TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። @tikvahethiopia
#BREAKING

የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ፦

" የሚኒስትሮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ በሚመለከት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ሕውሃት እና ግብረአበሮቹ በሃገራችን ህልውና እና ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ በመሆኑ እና ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 ፀድቆ በስራ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑ እና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 አንቀጽ 11(2) በተደነገገው መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው በመሆኑ የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጥልቀት ተወያይቶ በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#State_of_Emergency

ለ6 ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ እንዲያጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፋል።

ም/ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ መሆኑን ገልጿል።

አክሎም ስጋቱን በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን በመግለፅ ለ6 ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አሳውቋል።

በዚህም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የ6 ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው ህ/ተ/ም/ቤት የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ እንዲተላለፍ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ከእስር ተለቀቀ። ላለፉት 3 ወራት ከሶስት ቀን በእስር ላይ የነበረው የአሐዱ ሬዲዮ የዜና ክፍል ሀላፊ ክብሮም ወርቁ ዛሬ ከሰአት በኃላ ከእስር ተፈትቶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉን ጠበቃው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ መናገራቸውን አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን አሳውቋል። @tikvahethiopia
ፎቶ : ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ተቀላቅሏል።

ጋዜጠኛው ከእስር መፈታቱን በተመለከተ በተረጋገጠ ፌስቡክ ገፁ ላይ " ከጥቅምት 18 እስከ ጥር 18 ... በእግዚአብሔር ምህረት ተፈትቻለሁ ፤ አመሰግናለሁ " ብሏል።

ጋዜጠኛ ክብሮ ወርቁ ላለፉት 3 ወራት በእስር ቆይቷል። ዛሬ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ ቤት በመታወቂያ ዋስትና ነው ከእስር የተፈታው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል ?

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቷል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መረጃ ነው።

ለ6 ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ እንዲያጥር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፋል።

በዚህም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የ6 ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው ህ/ተ/ም/ቤት የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው #የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ በማፅደቅ ለምክር ቤቱ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደተነሳ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

ኢትዮጵያ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ናት።

@tikvahethiopia
#Safricom_Ethiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን ትላንት የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።

በዚሁ የውይይት መድረክ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚያካሂደው የኔትወርክ ግንባታ ቀጥተኛ አስተዋጽዖ ካላቸው ልዩ ልዩ ሚኒስቴትር መስሪያ ቤቶችና የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትብብሩን በማጠናከር በቀጣይ ስለሚያስፈልጉን ድጋፎች መምከሩን ገልጿል።

ሳፋሪኮም ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርግልን ያልተቋረጠ ድጋፍ ለደንበኞቻችን ምርጥ የሆነውን አገልግሎት ለማቅረብ እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ በብቃት እንድንደግፍ የሚያስችለን ነው " ብሏል።

አገልግሎቱን ለመጀመር እየተጋ መሆኑንም ገልጿል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ አገልግሎቱን በይፋ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle📍

በዛሬው ዕለት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ከባለፈው መስከረም ወር ወዲህ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የመጀመሪያውን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፎችን ማድረስ መቻሉን አሳውቋል።

አስፈላጊ መድሃኒቶችን ያካተተው የአስቸኳይ ህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት በክልሉ በጣም ለተጎዱ የጤና ተቋማት ይደርሳል ተብሏል።

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጨማሪ በረራዎችን በማዘጋጀት በያዝነው እና በቀጣይ ሳምንታት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፉን ለመቀጠል አቅዷል፡፡

በተመሳሳይ ድርጅቱ በአማራ እና አፋር ክልሎች በግጭቱ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አስቸጋሪ ለሆነባቸው የጤና ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ምንጭ : https://www.icrc.org/en/document/ethiopia-icrc-aid-flight-delivers-lifesaving-medical-supplies-tigray

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ ስለብሄራዊ ቡድኑ ምን አሉ ?

የጊኒ ብሄራዊ ቡድን በካሜሮን የ2021 አፍሪካ ዋንጫ በጊዜ ከተሰናበቱት ሀገራት መካከል እንደምትገኝበት ይታወቃል።

ቡድኑ ወደ ካሜሮን በተሸኘበት ምሽት አሁን ጊኒን እያስተዳደር ያለው የጁንታ መሪ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ ለቡድኑ አባላት ያስተላለፉት መልዕክት መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር የሁላችንም ትውስታ ነው።

ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ የሀገሪቱን ባንዲራ 🇬🇳 ለቡድኑ ካስረከቡ በኃላ ባስተላለፉት መልዕክት የቡድኑ አባላት ዋንጫውን ይዘው እንዲመጡ ካልሆነ ግን በእነሱ ላይ ኢንቨስት የተደረገውን እያንዳንዱን ገንዘብ እንዲመልሱ /እንዲተኩ ነበር ያሉት።

ቡድኑም በአፍሪካ ዋንጫው ሳይሳካለት ቀርቶ በጊዜ ተሰናብቷል ፤ ይህን ተከትሎ የጁንታውን መሪ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ አስተያየት ብዙዎች ሲጠብቁት ነበር።

ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያም ዝም አላሉም።

ኮሌኔሉ ብሄራዊ ቡድኑን 'ይቅር' እንዳሉ ገልፀው ፤ በወቅቱ ያን ንግግር የተናገሩት ቡድኑን ለማበረታታ ብቻ መሆኑ አሳውቀዋል። " የቡድን ግንባታ ጊዜ እንደሚወስድ እገነዘባለሁም " ብለዋል።

ነገር ግን ለቡድኑ የተሰጠው ገንዘብ ሩብ ፍፃሜ ፣ ግማሽ ፍፃሜ እና የፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚሸፍን ሲሆን ያ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ይመለሳል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ ግለሰቦች የሙሉ አምባሳደርነት እና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ።

በዚህም መሠረትም፡-

1/ አቶ ተፈራ ደርበው
2/ አቶ ደሴ ዳልኬ
3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ
4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ
5/ ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም
6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ
7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ
8/ አቶ ረሻድ መሀመድ
9/ አምባሳደር ጀማል በከር
10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ
11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ
12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው
13/ አቶ ጣፋ ቱሉ
14/ ዶክተር ገነት ተሾመ
15/ አቶ ዳባ ደበሌ
16/ አቶ ፍቃዱ በየነ የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ።

1/ አቶ አሳየ አለማየሁ
2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ
3/ አቶ አወል ወግሪስ
4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት
5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ
6/ አቶ አክሊሉ ከበደ
7/ አቶ ሰይድ መሐመድ
8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
9/ አቶ ዘላለም ብርሃን
1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ
11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 42ቱን መለየቱን የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ አሳውቀዋል።

አቶ ታገሰ ፥ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች 632 የእጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቅረባቸውንና አብዛኛዎቹ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ልምድና ዕውቀት ያላቸው መሆኑን መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

አዋጁ ለአፈ-ጉባኤውና ለአፈ-ጉባኤው ጽ/ቤት በሰጠው ስልጣን እንዲሁም በአዋጁ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ከቀረቡት 632 ዕጩዎች መካከል 42ቱ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀረቡ 42 ዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር እየተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ሳምንት ደግሞ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራር አካላት በሚገኙበት በዕጩዎች የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ላይ ምክክር ተደርጎ ግብአት የሚሰበሰብ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በማስከተልም በም/ቤቱ ድረ-ገጽና በማህበራዊ ሚዲያ የእጩዎችን ማንነት በመግለጽ በቂ ግብአት ከተሰበሰበ በኋላ ሰብሳቢና ም/ሰብሳቢን ጨምሮ 11ዱ ዕጩ ኮሚሽነሮች ለም/ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀና ዕጩዎች ከተሰየሙ በኋላ ወደ ስራ እንደሚገባም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ ይለቀቁ " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኢፌዲሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ አበረታች እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ፤ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የነበረው ሁኔታ በመሻሻሉና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት የአዋጁ አስፈላጊነት እየተገመገመ ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ የነበረ መሆኑ አስታውሷል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት በመንግስት የቀረበለትን ውሳኔ ሃሳብ በአፋጣኝ እንደሚያጸድቀው ኢሰመኮ ተስፋውን የገለፀ ሲሆን የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪውን አቅርቧል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው አዋጅ የተነሳ መሆኑን ከሚያጸድቅበት ቀን ጀምሮ ከእስር ያልተለቀቁ ሰዎች የሚኖሩ ቢሆን፤ ከ48 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት አለመቅረብ እስሩ ከሕግ ውጭ የሚያደርገው በመሆኑ የሁሉም የሕግ አስከባሪ አካላት የሕግ ማስከበር ተግባራት የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ በመደበኛው ሥርዓት እንዲከናወኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት /USAID/ አማካይነት በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል፣ 400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል፣ በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በኢፋ /Iffa/ እና በUSAID ተግባራዊ የሚደረጉ 2ቱ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራውንና 9 ሚሊዮን ሰዎች ራሳቸውን ከድህንነት እንዲያወጡ የሚያግዘውን የማኅበራዊ የምርት ደህንነት ወይም ሴፍቲኔት መርኃግብር እንደሚያጠናክር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተካሄዱት ለሚገኙ ተመሳሳይ መርኃግብሮች ቀዳሚውን ድጋፍ እየሰጠ ያለው ዩኤስኤድ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ እኤአ ከ2015 ጀምሮ ወደ 60 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

አሁን የሚካሄዱት ሁለቱ መርኃግብሮችም በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና የጋራ ፍላጎት እንደሚያረጋግጡም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በዚህ ሳምንት ውስጥ ይፋ የተደረጉት ሁለቱ ፕሮጀክቶች USAID ባላፉት 5 ዓመታት ውስጥ በ220 ቢሊዮን ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡

የሚሰጠው ድጋፍ በሁሉም አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ጤናማና የበለጸገ ህይወት እንዲመሩ የሚያግዝ መሆኑንም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ / ቪኦኤ

@tikvahethiopia