የሰለሞን ባረጋ ድል !
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከአስራ ሶስት ዓመታት በኋላ በውድድር መድረኩ ለ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ማስገኘት ችሏል።
ኢትዮጵያ በርቀቱ በኦሎምፒክ ድል ማድረግ የቻለችው በ ቤጂንግ ኦሎምፒክ ላይ ነበር።
ሰለሞን ባረጋ በ ኦሎምፒኩ በግሉ የመጀመሪያውን ወርቅ አሳክቷል።
ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በ በላይነት ሲያጠናቅቅ የዓለም ሪከርድ ባለቤቱን ጆሽዋ ቼፕቲጌ አስከትሎ በመግባት ነው።
እንኳን ደስ አለን በድጋሚ 🇪🇹
@tikvahethsport

TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP #Tigray የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ትግራይ ውስጥ የሚያደርሰው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት በዚህ አርብ እንደሚያልቅበት ገለፁ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በትግራይ ውስጥ ሊመግብ ላሰባቸው ሰዎች ሁሉ ለመድረስ በቀን 100 የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልገው አንስተዋል። ባስሌይ ፥ "ለትግራይ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች…
"ወደ መቐለ የተንቀሳቀሰው የእርዳታ አቅርቦት በባሕር ላይ የውሃ ጠብታ ያህል ነው" - ክሌር ኔቪል
በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ግጭት ወደ ትግራይ መግባት ያልቻሉት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቐለ ጉዞ ጀምረዋል።
ይህን ያሳወቁት በኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኮምዩኒኬሽንስ ባለሙያ የሆኑት ክሌር ኔቪል ናቸው።
ኔቪል ለቢቢሲ በሰጡት ቃላቸው የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ ከ200 በላይ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ሰመራ ተነስተው ወደ ትግራይ መቐለ ጉዞ ጀምረዋል ብለዋል።
ምንም እንኳን ዛሬ ከ200 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች የእርዳታ አቅርቦት ይዘው ወደ ትግራይ ቢያቀኑም አሁንም ካለው ፍላጎት አንጻር አናሳ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ወደ መቐለ የተንቀሳቀሰው የእርዳታ አቅርቦት "በባሕር ላይ የውሃ ጠብታ ያህል ነው" ሲሉ ገልፀውታል።
ባለፈው ማክሰኞ ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊይ በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት ዛሬ ዓርብ ይጠናቀቃል ማለታቸው ይታወሳል።
በሌላ ከትግራይ ጋር በተያያዘ መረጃ በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ 100, 000 ሕጻናት ለሕይወታቸው ለሚያሰጋ የአልሚ ምግብ እጥረት ሊጋለጡ እንደሚችሉ UNICEF አስታውቋል።
ድርጅቱ ዛሬ አርብ ባወጣው መግለጫ በምግብ እጥረት ለከፋ ጉዳት ተጋልጠዋል የተባሉ ልጆች ቁጥር ከዓመታዊ የአማካይ አኃዝ በአስር እጥፍ ከፍ ያለ ነው ብሏል።
የሚያጠቡ እናቶች እና ነፍሰጡር ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ሲልም አሳውቋል። UNICEF በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ምግብ እና ሌሎች ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሴቶች እና ሕጻናት አስፈላጊውን ድጋፍ ማቅረብ እንዲቻል ያልተገደበ እንቅስቃሴ ሊፈቀድልን ይገባል ብሏል።
@tikvahethiopia

ቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት ሊሰጠው ነው። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የክብር ዶክትሬት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ አፀደቀ። ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል። ቴዲ አፍሮ ነገ ወደ ጎንደር በመሄድ ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን የሚቀበል ይሆናል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 24 በተለያዩ…
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነገ ተማሪዎቹን ያስመርቃል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 710 ተማሪዎች ነገ ቅድሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም የሚያስመርቅ ይሆናል።
ትላንት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት እንዲሰጥ ማፅደቁ አይዘነጋም።
ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት የሚቀበል ሲሆን ለዚህ ፕሮግራም ዛሬ ጎንደር ከተማ መግባቱ ታውቋል።
ቴዲ አፍሮ ጎንደር ሲገባ የዩንቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ፣ ም/ፕሬዝዳንት ፣ የከተማዋ ከንቲባ ሞላ መልካሙ እና የጎንደር የባሕል ማዕከል በጎንደር አየር ማረፊያ ተገኝተዉ አቀባበል አድርገውለታል።
ፎቶ ባለቤት ፡ ሞገስ መኮንን

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 7,114 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 395 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 33 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ለማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ ፦
1. የመረጃ ምንጩ ያለታወቁ ቀልብ የሚስቡ መረጃዎችን ሼር ከመድረግ ተቆጠቡ።
2. የሠራዊቱ ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ፣ የሚጓጓዙ የጦር መሳርያዎች አይነትና ብዛት ፣ የሎጂስቲክስ ድጋፍ እንቅስቃሴዎችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ሚዲያ አትለጥፉ ፤ ይህን የሚፈፅም ስትመለከቱ አስቆሙ፡፡ ፍቃደኛ ካልሆነ ለፀጥታ ሃይሎች ወዲያው ጠቁሙ።
3. በመንግስት በተወሰነው የተናጠል ተኩስ አቁም ወቅት የሚደረግ የጠላትን ትንኮሳ መከላከል ሥራ በማህበራዊ ሚዲያ አትለጥፉ።
4. አንዳንድ ዩ-ቲዩበሮች ለሽርፍራፊ ሳንቲም ብላችሁ " ሰበር ! ሰበር ! " እያላችሁ ምንጩ ያለታወቀና ያለተረጋገጠ አሉባልታ በመንዛት የወገናችሁንና የሀገራችሁን ጥቅም አሳልፋችሁ ለጠላት አትስጡ።
5. ወቅታዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት በታወቀ መንግስታዊ ወይም በሚመለከተው የመከላከያ ሃላፊ ወይም አዛዥ ያልተሰጠ መረጃ ከሆነ አትመኑ ፣ ሼርም አታድርጉ።
6. ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ በሰራዊቱ ግዳጅ አፈፃፀም እና በህዝቡ ሞራልና ስነ-ልቦና የበላይነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩና ጠላት ሆን ብሎ የሚለቃቸውን መረጃዎች ባለማሰራጨት ተባበሩ።
“FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት”
* ዝርዝር የማሳሰቢያው ሀሳብ ከላይ ተያይዟል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡
በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡
#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።
#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።
#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።
#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ
የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።
#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ
የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።
አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።
#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ
ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።
ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።
ምንጭ፦ ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ
@tikvahuniversity

"...ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት የመስጠት ምንም አይነት ሃሳብ የለንም" - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በመረጃው ዙሪያ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነትና ፓርትነርሺፕ ዳይሬክተር የሆኑትን ማንእንዳንተ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ጠይቋል።
"የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የሚያስባቸው ሰዎች አሉ። ገና በዕጩነት የቀረቡ ሰዎች አሉ፤ ይሁን እንጂ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዕጩዎቹ ዝርዝር ውስጥ የሉም" ብለዋል።
"በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወረው መረጃም #ሐሰት" መሆኑን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም ማስመረቁ ይታወሳል።
ሌላ ዙር የምረቃ ስነ ስርዐት በመስከረም 2014 ዓ.ም መጨረሻ ወይም ጥቅምት 2014 ዓ.ም መጀመሪያ ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ይቀላቀሉ : @tikvahuniversity

#Tokyo2020 🇪🇹 #ETHIOPIA
ሰለሞን ባረጋ ወርቁን አጥልቋል !
በትላንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወርቅ ያስገኘው ሰለሞን ባረጋ ከደቂቃዎች በፊት ከቀድሞው የኬንያ አትሌት እና ከአሁኑ የ ኬንያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፖል ቴርጋት ወርቁን ተረክቦ አጥልቋል።
ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከዓለም ሰላሳ ሰባተኛ ላይ ስትቀመጥ ከአፍሪካ በሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ ከደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ በመቀጠል ሶስተኛ ላይ ተቀምጣለች።
@tikvahethsport
ሰለሞን ባረጋ ወርቁን አጥልቋል !
በትላንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወርቅ ያስገኘው ሰለሞን ባረጋ ከደቂቃዎች በፊት ከቀድሞው የኬንያ አትሌት እና ከአሁኑ የ ኬንያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፖል ቴርጋት ወርቁን ተረክቦ አጥልቋል።
ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከዓለም ሰላሳ ሰባተኛ ላይ ስትቀመጥ ከአፍሪካ በሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ ከደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ በመቀጠል ሶስተኛ ላይ ተቀምጣለች።
@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። #ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡ #ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ የደብረ…
ፎቶ : አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ እና መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 6,574 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ፣ የክብር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ፣ የዩኒቨርሲቲው እና የፌዴራል መንግስት አመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።
በዛሬው ምረቃ ስነ ስርዓት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በዩኒቨርሲቲው የተበረከተለትን የክብር ዶክትሬት ተረክቧል ፤ ለታዳሚውም ንግግር አድርጓል።
የፎቶ ባለቤት ፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፣ የውሃ ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር