TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አንደኛ አመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው !

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አንደኛ አመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

@tikvahethiopia
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካሻሻላቸው መመሪያዎች መካከል ፦

(በሪፖርተር ጋዜጣ)

ትውልደ ኢትዮጵያውያን በውጭ ምንዛሪ የሚያስቀምጡትን ገንዘብ በምን ዓይነት አግባብ መጠቀም እንደሚኖርባቸው የሚያመለክተው መመሪያ አንዱ ሲሆን እስካሁን ሲሠራበት የነበረውን አሠራር በተወሰነ ደረጃ የሚቀይር ነው፡፡

አንድ ዳያስፖራ በውጭ ምንዛሪ የሚያስቀምጠውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ቀድሞ ከነበረው አሠራር በተለየ እንዲሠራበት የሚያደርግ ነው፡፡

ቀደም ብሎ በነበረው መመርያ በውጭ ምንዛሪ አካውንት ከፍተው ማስቀመጥ የሚችሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ከሚያስቀምጡት የውጭ ምንዛሪ 30 በመቶውን መኪናና ሌሎች ዕቃዎችን ለመግዛት እንዲጠቀሙ ያደርግ ነበር፡፡

አሁን ግን በ30 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ዕቃ ማስመጣትን ማለትም እንደ መኪናና የመሳሰሉትን ዕቃዎች እንዳያመጡ ከልክሏል፡፡

በቀደመው መመርያ ከሚያስገቡት የውጭ ምንዛሪ 70 በመቶ ደግሞ የውጭ ምንዛሪው ለ28 ቀን እንዲቀመጥላቸው ተደርጎ የውጭ ምንዛሪውን ዕቃ እንዲያመጡበትና ሊጠቀሙበትም ይችሉ ነበር፡፡

በአዲሱ መመርያ መሠረት ግን ለ28 ቀናት ይቀመጥላቸው የነበረው አሠራር ቀርቶ፣ በውጭ ምንዛሪ ማስቀመጥና መገልገል የሚችሉበት የውጭ ምንዛሪ መጠን ወደ 45 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

ሆኖም ቀሪውን 55 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ባስገቡበት ዕለት በዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ ለባንኮች እንዲሸጡ የሚያስገድዳቸው መመርያ ነው፡፡  

More : telegra.ph/Reporter-Newspaper-03-14

@tikvahethiopia
#PhiBela

ንብረትነቱ የባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የሆነው ቡሬ ከተማ የሚገኘው የፊብላ ዘይት በመላው ሀገሪቱ እንዲሁም በአማራ ክልል ከተሞች እየተሰራጨ መሆኑ ተገልጿል።

የፊቤላ ዘይት አሁን ላይ እየተሰራጨባቸው ካሉ ከተሞች አንዷ የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ናት።

የምርቱ ስርጭት በዘይት ዋጋ ላይ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ትርጉም ባለው ደረጃ ይረጋጋዋል ተብሎ ታምኗል።

አሁን በገበያ ላይ ካለው የዘይት ዋጋ አንፃር የፊብላ ዘይት ምርት በቅናሽ ዋጋ ነው ለገበያ የቀረበው።

እንደአማራ ኮሚኒኬሽን መረጃ ዘይቱ በቀጣይ ቀናት አማራ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
በሃላይደጌ ፓርክ በተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትር እስኩየር በላይ ሳርና ቁጥቋጦ ወድሟል !

ባለፈው ሀሙስ ቀትር ላይ በፓርኩ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተውን የእሳት አደጋ በአብዛኛው መቆጣጠር እንደተቻለ የፓርኩ አስተባባሪ አቶ መሐመድ እድሪስ ተናግረዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ፦

- የአፋር ክልል እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን፣
- የክልሉ የልማት ድርጅቶች፣
- የአሚባራና ሃሩካ ወረዳ ነዋሪዎች እና አመራሮች
- የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከፍተኛ ተሳትፎና ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በአካባቢው ባለ ከፍተኛ ንፋስና ሙቀት ቃጠሎውን ፈጥኖ ለመቆጣጠር አላስቻለም ተብሏል።

እስከ ትናንት ምሽት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በነበረባቸው አካባቢዎች እሳቱን ለማጥፋት በተደረገ ጥረት አብዛኛውን ክፍል መቆጣጠር እንደተቻለ ተነግሯል።

ዛሬም በፓርኩ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተበታትነው የሚገኙ አነስተኛ እና ቀላል እሳቶችን የማጥፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የተጠቆመ ሲሆን አደጋው በቁጥጥር ስር የሚውልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል።

ለ3 ቀን በዘለቀው ቃጠሎ ከ100 ኪሎ ሜትር እስኩየር በላይ የሸፈነ ሳርና ቁጥቋጦ ሙሉ በሙሉ ውድሟል።

በቃጠሎው በዱር እንስሳት እንዲሁም በአእዋፎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተጠቁሟል።

የእሳት አደጋው መንሰኤ #ሰው_ሰራሽ መሆኑን ተገልጿል።

ዝርዝር የአደጋው መንስኤና የጉዳት መጠን በሚመለከታቸው አካላት ተመርመሮ ይገለፃል ተብሏል። ~ ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ በቃሉ ወረዳ በ07 ቀበሌ የቃሉ ኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ እና የተውፊቅ ሙስጂድ ግንባታ የማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው በኡስታዝ አቡበክር አህመድ ሲሆን በስነ ስርዓቱ ላይ ኡስታዞች እና መሻይኾች ተገኝተው ነበር።

Photo : Ustaz Abubeker Ahmed
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እነ አቶጃዋር መሃመድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ተወሰዱ ! እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ሃምዛ ቦረና ዛሬ ጥዋት ላንድ ማርክ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን አሳውቋል። ትላንት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአቶ ጃዋር ፣ አቶ በቀለ ፣ በአቶ ሀምዛ እና አቶ ደጀኔ የህክምና ጉዳይ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠውን…
እነአቶ ጃዋር ዛሬ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ቃሊቲ ተመልሰዋል።

በላንድ ማርክ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ላይ የነበሩት አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሀምዛ ቦረና ዛሬ ከሆስፒታል ወጥተው ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መመለሳቸውን ከኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

እነ አቶ ጃዋር በላንድ ማርክ ሆስፒታል ለ12 ቀናት ክትትል አድረገዋል።

የጤናቸው ሁኔታ በመሻሻሉ ነው ከሆስፒታል የወጡት።

እንደ ጠበቆቻቸው ገለፃ ፖለቲከኞቹ ለ40 ቀናት የምግብ አድማ አድርገው ፥ በኃላም ላንድ ማርክ ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና ሱፐር ኢንቴንደንት ሁሴን ሸቦ ተማፅነዋቸው አድማውን አቁመዋል።

እነ አቶ ጃዋር አድማውን ባቆሙበት ወቅት እነደተገለፀው አድማውን ያቆሙት ጥያቄያቸው ምላሸ አግኝቶ ሳይሆን ፤ "ሃኪሞቻቸው ፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች ባደረጉት ልመና እና፣ ጫና በርትቶባቸው እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
በ5 የሶማሊ ክልል ተወላጅ ወጣቶች ኢንቨስት የተደረገ "ሚና" የተሰኘ የውሃ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ !

ሚና የውሃ ፋብሪካ በ80 ሚሊየን ብር ወጪ በፋፈን ዞን ጉርሱም ወረዳ ደገህሌ ከተማ የተገነባ ሲሆን ዛሬ ተመርቋል።

ፋብሪካው በአምስት የክልሉ ተወላጅ ወጣቶች ኢንቨስት የተደረገ ነው።

በሰአት 12 ሺህ ሊትር ፣ በቀን 288,000 የታሸገ ውሃ የሚያመርት ሲሆን ፤ በ28 ሺህ ካ.ሜ ላይ አርፏል።

በምርቃት ስነ ርዓቱ ላይ ተገኝተው ፋብሪካውን የመረቁት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ፥ በሶማሊ በተፈጠረው አስተማማኝ ሰላምና ለውጥ አማካኝነት በርካታ ኢንቨስተሮች ወደ ክልሉ ለመሳብ መቻሉን ገልፀዋል።

PHOTO : Abdulkadir
@tikvahethiopia
#Attention😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,895 የላብራቶሪ ምርመራ 1,413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 1,669 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 175,467 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,550 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 143,710 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 467 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፦

ለኣክሱም ዪኒቨርስቲ ኤክስቴንሽን /ኢ- መደበኛ/ እንዲሁም መደበኛ የሁለተኛ ድግሪ (ማስተርስ) ተማሪዎች ት/ት የሚጀሙሩበት ቀን ጥሪ አቀረበ።

- ለነባር ወይም ስንየር የኤክስተንሽን(ኢ-መደበኛ) ድግሪ ተማሪዎች ከመጋቢት 11/2013ዓ/ም ጀምሮ እንዲገቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤

- ከመጋቢት 15 -16/2013ዓ/ም ባለው ጊዜ ለሁሉም #መደበኛ# የሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ተማሪዎች የአንደኛ ሴሚስተር ኖርማል ምዝገባ ይካሄዳል።

- ለሁሉም የኤክስተንሽን (ኢ-መደበኛ) ማስተርስ ተማሪዎች ከመጋቢት 18-19/2013ዓ/ም ባለው ጊዜ የአንደኛ ሴሚስተር ኖርማል ምዝገባ ያደርጋሉ።

(ጌታቸው ካሕሱ /የአክሱም ዩኒቨርስቲ አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት ሃላፊ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,895 የላብራቶሪ ምርመራ 1,413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 1,669 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 175,467 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,550 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 143,710 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን ሰዓት…
የዛሬ መጋቢት 5 ሁኔታ ፦

24% national positivity rate.The higest so far!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰው አንድ ሰው በኮቪድ ተይዞዋል ወይም ኮቪድ ሊኖርበት ይችላል እንደማለት ነው።

ከ20% በላይ የበሽታው ስርጭት የሚታይባቸው ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች ፦
1. ሲዳማ-39%
2. ኦሮሚያ-38%
3. ድሬዳዋ-25%
4. ሐረር-25%
5. አዲስ አበባ-24%

እነዚህ ቁጥሮች ምን ማለት እንደሆኑ አለመገንዘብ በእራስ እና በሀገር ላይ ሞት እንደማወጅ ይቆጠራል።

ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር

#SPHMMC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
65 ሺህ ብር ወድቆ ያገኘው ወጣት በታማኝነት ለባለቤቱ መለሰ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ የአይሰጋ ቀበሌ ነዋሪና የጎሚስታ ስራ የሚሰራው ወጣት #ያዩ_ሁነኛው መህሩም ተራራ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ 65 ሺህ ጥሬ ብር ያገኘ ቢሆንም ገንዘቡ ለጠፋበት ለአቶ ሰለሞን ጫቅሌ ምንም ሳይቀንስ 65 ሺህ ብሩን በታማኝነት እንደመለሰለት የቋራ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

አቶ ሰለሞን ፥ ገንዘቡን ላገኘለት ወጣት 10 ሺህ ብር ቢሰጠውም ወጣቱ ገንዘቡ አልቀበልም በሚል ሙሉ ታማኝነቱ እና ደግ ስራውን ከፈጣሪው ማግኘት በመፈለጉ ሊቀበለው አለመቻሉን ገልጿል።

ወጣቱ ሰርተን ከምናገኘው ገንዘብ ውጭ የሰው ገንዘብ መጥቶ ሊጠቅመን ይልቅና የራሳችንንም ይዞብን ስለሚጠፋ ሁላችንም የሰው ገንዘብ የሰው ከመሆኑ በዘለለ ለኛ ስለማይጠቅም ሁላችንም ፈጣሪ ሰርተን የምናገኘውን በረከት ያደርግልን ዘንድ ጎን መዋል ይኖርብናል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ከሳምንታት በፊት #ጉሌድ_ኢብራሂም_ኡመር የተባለ በጅጅጋ ከተማ በባጃጅ ሹፍርና የተሰማራ ወጣት የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጣቸው እናት 300,000 ብር (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባጃጁ ላይ ረስተው ቢወርዱም የብሩ ባለቤት የሆኑትን እናት በመፈለግ የተቀመጡበት ቦታ ድረስ ሄዶ መልሶላቸው ነበር፤ በማህበራዊ ሚዲያም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለወጣት ጉሌድ ኢብራሂም ኡመር ምስጋና ሲያቀርቡ ነበር።

ለዚህ ተግባሩ የሶማሊ ክልል ፕሬዜደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድም ምስጋና አቅርበውለት እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ሃሳብን ለመግለፅ መሳድብን ምን አመጣው ?

ባለፉት 2 ቀናት የቲክቫህ አስተያየት መስጫ እንዲከፈት ተደርጎ ብዙ ታዝበናል ፤ ይህ የሀገራችንን የማህበራዊ ሚዲያው ሁኔታ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።

ስድብ፣ ጥላቻ፣ሰዎችን ለማሸማቀቅ አንገት ለማስደፋት መሞከር፣ያለማስረጃ፣ ያለምንጭ መናገር ተላምደነው አብረን መኖር ከጀመርን ሰነባብተናል።

ብዙ ሺዎች ሃሳባቸውን በአግባቡ የሚገልፁ ቢኖሩም የጥቂቶች ስድብ፣ጥላቻ ብዙዎችን ይመርዛል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆነ በማንኛውም ቦታ ሃሳብን ለመግለፅ መሳደብ /ሰዎች ማሸማቀቀ፣ አንገት ማስደፋት አይጠበቅብንም። በጨዋ ቋንቋ ማስረዳት ከቻልን እሰየው ፣ የማንግባባት ከሆነ ደግሞ ሌላ ጊዜ ከስሜታዊነት ነፃ ስንሆን መነጋገሩ መልካም ነውም

ከኛ ተቃራኒ ሃሳብ ሲገጥመን ፥ ለምን በትህትና ማስረዳት አቃተን ? ወንድሜ ፣ እህቴ ይህ እንዲህ ነው፤ ሃሳብን /ሃሳብሽን አልደግፈውም በዚህ ምክንያት ... ፤ እስቲ እንዲገባኝ አስረዳኝ/አስረጂኝ ... እያልንም ማውራቱ እንዴት ከበደን ?

ጥላቻ፣ ተቃራኒ ሃሳብ ለማስተናገድ አለመፈለግ፣ በቡድን ማሰብ/መፍረድ ፣ ጅምላ ፍረጃ፣ ሰዎችን ማሸማቀቅ ፣ ተጎዳን የሚለው ላይ መሳለቅ ውሎ አድሮ ሀገርን አደጋ ላይ መጣሉ አይቀርም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የጥላቻ ንግግርን በመቃወም ከክልል ክልል የዞርነው ውጤቱን ስላወቅን ነው።

ቲክቫህ መደበኛ ሚዲያ አይደለም ፤ እርስ በእርስ መረጃ ለመቀያየር ፣ ስለሀገር ጉዳይ የምንመክርበት፣ ለተቸገሩት የምንደርስበት ፕላት ፎርም ነው።

ጋዜጠኛው፣ሃኪሙ፣ነጋዴው፣ባለሃብቱ፣ ተቃዋሚው፣ ባለስልጣኑ ፣ ተማሪው፣ አስተማሪው የቲክቫህ አባል ነው።

ቲክቫህ ውስጥ ስድብ ፈፅሞ አይፈቀድም ፤ ተሳዳቢዎችን የመምከር ከፍ ሲል ከአባልነት የመቀነስ ስራ እንሰራለን።

@tikvahethiopia
#Gambella

ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ በሰው እና በቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ፑኩሙ ቀበሌ ንፋስ ቀለቀቅሎ በጣለ ዝናብ በርካታ ቤቶችና ሰው ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ፡፡

የፑኩሙ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጆን ኡጁዋቶ እንዳሉት በቀን 04/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5 አካባቢ ንፋስ ቀላቀሎ በጣለው ዝናብ በቀበሌው ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

በደረሰው ጉዳትም 55 የቆርቆሮና 20 የሳር ቤቶች በድምሩ 75 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ትምህርት ቤትን ጨምሮ አራት የመንግስት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁመው በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ መድረሱን አመልክተዋል፡፡

በመሆኑም በደረሰው አደጋ መልሰው ለመቋቋም የወገንና የመንግስት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋትቤል ሙን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል ብለዋል፡፡

በአደጋው የደረሰ ተጨማሪ ጉዳት እንዳለ ለማጣራት እና እርዳታ ለማሰባሰብ ከተለያየ አካላት የተውጣጣ ቡድን ወደ ስፍራው እንደሚላክ አስረድተዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች የፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ቦታው ላይ በመገኘት ምልከታ ማድረጋቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia