TIKVAH-ETHIOPIA
" የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስጀመር ከጸጥታ አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮም በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ዳግም አገልግሎት ለማስጀመር ከጸጥታ አካላት ጋር ንግግር መጀመሩን አሳውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ የኮሙኒኬሽን ኤክስፐርት አቶ መሳይ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የተቋረጠውን አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር ንግግር…
#UPDATE
በአማራ ክልል ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት ዳግም መጀመሩን አል ዓይን ኒውስ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በአማራ ክልል የሞባይል ዳታ አገልግሎት መስራት ጀምሯል።
ከሰሞኑ ኢትዮቴሌኮም በአማራ እና በአፋር ክልል ዳግም አገልግሎቱን ለማስጀመር ከጸጥታ አካላት ጋር ንግግር መጀመሩን ገልጾ ነበር።
ከሀገሪቱ የጸጥታ ተቋማት ጋር እየተነጋረ እንደሆነ በገለጸ በቀናት ውስጥ አገልግሎቱ ተጀምሯል።
በዚህም መሰረት በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረታቦር፣ ፣ በወልዲያ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደብረብርሃን፣ በላሊበላ የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩን ከነዋሪዎች ማረጋገጡን አል ዓይን ኒውስ ገልጿል።
@tikvahethiopia

#SUDAN በሱዳን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት እንዲሁም የሱዳንን ወታደራዊ ክንፍ በመቃወም እና ሙሉ በሙሉ ሲቪል አስተዳደር በመጠየቅ የሚካሄደው ሰልፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ትላንት በተካሄደ ህዝባዊ ሰልፍ 4 ሰዎች በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል። እንደ ሱዳን የዶክተሮች ቡድን መረጃ አራቱ የተገደሉት ዜጎች ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ ነው። የሱዳን መንግስት…
#UPDATE
በሱዳን ካርቱም ኢንተርኔት በድጋሚ ተዘጋ።
በሱዳን ሊካሄድ ከታሰበ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መዘጋቱ ተሰምቷል።
በቅርቡ በተደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን “ ሰማዕታትን ለማስታወስ ” በሚል እንዲሁም ጥቅምት ወር ላይ ወታደራዊ ክንፉ ያደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወምና ሙሉ የሲቪል አስተዳደር ይመስረት በሚል ለዛሬ ሰልፍ ተጠርቷል።
ከሰልፉ ጋር በተያያዘ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሞባይል ኢንተርኔት ተቋርጧል ፤ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችም በከተማይቱ ተሰማርተዋል፤ ከካርቱም ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች በፀጥታ ኃይሎች ተዘግተዋል።
ከቀናት በፊት ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በኦምዱርማን ከተማ በሱዳን ፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች 6 ደርሰዋል።
የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ መረጃ የሱዳን ተቃውሞ ከተጀመረ አንስቶ አጠቃላይ የሞቱ ሰዎች 54 መድረሳቸውን ያመለክታል።

#ተጠናቋል
የቁስቋም-እንጦጦ መንገድ ተገንብቶ ተጠናቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጫካውን በመሰንጠቅ በአጭር ጊዜ ፣ በከፍተኛ ጥራት ግንባታውን ያከናወነው የባለስልጠን መሥሪያ ቤቱ ራስ ኃይል መንገድ ግንባታ ክፍል ነው ሲል አሳውቋል።
3.6 ኪ.ሜ. የሚረዝመው ይህ የጫካ ውስጥ ውበት አስቸጋሪውን አሮጌ መንገድ በመተካት የእንጦጦን ጉዞ አቅልሎታል ተብሏል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

#UPDATE በሱዳን ካርቱም ኢንተርኔት በድጋሚ ተዘጋ። በሱዳን ሊካሄድ ከታሰበ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በድጋሚ መዘጋቱ ተሰምቷል። በቅርቡ በተደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሱዳን የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን “ ሰማዕታትን ለማስታወስ ” በሚል እንዲሁም ጥቅምት ወር ላይ ወታደራዊ ክንፉ ያደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወምና ሙሉ የሲቪል አስተዳደር ይመስረት በሚል ለዛሬ…
#Update
የሱዳን ፀጥታ ኃይሎች ዛሬ 2 ሰዎችን እንደገደሉ የዶክተሮች ኮሚቴ አስታወቀ።
ዛሬ እሁድ በሱዳን ወታደራዊ አገዛዙን ለመቃወም አደባባይ ከወጡ ሱዳናውያን መካከል የፀጥታ ኃይሎች 2 ሰዎችን መገደላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው እንዳሳወቀው የመጀመሪያው ሰው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገኝ ወጣት ሲሆን በዋና ከተማይቱ ካርቱም በጭንቅላቱ ላይ በደረሰ ጉዳት ሲሞት ሁለተኛው ሰው ደግሞ በኦምዱርማን ደረቱ ላይ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፋል።
የዛሬው ግድያ እኤአ ከጥቅምት 25 አንስቶ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት የሞቱ አጠቃላይ ሰዎችን ቁጥር ወደ 56 ከፍ ማድረጉ ተገልጿል።
የጸጥታ ሃይሎች ስለተገደሉ ሰዎች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ለ12ኛ ዙር የተደረገ ከፍተኛ ተቃውሞ ነበር።
በካርቱም ከተማ ተቃዋሚዎች ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት ሲያመሩ የጸጥታ ሃይሎች አስለቃሽ ጭስ ስለመተኮሳቸው መነገሩን ሮይተርስ አስነብቧል።

የጋዜጠኞች ግድያ ... #በ2021
የጎርጎሮሳውያኑ 2021 ተጠናቆ ከትላንት ጀምሮ አዲሱ ዓመት 2022 ገብቷል።
በተሰናበተው 2021 በመላው ዓለም 45 ጋዜጠኞች ተገድለዋል።
የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ2021 የተመዘገበው የጋዜጠኞች ግድያ ከየትኛውም አመት ከተመዘገበው ዝቅተኛ ቁጥር አንዱ ነው ብሏል።
በአንድ ሀገር ከፍተኛ የተመዘገበው አፍጋኒስታን ውስጥ ሲሆን 9 ጋዜጠኞች ተገድለዋል እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ግድያ የተመዘገበባቸው በሜክሲኮ 8 ፣ በህንድ 4 ፣ በፓኪስታን 3 እንደሆነ ተገልጿል።
አፍጋኒስታንን የሚያጠቃልለው ኤዥያ-ፓሲፊክ አካባቢ 20 ግድያዎች የተመዘገቡበትና ከፍተኛው ሲሆን አሜሪካ 10 ፣ አፍሪካ 8 ፣ አውሮፓ 6 እና መካከለኛው ምስራቅ እና አረብ ሀገራት 1 ተመዝግቧል።
በኢራን በደረሰ “አሰቃቂ አደጋ” የ2 ጋዜጠኞች ሞትም ጠቅሷል።

ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው ? የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ሊለቁ መሆኑን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ መረጃውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ዛሬ መስማቱን ገልጿል። ለሚዲያ ማብራሪያ መስጠት ያልተፈቀደላቸው አንድ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላ ሀምዶክ የቢሮ ሰራተኞቻቸውን አደራ እንዲያስረክቡ ማዘዛቸውን ፤ ሰራተኞቹም ይህን ከእሁድ ማታ ጀምሮ መተግበር…
#BREAKING
ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል።
አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት።
ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ምንጭ መስማቱን መዘገቡ ይታወሳል።

#UPDATE😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ በ5 ወር ውስጥ ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ይህም በ5 ወር የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው። ባለፈው ወር ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ዝርያ ሪፖርት አድርጋለች።
🇮🇱 እስራኤል ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ ከፍተኛውን የኮቪድ-19 ኬዝ ሪፖርት አደርጋለች። ባለፉት 24 ሰዓት 4,197 ሰዎች በቫይረሱ መያዘቸው ተረጋግጧል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት በኦሚክሮን ዝርያ ስርጭት ሳቢያ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ሊጨምሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
🇮🇳 ህንድ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ለ5ኛ ተከታታይ ቀን በእጅጉ መጨመር ያሳየ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
🇵🇸 በፍልስጤም ፤ ጋዛ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር 4ኛው ማዕበል እየመጣ መሆኑን አስጠንቅቋል።
🇶🇦 ኳታር በሶስተኛው የኮሮና ቫይረስ ማዕበል ላይ እንደምትገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ነዋሪዎች የማጠናከሪያ/ተጨማሪ ክትባቱን እንዲወስዱ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
🇪🇹 በሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 11,213 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 32 ሰዎች ህይወታቸው አልፋል።

#LALIBELA ከፊታችን ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ላሊበላ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ አሳውቋል። @tikvahethiopia
#UPDATE
ወደ ላሊባላ ከተማ በረራ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ ዕለታዊ በረራውን ዛሬ ጀምሯል።
አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች በአየር መንገዱ መተግበሪያ በመጠቀም ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚችሉ አስታውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።
በአዲሱ የተቋማት አደረጃጀት መሰረት ቀደም ሲል በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሲሰራ የነበረው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ በውክልና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ቢሮው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ በመግለፅ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።
አሽከርካሪዎች አዲስ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት በሚሄዱበት ወቅት ምን ያስፈልጋቸዋል ?
- የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም የታደሰ ፓስፖርት፣
- ሲኦሲ ዋናውን፣
- የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን፣
- የ10 ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ሆኖ ትክክለኛነቱ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ ሰነድ በመያዝ በአካል በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

#BREAKING ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል። አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት። ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው…
#Update
አሜሪካ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቅ በኋላ፣ የሱዳን መሪዎች ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው መግባባትን መፍጠር እና ቀጣይነት ያለው የሲቪል አስተዳደርን ማረጋገጥ አለባቸው ብላለች።
ሀገሪቱን ይህን ያለችው የጠ/ሚር አብደላ ሀምዶክ ስልጣን መልቀቅን ተከትሎ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጠር ያለ መግለጫ ነው።
አሜሪካ ቀጣዩ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ካቢኔ የህዝብን የነጻነት፣ የሰላም እና የፍትህ ግቦች ለማሳካት በህገ-መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት መሾም አለበት ብላለች።
አሜሪካ በመግለጫዋ ላይ የሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲን ለማስፈን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከጎናቸው መቆሟን እንደቀጠለች ገልፃ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቆም አለበት ስትል አስታውቃለች።

#ጥንቃቄ
የጤና ባለሙያዎች ህብረተሰቡ ለኮቪድ -19 የሳል ማስታገሻ በሚል ከሚወሰዱ መድኃኒቶች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
ከኮቪድ - 19 መስፋፋትን ተከትሎ በየፋርማሲዎች የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶች ፍላጎት መጨመሩን ባለሙያዎች እየገለፁ ይገኛሉ።
የአለርት ሆስፒታል የፋርማሲ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አሸብር ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ ከኮቪድና ጉንፋን ወረርሽኞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካቶች ያለሐኪም ምክር ከየፋርማሲው የሳል ማስታገሻ መድኃኒቶችን እየወሰዱ ነው ብለዋል።
ይህ ልምድ ለተጓዳኝ በሽታዎች መባባስ የሚዳርግ በመሆኑ መጠንቀቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በተለይ በከተሞች ላይ የጉንፋን በሽታ ይዞኛል የሚሉ በርካታ ሰዎች “ፍሉ ስቶፕ” የተሰኘውን ማስታገሻ መድኃኒት በመግዛት ያለሐኪም ምክር እየወሰዱ ይገኛሉ ያሉት አቶ ዮናስ፤ ተመሳሳይ መድኃኒቶችን ያለባለሙያ ምክር መውሰድ በተለይ የደምግፊት፣ ስኳር፣ አስምና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ላለባቸው ሰዎች አደገኛ ነው ብለዋል።
ተመሳሳይ መድኃኒቶች በመንግሥት ሆስፒታሎች በሚገኙ ፋርማሲዎች ውስጥ ያለሐኪም ትዕዛዝ እንደማይሸጡ የጠቆሙት አቶ ዮናስ፣ በግል ፋርማሲዎች ግን መድኃኒቱን ለጠየቀ ሁሉ የመሸጥ ልምድ እንዳለ አስረድተዋል።
ሰዎችም የጉንፋን ምልክት ስላሳዩ ብቻ ያለሐኪም ምክር ማስታገሻዎችን መውሰዳቸው ለከፋ የጤና ችግር እንደሚያጋልጥ በማወቅ በቅድሚያ መመርመር ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ያለበለዚያ ግን ለውስብስብ የጤና ችግር የመዳረግ እድላቸው ይሰፋል ሲሉ አሳስበዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-01-03
ምንጭ፦ ኢፕድ