TIKVAH-ETHIOPIA
#GONDAR በጎንደር ከተማ ለቀድሞ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በስማቸው ጎዳና ተሰየመላቸው። መንገዱ ከማራኪ ማዞሪያ እስከ ሽንታ ድልድይ ያለው መሆኑ ተገልጿል። በሌላ በኩል ለክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በስማቸው ጎዳና ተሰይሞላቸዋል። በአሁን ሰዓት የጎዳና የመሰየም ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል። የተሰየመው ጎዳና ከኮሌጅ…
ፎቶ : በጎንደር ከተማ ለቀደሞው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ በስማቸው ጎዳና የመሰየም ስነስርዓት ተከናውኗል።
ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በር - ሽንታ ወንዝ ድልድይ ያለዉ የአስፓልት መንገድ ነው በኢ/ር ስመኘዉ በቀለ ስም የተሰየመው።
Photo Credit : ጎንደር ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopia

በአፋር ክልል የተፈናቀሉ 76 ሺ ዜጎች ...
የአፋር ክልል አደጋ መከላከል ቢሮ ህወሓት በአፋር በኩል በከፈተው ጥቃት ምክንያት 76 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለው እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አሳውቋል።
ተፈናቃዮቹ በአብዛኛው በአራት የአፋር ክልል ወረዳዎችና ከጭፍራ የተሰደዱ መሆናቸውን ተገልጿል።
ሰዎቹ በትንኮሳው ምክንያት ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ተበታትነው የነበሩ በመሆኑ በአፋጣኝ ዕርዳታ ለማድረስ አዳጋች አድርጎት እንደነበር ተነስቷል።
አሁን ላይ ተፈናቃዮቹን በ9 የመጠለያ ቦታዎች ማሰባሰብ በመቻሉ መንግሥት ለተፈናቃዮቹ ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ከመንግሥት ድጋፍ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች የበኩላቸውን እርዳታ ማቅረብ ጀምረዋል። ድጋፍ ማድረግ ከጀመሩ ተቋማት መካከል የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ተጠቃሽ ናቸው።

#ItsMyDam🇪🇹
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለግድቡ ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠናክሮ መቀጠሉን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ፅ/ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃይሉ አብረሃ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፥ በቅርቡ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ ታስቦ በተሰራው ዘመናዊ የሃብት ማሰባሰቢያ ሥርዓት (www.mygerd.com) አማካኝነት ከ132 ሺ ዶላር በላይ ተሰበብስቧል ብለዋል።
ገንዘቡ የተገኘው ከ1 ሺ 29 ለጋሾች መሆኑንም ገልፀዋል።
በድረገፁ ከሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ በተጨማሪም #የቴሌብር የሃብት ማስባሰቢያ ተከፍቶ እስካሁን 30 ሺ ብር መሰብሰቡን አቶ ኃይሉ አብርሃ ተናግረዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ15 ቢሊዮን 729 ሚሊዮን ብር በላይ ከሕዝቡ መሰብሰቡን ተጠቁሟል።
በሌላ መረጃ ፦ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ተሰብስቧል።
በ24 ሰዓት የተሰበሰብው 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በጎፈንድሚ በኩል ነው። ጎፈንድሚው በድር ኢትዮጵያ በኩል ከ1 ወር በፊት የተከፈተ መሆኑን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን 1,005,060 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል።

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,547 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 200 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አምስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 87 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

#Alert🚨
በኢትዮጵያ 3ኛው ዙር የኮቪድ-19 (3rd Wave) ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው።
በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት 3ኛው ዙር (3rd Wave) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል።
ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ነው። በሀገራችን የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር (3rd Wave) ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት ጀምሯል።
በአማካኝ በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንዲሁም ወደፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።
ሁለተኛው ዙር (2nd wave) ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ የታዩ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛ ዙር (3rd wave) ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ ፦
- እያንዳንዱ ግለሰብ ፣
- ቤተሰብ ፣
- ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣
- የሐይማኖት ተቋማት ፣
- ሲቪክ ማህበራት ፣
- አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣
- የጤና ባለሙያዎች ፣
- መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ማስክ ማድረግ ፣ የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከል እና መቆጣጠር ተግባር ላይ በባለቤትነትና በኃላፊነት ስሜት አጠናክረው እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ክፍል ሞላ።
በአሁኑ ሰዓት የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ፅኑ ህሙማን ክፍል በኮቪድ -19 ታማሚዎች መሙላቱን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።
ሁሉም ሰው እንዲጠነቀቅም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ ተነጋገሩ።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን "Turkish Presidency" በይፋዊ ትዊተር ገፁ አሳውቋል።
ሁለቱ መሪዎች በስልክ ባደረጉት ቆይታ የቱርክ-ኢትዮጵያ ግንኙነትን እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ቱርክ ለኢትዮጵያ መረጋጋት እና ሰላም ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ማንኛውንም ዓይነት (ሁሉን አቀፍ) ድጋፍ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

#Tokyo2020 🇪🇹 #ETHIOPIA
በ1,500 ሜትር ማጣሪያ በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊያኖቹ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ለምለም ሀይሉ ከ ምድባቸው አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ለግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።
በሶስተኛው ምድብ ተወዳድራ የነበረው አትሌት ድርቤ ወልተጂ 12ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
የ1,5000 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር በመጪው ረቡዕ ከቀኑ 7:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።
@tikvahethsport

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ሲፋን ሀሰን ከወደቀችበት ተነስታ ድል አደረገች።
ትላንት በተካሄደ የ1,500 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኔዘርላንዳዊቷ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ሲፋን ሀሰን በመጨረሻው ዙር ላይ ተጠልፋ ብትወድቅም ተነስታ ውድድሯን #አንደኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
በርካቶችንም በጥንካሬዋ እና ተስፋን ባለመቁረጧን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ እያሞጋገሷት ነው።
ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ ኦሎምፒክ በምትወዳደርባቸው የውድድር ዘርፎች ውጤት ታስመዘግባለች ተብለው ከሚጠበቁ የዓለማችን አትሌቶች ቅድሚያ የተሰጣት ናት።

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !
ዛሬ በቶኪዮ ኦሎምፒክ መላው የዓለም ህዝብ በጉጉት የሚጠብቃቸው ውድድሮች ይካሄዳሉ። ውድድሮቹ የወንዶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል እና የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ናቸው።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም በውድድሮቹ በእጅጉ ይጠበቃሉ።
ቀን 9:15 ላይ የወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ የሚጠበቁ አትሌቶቻችን ናቸው።
ቀን 9:40 ላይ ደግሞ የሴቶች 5,000 ሜትር ፍፃሜ ሲካሄድ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና እጅጋየሁ ታዬ ተጨማሪ ሜዳሊያ ለሀገራችን ለማስገኘት ይሮጣሉ ።
ድል ለሀገራችን !

ችሎት !
አቶ ስብሃት ነጋ ፣ ወ/ ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እንዲደርሳቸው ተደረገ፡፡
በማረሚያ ቤት የሚገኙት አንባሳደር አባይ ወልዱና ዶ/ር አስገዶም ተስፋዬ ስም ዝርዝራቸው ከመጥሪያው ጋር ተካቶ ስላልታዘዝኩ አላቀረብኳቸውም ሲል ማረሚያ ቤት ምላሽ የሰጠ ሲሆን 19 ኙ ተከሳሾች ግን በችሎት ተገኝተዋል፡፡
ያልቀረቡት ቀሪዎቹ እነ ዶ/ር ደብረፅዮን፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ጨምሮ 41 ተከሳሾችን ፖሊስ አፈላልጉ ለማቅረብ በትግራይ ክልል ካለው ፀጥታ ችግር አንፃር እንደሚቸገር መግለጹን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አብራርቷል፡፡
ነገር ግን በችሎት የተገኙ ተከሳሾች የመኖሪያ አድራሻቸውን፡ የትዳር ሁኔታቸውን እና የስራቸውን ደረጃ አጠቃላይ ማንነታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስመዝግበዋል፡፡
ጠበቆቻቸው ዘራይ ወልደሰንበትና ታደለ ገ/መድህን ክሱን ተመልክተን ተወያይተን ዋስትና ለመጠየቅ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ክሱ ሰፊ በመሆኑ እና ያልተሟላ የምስል ማስረጃ ባለመሟላቱ ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት እንደሚያስፈልግ አብራርቷል፡፡
በዚህም ዓቃቢህግ አሟልቶ ያለቀረበውን የምስል ማስረጃ ከቀጠሮ በፊት እንዲያቀርብ በማዘዝ ክሱን በችሎት ለማሰማት ለነሀሴ 11 ቀን 2013 ዓ /ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል፡፡
የመረጃ ባለቤት ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
@tikvahethiopoa

ፎቶ : የደቡብ ልዩ ኃይል ደንብ ልብስ ዛሬ በይፋ ተቀይሯል።
የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞው የደምብ ልብስ በይፋ ከዛሬ ጀምሮ ተቀይሯል።
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞውን የደንብ ልብስ መቀየር ያስፈለገው ጥራቱን ያልጠበቀና የልዩ ኃይሉን ክብር የማይመጥን በመሆኑ ነው ብሏል።
ደንብ ልብሱን ያመረተው ፋብሪካም ዩኒፎርሙ ከታለመለት ዓለማ ውጭ እንዲውል በማድረጉ መሆኑንም ገልጿል።
የደንብ ልብሱ ህገወጥ ሲከናወንበት እንደነበርም አክሏል።
አዲሱ የደንብ ልብስ ጥራቱን የጠበቀና የልዩ ኃይሉን ክብር የሚመጥን ከመሆኑንም በላይ የወንጀል ድርጊቶችን መከላከል የሚስያችል መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽ ገልጿል።
Photo Credit : SRTA

የወልዲያና አካባቢዋ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ማሳሰቢያ ተሰጣቸው።
"ስለወታደራዊ እንቅስቃሴ በዚህ ገቡ ወጡ" የሚል ጽሑፍ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚለቁ የወልድያና አካባቢዋ የፌስቡክ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
በብዕር ስምም ይሁን በተጸውኦ ስም የሚፅፉ ለወታደራዊ ስራው እንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ አስገንዝቧል።
ከተማ አስተዳደሩ "ስክሪን ሹት" በማድረግ ለሚመለከተው አካል ለማስረከብ መስራት ያለበትን ሥራ እየሰራን መሆኑ የገለፀ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን ማህበራዊ ሚዳያ ተጠቃሚዎች "ከድርጊታችሁ ታቀቡ" ሲል አሳስቧል።
የወልዲያ ወጣቶችም "አንታወቅም በሚል" በብዕር ስም የሚጽፉትን በማጋለጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።