የቻይና ጦር ሀይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
የመከላከያ ሚንስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ተገኝተው ነበር።
ሚኒስትሩ ፥ የቻይና መንግስት ከሀገር መከላከያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ፣ በቅርቡ የተመድ በኢትዮጵያ ላይ ባደረገው ስብሰባ ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየችው ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምሳደር ዣዎ ዢያን የቻይና የጦር ሀይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ያደረገው ድጋፍ በሁለቱ ወዳጅ ሀገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ማሳያ ነው ብለዋል።
አምባሳደር ዣዋ ዢያን፥ የቻይናና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንኙነት በተለያዩ መልኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይህም በሁለቱ ሀገራት አመራሮች የተፈረመው የስትራቴጂክ ግንኙነት አንዱ አካል ነው ብለዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዋጂን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በርክክቡ ወቅት ተገኝተው እንደነበር ሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።
@tikvahethiopia

#Attention📣
የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮቪድ-19 ቫይረስ አሳሳሳቢ ዝርያ እንደሆነ እና ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ ቫይረሱ እስካሁን ድረስ በ44 ሃገራት እንደተሰራጨ ገልጿል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት / EPHI / ፤ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለኮቪድ-19 አጋላጭ ሁኔታዎችን በማስቀረት የመከላከያ መንገዶቸን በጥንቃቄ እንዲተገብር አሳስቧል።
በዚሁ አጋጣሚ በህንድ የሰው ልጆች እንደቅጠል እየረገፉ ነው። ሆስፒታሎች ሞልተዋል፣ የኦክሲጅን እጥረትም አጋጥሟል።
ባለፉት አምስት ቀናት ብቻ ህንድ ውስጥ 19,952 ሰዎች ሲሞቱ 1,750,209 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ፦ - የሟቾች ቁጥር ጨምሯል ፤ ከሁለቱም ወገን 90 ሰዎች ተገድለዋል። - እስራኤል በጋዛ በከፈተችው የአየር ጥቃት 83 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጥኤም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። 18ቱ ህፃናት ናቸው። - የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ የሮኬት ማምረቻ እና ማከማቻ መጋዘንን ጨምሮ 600 የተመረጡ ኢላማዎችን መትቻለሁ ብሏል። ከወታደራዊ ኢላማዎች መካከል በትምህርት…
ቴልአቪቭ የገባው የግብፅ ልዑክ ከምን ደረሰ ?
ተኩስ አቁም ስምምነት ይደረግ ዘንድ ለማሸማገል እስራኤል ቴልአቪቭ የገባው የግብፅ ልዑክ ምንም አይነት አውንታዊ ውጤት እንዳላገኘ አንድ የግብፅ የደህንነት ምንጭ ለDPA ተናግረዋል።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ለጊዜውም እንኳን ቢሆን ተኩስ ይቆም ዘንድ የቀረቡትን ሃሰቦች በሙሉ ውድቅ አድርጋለች።
እስራኤል ወደ ተኩስ አቁም ድርድር ለመምጣት ፥ የሃማስ እና የሌሎች አንጃ ቡድኖችን ወታደራዊ አቅም ማጥፋት እና የምትፈልጋቸው በርካታ የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢላማ ማድረግ ትፈልጋለች ብለዋል የግብፁ የደህንነት ምንጭ።
በጋዛ የሟቾች ቁጥር የጨመረ ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ እስካሁን በትንሹ 119 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል፤ 31ዱ ህፃናት ናቸው። 830 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቤተሰቦች የእስራኤልን የአየር ጥቃት ሽሽት በሰሜን ጋዛ በUN ስር ባሉ ትምህርት ቤቶች ተጠልለዋል።
ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ በእስራኤል በኩል አንድ የህንድ ዜጋ ጨምሮ 6 እስራኤላውያን ተገድለዋል፤ አንድ ህፃን ልጅ ይገኝበታል።
ግጭቱ ይቆም ዘንድ ዓለም አቀፍ ተማፅኖዎችና ጥሪዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በማይካድራ ጭፍጨፋ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል ያላቸውን ኃይሎች መደምሰሱን ገለፀ።
መከላከያው ደመደስኩኝ ያለው ከሱዳን በመነሳት በማይካድራ አድርጎ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ 320 የህወሓት ሀይል ነው።
በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጡት የሀገር መከላከየ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፥ ቡድኑ በማይካድራ ጭፍጨፋ አድርሶ ወደ ሱዳን በመሸሽ ተደራጅቶ የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችንና መድሀኒቶችን በመያዝ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሙከራ ስለማድረጉ እና ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ መደምሰሱን ገልጸዋል።
ሀገራዊ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው በአሜሪካ ይገኙ የነበሩና ሀገርን በመካድ ሱዳን ካርቱም ከሚገኙ የህወሓት አመራሮች ጋር ወደ ሀገር ውስጥ የመገናኛ መሳሪያዎችና መድሀኒቶችን ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ ነበር ብለዋል።
በሱዳን መንገድ ላይ በውሀ ጥም የተንጠባጠቡ የህወሓት አባላቶችና እጃቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆኑት ሙሉ በሙሉ ሰራዊቱ እርምጃ ወስዶ ደምስሷቸዋል ሲሉም ተደምጠዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ብዛት ያለው የሬድዮ መገናኛ ፣ ሳተላይት ስልኮችና መድሀኒት በቁጥጥር ስር መዋሉን ሀላፊው ስለመግለፃቸው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ.pdf
"...በአክሱም ከተማ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ለመሸፋፈን ያለመ መግለጫ ነው" - አምነስቲ ኢንተርናሽናል
(አል አይን)
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከቀናት በፊት በአክሱም በነበረ ውጊያ 93 ሰዎች መሞታቸውንና ሟቾቹ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱ አብዛኞቹ በጦርነቱ የተሳተፉ መሆናቸውን በምርመራ መረጋገጡን መግለፁ ይታወሳል።
በምርመራው “በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው በመንገድ ላይ የነበሩ ንጹሀን” ጭምር መግደላቸውንም ነበር ዐቃቤ ህግ ያስታወቀው፡፡
በተጨማሪ የህወሓት ታጣቂዎች ኤርትራ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸው እንዲሁም በእስር ለነበሩ ወንጀለኞች የኤርትራ ወታደራዊ የደምብ ልብስ በመስጠት ከእስር ቤት መልቀቃቸው በአክሱም ለተፈፀመ ድርጊት ምክንያት እንደሆነ ገልፆ ነበር።
አምስነስቲ ኢንተርናሽናል ግን የጠቅላይ ዐቃቤ ህግን መግለጫ ተቃውሟል።
አምነስቲ ምን አለ ?
- ጥቃቱ ያነጣጠረው በታጣቂዎች ላይ ሳይሆን ንፁሀን ላይ ነው።
- ከሞት ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ንፁሀን መጠቃታቸውን በምርመራ አረጋግጫለሁኝ።
- በኤርትራ ሰራዊት ሲደረግ በነበረ ቤት ለቤት አሰሳ ወጣቶችና አዛውንቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሀን ተገድለዋል፤ እስከ አመሻሽ በቆየው የቤት ለቤት አሰሳ በርካቶች ቤተሰቦቻቸው ፊት ተረሽነዋል።
- ወንጀሉን በመፈጸም ረገድ የኤርትራ ጦር ሚናን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በልኩ አላስቀመጠም።
- ከምስክሮች በቃለ መጠይቅ እንዳረጋገጥኩት የቤት ለቤት አሰሳ ሲያካሂዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከለበሱት የደምብ ልብስ በተጨማሪ በባህል እና የቋንቋ ዘያቸው ይለያሉ።
- በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ጭፍጨፋ የመመርመር ኃላፊነት አለበት።
ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-05-14

#DrAbiyAhmed
በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል።
የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት በዓለ ሲመትን እንደሚታደሙም የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል።
የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት በዓለ ሲመትን እንደሚታደሙም የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethiopia
"...መላው ዓለም ችላ ቢልም ፤ ቱርክ ግን ዝም አትልም" - ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምትፈፅመው የአየር ድብደባ “በጣም ተቆጥቻለሁ” ሲሉ ተናገሩ።
ፕሬዜዳንቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልግም አሳሰበዋል።
ኤርዶጋን በኦንላይ ባደረጉት ንግግር ፥ አሸባሪ ሲሉ በጠሯት እስራኤል ፍልሥጤማውያን ላይ በፈፀመችው የጭካኔ ተግባር "አዝነናል ተቆጥተናልም" ብለዋል።
"የእስራኤልን የደም ማፋሰስ ተግባር ዝም ብለው የሚያዩ ወይም በግልፅ የሚደግፉ አንድ ቀን የእነሱ ተራ እንደሚሆን ማወቅ አለባቸው" ሲሉም ተደምጠዋል።
ኤርዶጋ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት የእየሩሳሌምን ሰላም ለማረጋገጥ እርምጃዎችን መውሰዱ “አስፈላጊ እና አስቸኳይ” መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻ ፕሬዜዳንት ኤርጎጋን መላው ዓለም እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምታደርደውን ግፍና ጭካኔ ቻላ ቢልም ቱርክ ግን ዝም አትልም ብለዋል።
በእስራኤል እና በፍልሥጤም መካከል በተነሳው ግጭት ሀገራት እና መሪዎች የተለያየ ሃሳቦችን እየሰጡ ነው።
ትላንት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በእስራኤል ላይ የፍልስጤም ታጣቂዎች የሚፈፅሙት የሮኬት ጥቃት መቆም እንዳለበት በመግለፅ ፤ አሜሪካ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ግልፅ ማድረጓን መግለፃቸው ይታወቃል።
48ኛው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዜዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ "አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ትቆማለች" ብለዋል፤ ይህ ትዊታቸውም PIN ተደርጓል።

ቃሊቲ እስር ላይ የሚገኙት አቶ እስክንድር ነጋ የፃፉት 'ድል ለዴሞክራሲ' የተሰኘ መፅሃፍ ገበያ ላይ እንደሚውል ተሰምቷል።
አቶ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆነው የፃፏቸው ፅሁፎች ስብስብ በመፅሐፍ መዘጋጀታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።
ባለቤታቸው ፥ መፅሀፉ በነገው ዕለት ግንቦት 7 ቀን 2013 በገበያ ላይ እንደሚውል ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
አቶ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆነው የፃፏቸው ፅሁፎች ስብስብ በመፅሐፍ መዘጋጀታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።
ባለቤታቸው ፥ መፅሀፉ በነገው ዕለት ግንቦት 7 ቀን 2013 በገበያ ላይ እንደሚውል ገልፀዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ክልል ጉዳይ የተናገሩበት ቪድዮ ፦ ይህ ከ14 ደቂቃ በላይ ርዝማኔ ያለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ጉዳይ የሚናገሩበት ቪድዮ የተቀረፀው በሞባይል ነው። ቪድዮው Dennis Wadley በተባሉና የሳቸው የቅርብ ወዳጅ በሆኑ ሰው በሞባይል የተቀረፀ መሆኑ ነው የተገለፀው። Dennis Wadley በአሜሪካ መቀመጫነቱን…
"...የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ንግግር ትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በትንሹ የሚያሳይ እንጂ የደረሰውን ሙሉ ግፍ የሚያስረዳ አይደለም" - መቐለ ሐገረ ስብከት
በመቐለ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢሳይያስ የተመራ ጉባኤ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ንግግር የተካተተውን ሐሳብ እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡
- የወረዳ ቤተክህነት ሠራተኞች፣
- የአብነት መምህራን፣
- ማኅበረ ካህናት፣
- ማኅበረ ምእመናን፣
- ሰንበት ትምህርት ቤቶች
- የትግራይ ነገረ-መለኮት ምሩቃን ማኅበር በጋራ መክረው ትላንት በትግርኛ ቋንቋ ባወጡት መግለጫ በትግራይ ሴቶች ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው አረመኔያዊ ድርጊት ዘመን የማይረሳው ክፉ ታሪክ እንደሆነ ቅዱስነታቸው በከባድ ሐዘን መግለጻቸው ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ እንዲሁም የቤተክርስትያኒቷ አንድነት እንዲበታተን በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን ለማጥፋት የሚካሄደው ጦርነት በፋይናንስ እና በሃሳብ የደገፉ ቢሆኑም ለሃገሪቱ እና ለቤተክርስቲያኗ ግን ሰላም አላመጣም ይላል መግለጫው።
የቅዱስነታቸው ንግግር ትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በትንሹ የሚያሳይ እንጂ የደረሰውን ሙሉ ግፍ የሚያስረዳ አይደለምም ብሏል መግለጫው።
የቅዱስነታቸው ንግግር ከተሰራጨ በኋላ በትግራይ ክልል የሚደርሰው ግፍ እንዲታፈን የሚጥሩ አካላትን እንቃወማለን ከቅዱስነታቸው ጎን እንደምንቆም እናረጋግጣለን ማለቱን አዲስ ዘይቤ ድረገፅ አስነብቧል።

* የአሜሪካ መግለጫ !
የጄፍሪ ፌልትማንን የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት አስመልክታ አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በኩል መግለጫ አውጥታለች።
በመግለጫዋ ምን አለች ?
- የአፍሪካ ቀንድ በወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቁማለች፤ በቀጣይ ሳምንታትና ወራት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ለቀጠናው ህዝቦች ለራሷ ፍላጎቶች ጭምር ትልቅ እንደምታ እንደሚኖራቸው አስታውቃለች፡፡
- በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የፖለቲካና የጎሳ ጽንፈኝነት እጅጉን እንደሚያሳስባት ገልፃለች።
- በትግራይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፍ እና ጭካኔዎች እንዲሁም ኢ-ሰብአዊ ሁኔታዎች ተቀባይነት የላቸውም ብላለች።
- በትግራይ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም፣ የህይወት አድን እርዳታዎችን ለማድረግ እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር እንደምትሰራ አስታውቃለች።
- በትግራይ ያጋጠመው ችግር ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሃገራዊ ለውጥ ለገጠሙት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማሳያ ሆኖ በምልክትነት ሊጠቀስ እንደሚችል ገልፃለች።
- ጄፍሪ ፌልትማን ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ ጋር በአስመራ በነበራቸው ቆይታ የኤርትራ ወታደሮች በቶሎ መውጣት የግድ ስለመሆኑ አፅንዖት ሰጥተው እንደነገሯቸው አሜሪካ አሳውቃለች።
- የግድቡ ጉዳይ የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት በማከለ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚችል አሜሪካ አሳውቃለች።
- በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር በአስቸኳይ ሊጀመር እንደሚገባ አሜሪካ አሳስባለች።
በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-05-14-2
ምንጭ፦ አል አይን

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
ባለፉት 24 ሰዓት 13 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 4,270 የላብራቶሪ ምርመራ 453 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,636 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 265,413 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,964 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 217,370 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 620 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,436,665 ደርሷል።
#Purpose

* የአሜሪካ መግለጫ ! የጄፍሪ ፌልትማንን የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት አስመልክታ አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በኩል መግለጫ አውጥታለች። በመግለጫዋ ምን አለች ? - የአፍሪካ ቀንድ በወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቁማለች፤ በቀጣይ ሳምንታትና ወራት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ለቀጠናው ህዝቦች ለራሷ ፍላጎቶች ጭምር ትልቅ እንደምታ እንደሚኖራቸው አስታውቃለች፡፡ - በኢትዮጵያ…
አሜሪካ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ፦
"...ጄፍሪ ፌልትማን በውሃ እና በግድቡ ደህንነት እና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ስጋት አለን ከሚሉት ከግብጽ እና ሱዳን መሪዎች ጋር መክረዋል።
ጉዳዩ የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት በማከለ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል።
ለዚህም በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር በአስቸኳይ ሊጀመር እንደሚገባ እናሳስባለን።
በ2015ቱ የመርሆዎች ስምምነት መግለጫ (DoP) እና የአፍሪካ ህብረት ቢሮ ባሳለፍነው ክረምት የሰጠው መግለጫ ለድርድሩ መሰረት ሆኖ ያገለግላል በሚል እናምናለን።
አሜሪካ ለድርድሩ ስኬት ቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ ድጋፎችን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት።"
#AlAIN