TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
PHOTO: የወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ መደበኛ ስርጭት መጀመሩን አስመልክቶ ይፋዊ ስነ ስርዓት በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በስነስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ይህ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀደም ሲል ከኢመብባ ፍቃድ አግኝቶ የሙከራ ስርጭት ሲያካሂድ ነበር።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
ካቡል ኤርፖር ት አካባቢ ውጥረት ነግሷል። የ #ISIS የአፍጋኒስታን ቅርጫፉ ከአፍጋኒስታን የሚወጡ የአሜሪካ ዜጎች እና ሌሎችም ላይ ጥቃት ሊፈፅም ነው የሚል መረጃ በመገኘቱ በካቡል ኤርፖርት አካባቢ ውጥረት ነግሷል። ቀደም ብሎ ካቡል ኤርፖርት መግቢያ ባለው የደህንነት ስጋት ከአፍጋኒስታን ሊወጡ ወደካቡል ኤርፖርት የሚሄዱ ሰዎች አዲስ መመሪያ እስኪደርሳቸው ወደኤርፖርት እንይሄዱ መልዕክት ከአሜሪካ ኤምባሲ…
#TerrorThreat

ከቀናት በፊት በአፍጋኒስታን " ካቡል ኤርፖርት " አካባቢ ISIS የሽብር ጥቃት ሊያደርስ መሆኑን መረጃዎች መውጣታቸው ተከትሎ አካባቢው ላይ ውጥረት ስለመንገሱ ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል።

በወቅቱ የአሜሪካ ኤምባሲ የደህንነት ስጋት እንዳለ ተናግሮ ነገር ግን ስጋቱ ምን እንደሆነ ሳይጠቅስ ከአፍጋኒስታን የሚወጡ የአሜሪካ ዜጎች እና ሌሎችም ወደ አካባቢው እንዳይሄዱ አስጠንቅቆ ነበር።

አሁን ደግሞ በርካታ ሃገራት ካቡል አየር ማረፊያ የሽብር ጥቃት ሊኖር ስለሚችል ዜጎቻቸው ወደ አየር ማረፊያ እንዳይሄዱ አስጠንቅቀዋል።

አውስትራሊያ፣ አሜሪካ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ ከሰጡ መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ከአየር ማረፊያው ውጪ ያሉ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል።

የተለያዩ ሃገራት ከተቀመጠላቸው የነሃሴ 25 ቀነ ገደብ በፊት ዜጎቻቸውን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት እየተሯሯጡ ነው።

እስካሁን ባለው ሪፖርት መሰረት ከAugust 14 ጀምሮ 82,300 ሰዎች ከአፍጋኒስታን የወጡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 19,000 ማክሰኞ ዕለት ተው ከካቡል የወጡት።

ዛሬ በተገኘው መረጃ አሜሪካ አሁንም 1 ሺህ 500 የሚደርሱ ዜጎቿን ከአፍጋኒስታን አላስወጣችም።

መረጃው ከቢቢሲ፣ ሲኤን ኤን እንዲሁም ከቪኦኤ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#SUDAN

"...ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ በዘንድሮው ክረምት የደረሰብኝ የጎርፍ አደጋ የለም" - ሱዳን

የሱዳን የመስኖ እና ውሃ ሃብት ሚኒስትር ያሲር አባስ (ፕ/ር) ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ዘንድሮ ያጋጠማት የጎርፍ አደጋ እንደሌለ አስታወቁ፡፡

ፕ/ር ያሲር አባስ ኢትዮጵያ ግድብ እየገነባች ካለችበት የዓባይ ውሃ ይልቅ ዘንድሮ ነጭ ዓባይ ሱዳንን ለጎርፍ አደጋ አጋልጧታል ብለዋል፡፡

ይህ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት ታይቶ አይታወቅም ነው አባስ ያሉት፡፡

ክረምት በመጣ ጊዜ በቀን ወደ ሱዳን ይገባ የነበረው ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር መጠን ያለው የነጭ ዓባይ ውሃ ዘንድሮ በቀን ከ120-130 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

ሆኖም በተያዘው ክረምት ሊያጋጥም ይችል የነበረውን የጎርፍ አደጋ በሮዜሪዬስ እና ሜሮዔ ግድቦች የተያዘውን ውሃ በአግባቡ በመልቀቅ ለመቆጣጠር መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡን 2ኛ ዙር ሙሌት በተናጠል ከማከናወኗ ውጭ ክረምቱን ተከትሎ በሱዳን ካጋጠሙ የጎርፍ አደጋዎች ጋር የተያያዘ ተጽዕኖ እንደሌለው ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ከሙሌቱ በፊት መረጃን በወጉ ለመለዋወጥ አለመቻሉ ለቅድመ መከላከል ተግባራት ከፍተኛ ወጪ፣ ለተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ተጽዕኖዎች ዳርጎናልም ነው ፕ/ር ያሲር አባስ ያሉት፡፡

አባስ አል ፋው እና አል-ራሃድ በተሰኙ ከተሞች በእርሻ መሬቶች ጭምር የደረሰውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ የቀረቡ ሪፖርቶችን ገምግመናል፤ ተወያይተናልም ብለዋል፡፡

ሱዳን ከሙሌቱ በፊት የመረጃ ልውውጥ አልነበረም ትበል እንጂ ኢትዮጵያ ግን ሙሌቱን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎችን ልኬያለሁ ስትል ከአሁን ቀደም ማስታወቋ የሚታወስ ነው፡፡

የመረጃ ባለቤት ፡ #አል_አይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምስራቅ_ወለጋ ከነሃሴ 12 ቀን 2013 አንስቶ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃትና ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች እና የዞኑ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። ስማቸ እንዳይገለጽ የፈለጉ ነዋሪ ፤ በአካባቢው በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው "ሸኔ" የተሰኘው ቡድን ታጣቂዎች ቀደም ብሎ እንደሚንቀሳቀሱ አስታውሰው፤ በነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት…
#ምስራቅ_ወለጋ : "የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል" - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮምያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ ኪራሙ ወረዳ ነሃሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በአካባቢው ተሰማርተው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሌላ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ፣ ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. የ”ኦነግ ሸኔ” ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ማድረሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገለፀ።

ነሃሴ 12/2013 ዓ.ም. በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ሰዎች እንዳስረዱት ኮሚሽኑ አሳውቋል።

በዚህ የተነሳ ሌላው የወረዳው ነዋሪዎች፣ በተለይ ሴቶችና ሕጻናት ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሸሻቸውንና በቀጣይ ቀናት ከነዋሪዎች የተውጣጡ ሰዎች ብሔርን መሰረት ያደረገ የአጸፋ ጥቃት በማድረሳቸው 60 ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎችም ወደ አማራ ክልልና ወደ ኪራሙ ከተማ መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ወደ አከባቢው በመመለሳቸው ጊዳ ኪራሙ ወረዳ የተረጋጋ መሆኑን ነዋሪዎች ያስረዱ ቢሆንም በጊዳ ኪራሙና በሌሎች አጎራባች ወረዳዎች አሁንም ድረስ የፀጥታ ስጋት አለ ብሏል።

ኢሰመኮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ክትትሌን ቀጥላለሁ ያለ ሲሆን ፥ የአካባቢው ፀጥታ የደረሰበት አስጊ ደረጃ ወደ አጎራባች አካባቢዎች እንዳይዛመትና የበለጠ ሰብአዊ ቀውስ እንዳያደርስ አስቸኳይ እርምጃ አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#EMA

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ትላንት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ "አሸባሪዎችን ከእነአስተሳሰባቸው ቀብረን ኢትዮዽያን እናስቀጥላለን" በሚል ርዕስ ያሰፈሩትን ጹሑፍ ተንተርሶ አዲስ ስታንደርድ ሚዲያ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉመው በዋና ዳይሬክተሩ ያልተባለ እና ከፍተኛ የደኅንነት አንድምታ ያለው መልዕክት ጨምሮ መዘገቡን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ለጃክሊን ፐብሊኬሽን (አዲስ ስታንዳርድ) በጻፈው ደብዳቤ

''...ነውረኛ ድርጊቶች እንኳን ሊገስፁ ቀርቶ እንዲያውም ቀለብ ከመስፈር ጀምሮ የህክምና መድሀኒቶችና የመገናኛ መሳሪያዎችን እያመቻቹ መገኘታቸው ሳያንስ መንግስትን ሲተቹ፤ ሲጎነትሉና ሲያስፈራሩ ማየት ልብን ያደማል፤ ጨጏራ ይመልጣል፤ ቆሽትን ያሳርራል።'' የሚለውን የዋና ዳይሬክተሩን ጹሑፍ

“Let alone condemning, these countries are helping the T.P.L.F. including feeding it, providing medicine, communication equipment and providing arms ” በሚል መተርጎሙ ሀሰተኛ ያልተባለና የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ያነሳል።

ባለሥልጣኑ ሚዲያው አንባቢውን እና የደኅንነት ተቋሙን ይቅርታ እንዲጠይቅና ለፈጸመው ከባድ ጥፋትም በአስቸኳይ እርማት እንዲያደርግ ያዛል።

አዲስ ስታንደርድ በድረገጹ ላይ ዘገባው ላይ ለነበረው የትርጉም ስህተት በኤዲተሮቹ በኩል ይቅርታ ጠይቋል።

ስህተቱ ''በትርጉም ወቅት የተፈጸመ ስህተት መሆኑን እና የዋና ዳይሬክተሩን መግለጫ በተሳሳተ መንገድ ለማቅረብ የተደረገ ሙከራ አለመሆኑን ለአንባቢዎቻችን ማረጋገጥ እንፈልጋለን'' ብሏል።

telegra.ph/EBA-08-26

@tikvahethiopia
"...በግድ የለሽነት በሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ላይ የሚደረግ አሉታዊ ፍረጃ ተገቢ አይደለም" - ኢመብባ

በግድ የለሽነት በሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ላይ የሚደረግ አሉታዊ ፍረጃ ተገቢ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙህኃን ባለስልጣን አሳወቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በቅርቡ ከሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በህዝብና በንግድ መገናኛ ብዙኋን የተስተዋለው የዘገባ ሽፋን ሙያዊ መርኅን በበቂ ሁኔታ የማያሟላ ነው ሲል ገልጿል።

''በግድ የለሽነት በሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ላይ የሚደረግ አሉታዊ ፍረጃ ለተጎዱ ዜጎቻችን በትጋት ሰብዓዊ እርዳታ የሚሰጡ በርካቶችን የሚጎዳ ነው። የጅምላ ፍረጃው የማይገመት አደጋ የሚያስከትልም ነው። ሚዛናዊ የአዘጋገብ መርኅም አይደለም።'' ሲል መግለጫው ጠቅሷል።

የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎች በዜና አዘጋገባቸው ከስሜት ቆስቋሽ ዘገባ ተቆጥበው የላቀ ፍትሐዊና ሚዛናዊ አዘጋገብን ለማረጋገጥ ንቁና ጠንቃቃ እንዲሆኑ በሚያሳስበው በዚሁ የባለሥልጣኑ መግለጫ የግጭት ወቅት ዘገባ ከባድ ኃላፊነት የሚጠይቅ መሆኑን በመጥቀስ ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ጉዳት ለመቀነስ መሰራት እንዳለበት ጠቁሟል።

ከሰሞኑ የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት ባለማክበራቸው ምክንያት የተወሰኑ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በሚመለከተው አካል አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸውና መገናኛ ብዙኀንም ሁነቱን የተመለከቱ ዘገባዎችን መስራታቸውን ያስታወሰው ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ''የመገናኛ ብዙኃን በመረጃ ላይ ተመርኩዘው በተለያዩ አካላት ላይ ምርመራ በማካሄድ እና በማጋለጥ ስህተትን የመግለጥ የጋዜጠኝነት ሞያዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣታቸው ሙሉ ለሙሉ እውቅና እየሰጠ ያበረታታል'' ሲል አክሎ ገልጿል።

@tikvahethiopia
"...የእሳት ቃጠሎውን በቀላሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል" - አዲስ አበባ ፖሊስ

ዛሬ ነሀሴ 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ የአባላት ማረፊያ ክፍል ውስጥ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ነበር።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተነሳው ቃጠሎ መጠነኛ እንደነበር ገልጾ ፤ ቃጠሎውን በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና በፖሊስ አመራርና አባላት ትብብር በቀላሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል ሪፖርት አድርጓል።

የእሳቱ መነሻ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TerrorThreat ከቀናት በፊት በአፍጋኒስታን " ካቡል ኤርፖርት " አካባቢ ISIS የሽብር ጥቃት ሊያደርስ መሆኑን መረጃዎች መውጣታቸው ተከትሎ አካባቢው ላይ ውጥረት ስለመንገሱ ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል። በወቅቱ የአሜሪካ ኤምባሲ የደህንነት ስጋት እንዳለ ተናግሮ ነገር ግን ስጋቱ ምን እንደሆነ ሳይጠቅስ ከአፍጋኒስታን የሚወጡ የአሜሪካ ዜጎች እና ሌሎችም ወደ አካባቢው እንዳይሄዱ አስጠንቅቆ ነበር።…
#ካቡል

በአፍጋኒስታን ካቡል ኤርፖርት ውጭ ፍንዳታ ተከሰተ።

አሜሪካ፣ ዩናይትስ ኪንግደም፣ አውስትራሊያ ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ በሰጡ በሰዓታት ውስጥ በኤርፖርቱ በ "አቤይ መግቢያ" ውጭ በኩል ፍንዳታ ተከስቷል።

ሀገራቱ ጥቃት ሊፈፀም ስለሚችል ከኤርፖርት በውጭ በኩል ያሉ ሰዎች ከአካባቢው በአቸኳይ እንዲርቁ አስጠንቅቀው ነበር።

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ስለተከሰተው ፍንዳታ የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል፤ ፍንዳታ የቦንብ እንደሆነም ጠቁመዋል።

እስካሁን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ወይም እንደሞተ ተጨባጭ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ትላንትና ምሽት ላይ ወደኤርፖርት ለመግባት በአቤይ መግቢያ በኩል 5,000 የሚደርሱ አፍጋናውያን እንዲሁም ምናልባትም የተወሰኑ አሜሪካውያን እንደነበሩ ተነግሯል።

Photo Credit : Zee

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ካቡል በአፍጋኒስታን ካቡል ኤርፖርት ውጭ ፍንዳታ ተከሰተ። አሜሪካ፣ ዩናይትስ ኪንግደም፣ አውስትራሊያ ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ በሰጡ በሰዓታት ውስጥ በኤርፖርቱ በ "አቤይ መግቢያ" ውጭ በኩል ፍንዳታ ተከስቷል። ሀገራቱ ጥቃት ሊፈፀም ስለሚችል ከኤርፖርት በውጭ በኩል ያሉ ሰዎች ከአካባቢው በአቸኳይ እንዲርቁ አስጠንቅቀው ነበር። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ስለተከሰተው ፍንዳታ የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል፤…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update

አሁን ይፋ በሆነ ሪፖርት ከካቡል ኤርፖርት ውጭ በደረሰው ፍንዳታ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከጎጂዎቹ መካከል የአሜሪካ ሰዎች እንዳሉበት CNN ዘግቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቃላቸውን ለአልጀዚራ የሰጡ አንድ በታሊባን ቡድን ውስጥ በኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ግለሰብ ከ " ካቡል ኤርፖርት " ውጭ በደረሰው ፍንዳታ 11 ሰዎች (ህፃናት ልጆችን ጨምሮ) መገደላቸውን ሪፖርት አድርገዋል።

Video Credit : ASVAKA

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ የጦር ፍርድ ቤት በሀገር እና በሀገሪቱ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ባላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የተከሰሱበት ክስ ዋና ጭብጥ ምንድናቸው ?

- ከሀገር አፍራሽ አሸባሪዎች ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል፣
- ክህደት በመፈፀም ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሓት ቡድን ለመቀላቀል በማሴር፣
- ሽብርተኛ ተብሎ ለተፈረጀው የ "ሸኔ" ቡድን መረጃ ማቀበል፣
- ከግዳጅ ቀጠና በመሸሽ የወገን ጦርን ለአደጋ ማጋለጥ፣
- ያለ በቂ ምክንያት ሲቪሎችን በመግደል፣
- የበላይን ትዕዛዝ ችላ በማለት ለንፁሐን ሞት ምክንያት መሆን
- የመንግሥትና የህዝብን ወታደራዊ ንብረትን ይዞ ለመሸሽ ሙከራ ማድረግ የሚሉ ክሶች ዋነኛ ጭብጥ ሆነው ቀርቧል፡፡

ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ሲመረምር ቆይቶ ተከሳሾች እራሳቸውን መከላከል ባለመቻላው የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

1. ሻለቃ ክፍሌ ካሳይ በ17 አመት ፅኑ እስራት
2. ኮሎኔል ክፍሌ ፍሰሃዬ በ14 ከ 2 ወር ፅኑ እስራት
3. ሀምሳ አለቃ መብራቱ ጥላዬ በ18 አመት ፅኑ እስራት
4. መሰረታዊ ወታደር መኮንን ክንፈ በ13 አመት ፅኑ እስራት
5. ሀምሳ አለቃ ፈረደ ይባስ በ11 አመት እስራት
6. ምክትል አስር አለቃ ሀጎስ በርሄ በ11 አመት ፅኑ እስራት
7. ምክትል ክፍሌ ንጉስ በ9 አመት ፅኑ እስራት
8. ኮሎኔል ካሱ ሀብቱ በ11 አመት ከ2 ወር
9. ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋ በ8 አመት ፅኑ እስራት
10. ሌተናል ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ በ10 አመት ከ2 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወታደራዊ ፍ/ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

@tikvahethiopia