TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#UN #RUSSIA

ዛሬ በተካሄደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ስብሰባ ላይ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ መናገር ሲጀምሩ በምክር ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከነበሩ ተሳታፊዎች ብዙዎቹ ተነስተው ወጥተዋል።

ሰርጌይ ላቭሮቭ በምክር ቤቱ ፊት በአካል ከመገኘት ይልቅ በቪድዮ ኮንፈረንስ እንዲያደርጉ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በንዴት መንፈስ ሆነው ወደ ጄኔቫ ለመጓዝ በሰማዮቻቸው ላይ እንዳይበርሩ ሃገሮቹ መከልከላቸውን፣ በዚህ የአውሮፓ ኅብረት የመንቀሳቀስ ነፃነታቸውን መጋፋቱን ገልፀዋል።

ላቭሮቭ ለ8 ደቂቃ በቆየ ንግግራቸው " በዋሺንግተን ይመራል " ያሉትን " የምዕራቡን የጋራ ፖሊሲ " ሲያወግዙ ይህም " የኪየቭን አገዛዝ ላለፉት 14 ዓመታት በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዲያካሂድ አድርጎታል " ብለዋል።

የዩክሬኑን አስተዳደርን በወንጀል አድራጎቶች የኮነኑት ሰርጌይ ላቭሮቭ " በሩሲያና ተገንጣዮቹ ዳኔትስክ እና ሉሃንስክ ውስጥ ባሉ ሩሲያኛ ተናጋሪ ዜጎቹ ላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጦርነት አውጆ ቆይቷል " ሲሉ ከስሰዋል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን " ዕጣ ፈንታቸውን በግድ የለሽነት እያዩ መቀጠል ባለመቻላቸው ለአካባቢዎቹ ነፃነት ዕውቅና ሰጥተው " ነዋሪዎቻቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተዋል " ብለዋል።

ይህንን ቀደም ሲል በፑቲን በራሳቸው የተነገረ ምክንያት " ማሳሳቻ ሃሰተኛ መረጃ የማሠራጨት ዘመቻ" ሲሉ ያጣጣሉት ምዕራባዊያን መንግሥታት ሩስያ አካሂዳዋለች ላሉት ወረራ ታይቶ በማይታወቅ ስፋት ምላሽ ሰጥተዋል።

ላቭሮቭ በእነሱም ላይ ውግዘት ማሰማታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ቪድዮ - ተሳታፊዎች ተነስተው ሲወጡ (Elisabeth Tichy-Fisslberg)

@tikvahethiopia
#ዓድዋ2014 #ዓድዋ126

የ126ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው።

በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ ሚኒሊክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ እና በተለያዩ ትዕይንቶች ታጅቦ በድምቀት ተከብሯል።

በተጨማሪም በአሁን ሰዓት በዓድዋ ድልድይ እየተከበረ ይገኛል።

ከበዓሉ ጋር የተያያዙ በርከታ መረጀዎች ከፎቶዎች ጋር በ @tikvahethmagazine ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ዓድዋ126

126ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ ሩስያ እና አሜሪካ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤፍጌኒ ተረክህን የዓደዋ ድል የኢትዮጵያ ህዝብ በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ፊት ለነጻነቱ እንዲበቃ የነጻነት እና የድፍረት ምልክት ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል። ለገለልተኛ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖሊሲዋ ጠንካራ ማበረታቻ ሆኖ አገልግሏል ብለዋል።

አምባሳደሩ '' የዓድዋ ጦርነት ያለምንም ማጋነን በባርነት የነበሩ አፍሪካዊያን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ነፃ ለመውጣት ላደረጉት ትግል መሪ ኮከብ ነበር።'' ሲሉ ነው የገለጹት።

" ይህ ክስተት በሩሲያና በኢትዮጵያ ግንኙነት መመስረት ሂደት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ የሚያስደስት ነው " ያሉት አምባሳደሩ በጦርነቱ የቆሰሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ጦር ጀግኖችን ለማዳን የሩሲያ ሐኪሞች መርዳታቸውንም አስታውሰዋል።

ከዓድዋ ጦርነት በኋላ ብዙም ሳይቆይ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ለተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የአድዋ ድል የማዕዘን ድንጋይ መሆኑ አያጠያይቅም ነው ያሉት።

በሌለ በኩል አሜሪካ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

@tikvahethiopia
#ስንዴ

#ዩክሬን እና በ #ሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ ብዙ ማይሎች ርቆ ነው። ነገር ግን ጦርነቱ በርካታ ሰዎችን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል ተብሎ ተፈርቷል።

🌾 ሩሲያ እና ዩክሬን በድምሩ 29 በመቶውን የአለም ስንዴ ወደ ውጭ ይልካሉ። ሀገራቱ አሁን ከገቡበት ጦርነት ጋር ተያይዞ በ13 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስንዴ ዋጋ ንሯል።

ይህ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ በርካታ ሀገራት አስከፊ የሆነ ችግር የሚገጥማቸው ሲሆን በተለይም 3 ሀገራት ለከፍተኛ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ ፤ እነዚህ 3 ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇾🇪 የመን

🌾 በጦርነት የደቀቀችው ሀገር የመን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የምግብ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት ፤ ሀገሪቱ ቢያንስ 27 በመቶውን ስንዴ ከዩክሬን እና 8 በመቶውን ከሩሲያ በመግዛት ላይ ነው የምትገኘው።

🥖 በየመን ለ7 አመታት የዘለቀው ግጭት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝቦቿን ለረሃብ ዳርጓል፤ አሁን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ችግሩን በአስከፊ ሁኔታ እያባባሰ ነው።

🇪🇬 ግብፅ

🌾 90 % የሚሆነው የግብፅ ስንዴ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ነው የሚገባው። ግጭቱ አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያደረሰ ነው።

🌻 ሩሲያ እና ዩክሬን በግብፅ የሱፍ አበባ ዘይት ዋነኛዎቹ አቅራቢዎች ናቸው።

👨‍🍳 የዳቦ ጋጋሪዎች ከወዲሁ የዱቄት እና የምግብ ዘይት ዋጋ በጣም ውድ ሆነብን እያሉ ነው።

📈 አንድ ዳቦ ጋጋሪ በዱቄት ዋጋ ከ50% በላይ ጭማሪ እና የምግብ ዘይት ዋጋ ላይ አነስተኛ ጭማሪ በመታየቱ ንግዱ ተጎድቷል ብሏል።

🇱🇧 ሊባኖስ

🌾 ሊባኖስ ከዩክሬን 60 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ ምርት ታስገባለች።

ሊባኖስ የዩክሬን የሩስያ ጦርነትን ተከትሎ አማራጭ የስንዴ አቅርቦትን እንደምትመለከት ገልፃለች።

🇷🇺 የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ሩሲያ ላይ እንደጉድ እየወረደ ባለው #ማዕቀብ የተነሳ ሩሲያውያን ላይ የከፋ ተፅእኖ ይዞ እየመጣ ነው። ዩክሬንም የጦር ሜዳ በመሆኗ ዜጎቿ ሀገር ጥለው እየተሰደዱ ነው።

ነገር ግን ቀውሱ ከሩሲያ እና ዩክሬን ባለፈ #የስንዴ_ዋጋን እንዲጨምር በማድረግ በመካከለኛው ምስራቅም ምግብ በጣም ውድ እንዲሆን እያደረገው ይገኛል።

@tikvahethiopia
#US #CHINA

ቻይና በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች።

በአሜሪካ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ ለቻይናውያን ዜጎች አሳሳቢ ነው ብሏል።

በመሆኑም አሜሪካ የሚገኙ ቻይናውያን ዜጎች ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኤምባሲው አሳስቧል።

በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚንፀባረወቅ ጥላቻ እየጨመረ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

በቻይና ዜጎች እና የእሲያ ፊት ያላቸው ሰዎች ላይ ሆን ተብሎ የሚፈፀሙ " ተንኮል አዘል " ጥቃቶች የቻይና ዜጎች ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑንም ኤምባሲው አስታውቋል።

የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ መካከልም በቻይና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን እንደሚገኙበትም ጠቅሷል።

በቻይናውያን ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ መሰል ጥቃቶች በአሜሪካ እየተበራከቱ መሆኑን ያስታወቀው ኤምባሲው፤ በአሜሪካ የሚገኙ የቻይና ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ለግል ደህንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያድርጉ አሳስቧል።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ነው ያስነብበው።

@tikvahethiopia
#ከመልሚ

በከተሞች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለሚጠቀሙበት መንገድ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉበት ስርዓት እየተዘረጋ ነው።

ይህ ስርዓት ከተሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ ሊሠሯቸው ይገባል ተብለው በዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻው የጥናት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ተናግረዋል።

የከተማ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚደረገው ጥናት የአዳማ፣ የድሬዳዋ እና የባህር ዳር ከተሞችን ናሙና በመውሰድ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በጥናቱ በአጠቃላይ በከተሞች ውስጥ ያለው የተሽከርካሪዎች ምልልስና በመንገዶች ላይ የሚያሳድሩት ጫና የሚዳሰስ ሲሆን መንገዶቹ ጥገና ሆነ መልሶ መገንባት ሲያስፈልጋቸው ከተጠቃሚዎች በሚያገኙት ገቢ የሚሠሩበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው ብለዋል።

በ3ቱ ከተሞች በሚወሰደው ናሙና መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች፣ የከተማ መንገድ ተጠቃሚዎች ክፍያ ይጠይቃሉ ብለዋል።

ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ፤ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ተመሳሳይ ክፍያ ባይከፍሉም በጥናቱ ግኝት መሠረት በመንገዶች ላይ እንደሚኖራቸው ተፅዕኖ ክፍያ ይጠየቃሉ ያሉ ሲሆን " ክፍያው ሁሉንም ባለ ሞተር ተሽከርካሪዎች ብቻ ያካትታል። ሞተር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ አልተካተቱም " ብለዋል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል መክፈል አለባቸው የሚለው ሆነ መቼና የት ይከፍላሉ የሚለው እንደሚለይና ሥርዓቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለፃቸውን #ሪፖርተር_ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዳጅ📈 ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በ10 % ወደ ' 107 ዶላር ' ከፍ ብሏል፤ ይህም እኤአ ከ2014 በኃላ ከፍተኛው እንደሆነ ነው የተነገረው። ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የምትገኘው ሩሲያ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የነዳጅ ዘይት አምራችና ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ ሀገር ነች። አጠቃላይ ሩሲያ በዓለም የነዳጅ ምርት 10 % ድርሻ አላት።  የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት፤ ጦርነቱን…
ነዳጅ📈

ዛሬ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል #ከ110_ዶላር በላይ መድረሱን AFP ዘግቧል።

በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት የ1 በርሚል ነዳጅ ዋጋ በ5.06 በመቶ ጨምሮ 108.64 ዶላር ደርሷል።

ሁለቱም ላይ እንደእኤአ ከ2014 በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው ጭማሪ መሆኑ ተነግሯል።

የቀጠለው የ #ሩስያ እና #ዩክሬን ጦርነት መላው ዓለም ላይ ተፅእኖው በየዕለቱ እያየለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ አካባቢ በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባውን የዳታ ማዕከል አስጎብኝቷል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም በስፍራ ተገኝተው ማዕከሉን ተመልክተዋል። የዳታ ማዕከሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን መረጃዎች የሚይዝበት ሲሆን የኢትዮጵያ ደንበኞቹ መረጃቸው በዚሁ በኢትዮጵያ ውስጥ ይቀመጣል። ሳፋሪኮም ፤ የሙከራ የድምጽ…
ፎቶ ፦ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 2ኛው የዳታ ማዕከል አዲስ አበባ ገብቷል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቦሌ አከባቢ ሁለተኛውን የዳታ ማዕከል በማቋቋም ላይ እንደሚገኝ መግለፁ ይታወሳል።

ድርጅቱ ከፊታችን ሚያዝያ 1 /2014 ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

Photo Credit : Pedro Rabacal

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WW3 " ምዕራባውያን ሩስያን ወደ 3ኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ ነው " - የቤላሩስ ፕሬዜዳንት የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የምዕራባውያን ማዕቀቦችን " ሩሲያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ " ነው ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋል። የ #NATO ሀገራት ሩስያን ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እየገፉ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንት ሉካሼንኮ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ…
#WWIII

" 3ኛው የዓለም ጦርነት በኑክሌር የታገዘ እና አውዳሚ ይሆናል " - ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ እንደተናገሩት ሶስተኛው የዓለም ጦርነት የሚካሄድ ከሆነ የኑክሌር ጦር መሳሪያን ያካተተ እና አውዳሚ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ላቭሮቭ ሀገራቸው ሩሲያ ፥ ኪየቭ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ከያዘች " እውነተኛ አደጋ " ይጠብቃታል ያሉ ሲሆን ፤ ሀገራቸው ዩክሬንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድታገኝ እንደማትፈቅድ ተናግረዋል።

ከአንድ ቀን በፊት ሚኒስትሩ ዩክሬን የኑክሌር መሳሪያ ለመታጠቅ እየሞከረች መሆኑን ተናግረው ይህ ትልቅ ስጋት በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባው አጥብቀው አስጠንቅቀው ነበር። በተጨማሪ ምዕራባውያን ሀገራት በቀድሞ ሶቪየት ኅብረት አገሮች ውስጥ የጦር ሰፈር እንዳይገነቡ አስጠንቅቀው ፤ ሩሲያ ዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለማግኘት የምታደርገውን ሙከራ እንደምታስቆም ተናግረው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሰርጌ ላቭሮቭ ከዩክሬን ጋር የሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንደሚቀጥልና ሀገራቸውም ለዚህ ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል፤ ነገር ግን ዩክሬን የአሜሪካንን ትዕዛዝ እየተቀበለች መሆኑን ተናግረዋል።

ሩስያ በዩክሬን ላይ እያካሄደች የምትገኘውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ግቡን ሳይመታ ወደኃላ እንደማትመለስ እየገለፀች ትገኛለች።

@tikvahethiopia