በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር አካባቢዎች የእንስሳት ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኬንያ እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች የእንስሳት ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን አሳውቋል።
ለክትባት ዘመቻው ድጋፍ ያደረገው የክፍለ አህጉራዊ የአርብቶአደር ኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት (RPLRP) መሆኑ የተገለፀ ሲሆን እኤአ ከ2018 ጀምሮ 8 ሚሊዮን እንስሳትን እንዲከተቡ በማድረግ ረገድ 300 ሺህ አባወራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ አድርጓጋ።
የክትባት ዘመቻው ዛሬ በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ የተለያዩ እንስሳትን በመከተብ የተጀመረ ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ በኬንያ በኩል እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

#HappeningNow : የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት 2ኛ ዙር የጸረ ሽምቅ ፖሊስ በባምባሲ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እያስመረቀ ይገኛል።
Photo Credit : BGMMA
@tikvahethiopia
Photo Credit : BGMMA
@tikvahethiopia
#Sudan : ሱዳን በወረራ በያዘችው በኢትዮጵያ ግዛት ስር በነበረው " አልፋሽቃ " ከ25 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ142 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ሰበሰብኩ አለች።
ይህ አካባቢ ሱዳን ባሳለፍነው ዓመት በወረራ መያዟ ይታወቃል።
በምስራቅ ሱዳን የሚገኘው የገዳሪፍ ክልል የግብርና ቢሮ ተጠባባቂ ሚኒስትር አህመድ ሃሳ አሎባ በሰጡት መግለጫ፤ “ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት አልፋሽቃ ስኬታማ የግብርና ስራ አከናውናለች” ብለዋል።
“በአሁኑ የእርሻ ወቅት በአልፋሽቃ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር አልነበረም” ያሉት አህመድ ሃሳ አሎባ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ ምክንያት የእርሻ ስራው የፀጥታ ስጋት ባለባቸው ስፍራዎች በሀገሪቱ ታጣቂ ሀይሎች መከናወኑንም አስታውቀዋል።
በዘንድሮው የእርሻ ወቅት በአልፋሽቃ በ142 ሺ 800 ሄክታር መሬት ላይ በተከናወነው ስራ ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ እና ማሽላ በስፋት መመረቱን ያስታወቁት ተጠባባቂ ሚኒስትሩ፤ የሱፍ አበባን ጨምሮ ሌሎችም የቅባት እህሎች መሰብሰባቸውን ገልፀዋል።
አልፋሽቃ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ግዛት ስር የነበረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የተለያዩ የእርሻ ስራዎችን ሲያከናውኑበት ነበረ።
ይህን አካባቢ ካለፈው አመት አንስቶ የሱዳን ጦር በወረራ ይዞታል።
ኢትዮጵያ የሱዳን ጦር ከያዛቸው ሉዓላዊ የኢትዮጵያ መሬቶች ለቆ እንዲወጣ እና ከአሁን ቀደም የተጀመሩ ድርድሮች እንዲቀጥሉ፤ በእነዚህ አካባቢዎች ድልድይና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መገንባቱን እንዲያቆም ጭምር አሳስባ እንደነበር አይዘነጋም።
Credit : አል ዓይን

TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle : በትግራይ ክልል መዲና መቐለ ዛሬ ጥዋት የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ የክልሉን ቴሌቪዥን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስም በመቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን የረድኤት ተቋማት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የዛሬ ጥዋቱ ጥቃት በዚህ ሳምንት ሁለተኛው ነው ተብሏል። የጥዋቱ የአየር ድብዳ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ በተባለው ተቋም ኢላማ ያደረገ እንደነበርም ተሰምቷል።…
#Mekelle : በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን ሮይተርስ ዘግቧል።
የዛሬው ጥቃት በአራት ቀናት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተፈፀመ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐሙስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠዋል።
የዛሬው የአየር ድብደባ ኢላማ ያደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዞታ የነበረ (ሰሜን ዕዝ)ና በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር /TPLF/ የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን ዶ/ር ለገሰ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ዶክተር ለገሰ ፥ የአየር ድብደባው የተፈፀመው በወታደራዊ ስፍራ ስለሆነ ምንም የሲቪሎች ጉዳት አልደረሰም ብለዋል።
የዛሬው ጥቃት ከሰዓት ከ9 ሰዓት በኋላ የተፈጸመ መሆኑን ተገልጿል።

Photo
#Update
የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን እና የጋና ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ ኦርላዶ ስታዲየም እንዲካሄድ #ኢትዮጵያ መርጣለች።
የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ከታገደ በኋላ ኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሀገር ውጭ ለማድረግ በመገደዱ፤ የኢ.እ.ፌ በአማራጭነት ኬንያ፣ ዚምቧቤን እና ደቡብ አፍሪካን መርጧል።
ሶስቱም ሀገራት ይህንን ጨዋታ ለማስተናገድ ፈቃደኝነታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የዚምቧቤ ስታዲየም የዚምቧቤን እና የኢትዮጵያን ጨዋታ ብቻ እንዲያስተናግድ በገደብ የተፈቀደለት እንጂ ሌላ ጨዋታ ማካሄድ እንደማይችል ካፍ በማረጋገጡ፤ ኬንያ ፈቃደኝነቷን የገለጸች ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዚምቧቤ ለመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታው ማቅናቱ ስለማይቀር፤ በአንድ የአውሮፕላን ጉዞ እና መጠነኛ ወጪ ጨዋታውን በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ወስኗል።
በመሆኑም ጨዋታው ፊፋ በሚያስቀምጠው ቀን በደቡብ አፍሪካ ኦርላዶ ስታዲየም ለማድረግ የኢ.እ.ፌ ከደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተስማምቷል።
Credit : EFF

ዛሬ 3ኛው ዙር ከፍተኛ የፌደራል ግብር ከፋዮች የእውቅና ስነስርዓት ጠ/ሚ ዶ/ት ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተከናውኗል።
ስነ ስርዓቱ በአንድነት ፓርክ የተከናወነው ሲሆን የአሠራር ሂደታቸውን ኃላፊነት በተሞላው መንገድ ላከናወኑ እና በወቅቱ ግብር ለከፈሉ 300 የንግድ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
እውቅና የተሰጣቸው አካላት ብዛት ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር በ100 ብልጫን ማሳየቱ አበረታች መሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪ ፦
• ኸርበርግ ሮስ ኃ.የተ.የግ.ማ፣
• አርዱነጃ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ፣
• አፐር ናይል ትሬዲንግ የተሰኙት 3 ተቋማት ኃላፊዎች ሙስናን በማጋለጥ ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
ይህ ዓመታዊ የእውቅና መርኃ ግብር መላው የንግድ ማኅበረሰብ ሕግን አክብሮ ሁሉን የሚጠቅም ሥራን እንዲከውን ለማበረታታት የታለመ መሆኑን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#NewsAlert : የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሹመት መስጠቱን አሳወቀ።
የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን ፥ ዛሬ የተሰጠው ሹመት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ ሙሉ በሙሉ ተካሂዶ መንግስት እስኪመሰረት ድረስ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።
በዚህም መሰረት ፦
- ከቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤህነን) አቶ አብዱሠላም ሸንገል የክልሉ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ፣
- ከቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ቦዴፓ) አቶ አመንቴ ገሺ የክልሉ መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪ ፦
-ከቤህነን ፓርቲ አቶ መርቀኔ አዙቤር የክልሉ ዳያስፖራ ጽህፈት ቤት ሃላፊ እና አቶ መሃመድ እስማኤል ደግሞ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ፣
- ከቦዴፓ ፓርቲ አቶ መልካሙ ጅራ የመተከል ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
Credit : ENA

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 29 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,340 የላብራቶሪ ምርመራ 524 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 518 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

" የሰላም ፍኖተ ካርታ "
አዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ፎኖተ ካርታ እንደሚኖረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አሳውቀዋል።
ይህን ያሳወቁት ዛሬ በነበራቸው ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
አምባሳደር ዲና ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት በህገወጥ መንገድ ፣ በትጥቅ ትግል፣ በጠብመንጃ ችግር እየፈታለሁ ከሚሉ ኃይሎች ውጪ ያለው ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነው፤ ከዚህ በፊትም ይህንን ገልጿል" ሲሉ ተናግረዋል።
አምባሳደር ዲና ፥ አዲሱ መንግስት በዚህ ጉዳይ እየሰራበት እንደሆነ ይህም በቀርቡ እንደሚታወቅ ነገር ግን አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

#ETHIOPIA
ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች አጥኚ እና ተመራማሪ ናቸው።
በተጨማሪ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፀጥታ ተቋማትን በፀጥታ አመራር ተጠያቂነት እና በብሄራዊ ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሰጡ ባለሞያ ናቸው።
በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በደቡብ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ሱማሊያ እና ኢትዮጵያ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የጥናት ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በዚህ ምክንያት ቀጠናውን በተለይ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመረዳት እድል የሰጣቸው ሰው ናቸው።
ከሰሞኑን ከቪኦኤ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ በተለይ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፕሮፌሰሯ ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና ለኢትዮጵያ ቀውስ በአብዛኛው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን በቃለምልልሳቸው ወቅት ፦
- በሰሜን ኢትዮጵያ ትርክትን ለመቆጣጠር የሚደረግ የመረጃ ጦርነት፣
- በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር፣
- የኢትዮጵያ አዲስ መንግስት ለሀገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋት እና ለውጭ ግንኙነት ሊያመጣ ስለሚችለው ለውጥ፣
- በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እና በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኩል ተፈፀመዋል ስላሉት የፖለቲካ ስሌት ስህተት፣
- አምና ጥቅምት ወር የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት (ሰሜን ዕዝ) ላይ ስለፈፀመው ጥቃትና ኢትዮጵያ መንግስት ስለወሰደው እርምጃ፣
- የሰሜኑ ጦርነት እና የማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃዎች ተፅእኖ ፣
- ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ሁኔታ የክልል ልዩ ኃይሎች ያላቸው ድርሻ፣
- ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ እንድትወጣ ሊደረግ ስለሚገበው ጉዳይም ፕሮፌሰሯ አብራርተዋል።
ከሰሞኑን ቪኦኤ ከፕ/ር አን ፊትዝዠራልድ በተጨማሪ የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትን ዴቪድ ሺን ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን እሳቸውም በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
መልካም ንባብ 👇
https://telegra.ph/VOA-10-21

Telegraph
VOA
Professor Abb Fitz-Gerald ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች አጥኚ እና ተመራማሪ ናቸው። በተጨማሪ ለበርካታ አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ የፀጥታ ተቋማትን በፀጥታ አመራር ተጠያቂነት እና በብሄራዊ ደህንነት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሰጡ ባለሞያ ናቸው። በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን በደቡብ…