆጣጠር እንዲሁም ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቀረት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መረጃውን ከደቡብ ኦሞ ዞን ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#Japan

በአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።

ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረገው የጃፓን መንግስት ሲሆን ለ1 አመት ይቆያል ተብሏል። ለዚህ ፕሮጀክት ስኬትም የጃፓን መንግስት 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል።

የተባበሩት መንግስታት ደርጅት የስነህዝብና ፈንድ በኢትዮጵያ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ይከታተላል የቴክኒክ ድጋፍም ያደርጋል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ እና ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸውን ሴቶች የሚደግፍ እና በስነ- ተዋልዶ ጤና ላይ አተኩሮ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል በአራት ወረዳዎች (በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፣ በአዊ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች) የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ደግሞ በመተከል ዞን ስር ባሉ ሁለት ወረዳዎች (ዳባጤ እና ዳንጉር) ወረዳዎች የሚተገበር ይሆናል።

መረጀው የኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ መጋቢት 18 /2014 በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል። ይህ የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባኤው በተለያዩ የፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮችና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የማስጀመሪያ ስነስርዓት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣አባላት፣ የሌሎች የፖለቲካ…
#Freedom_and_Equality

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት አካሂዷል።

ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡

ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል የስያሜ ለውጥ አድርጎ አባላቱንም በ10 አሳድጓል፡፡

በዚህም መሰረት 28 አዳዲስ ቋሚ የብሄራዊ ም/ቤት አባላት በክልሎች እጩ አቅራቢነት ቀርበው በሚስጥር ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጉባኤው 45 ቋሚና 15 ተለዋጭ አባላት ያሉት ብሄራዊ ምክር ቤት አጽድቋል፡፡

በጉባኤው ከ900 በላይ አባላት ከመላው ኢትዮጵያ የተሳተፉ መሆናቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Update

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ደግም ያገረሸው ግጭት በመኃል ለቀናት ጋብ እያለ የመጣ ቢሆንም ከመጋቢት 15 ወዲህ ግን ለተከታታይ 4 ቀናት ያለመቋረጥ በቀጠለ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን፤ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸዋል።

በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር በኩል " ዲማያ " የሚባል አካባቢ ወደ 6 ሰው እንደሞተና በርካታ መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጠሉ እንዲሁም በኧለ ልዩ ወረዳ በኩል " ዳታኔ " በሚባል አካባቢ ቤቶች እንደተቃጠሉ ና ወደ 10 ሰው እንደሞተ ነው መረጃ የሰጡን ቤተሰቦቻችን የገለጹት።

በአጠቃላይ በሁለቱም በኩል ከ50 በላይ የሚሆኑ ቤቶች መቃጠላቸው ተጠቅሷል።

ይህን ክስተት አስመልክቶ ለቲክቫህ ቤተሰቦች መረጃ የሰጡት የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰራዊት ቲቶ ፥ " በሁለቱ ማኅበረሰብ መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ከፍተኛና ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፤ እንደዚሁም የቤት ንብረት ቃጠሎዎች አሉ።'' ሲሉ አረጋግጠዋል።

ምን ያህል ? ለሚለው ጥያቄ ግን ፥ " የጸጥታ ችግር ሲባል ቀላል ነገር አንደለም ራስህ በአካል ሄደህ ካላጣራህና ካልመዘገብክ በቁጥር የደረሰውን ጉዳት እንዲህ ነው ማለት ይከብዳል። አንዳንድ ቀጠናዎችም በጸጥታ ምክንያት ገብቶ ማረጋገጥ አልተቻለም " ሲሉ ነው የመለሱት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ደግም ያገረሸው ግጭት በመኃል ለቀናት ጋብ እያለ የመጣ ቢሆንም ከመጋቢት 15 ወዲህ ግን ለተከታታይ 4 ቀናት ያለመቋረጥ በቀጠለ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን፤ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸዋል። በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር በኩል " ዲማያ " የሚባል አካባቢ…
#Update

ዳግም ባገረሸው የኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ልዩ ወረዳ ግጭት የሁለቱ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታው መዋቅር፣ ፖሊስና የክልሉ ልዩ ኃይል አመራሮች በተገኙበት የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት የሁለትዮሽ ዉይይት ዛሬ አካሂደዋል።

ዛሬ በነበረው ውይይት ላይ ሰው ሰራሽ ችግሮች ሲከሰቱ እንደመንግስት እና አጎራባች ህዝቦች ትክክለኛ መረጃ አለመናበብ ፣ በሀሰት የመፈራረጅ አዝማሚያዎች እና ህዝብን ለግጭት የሚዳርጉ ትንኮሳ እና ኡሉባልታዎች መኖራቸው ተገምግሟል።

በውይይቱ በኮንሶ ዞን ኮልሜ ክላስተር እና ኧሌ ህዝቦች መካከል ለሠላም ግንባታና ቀጠናውን ለመረጋጋት የሁለትዮሽ የውሳኔ ሀሳብን መተላለፉ ታውቋል።

በዚህም ፦

👉 ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ድምፅ እንዳይሰማ ፤

👉 በኮልሜና ኧሌ ህዝቦች መካከል ሠላምና ደህንነት የሚከታተሉ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ቡድን አቋቁሞ ስለ ሠላም እንዲሰሩ ወደ ተግባር ማስገባት፣

👉 የፖለቲካ አመራሩ በሁለቱም መዋቅሮች ህዝባዊ ዉይይቶችን እንዲያደርጉ፣

👉 በክልሉ በኩል የተጀመሩ ስለ ሠላም እና አንድነት ሥራዎችን ማስቀጠልና የህዝቡን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሁሉም እንዲረባረብ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተደርሷል።

የኮንሶ ዞን ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሰራዊት ቲቶ ለቲክቫህ ፤ " ቡድኑ ከልዩ ኃይሉ ጋር የሚተባበርና በትኩረት ሊሰራ የሚችል ከአሌ ልዩ ወረዳ የተወጣጣ ከኮንሶ ዞንም የተወጣጣ የፖሊስ ሰራዊትና የሚሊሻ ሰራዊት በሁሉም ቀጠናዎች በመናበብ ከልዩ ኃይሉም ጋር በመናበብ ውስጥ ለውስጥ የሚከሰቱ ጥቃቅን ችግሮች ጨምሮ በይበልጥ እንዲከታተል ለማድረግ የታሰበ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia