TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ማኅበረ_ኀዳፌ_ነፍስ

ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ ለኦርቶዶክሳዊያን የበገና፣ የክራር እና የመሰንቆ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል።

📍ቦታው ፒያሳ Downtown ህንጻ ላይ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0956861468 / 0912085085 / 0933673370 ላይ መደወል ይቻላል።

ወይንም በቴሌግራም በውስጥ መስመር ለማውራት በማኅበሩ የቴሌግራም አካውንት @Hadafe_nefese 👈 በመጫን የፈለጉትን ጥያቄ ሊጠይቁን ይችላሉ።

የቤት ለቤት ትምህርት መከታተል ለምትፈልጉ ደግሞ ለ6 ወራት ትምህርቱ ይሰጣል።

ከላይ በፎቶው የተያያዘው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአራዳ ጊዮርጊስ የነበረ የምርቃት መርኀ-ግብራችንን ነው።
#ETHIOPIA

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ በሃይማኖት አባቶች ፀሎትና ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በተውጣጡ የአገር ሽማገሌዎችና እናቶች ምርቃት የተከናወነበት የሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አከናውኗል።

የምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ በወቅቱ ባሰሙት ንግግር፤ በኢትዮጵያ እርስ በርስ የማያግባቡ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት፣ በመነጋገርና በመደማመጥ " የሕዝብ ለቅሶና ዋይታ መርገብ ብቻ ሳይሆን መቆም አለበት " ብለዋል።

ፕ/ር መስፍን ኢትዮጵያ ብዙ ፈተናዎችን እያለፈች መሆኗን የገለፁ ሲሆን፦
👉 ግጭት፣
👉 ጦርነት፣
👉 መፈናቀል፣
👉 ስደት፣
👉 ሥራ አጥነት፣
👉 የምግብ ረሃብ፣
👉 የመልካም አስተዳድር ረሃብ፣
👉 ቸነፈር፣
👉 ድርቅ፣
👉 የእንስሳት ዕልቂት፣
👉 የኤችአይቪና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣
👉 የኑሮ ውድነትና ሌሎችም ችግሮች ውስጥ እያለፈች መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽ፣ ምክንያታዊ፣ ተዓማኒ እና 120 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትክክለኛና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በውይይቱ እንዲወከል በማድረግ፣ ግልጽ የሆነ የአመቻችነት ሥራ እንደሚያከናወኑ አስረድተዋል፡፡

ሊካሄድ የታሰበው አገራዊ ምክክር በመደማመጥ በሚገባ ከተከናወነ ወደ መግባባትና መፍትሔ አዋጭ መንገድ መግባት እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጦርነት በፊት በሃይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎችና በእናቶች አማካይነት ተጀምሮ የነበረው የሰላም ጥረት ተደምጦ ቢሆን ኖሮ አሁን የሚታየው ምስቅልቅል ባልተፈጠረ ነበር ብለዋል፡፡

አሁንም ለመስማት ብቻ ሳይሆን ለመደማመጥ አዳጋች የሆኑ፣ ሕዝቡን እየለያዩና እያቆረቆሱ ያሉ አጀንዳዎችን ነቅሶ በማውጣት ለብሔራዊ ምክክር ራስን ዝግጁ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ በሃይማኖት አባቶች ፀሎትና ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በተውጣጡ የአገር ሽማገሌዎችና እናቶች ምርቃት የተከናወነበት የሥራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አከናውኗል። የምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ በወቅቱ ባሰሙት ንግግር፤ በኢትዮጵያ እርስ በርስ የማያግባቡ ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት፣ በመነጋገርና በመደማመጥ " የሕዝብ ለቅሶና ዋይታ መርገብ…
#ETHIOPIA

ፕ/ር መስፍን አርዓያ (የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር) ፦

" ... የምክክር ኮሚሽኑ አመቻች እንጂ አደራዳሪም ሆነ እርቅ አስፈጻሚ አይደለም።

ኮሚሽኑ የድርድር ሥራ እንደማይሰራ፤ ዕርቅ እንደማያስፈጽም ሕዝብ ሊያውቅ ይገባል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችና አባላትን ለምክክሩ የሚረዱ መድረኮችና አጀንዳዎችን በማመቻቸት አስፈላጊው ሥራ ለማከናወን የተመረጥን መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል።

የኮሚሽኑ ሥራ አጀንዳ ነቅሶ ሕዝብን ለውይይት መጋበዝ ነው። ለሕዝብ ከሚቀርቡት አጀንዳዎች ውስጥ መግባባት ላይ የሚያደርሰውን መንገድ እናመቻቻለን።

በዚህ አካሄድ ኮሚሽኑ አመቻች ሲሆን ዋናው ወሳኙ ሕዝብ ነው።

ምክክሩ ወደ ' ብሔራዊ እርቅ ' የሚወስድ ከሆነም በእራሱ አሰራርና አካሄድ መሰረት ወደ እርቅ ይሄዳል እንጂ ኮሚሽኑ ሽምግልና እና አሊያም ብሔራዊ እርቅ ማስፈጸም ውስጥ አይገባም።

አንዳንድ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን አሸማጋይ አሊያም አደራዳሪ አድርጎ የሚያይ ካለም የተሳሳተ ነው። የኮሚሽኑ ኃላፊነት አካታች በሆነ መንገድ ሁሉንም ጉዳይ አለኝ የሚል ወገንን በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ እንዲመክር ማድረግ ነው። "

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 18 እንደሚያካሂድ አሳውቋል። የጉባኤው ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿል። 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነእፓ አሳውቋል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ከሰጣቸው…
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ መጋቢት 18 /2014 በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል።

ይህ የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው በተለያዩ የፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮችና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የማስጀመሪያ ስነስርዓት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣አባላት፣ የሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየታደሙ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቻይና ከትላንናው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ እስካሁን አንድም የተረፈ ሰው አልተገኘም ብላለች። ትናንት 132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረ " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል። ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ማግኘት አለመቻሉን…
" የተረፈ ሰው የለም "

ባለፈው ሰኞ 132 ተጓዦችን እና የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የቻይናው አውሮፕላን መከስከሱን ተከትሎ ሁሉም በውስጡ የነበሩት ሰዎች መሞታቸውን ቻይና አረጋግጣለች።

132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረው " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል።

ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም ምንም የተረፈ ሰው እንደሌለ ትላንት ተረጋግጧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ መረጠ። አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ተመርጠዋል። ፕ/ር መረራን ለሊቀመንበርነት የጠቆሟቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ሲሆኑ የጉባኤው አባላቶች ለሊቀመንበርነት እና ለተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርነት አቶ ጃዋር መሀመድን ቢጠቁሙም ጥቆማውን Decline ማድረጉ ተገልጿል። በሌላ በኩል ፤…
#OFC

ትላንት በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተመረጡት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባላት በጉባኤው ፊት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።

በሌላ በኩል ፤ የፓርቲው የኦዲት እና ኢንስፔክሽን አባል የሆነው የተመረጡ አባላትም ቃለመሃላ ፈፅመዋል።

ትላንትና በነበረው የመጀመሪያው ቀን የኦፌኮ ጠቅላላ ጉባኤ ፕ/ር መረራ ጉዲና - ሊቀመበር ፣ አቶ በቀለ ገርባ - ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ - ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው እና የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባላት መመረጣቸው ይታወሳል።

አቶ ጃዋር ምንም እንኳን ለሊቀመንበርነት እና ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርትነ በጉባኤተኛው ተጠቁመው ውድቅ ቢያደርጉም ጉባኤው የፓርቲው ም/ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።

የኦፌኮ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ለረጅም ዓመታት በውጭ ሀገር ሆነው የ " ኢህአዴግ " መራሹን መንግስት ተገዶ ወደ ለውጥ እንዲገባ በማስገደድ በሚዲያው እና በአክቲቪዝሙ መስክ ጉልህ ድርሻ የተጫወቱ ሲሆኑ በኃላም ወደ ሀገራቸው በመግባት ምርጫቸውን ኦፌኮ በማድረግ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካውን ዓለም ሊቀላቀሉ ችለዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ለአንድ አመት ከመንፈቅም ታስረው ከወራት በፊት ታህሳስ 29/2014 ዓ/ም መፈታታቸው አይዘነጋም።

Photo Credit : Ubuntu TV

@tikvahethiopia
#Djibouti #Ethiopia

የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ " ያሉ ሲሆን " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🌧 ቦረና 🌧 ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ አስከፊ ድርቅ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎች ዝናብ ጥሏል። ይህም ነዋሪዎች ላይ ደስታን ፈጥሯል። ከሰሞኑን በእነዚህ አከባቢዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ የሚያሳይ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ይገኛሉ። ቃላቸውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል የሰጡት የቦረና ዞን ኤልዋዬ ወረዳ ነዋሪው አባ ሾባ ሞሉ ዝናብ…
#BORANA

ከሰሞኑን በከፍተኛ ድርቅ ውስጥ የነበሩ የቦረና አካባቢዎች ዝናብ አግኝተዋል።

ነዋሪዎች ክብር ለፈጣሪ ይሁንና ፈጣሪያቸውን በማመስገን ከብቶቻቸው የዝናብ ዉሃ ሲጠጡ ሚያሳዩ ፎቶ እና ቪዲዮ በማሕበራዊ ሚዲያዎች እያጋሩ ይገኛሉ።

ከሰሞኑ ዝናብ ጋር በተያያዘ አቶ ሙስጠፋ ከዲር በኦሮሚያ የቡሳ ጎኖፋ ጽ/ቤት ሀላፊ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የተናገሩት ፦

" በሁሉም ወረዳዎች ላይ ዝናብ ዘንቧል። በቂ ባይሆንም በቦረና ወረዳ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምዕራብ ባሌ ዘንቧል።

ጅማሬው ጥሩ ይመስላል። የአየር ትንበያ ዝናብ እንደሚዘንብ ያሳያል። አሁን ያለው ዝናብ የነበረውን ችግር ይፈታል ባንልም፣ ዉሃ ያገኛሉ።

ነገር ግን የሰው እርዳታ ብያንስ ለሚቀጥሉት ሶሰት፣ አራት ወራት ሊቀጥል ይገባል።

ዝናብ ስለጣለ ብቻ እህል አይበቅልም ፣ ሰብል አይዘራም። ስለዚህ የማሕበረሰቡ እርዳታ መቋረጥ የለበትም።

በወንዝ አከባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ፤ ከብቶቹን ለጊዜው በማቆያ ውስጥ እንዲያገግሙ ማድረግ አለባቸው። "

@tikvahethiopia
🌧 ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ - ዝናብ ጥሏል 🌧

በታሪኳ እጅግ አስከፊ በሆነ ድርቅ ላይ የምትገኘው እና 4.5 ሚሊዮን ህዝቧ ለረሃብ የተጋለጠው ጎረቤታችን ሶማሊያ ዝናብ አግኝታለች።

በሀገሪቱ ብዙ ክፍሎች ላይ ዝናብ መጣሉን የሚገልፁ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።

አሁንም ከፍተኛ ደመና በተለያዩ ቦታዎች የሚታይ ሲሆን ብዙ ቦታዎች ተጨማሪ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል።

ዝናቡ ሲጠፋ የድርቅ አደጋ ፤ ዝናቡ ሲገኝ ደግሞ የጎርፍ አደጋው ያሳስባልና ነዋሪዎች በጎርፍ ከሚመጣው አደጋ እንዲጠነቀቁም መልዕክት እየተላለፈ ነው።

የሀገሬው ሰው በማህበራዊ ሚዲያው #አልሃምዱሊላህ እያለ ለፈጣሪው ምስጋናን እያቀረበ ነው።

ቪድዮ - ሃሩን ማሩፍ

@tikvahethiopia
🌧 ኢትዮጵያ - ሶማሌ ክልል 🌧

" በሶማሌ ክልል አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ ጀምሯል " - የሶማሌ ክልል መንግሥት

የሶማሌ ክልል መንግስት ዛሬ አመሻሽ ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የድርቁ ጉዳይ አንዱ ነው።

ክልሉ በመግለጫው ላይ ፤ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ በሰራው ስራ ድርቁን መቋቋም መቻሉን ገልጿል።

ከክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጎን በመሆን ድጋፍ እና ትብብር ያደረጉ አካላት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን በማንሳትም ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።

አሁን የድርቅ አደጋ ጊዜ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ያሳወቀው የሶማሌ ክልል መንግስት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መጣል በመጀመሩ፣ ድርቁን ለመቋቋም እንደተሰራው አሁንም በድህረ ድርቁ እና በዚህ መሸጋገሪያ ወቅት ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን አሳውቋል።

በክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መዝነብ በመጀመሩ በአጠቃላይ ከሚጥለው ዝናብ በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በዝናቡ ምክንያት በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች፣ ወረርሽኝና ተዛማጅ ጉዳዮች ለመከላከል ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተሰሩ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia