#PP
የገዢው ብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአሁን ሰዓት ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
ስብሰባው በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#US
አሜሪካ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተዋጊዎች በአማራ ክልል በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ 2021 የጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች በጣም እንዳሳሰባት ገልጻለች።
ሀገሪቱ ይህን ያለችው በቅርቡ የወጣውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን ተከትሎት ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።
ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱትን የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች።
ለችግሩ ዘላቂ እልባት መስጠት እንዲቻል ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚለው ጽኑ አቋሟ መሆኑንም ሀገሪቱ ገልፃለች።
አሜሪካ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹት ሪፖርቶች ቀጣይነት ያለውን ወታደራዊ ግጭት በእስቸኳይ ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ብላለች።
ግጭቶች እና የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲዳረስ እና ሰላማዊ የመፍትሔ መንግዶችን ለማፈላለግ ከግጭቱ ተዋናዮች ጋር ተቀራርባ መስራቷን እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

#ችሎት በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ዋና ዳሬክተር በነ አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው የነበሩ 22 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ30 ሺ ብር ዋስ አሲዘው ከእስር ተፈተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ። ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ዋስትና ከተፈቀደላቸው መካከል የብሔራዊ መረጃ…
#Update
የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ 22 ሰራተኞች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን የዋስትና መብታቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻረ።
ውሳኔውን የሻረው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው።
የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት ቢሮ ምክትልዳሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን እና የተቋሙ የፀረሽብር ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 22 ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠይቀው የነበረ ሲሆን ከሳሽ ዓቃቤ ህግም ዋስትናው ሊፈቀድ እንደማይገባ እና ተደራራቢ ክስ እንዳለባቸው በማመላከት ተከሳሾቹ ቢወጡ ላይመለሱ እንደሚችሉ እና ከህወሓት የሽብር ቡድን ጋር ሊቀላቀሉ ይችላሉ ሲል በመቃወም ዘጠኝ ነጥቦችን ጠቅሶ መቃወሚያ አስገብቶ ነበር።
መዝገቡን የመረመረው ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በዛሬው ቀጠሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር በሁለት አብላጫ ድምጽ በአንድ ዳኛ ልዪነት ተከሳሾቹ ከነበራቸው ስልጣን አንጻር በወንጀለኛ መቅጭያ ስነስርአት ህግ አንቀጽ 67/ሀ መሰረት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታን ፣ በዋስ ቢወጡ ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ የሚለውን ግምት በመያዝ እና ተደራራቢ ክስ የቀረበባቸው እና ቅጣቱን በመስጋት ቢወጡ ተመልሰው ላይመጡ ይችላሉ የሚል ግምት በመያዝ ጭምር ዋስትናውን መሻሩን ችሎቱ በጽ/ቤት አብራርቷል።
ባሉበት ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ውሳኔ ተሰጥቷል።
More : https://telegra.ph/Update-02-23
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#ሰዎች_ለሰዎች
ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል።
በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል።
በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት ጸድቋል። ድርጅቱ ዘንድሮ የተቋቋመበትን 40ኛ ዓመት ያከብራል።
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

#ችሎት እነ አቶ አብዲ ኢሌ ተቃውሞ አሰሙ። ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ-ሽብር እና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ 17 ተከሳሾች ተቃውሞ አሰምተዋል። እነ አቶ አብዲ ኢሌ ከኛ ጋር ታስረው የነበሩት እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ ነው ተቃውሞ ያሰሙት። …
#ችሎት
" የስነልቦና ጉዳት ስለደረሰብን ምስክር የመስማት ፍላጎት የለንም ስለዚህ ረጅም ቀጠሮ ይሰጠን " ሲሉ እነ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ፍርድ ቤቱን ጠየቁ።
" ከሌሎች የተለየ ወንጀልሳንሰራ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም " በማለት 2 ቀጠሮ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ኡመርን ጨምሮ 11 ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ ቀርተው ነበር።
ዓቃቤ ህግም ተገደው እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ችሎቱን ጠይቆ ነበር።
ፍርድ ቤቱ መርምሮ በጉዳዩ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን በዛሬው ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ተከሳሾቹም የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ባሉበት ሁኔታ ምስክር የመስማት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ እረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
ከሳሽ ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ጥያቄያቸው ከህግ አንጻር አሳማኝ አደለም ሆኖም እረጅም ቀጠሮ ቢሰጣቸው እንደማይቃወም አብራርቷል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ቀሪ የአቃቢህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 19 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የማህበር ቤት ምዝገባ ተጠናቀቀ። ባለፉት 25 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበር ቤት ምዝገባ 12 ሺህ 609 ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የማህበር ቤት ምዝገባ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡ ቢሮው በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች…
#AddisAbaba
የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባቸውን ዳግም በአካል እንዲያረጋግጡ ተጠየቀ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ካሉት የቤት አቅርቦት አማራጮች አንዱ የሆነውን የማህበር ቤት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች በማጠናቀቅ ማህበራቱ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን ገልጿል።
ቢሮው ከአሁን በፊት ፍላጎት ያላቸውን ነባር የ20/80 እና 40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች ተደራጅተው እንዲሰሩ በኦላይን ምዝገባ ማካሄዱን ነው ያስታወሰው።
ዛሬ ሩቡዕ ባወጣው ማስታወቂያ ደግሞ ከዚህ በፊት በኦላይን የተመዘገቡ የማህበር ቤቱ ፈላጊዎችን ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ድረስ በኦላይን ያከናወኑትን ምዝገባ በአካል እንዲያረጋግጡ አሳውቋል።
ለዚህም በአዲስ አበባ በራሳችሁ / በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም በሽያጭ አለማስተላለፋቸውን የሚገልጽ ቅፅ ከሚኖሩበት ወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በመውሰድ በተጠቀሰው ጊዜ ብቻ ምዝገባውን እንዲፈጽሙ ጠይቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በማስታወቂያው ተመዝጋቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከሚኖሩበት ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።

" በህዝበ ውሳኔ አንስማማም፤ ህዝበ ውሳኔ እንደማናካሂድ መላው የአማራ ህዝብ ማወቅ ይገባዋል ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ማወቅ አለበት " - ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት [በራሱ ፕሮግራም] ከተለያዩ ተቋማት እና ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ማድረጉን አስታውቋል።
ይህንንም አስመልክቶ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮ/ሌ ደመቀ በማህበራዊ ሚዲያ " ተጠርተው ነው የሄዱት ፣ ድርድር ሊደረግ ነው " እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ሀሰት መሆኑንም አመልክተዋል።
ኮሚቴው ወደ አዲስ አበባ የመጣበት ምክንያት ሲያስረዱ አካባቢው ላይ ፦
- የመልሶ ማቋቋም ስራ አልተሰራም
- የበጀት ምደባ አልተደረገም
- የወሰን እና የማንነቱን ጉዳይ እውቅና አልሰጠም ፣ ምንም እንኳን ብልፅግና ፓርቲ / አካባቢው ለማስተዳደር ውክልና ቢሰጠንም / የአማራ ክልል ብፅግና ፓርቲም ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ማህበረሰቡ ተገቢ አገልግሎት እያገኘ አይደለም ስለዚህ ይህንና ተያያዥ ጉዳዮች መንግስት ከምን አደረሰው የሚለውን ለማጣራት እንዲሁም ለመጠየቅ ነው የመጣነው ብለዋል።
ኮሚቴው ፥ በአዲስ አበባ ቆይታው ከፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብልፅግና ፓርቲ እና ምክትል ጠ/ሚ ጋር መገናኘቱንና መወያየቱን ገልፀዋል።
" ፕሮግራም አስይዘን ካለመምጣታችን አኳያ ፣ በድንገት ብንመጣም መስሪያ ቤቶቹ በጥሩ ሁኔታ አስተናግደውናል፤ በአብዛኛው የተገኘው ሀሳብም ጥሩ ነበር " ብለዋል።
" መሆን ስላለበት ጉዳይ ተነጋግረናል " ያሉት ኮ/ሌ ደመቀ በተለይ የበጀቱ ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለገንዘብ ሚስቴር ቢፅፍም ሚኒስቴሩ መልስ ሰጥቶ ወደ ማህበረሰቡ ስላልደረሰ ይህን ጉዳይ ተነጋግረንበታል ብለዋል።
ኮሚቴው በአ/አ ቆይታው ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ስራ ስለተደራረበባቸው ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ እና በቀጣይ ቀጥሮ እንገናኛለን ማለታቸውን ኮ/ሌ ደመቀ ተናግረዋል።
" የአካባቢውን ጉዳይ መንግስት ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥቶ ማየት አለበት " የሚሉት ኮ/ሌ ደመቀ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩ መጨረሻው በህዝበ ውሳኔ እንደሚሆን ሀሳብ መስጠቱን ያነሱ ሲሆን በኮሚቴው በኩል ግን " በህዝበ ውሳኔው " አለመስማማቱን ተናግረዋል።
ኮ/ሌ ደመቀ ዘውዱ ፥ " በህዝበ ውሳኔ እንደማናካሂድ መላው የአማራ ህዝብ ማወቅ ይገባዋል ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ማወቅ አለበት ፤ ይሄን አካባቢ ወደ ህዝበ ውሳኔ የሚያስኬድ ምክንያታዊ ውሳኔ ስላልሆነ ያንን እንደ ኮሚቴ አንቀበለውም፤ እንደህዝብም አንቀበለውም። " ብለዋል።
ምክንያቱን ሲያስረዱም " በህገመንግስትም አልሄድንም ህግ ተጥሶ፣ የህዝብ መብት ተረግጦ ብዙ ባለአባቶች ተገለው ተሰውረው ያህንን አካባቢ ድርጅቱ TPLF ሆን ብሎ መሬት ፈልጎ አካባቢ ፈልጎ የወረረው አካባቢ ስለነበር አሁን የሚፈታው በህግ ነው የሚለው ምክንያታዊ ነው ብለን አናስብም። ብዙ የህግ ባለሞያዎችን አማክረናል ይሄ ጉዳይ በህግ እስካልሄደ በህግ አይደለም የሚመለሰው በፖለቲካ ውሳኔ ነው የመጨረሻ እልባት ማግኘት ያለበት የሚል ሀሳብ እየሰጡ ነው እውነት ነው ምክንያታዊም ነው የነሱ ሃስብ በሚል አጥጋቢ ምክንያት ስላገኘን በዚህ ምክንያት ህዝበ ውሳኔ ፌዴሬሽን ም/ቤት ብሎ የሚያስበው ትክክል አይደለም፤ በዛ ባይሆን የሚል ነው " ብለዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ፥ " በገዛ በራሳችን መሬት፣ በገዛ በራሳችን ርስት የትግራይ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ወሳኞች ሆነው ሊመጡ ይገባል ብለን አናምንም ፤ እንደኢትዮጵያውያን አብረን በጉርብትና መኖር እንችላለን ፣ ይሄን አካባቢ ግን በህዝበ ውሳኔ ለጨረታ ወጥቶ ምንደራደርበት ጉዳይ እንዳልሆነ ግን መላው ህዝብ ሊያውቀው ይገባል። ይሄን ሃሳብ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ገልፀናል። ሌሎችም የሚመለከታቸው የመንግስት አመራሮችም ይሄን ጉዳይ በትክክል አይተው ሊፈቱት ይገባል እኛ ወደ አካባቢው መጥተናል ተመልሷል እውቅና ግን ማግኘት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።
አካባቢው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጀት ሊመደብለት ይገባል ያሉት ኮሎኔል ደመቀ ፥ መድሃኒት የለም፣ ታማሚዎች አይታከሙም ፣ወላዶች እየታከሙ አይደሉም ፣ ህፃናቶችም እየሞቱ ነው ፣ ውሃ የለም ፣መብራት የለም ፣ እዛ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችም ሞያተኖች መብታቸው እየተጠበቀ አይደለም ፤ ስለዚህ መንግስት በአፋጣኝ የዚህን ህዝብ ችግር አይቶት ሊፈታው እና መፍትሄም ሊሰጠው ህዝቡም ከችግር የሚወጣበትን ነገር ሊፈጥር ይገባል ብለዋል።

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጽን ይመለከታል ፦
በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዙር ከቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293,865 ሴት 250,703 ድምር 544,568 ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27,979 ሴት 26,456 ድምር 54,435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተናው ተሰጥቷል። በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321,844 ሴት 277,159 ድምር 599,003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።
የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል።
በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።
በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ነገር ግን በተናጠል የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 141 ተማሪዎች ላይ ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው የተለያየ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።
ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለፃል ? በርካታ የ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ' ተማሪዎች ፣ ወላጆች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ እንደሚገለፅ መረጃ እንድናጋራቸው ጠይቀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት እየተጠናቀቀ ይገኛል። እስከ የካቲት 15 ድረስ ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 20 ድረስ የውጤት…
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።
በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።
ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።
ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።
ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot
4) በ9444 SMS ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል…
#ማሳሰቢያ
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አውንታዊ ድጋፍ ለሚሹ አመልካቾች student.ethernet.edu.et በመግባት ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።
በተመሳሳይም በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።
ኤጀንሲው ምላሹን በማመልከቻ ቅጹ ላይ በሚያስቀምጡት አድርሻ እንደሚያሳውቅ የገለፀ ሲሆን በአካል ወደ ኤጀንሲው መምጣት አያስፈልግም ብሏል።

#WeCare
በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ስፔሻሊስት የሆኑ ዶክተሮችን ኦንላይን በቪድዮ፣ በድምጽ አልያም በ አጭር መልእክት ማግኘት የሚያስችል አዲስ አገልግሎት ተጀመረ።
ለራስዎ ፣ ለልጅዎ ወይም ለቤተሰቦ የሚሰማዎትን ህመም ወይም አጠራጣሪ ነገር በ WeCare መተግበሪያ በሙያው የተካኑ ሐኪሞችን በፍጥነት በማማከር እፎይታ ያግኙ!
መተግበሪያውን ለማውረድ : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
አጠቃቀሙን ለመረዳት ቻናሉን @wecareet ይቀላቀሉ
ለበለጠ መረጃ : 9394 በመደወል ማብራሪያ ይጠይቁ!

#ሰዎች_ለሰዎች ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል። በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል። በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት…
#ሰዎች_ለሰዎች
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት አውሏል።
ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ድርጅት የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ በሆኑት በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም ተቋቁሞ ላለፉት 40 ዓመት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እና ድጋፎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
ድርጅቱ እስካሁን በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት ማዋሉን ጠቅሷል። በዚህም 6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረጉን ገልጿል።
በዚህ ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መድቦ በአምስት የተለዩ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የጀርመን ሥራ አመራር ቦርድ ተጠሪ ዶክተር ሰባስቲያን ብራንዲስ ትላንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/MFM-02-23

Telegraph
MFM
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት አውሏል።
#UkraineCrisis
የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ?
ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች።
አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ።
ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት የሆነውን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶን) እንደማትቀላቀል ምዕራባውያን ዋስትና እንዲሰጡ ነው።
እንደቀድሞዋ የ " ሶቪየት ሪፐብሊክ " አካል የነበረችው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጥልቅ ማህበራዊ እና ባህላዊ ግንኙነት አላት። ሩስኪ በሰፊ የሚነገርባት ቢሆንም ሩሲያ እአአ በ 2014 ከወረረቻት ጊዜ ጀምሮ ግንኙነቶቹ ተበላሽተዋል።
እአአ በ2014 መጀመሪያ ላይ የሩሲያ ደጋፊ የነበሩት ፕሬዚዳንቷ ከስልጣን ሲወገዱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ፈጸመች። ከዚያ ወዲህ የምስራቁ ጦርነት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድሏል።
ቀውሱ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው ?
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ውስጥ ላሉ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ሰጥተዋል ፤ እነዚህ ግዛቶች ዶኔትስክ እና ሉጋንስክ ይባላሉ።
ሩስያ በአማፂያን ቁጥጥር ስር በሚገኙ 2 የምስራቃዊ ዩክሬን ክልሎችን እንዲዘምቱ አዛለች፤ ምክንያት ? "ሠላምን ለማስፈን" እንደሆነ ነው የገለፀችው። የሩሲያ ጦር ወደ ሁለቱም ተገንጣይ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች እንዲገባ የሚያስችል ስምምነትም በፕሬዝዳንት ፑቲን እና በአስገንጣይ ኃይሎች መካከል አለ።
የሩሲያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጦር ከሩሲያ ውጪ እንዲሰማራ ፈቅዷል። ይህ ሁኔታ ነው ቀውሱን ያባባሰው እና አስፈሪ ያደረገው።
#BBC

#UkraineCrisis የሩስያ እና የዩክሬን ቁርሾ ምንድነው ? ዩክሬን ወደ አውሮፓ ተቋማት NATO እንዲሁም አውሮፓ ህብረት የምታደርገውን እርምጃ ሩሲያ ስትቃወም ቆይታለች። አሁን ደግሞ ዩክሬን #የምዕራቡ_ዓለም_አሻንጉሊት እንደሆነች እና በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ሃገር እንዳልነበረች ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገልፃሉ። ዋና ፍላጎታቸው ደግሞ ዩክሬን የ30 ሃገሮች የመከላከያ ሃይል ጥምረት…
#Ukraine
አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው ?
- ዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን አገሪቱን ሙሉ በሙሉ ለመውረር እንቅስቃሴው ተጀምሯል ብላለች።
- ዛሬ ማለዳ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮላድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ በአገራቸው ላጥ ጥቃት መክፈቷን አሳውቀዋል። የሚሳአኤል ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል። ሩሲያ ዛሬ ማለዳ ላይ የከፈተችው ጥቃት ኢላማ ያደረጉት የዩክሬን መሰረተ ልማቶችና የድንበር ጥበቃዎች ላይ ነው ብለዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰራዊቱ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋግጦ ኢላማዎቹ ከተሞች ላይ ሳይሆኑ የዩክሬን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች፣ የአየር መከላከያ እና የአየር ኃይል ተቋማት መሆናቸውን ገልጿል።
- ሩሲያ በማንኛውም ቀን "አውሮፓ ውስጥ ትልቅ ጦርነት" ልትጀምር እንደምትችል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አስጠንቅቀው ሩሲያውያን እርምጃውን እንዲቃወሙት ጠይቀዋል። ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን አስታውቀዋል። "ከሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር የስልክ ንግግር ለማድረግ ሞከርኩ። ውጤቱ ዝምታ ሆነ" ብለዋል ዜለንስኪ። ሩሲያ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የውጊያ መኪናዎች በዩክሬን ድንበር እንዳሏት ተናግረዋል። ሩሲያውያን በዩክሬን ጉዳይ እየተዋሹ መሆኑን ጠቅሰው ጥቃትን እንዲቃወሙ ተማፅነዋል።
- የቭላድሚር ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን #ዶንባስ ክልል ወታደሮቻቸው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሂዱ አዘዋል። በሩሲያ የሚደገፉ አማጺያኖች ጋር እየተዋጉ የሚገኙ የየክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የመቆጣጠር እቅድ እንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን ነገር ግን ማንኛውም አካል ሩሲያ ላይ አደጋ የሚጭር ነገር ካደረገ ምላሻችን ፈጣን ነው ብለዋል።