TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia : ኢሰመኮ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደህንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚሳስብ ነው ብሏል። በዚሁ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 /2014 ዓ/ም በደረሱ ሶስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። መስከረም 8 ቀን 2014 ደግሞ በውልማይ ቀበሌ በተፈፀመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ከነዋሪዎች ሪፖርት እንደደረሰው…
" በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ የሲቪል ሰዎችን ደህንነት ለማስከበር በቂ የፀጥታ ኃይሎች በቋሚነት ሊሰማሩ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በመስፋፋት ላይ በመሆናቸውና ባሕሪያቸውን እየቀየሩ ብሔር ተኮር ወደ ሆነ የእርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ የሚችል በመሆኑ፣ መንግስት በቂ የፀጥታ ኃይሎችን በአፋጣኝና በቋሚነት በአካባቢው ሊያሰማራ እንደሚገባ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 21 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 21 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,743 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 248 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 601 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት መፈፀሙን በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ መዘገቡን ሮይተርስ በድረገፁ አስነብቧል። ሮይተርስ ፤ በTPLF ቁጥጥር ስር ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን ሪፖርት እንዳደረገው በአየር ጥቃቱ በርካታ ሲቪሎች እንደተጎዱ ገልጿል ብሏል። የክልሉ ቴሌቪዥን 3 ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ10 በላይ ደግሞ መቁሰላቸው ዘግቧል። የመጀመሪያው ድብደባ…
#Mekelle : ዛሬ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ የአየር ጥቃት እንደነበር መገለፁ ይታወሳል።

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ኃላፊ አቶ አበበ ሃብቱ ለጀርመን ሬድዮ ማምሻውን በሰጡት ቃል በዛሬው ሁለት ጥቃት 8 ተጎጂዎች ወደሆስፒታሉ እንደመጡ ሁለት ህፃናትም እንደሞቱ ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ፤ በሞሶቦ አሬና በነበረው ጥቃት 2 እድሜያቸው 12 እና 14 የሆኑ ልጆች ሞተው ወደሆስፒታል እንደመጡ ፤ አንድ ሰው ደግሞ ወደ ድንገተኛ ክፍል መግባቱን አስረድተዋል።

በሁለተኛው ጥቃት ከፕላኔት ጀርባ ከ5 በላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደሆስፒታሉ እንደመጡና ድንገተኛ ህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ከዛሬው የአውሮፕላን ጥቃት በኃላ በመቐለ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ ነው የዋለው።

ዛሬ ከሰዓት ላይ ጥቃቱን መፈፀሙን በተመለከተ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተጠይቀው ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ "መንግሥት ለምን የራሱን ከተማ ያጠቃል? መቐለ የኢትዮጵያ ከተማ ነች" ሲሉ መልሰው ነበር።

ማምሻውን ደግሞ የኢፌዲሪ አየር ሃይል በመቐለ ህወሃት ሲጠቀምባቸው በነበሩ የመገናኛ አውታሮችና መሳሪያዎች ላይ የተሳካ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

እንደኢፕድ ዘገባ አየር ኃይሉ የወሰደው እርምጃ የፈደራል መንግስት ይዞታ በነበሩና ህወሓት አገር ለማፍረስ እየተጠቀመባቸው በቆዩ ይዞታዎች ላይ መሆኑ ገልጿል።

የአየር ድብደባው እንደ ፋና በመሰሉ የሚዲያና የኢንሳ ታወሮች እና መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበረና ተልዕኮውም በስኬት መጠናቀቁን ኢፕድ ዘግቧል።

ኢፕድ የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ይህም በተሳካ ሁኔታ መፈፀሙን ገልጿል።

@tikvahethiopia
ዛሬ ማምሻውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ TPLF በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመሸፈን ጩኸቱን ቀጥሎበታል ብሏል።

TPLF በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸም በዜጎች ላይ ከፍተኛ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቡድኑ በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች በግፍ መግደሉን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

TPLF እያደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግድያ እንዳይታወቅበት ለመሸፋፈን የተለመደውን "የተኩላ ጩኸት ቀጥሎበታል" ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ የህወሓት ቡድን በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉና የሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን አመላክቷል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በTPLF የሐሰት መረጃ ሳይወናበድ በሰሜን ወሎ፣ በጎንደር በዋግ ህምራ እና በአፋር ክልሎች የዜጎችን ጉዳት ሊመለከት እንደሚገባ መንግስት ጥሪ ያቀርባል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካንና አጋሮቿ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ሚዛናዊ ያልሆነ አቋም ዳግም እንዲመለከቱት መጠየቁን እንዲሁም የአውሮፓ ፓርላማ ያወጣው መግለጫ ከእውነታው የራቀ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስፍሯል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከትግራይ የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ ያገኛሉ" - የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከ150 በላይ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በማቅናት ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ይሁን እንጂ "ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ" የተማሪዎቹ ተወካዮች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል። በመቀጠልም በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር…
ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎች ምደባ ሊሰጣቸው ነው።

ከክልሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ ለመስጠት የትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ እንደሚገኝ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ነገ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

More : https://yangx.top/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎች ምደባ ሊሰጣቸው ነው። ከክልሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች እና ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ ለመስጠት የትምህርት ሚኒስቴር እየሰራ እንደሚገኝ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ነገ የምናደርሳችሁ ይሆናል። More : https://yangx.top/joincha…
#Update

በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርትቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከ ዛሬ 09/02/21014 ዓ.ም እስከ 12/02/2014 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ለመመዝገብ https://forms.gle/wYpZtTqpdQ417Bxx8 በመጠቀም የተቀመጠውን ፎርም እንዲሞሉ እና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ታግዷል።

የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች #እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አሳውቋል።

የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የካፍ የስታዲየም መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን እዲያስተናግድ መደረጉ ይታወሳል።

የተለያዩ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ስታዲየም ከዚህ በኋላ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን እና ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮችን እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ በትናንትናው እለት ጥቅምት 7/2014ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

በደብዳቤውም ላይ ከኦክቶበር 20 በፊት ኢትዮጵያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ጋር የምታደርገውን ጨዋታ በማን ሀገር በየትኛው ስታዲየም ለመጫወት እንደምትመርጥ ለካፍ በአስቸኳይ እንድታሳውቅ ካፍ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ካፍ ጨዋታውን ወደ ተጋጣሚዋ ሀገር እንደሚወስድ አሳውቋል ።

ለመታገዱ ምክንያት ምንድነው ? ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ታግዷል። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች #እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አሳውቋል። የባህር ዳር ብሔራዊ ስታዲየም የካፍ የስታዲየም መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን እዲያስተናግድ መደረጉ ይታወሳል። የተለያዩ የብሔራዊ…
#Hawassa #Jimma #AbebeBikela

ካፍ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መሟላት ካለበት መስፈርት አንጻር በርካታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ አሳውቋል።

ስታዲየሙ ለወደፊት የተጓደሉትን ነገሮች ካሟላ ወደፊት የካፍ የገምጋሚ ቡድን በመምጣት ጨዋታ ማስተናገድ ይችል እንደሆነ ይመልከተዋል።

ይህ እስካልሆነ ድረስ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም የኢንተርናሽናል ውድድር ማስተናገድ እንደማይል ተገልጿል።

የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በእድሜ ደረጃ ሚዘጋጁ ውድድሮችን እና የሴት የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በጊዚያዊነት ማስተናገድ እንደሚችል ካፍ አሳውቋል።

የካፍ ማረጋገጫ ደብዳቤውም በአጭር ቀናት ውስጥ ይላካል ተብሎ ይጠበቃል።

የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየምን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በኢ.እ.ፌ ክለብ ላይሰንሲግ የተገመገመ እና ሪፖርቱ የደረሰው ካፍ መጫወቻ ሳሩ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ሜዳው አጠገብ ያለው መሮጫ መም በምርጫ መም እንዲሰፍን ወይም በሳር ሙሉ በሙሉ እንዲሸፈን ከዚህ ቀደም የገለፀ ሲሆን መልበሻ ክፍሎቹ በአዲስ መልክ ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

Credit : EEF
Photo : File

@tikvahethiopia
#WolaitaSodo : የዎላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዎላይታ ጉታራ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም አድስ መንግስት ምሥረታ በዞኑ የሚካሄድ ሲሆን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የሌሎች የመንግሰት ኃላፊነት ሹመት ይፀድቃል።

@tikvahethiopia
#GamoZone : አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የጋሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር መረሀ ግብር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤው አቶ ብርሃኑ ዘውዴን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱን ተከትሎ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#Awi : አቶ እንግዳ ደኛው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ።

ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 22ኛ መደበኛ ጉባዔ አቶ እንግዳ ደኛው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ በላይነህ የኔሰው ደግሞ ምክትል አስተዳዳሪ እና የገጠር መሬት አስተዳደር መምሪያ ኃለፊ ሆነው ተሹመዋል።

መረጃው የአዊ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ኢብራሂም ኡስማን የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህን የሶማሊ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። አቶ ኢብራሂም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል። Photo Credit : SMMA @tikvahethiopia
#SomaliRegion : የሶማሊ ክልል ም/ቤት ሁለተኛ ቀን ውሎውን እያካሄደ ይገኛል።

ትላንት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ፣ አፈጉባኤ እና የምክትል አፈጉባኤ ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል።

በመቀጠልም 2 የኦብነግ (ONLF) አባላት ያሉበት 27 የክልሉ ስራ አፅፈፃሚ አካላት ሹመት ፀድቆ ነበር።

በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎ ምክር ቤቱ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ አቅራቢነት የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

* አጠቃላይ በሶማሊ ክልል ምክር ቤት የፀደቁ ሹመቶች ከላይ ተያይዟል።

Credit : Somali Communication & SMMA

@tikvahethiopia
#Gambella : ትላንት በጋምቤላ ከተማ በ2 ባጃጅ ውስጥ አንድ የቡድን መሳሪያ (ላውንቸር)፣ አንድ ክላሽንኮቭ፣ 76 የዲሽቃ ጥይትና 705 የክላሽንኮቭ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳውቋል።

የተያዙት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ከጋምቤላ ከተማ 01 ቀበሌ ወደ 03 ቀበሌ ሲዘዋወር መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የጦር መሳሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው ተብሏል።

አዘዋዋሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ በበኩሉ ፥ " ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለኦነግ ሸኔ ተላላኪዎች በተለይም ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ ለሚጠራው ድርጅት ለማስተላለፍ ሲሞክር ነው የታያዘው" ብሏል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች "ላውንቸር" የቡድን መሳሪያ እንጂ በግለሰብ የሚያዝ እንዳልሆነ ፖሊስ አስረድቷል። ይህ መሳሪያ ምሽግ ለመስበር፣ ተሸከርካሪና ትልልቅ ህንፃዎችን ለማውደም የሚያገለግል ነው።

* በጋምቤላ ክልል ባለፉት 3 ወራት 61 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተገኘው መረጃ።

Credit : ጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia