TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ሞጣ

ዛሬ "ሕብር እና ፍቅር ከሰባቱ ዋርካ ስር" በሚል መሪ ቃል በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አዘጋጅነት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ፣ የአብሮነት፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት መርሃ ግብር በሞጣ ሁለገብ ስታዲየም እየተካሄድ ነው።

ከ2 ቀናት በፊት "በፍቅር እንኖራለን፤ በአንድነት እንሻገራለን” በሚል መሪ ቃል የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች የይቅርታ መድረክ አካሂደዋል።

መረጃው የሞጣ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
እየተፈጠረ_ያለ_ችግር_ጋዜጣዊ_መግለጫ_18_09_13.pdf
964 KB
#እናት_ፓርቲ

እናት ፓርቲ በላከልን መግለጫ ፓርቲው በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ስር በሚገኙ ምርጫ ክልሎች በምርጫ ሂደት ፣ በዕጩዎች እና አባሎቹ ላይ እየደረሱ ነው ያላቸውን ችግሮች በዝርዝር አስረድቷል።

ደርሰዋል የተባሉት ችግሮች ፦
- ማስፈራርት፣
- በሽጉጥ የመግደል ሙከራ ማድረግ፣
- እስር ፣
- ዕጩዎች ላይ ክትትል የማድረግ ትእዛዝ መስጠት፣
- ባነር እና ማስታወቂያዎች መገንጠል፣
- በገጠር ቀበሌ ህዝብን እየሰበሰቡ የፓርቲው ስም እንዲጠፋ የማድረግ፣
- ስድብ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ናቸው።

ከእናት ፓርቲ የተላከልን መግለጫ እንደሚያስረዳው ፓርቲው አጋጠመኝ ያላቸው ችግሮች በአማራ ፣ በደቡብ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ነው።

* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ በPDF ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Shire የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል። የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል። ከእርዳታ…
"...የሲቪል ሰዎችን ደህንነትና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውንም አይነት ተግባራትን ያወግዛል" - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 16/2013 ጀምሮ በትግራይ ሽረ ከተማ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባቸው የመጠለያ ካምፖች ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ በርካታ ተፈናቃዮች ስላሉበት ሁኔታ ክትትል እያደረገ መሆኑ አሳውቋል።

መጠለያዎች መደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ያለውን የደህንነት ስጋት ሸሽተው የመጡ ሰዎች ብቸኛ የደህንነት ቦታዎች ሲሆኑ ፤ የሰብዓዊ አቅርቦት ፍላጎቱ አሁንም ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል ብሏል።

ኢሰመኮ በመጠለያዎቹ የሚወሰዱ ማናቸውም ህግ ማስከበር እርምጃዎችም ሆነ በመጠለያዎቹ ይገኛሉ ተብለው የሚታሰቡ ተጠርጣሪዎችን የመያዝ እርምጃ ተገቢውን የህግ ሂደት የተከተለ እና በመጠለያዎቹ ያሉ ተፈናቃዮችን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት አስገንዝቧል።

ኮሚሽኑ የሲቪል ሰዎችን ደህንነት እና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውም አይነት ተግባራት የሚያወግዝ መሆኑን በመግለፅ አፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በአፅንኦት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለአሜሪካ ሴኔት ምንድነው ያሉት ?

- ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀን ድርጅት (ሕወሃት)ን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

- የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዳይደርስ ጫና ያደረጉና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንደሚያቀርቡ መናገራቸውን ገልጸዋል፡፡

- እአአ ከ2005 ጀምሮ በተለያዩ 19 ጊዜያት ኢትዮጵያ እንደጎበኙና ኢትዮጵያን በደንብ እንደሚያውቋት ገልፀዋል ፤ ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የቆየች አገር ናት ብለዋል፡፡

- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ፣ የህዝቦች አንድነት እንዲጠናከርና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ቁርጠኝነት ያላቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

- ጠ/ሚኒስትሩ በአገሪቱ ሪፎርም በማድረግ የፖለቲካ እስረኞች ና ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ አድርገዋል ፤ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ስምምነት በማድረግ የማይቻል ሲመስለን የነበረውን ነገር እንደሚቻል አሳይተዋል ብለዋል።

- ጠ/ሚኒስትሩ በተወሰኑ ክልሎች ላይ ብቻ ትኩረት ሳያደርጉ አገርን በአንድነት ለመምራት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ለዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በበላይነት ሲዘውር የነበረው በሽብርተኛነት የተፈረጀ "ህወሓት" የበላይነቱን ላለማጣት ስለሚፈልግ ደስተኛ አልነበረም ብለዋል።

- ከኤርትራ ጋር በተደረገው የሰላም ድርድር ላይ "ህወሓት" ደስተኛ አልነበረም ፥ በአገሪቱ ሪፎርም ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኛ አልነበረም ብለዋል፡፡

- አሜሪካ በኢትዮጰያ ያለውን ሁኔታ በመረዳት በአገሪቱ ውስጥ ሰላም እንዲኖር መርዳት እንጂ፣ ማዕቀብ መጣል ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
2021.04.19_MUSE_REPORT.pdf
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EmmanuelMacron

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሩዋንዳ ይገኛሉ።

በ1994 ሩዋንዳ ውስጥ በነበረው አስከፊ የ "ዘር ጭፍጨፋ" ወቅት ፈረንሳይ 'ኃላፊነቷን' መወጣት አለመቻሏን/በጭፍጨፋው የነበራትን ሚና በይፋ እዉቅና ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንቱ እውቅናውን የሰጡት በኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ባደረጉት ንግግር ነው።

በወቅቱ የዘር ማጥፋት አገዛዝን ከመደገፍ አንስቶ ከጭፍጨፋው ጋር በተገናኘ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን ፈረንሳይ ችላ ብላ ነበር ብለዋል።

ፕሬዜዳትቱ ባደረጉት ንግግር ላይ ግልፅ እና ይፋዊ ይቅርታ አልጠየቁም።

ማክሮን ባሰሙት ንግግር ፥ ፈረንሳይ የዘር ጭፍጨፋው ተባባሪ አይደለችም ያሉ ሲሆን በወቅቱ ሀገሪቱ ለነበራት ኃላፊነት ፈረንሳይን ይቅር ሊሉ የሚችሉት ከአስከፊው ጭፍጨፋ የተረፉት ሩዋንዳውያን ናቸዉ ብለዋል።

የሩዋንዳው ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ የማክሮን ቃላቶች ከይቅርታም የበለጠ ዋጋ ያላቸው ነበሩ ሲሉ ገልፀዋል።

ከአንድ ወር በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀን ውስጥ ብቻ 800 ሺ ገደማ ቱትሲዎች በተጨፈጨፉበት የ1994ቱ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ፈረንሳይ የተባባሪነት ሚና እንደነበራት የሚያመለክት የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ወ/ሮ ኬሪያ ምስክርነታቸው ተነስቶ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የምስክርነት ጥበቃቸው ተነስቶ ዳግም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ።

ወ/ሮ ኬሪያ ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

የጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን እንደገለጹት፤ ወ/ሮ ኬሪያ ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት ተቀይረው ነበር ብለዋል።

ወ/ሮ ኬሪያ በጠቋሚዎችና ምስክሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 699 /2003 በገቡት ሥምምነት ዝርዝር የምስክርነት ቃላቸውን በፈቃዳቸው ሰጥተው ነበር።

በገዛ ፈቃዳቸው በጽሑፍና በሲዲ ምስክርነታቸውን ሰጥተው በኃላም በፍ/ቤት ውሳኔ ከእስር እንደተለቀቁና ጎን ለጎንም ለግለሰቧ አስፈላጊውን የምስክርነት ጥበቃ ሲደረግላቸው ነበር ብለዋል።

ይሁንና ወ/ሮ ኬሪያ ቆይተው ምስክር የመሆን ፍላጎት እንደሌላቸው እና ምስክርነት ሲሰጡ የቆዩት ተገደው እንደነበር በመግለፅ ምስክረነታቸው መቋረጡን አስረድተዋል።

በምስክሮች እና ጠቋሚዎች አዋጅ ቁጥር 699/2003 በአንቀፅ 11 መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚው ሥምምነቱንና ግዴታውን የማያከብር ከሆነ የጥበቃ ስምምነት ውሉ ስለሚቋረጥ አቃቤ ሕግም ለወ/ሮ ኬሪያ ምስክር በመሆናቸው ይሰጣቸው የነበረውን ጥበቃ ለማንሳት መገደዱን ነው የተናገሩት።

"ከዚህም በኋላ ወይዘሮ ኬሪያ ከዚህ ቀደም በተጠረጠሩበት ወንጀል የቅድመ ምርመራ ስራ እንዲጀመር አቃቤ ሕግ ዛሬ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል" ብለዋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በጉዳዩ ላይ ለመከራከር አልተዘጋጀንም ብለዋል።

ፍ/ቤቱ ወ/ሮ ኬሪያ በመጪው ሰኞ ዳግም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል።

ወ/ሮ ኬሪያ እስከ ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ መወሰኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬ ጠዋት ውሎው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትትን የመክፈቻ መልእክት ያዳመጠ ሲሆን፦ - ብጹዕ አቡነ ኤልያስ - ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ - ብጹዕ አቡነ ማርቆስ - ብጹዕ አቡነ አብርሃምን - ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ - ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ - ብጹዕ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የግንቦት 19/2013 ክንውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ፤ በመግለጫቸው ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል ፦

- በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የሰጠባቸውን 2 አጀንዳዎች ቃለ ጉባዔ ቀርቧል፡፡ በዚህም የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግር ቅዱስ ሲኖዶስ #አጽድቆታል፡፡

- ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሀገሪቱ በሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ስደትና መፈናቀል ዙርያ በሰፊው ተወያይቶ የመፍትሔ ሐሳብ የያዘ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ውሳኔው በዝርዝር በሚሰጠው መግለጫ ይገለፃል ብለዋል።

- የቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥፍራ የሆኑት የመስቀል እና የጥምቀት ቦታዎች አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩ የሚፈታበት ውሳኔ አሳልፏል፤ የውሳኔው ዝርዝር በአጠቃላይ መግለጫው ይቀርባል ብለዋል።

- በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት እደረሱ ያሉ ችግሮችን አስመልክቶ ሦስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ መርጧል፡፡

- በመላው ሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በሙሉ ስለ ሀገሪቱ ሰላም ጸሎተ ምኅላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/EOTC-TV-05-27 #EOTCTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሞነኛው የግብፅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዙሪያ : #Djibouti • የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡ - የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል። - የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ…
#Update

ጎረቤታችን ጅቡቲን እየጎበኙ ያሉት የግብፁ ፕሬዜዳት ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ሲል አል አይን (Al AIN) በድህረ ገፁ አስነብቧል።

ውይይታቸው በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር የተባለ ሲሆን ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን አንስተው ተነጋግረዋል።

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ፕሬዝዳንት ሲሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ ስምምነት ሳይኖር ኢትዮጵያ ግድቡን ለሁለተኛ ጊዜ መሙላት የለባትም የሚል አቋም አንፀባርቀዋል ተብሏል።

የግብፅ ባለስልጣናት በግድቡ ዙሪያ በተለያየ ጊዜ የሚያነሷቸው ሃሳቦች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ሙሌቱ አይቀሬ መሆኑን በተደጋጋሚ #አስረግጣ ተናግራለች።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,056 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 347 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 270,527 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 19 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,127 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,784,722 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹 #Anbesa🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ #Brand_Africa በ2021 በአፍሪካ እጅግ በጣም ከሚደነቁ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል ተካተተ።

አየር መንገዱ ኮቪድ - 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የህክምና ቁሳቁሶችንና የኮቪድ-19 ክትባትን በማማጓጓዝ ላስመዘገበው አስደናቂ ስራ የአምስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

በተጨማሪ #አንበሳ_ጫማ ከምርጥ ብራንዶች / ምርጥ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል በ4ኛ ደረጃነት ተካቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ህክምና ወጣ !

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ ታካሚ ሆድ ውስጥ በርካታ የተለያዩ የስለት መሳሪያዎች በቀዶ ጥገና ህክምና ሊወጣ እንደቻለ ወጣ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ለደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ገለጹ፡፡

የታካሚ የሕኪምና መረጃ መሠረት የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል እና በጨረር ምርመራ የተለያዩ ስለት ያላቸው ቁሳቁሶችና እስክሪቢቶ ጨምሮ ከሆዱ ሊገኝ ችሏል፡፡

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ፥ ግለሰቡ ታራሚ እና የአዕምሮ ህመምተኛ መሆኑን ገልጸው ከዕለታት አንድ ቀን እስክሪቢትቶ ሲውጥ ያየ ሌላ ግለሰብ በጠቆመው መረጃ መሠረት ነው ሊደረስበት የተቻለው።

በታካሚው ሆድ ውስጥ የነበሩ በርካታ ምስማሮች፤ እስክሪቢቶና ሌሎች የስለት ቁሳቁሶች በቀዶ ሕኪምና መውጣቸውን አቶ ተመስገን አስረድተዋል።

ከቀዶ ሕኪምና በኋላ ታካሚው በመልካም ጤንነት ላይ እንደምገኝ ተገልጿል።

ዶክተር በጋሻው መለሰ የቀዶ ሕኪምና ስፔሻሊስት ሐኪም ፥ ታካሚው መርፌንና ሌሎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በ4 ወራት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት መዋጡን ገልጸው ማረሚያ ቤቶች የታራሚዎችን ልዩ ባህሪያትንና ጤናቸውን መከታተል ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

አክለው ፥ ግለሰቡ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ የስነ ልቦና ክትትል እየተደረገለት በመሆኑ መሻሻል እየታየበት መሆኑን ዶክተር በጋሻው አብራርተዋል።

ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
@tikvahethiopia
“...ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” - ሄኮ ማስ

ጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሟን አመነች፡፡

ጀርመን እአአ ከ1904-08 ባሉት ዓመታት በናሚቢያ ዜጎች ላይ የፈጸመችውን ግድያ በጅምላ ጭፍጨፋነት ለመቀበል ስታቅማማ ቆይታለች፡፡

ነገር ግን 5 ዓመታትን በወሰደ ንግግር ጭፍጨፋውን ስለመፈጸሟ አምና ተቀብላለች።

ይህን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል የ1.3 ቢሊዬን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ተስማምታለች።

ጄኔራል ሎታር ቮን ትሮታ በሄሬሮ ጎሳዎች የተነሳውን የጸረ ቅኝ ግዛት ተቃውሞ ለማርገብ በማሰብ ሙሉ የጎሳው አባላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በማዘዝ 65 ሺ ገደማ የጎሳው አባላት መጨፍጨፋቸውን እና በትንሹ 1 ሺ የናማ ጎሳ አባላት መገደላቸውን የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄኮ ማስ “ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን” ብለዋል ባወጡት መግለጫ፡፡

ማስ በመግለጫቸው “ዓላማችን ተጎጂዎቹ የሚታወሱበትን እውነተኛ የእርቅ መንገድ መፈለግ ነው” ብለዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፥ በዛሬዋ ናሚቢያ ቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ የጭካኔ ድርጊቶችን “በይፋ ጅምላ ጭፍጨፋ ብለን እንጠራቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን #AP

@tikvahethiopia