" የጦር መሳሪያ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ሆሳዕና ከተማ ገብቷል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው " - የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ
የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጥቅምት 24/2014 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን ከአዲስ አበባ ያደረገ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 19331 ደ.ህ የሆነ ተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ጭኖ በወልቂጤ ከተማ በኩል ወደ በሆሳዕና ገብቷል ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑን ገልጿል።
ይሁንና ተሽከርካሪው በፍጥነት እያሽከረከረ ስለነበረ ሆሳዕና ከተማ ናረሞ አከባቢ በስራ ላይ የነበሩ ትራፊክ ፖሊሶች ለማስቆም ሲሞክሩ ጥሶ በማለፍ በ2 ሞተረኞች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል።
አሽከርካሪው ጉዳት አድርሶ ለማምለጥ ጥረት ቢያደርግም በአከባቢው ህበረተሰብና በፀጥታ አካላት ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።
በተጎጂዎቹም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት በመድረሱ በንግስት እሌኒ መህመድ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።
ጉዳቱን ባደረሰው አሽከርካሪ ምርመራ በማድረግ የማጣራት ስራ እያከናወነ ይገኛል።
ጉዳዩ ይህ ቢሆንም የጦር መሳሪያ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ሆሳዕና ገብቷል ተብሎ የሀሰት መረጃ የተሰራጨ ሲሆን ፖሊስ መረጃው ሀሰተኛ ነው ብሏል።
ህብረተሰቡ ትክክለኛነቱ ባልተረጋገጠ ወሬ ሳይረበሽ አካባቢውን ከፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር በመጠበቅ ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።
ነዋሪዎች ማንኛውም ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገባ ነገር ካጋጠማቸው 046550330 በመደወል ለፖሊስ መረጃ እንዲሰጡ ተጠይቋል።
(የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ)
@tikvahethiopia

#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።
ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።
መንግስት በመግለጫው "የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የሽብር ወሬ እያሰራጩ ናቸው" ብሏል። ቁልፍ ኢላማቸው ደግሞ በአመራሩና ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ፍርሃትም እንዲነግስ ማሸበር ነው ሲል ገልጿል።
በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።
በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ናቸውም ሲል ገልጿል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ ብሏል።
በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,341 የላብራቶሪ ምርመራ 327 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 420 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል።
ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡
ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።
ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደገገ ስለሆነ ከአ/አ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።
#AddisAbabaPolice
#Share #ሼር

ከሰሞኑን ተከታትለው የወጡት የተኩስ አቁም ጥሪዎች !
በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።
ከሰሞኑን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት በተከታታይ የተኩስ አቁም እና የድርድር ጥሪዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል።
1ኛ. #ሩሲያ፦ በድጋሚ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቃለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃለች ፤ ሰሞኑን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የተካሄዱት ጦርነቶች የሲቪል ዜጎችን ህይወት ጎድቷል ብለዋል።
ሩሲያ #የኢትዮጵያን_ግዛት_አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ብለዋል።
2ኛ. #ኬንያ ፦ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳስበዋል።
ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ጠይቀዋል።
ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል ኡሁሩ።
ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ያሉም ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።
3ኛ. #ኢጋድ ፦ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ ፥ እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዶ/ር ወርቅነህ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም ወገኖች ከግጭት ተቆጥበው በመካከላቸው ያለውን መካረር እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።
4ኛ. #ዩጋንዳ ፦ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሐገራት መሪዎች ጦርነቱ ሥለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሰበሰቡ ጠይቀዋል።
5ኛ. #አሜሪካ ፦ ዛሬም (ጥቅምት 26) አሜሪካ በድጋሚ በኢትዮጵያ ተኩስ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ማብቃት አለበት ፤ አሁኑኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድር መጀመር አለበት ብለል፤ ተኩስ እንዲቆምም ጠይቀዋል።
6ኛ. #AU ፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ ገልፀዋል።
ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ያወጡትን መግለጫ በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።
በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።
ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።
የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
በሌላ መረጃ ፦
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ለድርድር የሚሆን ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።
ምንጭ፦ UN ፣ AU ፣ ኢጋድ ፣ አል አይን ኒውስ ፣ Daily Nation ፣ António Guterres (Twitter) ፣ BBC ፣ Antony Blinken (Twitter)

TIKVAH-ETHIOPIA
" የጦር መሳሪያ ምዝገባ እስከ ነገ ድረስ ተራዝሟል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ በአዲስ አበባ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ትናንት በተላለፈው ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች በከተማዋ በሚገኙ ፓሊስ ጣቢያዎች በመቅረብ እያስመዘገቡ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፤ የከተማዋን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ከዚህ…
#AddisAbaba
በእጃቹ ያለውን መሳሪያ እስከ ጥቅምት 27 / 2014 ደረስ ማስመዝገብ ትችላላችሁ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ ምክንያቶች የጦር መሳሪያ ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም በድጋሚ መራዘሙን አሳውቋል።
የጦር መሳሪያ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ በአስራ አንዱ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በግንባር በመገኘት እንዲያስመዘግብ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች በእጃቸው ላይ የሚገኝን የጦር መሳሪያ ለተከታታይ 3 ቀናት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።
መሳሪያ በእጃቸው ላይ ያለ ሰዎች የማስመዝገብ ፍላጎቱ እያላቸው የምዝገባ ቀኑ በማጠሩ ፣ ያላቸውን የጦር መሳሪያ ሌላ ቦታ በማስቀመጣቸው እና ማስመዝገብ እንደሚቻል በቂ መረጃ ያልሰሙ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት ምዝገባው እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ/ም መራዘሙ ተገልጿል።
በእጁ ላይ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ያላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ የተጨመረውን ቀን ተጠቅሞ እንዲያስመዘግብ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

#SNNPRS
በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።
ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።
በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።
አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።
መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሆነ ተገለጸ። ፈተናዎች በቀጣይ ቀናት ወደ ፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰራጩ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ተናግረዋል። ፈተናዎቹ ወደ ፈተና ጣቢያዎች ከተሰራጩ በኋላ በየደረጃው ከተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አባላት ጋር የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ በቅንጅት እንደሚሰራም…
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 ጀምሮ ይሰጣል።
የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና) ከጥቅምት 29 - ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ገልጿል።
የብሄራዊ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የሚሰጥ መሆኑን በማወቅ በተረጋጋ ስነ-ልቦና ቅድመ-ዝግጅታቸውን እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል።
በሌላ በኩል ፥ አጠቃላይ የፈተናውን ቅድመ ዝግጅት እና አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ነገ ቅዳሜ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ተወካይ ዋና ዳይሬክተር በኩል መግለጫ ይሰጣል።

የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጥሪ ተደረገላቸው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፥ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ በዛሬው ዕለት ጥሪ አቀረበ።
የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው ጥሪ ፥ " በሀገራችን እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራን በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ሃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስዋፅኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል " ብሏል።
በዚሁ መሠረት ይህን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ - አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀትና ልምድ ያላቸውን አባላት የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት የሀገር መከላከያን እንዲቀላቀሉ ለቀረበው ጥሪ ሊያሟሉ ይገባቸዋል የተባሉት አጠቃላይ መስፈርቶች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

#Update ትምህርት ሚኒስቴር ፦ • በመቐለ ፣ • በዓዲግራት፣ • በአክሱም ፣ • በራያ እና በወልድያ ዩኒቨርስቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን በሙሉ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጊዜያዊ ምደባ ለመመደብ እንዲያስችል መምህራን በሚከተለው ሊንክ https://forms.gle/uEmVwqqDFQ7dFk5dA ተጠቅመው ከነገ ጀምሮ እስከ እሮብ 24/2/2014 ዓ.ም እንዲመዘገቡ መልዕክት አስተላልፏል። @tikvahethiopia
የመምህራን ምደባ በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል።
በመቐለ ፣ ዓዲግራት ፣ አክሱም ፣ ራያ እንዲሁም ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል።
መምህራኑ የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የኦንላይን አድራሻ አማካኝነት ምዝገባቸውን ከጥቅምት 22 እስከ 24/2014 ዓ.ም አድርገዋል፡፡
መምህራኑን በጊዚያዊነት ለመመደብ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
የመምህራኑ ጊዚያዊ ምደባ በቀጣይ ሳምንት ይፋ ሊደረግ እንደሚችልም ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በተገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።
More : @tikvahuniversity

#NEBE
በመላው ሀገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ማቋረጡን (suspend) አሳውቋል።
ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ መሆኑ ይታወቃል። በቢኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ በታህሳስ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ ነበር።
የኢ.ፌዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትላንትና ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ማጽደቁን ተቀትሎ ቦርዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ (suspend) መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

" አንድም አማፂያን አላየሁም " - ጋዜጠኛ ዳንኤል ሉቱያ
የዩጋንዳው ታዋቂ ጋዜጠኛ ዳንኤል ሉቱያ #ኢትዮጵያ ይገኛል።
ጋዜጠኛው በረራ ከማድረጉ በፊት CNN እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ሲከታተል እንደነበር ገልጿል፤ በዚህም ወደ ጦርነት ቀጠና የሚሄድ መስሎት እንደነበር በይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ ፅፏል።
ትላንት አዲስ አበባ አሁን ደግሞ አዳማ እንደሚገኝ የሚገልፀው ጋዜጠኛው በሄደበት ቦታ ምንም ነገር እንደሌለ ገልጿል። "የጥይት ድምፅ የለም፤ ውጥረት የለም፣ ባር ቤቶች ክፍት ናቸው ፣የተዘጋም መንገድ የለም" ብሏል።
እንደውም ካምፓላ ውስጥ ከአዲስ አበባ የሚበልጥ ወታደር እንዳለ ጠቁሟል።
ጋዜጠኛው ከከተማዋ 90 ኪሎ ሜትር ድረስ ርቆ መሄዱን ጠቁሞ ትላንት CNN ከተማዋ በአማፂያን ተከባለች ቢልም አንድም አማፂያን በመንገዱ እንዳላየ ፅፏል።
ከሰሞኑን በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በተቀናጀ ሁኔታ በሚመስል መልኩ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ካሉበት ሆነው ዘገባዎችን እያወጡ ሲሆን አዲስ አበባ ተከባለች የሚለው ሀሰተኛና የሽብር ወሬ ዋነኛው ነበር።