የቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም - Tikvah.pdf
230.4 KB
የ40/60 መኖሪያ ቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም :
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ካስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ለተጠቃሚዎች ያስተላለፋቸውን ቤቶች ቁልፍ ለቤት ባለቤቶች ከመጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ እያስረከበ እንደሚገኝ አስታውሷል።
የቤት ባለቤቶችም አስፈላጊ የሰነድ ማስረጃዎችን ይዛችሁን በPDF ፋይሉ በተገለፀው ፕሮግራም መሰረት የቤታችሁን ቁልፍ እንድትረከቡ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethiopia

"...ዘገባው የተሰራበት መንገድ ስህተት ነው" - አቶ ሀጂ ኢብሳ
By : am.al-ain.com
ከፈነዱ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያሰከትሉ የሚችሉ ተቀጣጣይ ኬሜካሎች በብዙ ድርጅቶች መጋዘን ላይ እንደሚገኙ የሚገልጹ ዘገባዎች ስህተት ናቸው።
የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ፣ ዘገባው የተሰራበት መንገድ ስህተት እንደሆነ ከአል ዓይን ድረገፅ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
አቶ ሀጂ ፥ "እውነታው በአዲስ አበባ ባሉ የስንዴ መጋዘኖች፣ ዩንቨርሲቲዎች፣ ሆስፒታሎችና የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መጋዘኖች አካባቢ ፣ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ እና ሊፈነዱ የሚችሉ ኬሚካሎች ተከማችተው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች በተከዘኑባቸው ቦታዎች ቢፈነዱ መጋዘኖቹ ካሉበት ስፍራ ጀምሮ እስከ 250 ሜትር ባሉ ስፍራዎች ውስጥ አደጋ ሊያደረሱ ይችላሉ የሚል ነው” ብለዋል።
አክለው ፥ “እኔን ዋቢ አድርገው የተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በ250 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ባሉ ከተሞች ላይ አደጋ ሊፈጠር የሚችል ኬሚካል ተከማችቷል የሚል ዘገባ ሰርተዋል። እኔ ለነዚህ የሚዲያ ተቋማት ይሄንን መናገሬን አላስታውስም። በዚያ መንገድ ተናግሬም ከሆነ ግን በአፍ ወለምታ በስህተት ነው ፣ ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል።
እነዚህን ኬሚካሎች ለማስወገድ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር ጥናቶችን እየተካሄዱ መሆኑን ያሳወቁት አቶ ሀጂ ፤ በያዝነው ሚያዝያ ወር ውስጥ ጥናቱ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ከመንግስት እውቅ እንዲሁም ፍቃድ ውጪ የገቡ ኬሚካሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ጥናቱ ሲጠናቀቅ የሌሎች አገራትን ልምድ ተጠይቆ ኬሚካሎችን በፍጥነት ይወገዳሉ ተብሏል።
@tikvahethiopiaBOT

"...ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በአዲስ አበባ ነዎሪዎች ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር ተሞክሯል" - የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት
"አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ የሚያወድም ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት አለ" በሚል በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ የትስስር ገፆች የተሰራጨው መረጃ የተዛባና የተሳሳተ በመሆኑ ፤ ነዋሪዎች የዕለተ ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ያለስጋት እንዲያከናወን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሳሰበ።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዳስታወቀው ፥ በትናንትነው ዕለት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ የትስስር ገፆች አዛብተው አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ማውደም የሚችል ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት አለ በማለት ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በከተማዋ ነዎሪዎች ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር እየሞከሩ ነው ብሏል።
በኤጀንሲው የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ አዛብተው በማቅረብ፤ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች "አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ማውደም የሚችል ጊዜው ያለፈበት የኬሚካል ክምችት በተለምዶ ላፍቶ በሚባለው አካባቢ አለ" የሚል ሃሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህብረተሰቡን የማደናገርና ከዚያም ባለፈ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር እየሞከሩ መሆኑን አሳውቋል።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በአ/አ አለ የተባለው የኬሚካል ክምችት ለከተማዋ ነዎሪዎች የደህንነት ስጋት የሚፈጠር አለመሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ያረጋገጠ ሲሆን ፤ ህብረተሰቡ በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ሳይወናበድ የዕለተ ተዕለት እንቅስቃሴውን ያለምንም ስጋት እንዲያከናውን አገልግሉት መስሪያ ቤቱ አበክሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡
More : telegra.ph/NISS-04-10

#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 35 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 7,278 የላብራቶሪ ምርመራ 1,739 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,093 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 227,255 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,146 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 169,038 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 933 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ሼህ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ አሚን አረፉ።
[Harun Media , Ustaz Abubeker Ahmed]
በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ በሆኑት በራያና አካባቢው ከፍተኛ እውቅና የነበራቸው እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሸራተኑ ጉባኤ ከተመረጡት 26 ኡለሞች ውስጥ አንዱ የነበሩት ሼህ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ አሚን በአዲስ አበባ ከተማ ህይወታቸው አለፈ።
ሼህ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ በኮቪድ-19 ምክንያት ነው ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው።
ሼይኽ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ በኢልማቸው አንቱታን ያተረፉ በርካታ ደረሶችን ያፈሩ ትልቅ አሊም የነበሩ ሲሆን የራያን እና የአካባቢውን ህዝበ ሙስሊም ኢልም በማስተማር ትልቅ ድርሻ የነበራቸው ታላቅ አሊም ነበሩ።
ሼክ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አሊሞች ማህበር ምክትል ዋና ፀሃፊ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የቀድሞው አል ሂጅራ መፅሄት የአረብኛው ክፍል ላይ በዋና አዘጋጅነት አግልግለዋል።
ሼይኽ ሂዝቡሏህ በ2004 ህዝበ ሙስሊሙ የመንግስትን የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሲያካሂደው በነበረው ሰላማዊ የመብት ትግል ወቅት ከሃቅ ጎን በመቆማቸው ኢማም ከነበሩበት መስጂድ እንዲነሱ ተደርገው ለእስር ተዳርገው የቆዩ ሲሆን እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ ህዝበ ሙስሊሙን በማገልገል ላይ ነበሩ።
ሼህ ሂዝቡሏህ ሙሐመድ በህዝበ ሙስሊሙ የጣለባቸውን አማና ለመወጣት በቅርቡ የተካሄደውን የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠ/ምቤት ጠቅላላ ጉባኤ ለመሳተፍ መጥተው አዲስ አበባ የሰነበቱ ሲሆን የጉባኤውን ውሳኔ አፈፃፀም ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ወደመጡበት ላለመመለስ ወስነው በአዲስ አበባ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ነዉ ህይወታቸው ያለፈው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የህግ ተመራቂዎቹ አቤቱታ : በአዲስ አበባ የሚኖሩ የ2012/13 ዓ.ም የህግ ትምህርት ተመራቂዎች በፌደራል ደረጃ ለህግ ተማሪዎች ይሰጥ የነበረዉን የቅድመ ስራ ስልጠና ዳግም መሠጠት እንዲጀምር ለተለያዩ የመንግስት አካላት በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
#Update
ስቴም ፓወር ከቪዛ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና 114 ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ለሦስት ወር ተከታትለው አጠናቀዋል።
በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከተካፈሉ ሰልጣኞች የሰሯቸው ፕሮጀክቶች የተለያዩ ምዕራፎችን አልፈው በቅርቡ ሥራዎቻቸውን ለኢንቨስተሮች የሚያቀርቡ ሲሆን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋርም ትስስር የሚፈጠርላቸው ይሆናል።
የስልጠናው ሁለተኛ ዙር ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን በዚህ ዙር ሦስት መቶ ሰልጣኞች ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በስልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶች እና ምዝገባውን https://telegra.ph/TRAINING-ANNOUNCEMENT-04-09 ላይ ያገኙታል።
https://forms.office.com/r/6cXD0LffWe
#STEMpower #VISA #TikvahEthiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹 የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት ለምታከናውነው የውሃ ሙሌት ሀገራቱ የግድብ ባለሙያዎችን ኢንዲመድቡ በይፋ ጋብዘዋል። ሚኒስትሩ ለሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለግብፅ ውሃ ሚኒስቴር በላኩት ድባዳቤ ነው ሁለቱ ሀገራት የፊታችን ሐምሌ እና ነሃሴ ወር ላይ የሚከናወነውን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ባለሙያን…
ሱዳን እና ግብፅ የኢትዮጵያን ጥሪ አንቅበልም ብለዋል :
ግብጽና ሱዳን ግድቡን የተመለከቱ መረጃዎችን ለመለዋወጥ በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ሃሳብ ሳይቀበሉት ቀሩ፡፡
የእርምጃውን በጎነት የጠቀሱት ሃገራቱ ኢትዮጵያ ሃሳቡን ለራሷ በሚስማማት መልኩ ማቅረቧን በመጠቆም ከመረጃ ልውውጡ አስቀድሞ አስገዳጅ ስምምነት እንዲኖር ጠይቀዋል፡፡
በሱዳን የመስኖ እና ውሃ ሃብት ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ ከመረጃ ልውውጡ በፊት አስገዳጅ ስምምነት ይኑር ብሏል።
ሚኒስቴሩ የመረጃ ልውውጡን በጎነት አስታውሶ “ሂደቱ በአስገዳጅ የህግና የስምምነት ማዕቀፍ ሊደገፍ” እንደሚገባ አስታውቋል፡፡
ካሳለፍነው ወርሃ ሰኔ ወዲህ በተደረጉ የሶስትዮሽ ድርድሮች 90 በመቶ ያህል ስምምነት ላይ ተደርሶባቸው በረቂቅ ደረጃ ከተዘጋጁ የስምምነት ሃሳቦች መካከል አንዱ የመረጃ ልውውጥ ጉዳይ መሆኑን መግለጫው አስታውሷል፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያ የመረጃ ልውውጡን “ለራሷ በሚስማማት መልኩ ለመቀበል መሻቷን የሚጠቁሙ አጠራጣሪ አዝማሚያዎችን” በደብዳቤውን ተመልክቻለሁ ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡
ግብጽም በኢትዮጵያ የቀረበውን የመረጃ እንለዋወጥ ሃሳብ አልቀበልም ብላለች።
የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር “በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ሙሌት ሊያጋጥም የሚችለውን ችግር በአስዋን ግድብ ባለው ከፍተኛ የውሃ ክምችት ለመቋቋም እንችል ይሆናል ነገር ግን የድርቅ አስተዳደር ጉዳይ አሳሳቢ ነው” ሲሉ ትናንት ቅዳሜ ለአንድ የሃገሪቱ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተናግረዋል፡፡
More : telegra.ph/AL-AIN-News-Agency-04-11
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

ስለታለቁ ህዳሴ ግድብ ማወቅ ያለብኝ ሰሞነኛ ጉዳይ ምንድነው?
- ሰሞኑን ኮንጎ ኪንሻሳ የሶስትዮች ውይይት ተደርጎ ያለስምምነት ነው የተጠናቀቀው ፤ ያለስምምነት ለመጠናቀቁ ሱዳንና ግብፅ ኢትዮጵያ ተጠያቂ ያደርጓታል።
- ሱዳን የድርድሩን አካሄድ የመቀየር አላማ ነበራት። ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት እንዳይመራና ሌሎች ተዋንያኖች አብረው ድርድሩን እንዲመሩ ትፈልግ ነበር፤ ግብጽ ደግሞ የሱዳንን ሃሳብ ትደግፍ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ይህን አልተቀበለችም።
- የታለቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዓመት ሙሌት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ነው።
- ኢትዮጵያ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ለምታካሂደው የውሃ ሙሌት ግብፅና ሱዳን የግድብ ባለሙያዎችን ኢንዲመድቡ በይፋ ጋብዛቸዋለች፤ግን ሁለቱም አልተቀበሉም።
- የሰሞኑን ድርድር ያለስምምነት ከተጠናቀቀ በኃላ የግብፅ እና ሱዳን ባለስልጣናት ፣ ሚዲያዎች፣ ታዋቂ ሰዎች ኢትዮጵያን ለማስፈራራት ሲሞክሩ ይታያል ፤ አንዴ ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን ሲሉ ያወራሉ (ጦርነት ማለታቸው ነው) አንድ ጊዜ ደግሞ ጦርነት አንፈልግም ፤ ከሰላም ውጭ አማራጭ የለም ይላሉ ፤ አቋማቸው በግልፅ ለማወቅም አስቸጋሪ ሆኗል ፤ ያም ሆነ ይህ የማይቀረው የ2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ጊዜ እየተቃረበ ነው።
- የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ ውስጥ ጉዳዮች በፈተና ውስጥ ቢሆንም ለአፍታም እንኳን የጉድቡን ጉዳይ አልዘነጋውም፤ በግድቡ ዙሪያ የሚሰሩ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ታዋቂ ሰዎች በግብፅና ሱዳን የሚሰነዘሩት ሀሰተኛ ክሶችን በአንድ በኩል በሌላ በኩል ሀገሪቱ የለየለት እልቂት ውስጥ ገብታ የግድቡ ስራ እንዲቆም የሚሰሩትን አካላት በማህበራዊ ሚዲያ ምላሽ በመስጠት እየታገሉ ነው ፣ መከላከያ ሰራዊቱ ቀን ከሌት ግድቡን እንደአይኑ ብሌን እየጠበቀው ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መሰጠት ተጀመረ።
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት "በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ጅዳ" እስከ አሁን ሳይሠጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ 3/08/2013 መሠጠት ጀምሯል።
ፈተናው የፊታችን ረቡዕ ይጠናቀቃል።
በሀገር ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከየካቲት 29 - መጋቢት 2 ድረስ መሰጠቱ ፤ በአጭር ጊዜም ፈተናው ታርሞ ውጤትና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት "በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ጅዳ" እስከ አሁን ሳይሠጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ 3/08/2013 መሠጠት ጀምሯል።
ፈተናው የፊታችን ረቡዕ ይጠናቀቃል።
በሀገር ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከየካቲት 29 - መጋቢት 2 ድረስ መሰጠቱ ፤ በአጭር ጊዜም ፈተናው ታርሞ ውጤትና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው !
[ነሲሓ ቲቪ]
በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም።
በተሚዝ አካባቢ ያለው የጨረቃ መጠባበቂያ ማእከል ውጤት ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ጨረቃ አልታየችም።
ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2013 የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማክሰኞ ደግሞ ረመዳን 1 ይሆናል።
ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይፋዊ መግለጫ ግን በመጠበቅ ላይ ነው።