TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Gofa

ጎፋ ዞን አስተዳደር በትግራይ ሰብዐዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ።

የዞኑ አስተዳደር ፥ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ፀጥታ ችግር እና አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው፣ ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ነው ያሳወቀው።

"ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ለተጎዱት እና ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ 7 ወረዳዎች እና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች እርዳታውን እንዳሰባሰበ ገልጿል።

ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰበውን ጤፍ = 107.4 ኩንታል ፣ ስንዴ 12 ኩንታል ፣ ባቄላ 4 ኩንታል በድምሩ 123.4 ኩንታል እህል በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲደርስ መላኩን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን እንዲያሳውቅ ተጠየቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን 'ቁርጥ' ያለ ቀን እንዲያሳውቅ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ፥ "ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ለማሳወቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉት 400 ሺህ ታብሌቶች ወደ አገር ውስጥ አልገቡም" ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እንደሚሰራና 'ታብሌቶቹ' ወደ አገር ሲገቡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደሚወሰን ተናግረዋል።

የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በ1 ሺህ 500 የፈተና ጣቢያዎች አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እንዳስረዱ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

"ዛሬም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል" - የአ/አ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ገለፀ።

በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉት የእሳት ቃጠሎዎች በከተማው ህዝብ እና አመራሮች፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል አስተዳደሩ።

አስተዳደሩ ፥ "የጥፋት አላማቸው ያልተሳካላቸው አካላት ሆን ብለው ህብረተሰቡን ለማሸበር እያደረጉት ያለው ተግባር እንደማይሳካ እናሳውቃለን" ብሏል በመግለጫው።

ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ፣ ሳይዘናጋ ነቅቶ አካባቢውን በመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ያለምንም ስጋት መደበኛ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል ይኖርበታልም ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ የደረሱ የእሳት አደጋዎች ፦

#1

በጉለሌ እጸዋት ማእከል የደረሰው የእሳት አደጋ 2 ሄክታር ቦታ የሸፈነ ነው። በአደጋው ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፤ ምን ያህል ንብረት ከውድመት እንደተረፈ ለጊዜው አልታወቀም።

#2

በጉለሌ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት ጽዮን ሆቴል አካባቢ በአንድ ሼድ ላይ በደረሰው የእሳት አዳጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ለውድመት ሲዳረግ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏል፡፡

#3

በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ኮሎምብያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖርያ ቤት ላይ በደረሰ አደጋ 20 ሺህ ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል፡፡

#4

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ማርያም አካባቢ በአንድ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 100 ሺህ ብር በሚጠጋ ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ከውድመት ማዳን እንደተቻለ ተችሏል።

#5

በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ማርያም አካባቢ ላይ በሚገኝ የእንጨት ክምር ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ንብረት ሲወድም ወደ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል።

#6

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 "እፎይታ የገበያ ማዕከል" ላይ በሚገኙ ሱቆች ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የጉዳት መጠን በማጣራት ላይ ይገኛል።

* ዛሬ ሰኞ ቦሌ ዘሀብ ሆቴል ፊት ለፊት እና ኡራኤል አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር (የጉዳት መጠን አልታወቀም)

(የእሳትና የአዳጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
Compiled By: ETHIO FM 107.8

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6_216
• በበሽታው የተያዙ - 734
• ህይወታቸው ያለፈ - 10
• ከበሽታው ያገገሙ - 106

አጠቃላይ 138,384 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,103 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 122,978 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

230 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጄነራል መኣሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆኑ !

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት ያገለገሉት ብ/ጄነራል መኣሾ ሀጎስ ስዩም የተመድ የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው መሰየማቸውን የተመድን መረጃ ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ገልጿል።

ብርጋዴየር ጄነራል መኣሾ ሃጎስ በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸው ታውቋል።

አዲሱን ሹመት ከጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸው ተመድ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ቤት ለተቃጠለባቸው እና ንብረት ለወደመባቸው አካላት ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። የአደጋው መንስኤም የተለያዩ እህሎች በተከመሩበት ቦታ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞይባል ስልክ ፈንድቶ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ የዚህ አይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ቢሆንም…
በእሳት አደጋ ንብረት ለወደመባቸው ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።

በ "ደቡብ አፍሪካ ኬፕታዎን ከተማ" የሚኖሩ የሀላባ ተወላጆች በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛው በደኔ በቅረቡ በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ የቤት ንብረት ውድመት ለደረሰባቸው ወገኖችን የ316,350 (ሶስት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሀምሳ ብር) ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ድጋፉን በወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ልማት ጽ/ቤት የጉዳት መጠን መረጃ መሰረት በዛሬው እለት በእያንዳንዱ አባ ወራ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉን የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ኑርዬ አሳውቀዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በደቡብ አፍሪካ ኬፕታዎን ከተማ የሚኖሩ የሀላባ ተወላጆች ላደረጉላቸው ወገናዊ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን እንዳቀረቡ የዞኑ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ ጋር እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በተለያዩ ዙሮች በሥራ ፈጠራና ፋይናንስ ላይ ለሚሰጠው የስልጠና ፕሮግራም የመክፈቻ መርኃግብር በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።

ለስልጠናው ከተመዘገቡ ከ3000 በላይ አመልካቾች ውስጥ በተለያየ መስፈርት የተመለመሉ 400 የሚሆኑ ሰልጣኞች በሁለት ዙር ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

በመጀመሪያ ዙር ስልጠናውን እንዲወስዱ የተመረጡ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ለሦስት ወራት ሥልጠናውን የሚያገኙ ይሆናል።

የመጀመሪያው ወር ስልጠና በአካል ተገኝተው ይወስዳሉ። በ2ኛው ወር ሰልጣኞቹ በመረጡት የቢዝነስ ኃሳብ ላይ ድጋፍ እንዲያገኙ እገዛ ይደረግላቸዋል። በ3ኛው ወር ኃሳባቸውን ለሦስተኛ አካል እንዲያስረዱ በማድረግ ሰልጣኞች የቢዝነስ ኃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ ምዕራፍ እንዲያደርሱት ይደረጋል።

በመጨረሻም በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፉ ሰልጣኞች ያቀረቡትን የቢዝነስ ኃሳብ ለኢንቨስተሮች እንዲሁም የቢዝነስ ኃሳቦች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ግለሰቦች እንዲያቀርቡ እድሉ ይመቻችላቸዋል ተብሏል።

በመክፈቻው መርኃግብር የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው፤ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ የስቴም ፓወር ዋና ስራ አስፈጻሚ ቅድስት ገብረአምላክን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶችና ሰልጣኞች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

#STEMPower #VISA #TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፍሊፖ ግራንዴ የማይኣይኒ ካምፕን ጎበኙ። የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አብረዋቸው ከመጡት የተመድ ሉዑካን ቡድን ጋር በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ዛሬ ጎበኝተዋል፡፡ ፊሊፖ ግራንዲ በማይአይኒ የኤርትራ ሰደተኞች መጠለያ ካምፕ ስደተኞችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከARRA ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በዛሬው ጉብኝት ላይ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት…
ፍሊፖ ግራንዴ ከጉብኝታቸው በኃላ ምን አሉ ?

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ ያደረጉትን ጉብኝነት ሲያጠናቅቁ በክልሉ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ትናንት በሰጡት መግለጫ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሳይሆኑ የሰብዓዊ እርዳታ ሊደርሳቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው ጉብኝት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል።

በጎበኟቸው በስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ያገኟቸው ስደተኞች ጾታዊ ጥቃቶች እንደደረሱባቸው ሪፖርት እንዳደረጉላቸው ተናግረው በአሁኑ ወቅት ጾታን መሠረት ያደረጉት ሪፖርቶችን በአሃዝ ማስቀመጥ እንደማይቻል ገልጸዋል።

ፍሊፖ ግራንዲ ፤ መንግሥት ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰተኞችን በገለልተኝነት አጣርቶ ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ምንም አይነት ክልከላዎች እንዳይኖሩ መጠየቃቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UNHCR

ፍሊፖ ግራንዴ ከምክትል ጠ/ሚ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ትላንት ውይይት ማደረጋቸው ታውቋል።

አቶ ደመቀ ከፍሊፖ ግራንዴ ጋር የነበራቸው ውይይት ፍሬያማ ነበር ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

መንግስት በትግራይ ክልል ስለሚሰጠው የሰብዓዊ ድጋፍ፤ ስደተኞችንበማስተናገድ ረገድ ያሉ ጥረቶች እንዲሁም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር መወያየታቸውንም አቶ ደመቀ ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ ፥ "የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ የሚያደርገውን ድጋፍ ትርጉም ባዘለ መልኩ ለመጠቀም የኢትዮጵያ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጫላቸዋለሁ" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፍሊፖ ግራንዴ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
በማይናማር ወታደሩ ስልጣን ተቆጣጠረ። በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰምቷል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተለቅመው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። በሚየንማር በወታደሩ እና በሲቪሊያን አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት…
"...የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም" - ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ትላንት የማይናማር ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በማይናማር ላይ ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል።

ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ሲሉ ገልፀዋል።

በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ስሟ ማይናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር።

አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ መሆኑን ባይደን አስታውሰዋል። (BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰራዊቱን በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ የነበረ ግለሰብን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገለፀ።

ግለሰቡ ፥ ‘የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖችንና ከፍተኛ የጦር አዛዦች በትግራይ ልዩ ሃይል ተገድለዋል’ የሚልና ሌሎች የሀሰት መረጃ ፍሪደም ትዩብ በተባለ የዩትዩብ አድራሻ ሲያሰራጭ ነበር ብሏል ሀገር መከላከያ።

ግለሰቡ ከአዲስ አበባ በመነሳት ኬንያ ከዛም ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ ለመውጣት ሲሞክር  ሃዋሳ ላይ በደቡብ ዕዝ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ግለሰቡ ስራውን እንዲሰራ የቀጠረው እንግሊዝ ሀገር የሚኖረው ዳዊት አብርሃ የተባለ ሰው መሆኑንና ለአገልግሎቱ 600 የአሜሪካ ዶላር ይከፍለው እንደነበር ማብራራቱን ገልጿል።

ደቡብ ዕዝ የሃሰት መረጃ ሲያሰራጭ የነበረውን ግለሰብ ጨምሮ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ 8 ሰዎችን እና 4 በህገ ወጥ ዝውውሩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላት ለፌዴራል ፖሊስ ማስረከቡን  አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot
#update

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፖለቲካ ፓርቲዎች እጩ ተመራጮችን የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የሚያስገድደው ሕግ እንዲሻር መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ፥ የፖለቲካ ፓርቲ ተመራጭ እጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብን የሚያስገድደው በፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ አንቀጽ 32 ፤ ንዑስ አንቀፅ 2 መሠረት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚል ነው፡፡

በዚህ መሠረት ፦

- የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ለአገራዊ ምርጫ 10,000 ለክልል ደግሞ 4,000 የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ የሚያስገድደው አሠራር ለመጪው ምርጫ ብቻ እንዲቀር ተደርጓል፡፡

- የግል የምርጫ ተወዳዳሪ 5,000 የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ እንዳለበት በሕጉ የተደነገገ ሲሆን ፤ በማሻሻያው በግማሽ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡

- የግል ተወዳዳሪ አካል ጉዳተኛ ከሆነ 3,000 የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ይጠበቅበት የነበረው 1,500 ብቻ እንዲሆን ተሻሽሏል።

የተጠቀሱት ማሻሻያዎች ለስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa

ከሀሙስ ጀምሮ የሐዋሳ ከተማ አሮጌው መናኸሪያ የቦታ ለውጥ ያደርጋል።

ከሀሙስ ጀምሮ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ የአሮጌው መናኸሪያ የቦታ ለውጥ እንደሚደረግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አሳውቋል።

ምክንያት ?

መናህሪያው ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ታድሶ ዘመናዊ እና የተሟላ አገልግሎት መስጠት አንዲችል አለምአቀፍ የግንባታ ጨረታ ወጥቶ ወደ ስራ ሊገባ በመሆኑ ነው።

ግንባታው መቼ ተጀምሮ ይጠናቀቃል ?

በሚቀጥለው ሳምንት የመናህሪያው ግንባታ የሚጀመር ሲሆን በቀጣይ 6 ወራት ግንባታው ይጠናቀቃል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ የውስጥ አስፓልት ፣ 2 ዘመናዊ የተገልጋይ ማረፊያ ሼድ፣ ሻወርና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያ ካሜራዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አገለግሎቶችን ይኖሩታል።

የተዘጋጀው ምትክ ቦታ የት ነው ?

የአሮጌው መናኸሪያ ዕድሳት እስኪጠናቀቅ በጊዜያዊነት መናኸሪያው አሁን ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደሚገኝበት አካባቢ ተደርጓል።

ምትክ ቦታው የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሀ፣ የጥበቃ እና ሌሎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች እንደተማሉለት ተገልጿል።

Via Hawassa City Administration
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia