TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለተመራቂ ተማሪዎች ከተዘጋጀው መድረክ ውጪ የተመራቂ ወላጆች እና ወዳጅ ዘመዶች በተለመደዉ መንገድ በመመረቂያ አዳራሽም ሆነ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው ምርቃቱን መታደም አልቻሉም።

ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢ.ቲ.ቪ ቋንቋዎች እና በኢ.ቲ.ቪ መዝናኛ ቻናሎች በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#update

የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው።

መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያየ የትምህርት መስክ ትምህርታቸውን የተከታተሉ 2,896 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በተመሳሳይ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለ7ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 59 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፦ በዛሬው ዕለት የኒውጄኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅም ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
አምቦ እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

አምቦ እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠኗቸውን ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቁ ነው፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ 827 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

አምቦ ዩኒቨርሲቲ እያሰመረቃቸው ያሉት ተማሪዎች ከ5 ሺህ 73 ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 810 ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።

የምረቃው ሥነ-ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው ሥር ባሉት ሃጫሉ፣ ጉደር ማሞ መዘምር፣ ወሊሶ ካምፓስና ዋናው ግቢ የሚያጠቃልል ነው። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰራር ስርአት (OTRLS) ነገ ይፋ ሊደረግ ነው። የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዲስ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጫ የአሰራር ስርአት አልምቶ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቋል። ሚኒስቴሩ ነገ በስካይ ላይት ሆቴል የቀጥታ የበየነ መረብ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱን (online trade registration…
#update

www.etrade.gov.et

ዛሬ የኦንላይን የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት መስጫ የአስራር ስርዓትን በይፋ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

የኦንላይን የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት መስጫ የአስራር ስርዓትን በይፋ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተካሄደው በስካይ ላይት ሆቴል ነው።

በአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተው ነበር።

የኦንላይን የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት ነጋዴዎች ወደ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ሆነ ወደ ክልል ንግድ ቢሮዎች መሄድ ሳያስፈልጋቸው በቤታቸው ወይም ካሉበት ቦታ በኮምፒውተር አልያም በእጅ ስልካቸው ኢንተርኔትን በመጠቀም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ዘመናዊ አሰራር ነው።

ምንጭ፦ የንግድ እና ኢንዲስትሪ ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
www.etrade.gov.et

ኢትሬድ ከተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች ጋር ካሉ ሲተሞች ጋር በመጣመር አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል ፡-

• ከባንክ ሲስተም ጋር >>> ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ክፍየዎችን ለመሰብሰብ

• ከገቢዎች ሚኒስቴር ካለ ሲሰተም ጋር >> አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና የግብር ክሊራንስን ለማረገገጥ

• ከኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ የአንድ መስኮት አገልግሎት ሲሰተም ጋር >> የኢንፖርትና ኤክስፖርትን የሚያግዙ አገልግሎቶችን ለማፋጠን

• ከኢትዮ ቴሌኮም >> የአጭር መልክትን (SMS) ለማስተላፍ ናቸው።

Via MoTI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
www.etrade.gov.et

የኦንላይን የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት መስጫ ሲስተም የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶችን ለመስጠትና ደንበኞች ካሉበት ሆነው አገልገሎት እንዲያገኙ ታስቦ የተገነባ ነው ተብሏል ፦

- ዋና ዋና 19 ልዩ ልዩ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት፣

- በኦንላይን የንግድ ድርጅት ሥም ለማጣራትና ለማስመዝገብ፣

- ስለንግድ ምዝገባዎ፣ ንግድ ፈቃድዎ እንዲሁም ስላስመዘገቧቸው የንግድ ሥሞች መረጃ ለመከታተል፣

- ከድርጅትዎ ጋር አብሮ የሚሰራ ሌላ ድርጅትን ሕጋዊነትን ለማረጋገጥ እና

- አዲስ የንግድ ሥራን ለመጀመር ለሚፈልጉ የሕብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ለመስጠት እና ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ፍሊፖ ግራንዴ የማይኣይኒ ካምፕን ጎበኙ።

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አብረዋቸው ከመጡት የተመድ ሉዑካን ቡድን ጋር በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ዛሬ ጎበኝተዋል፡፡

ፊሊፖ ግራንዲ በማይአይኒ የኤርትራ ሰደተኞች መጠለያ ካምፕ ስደተኞችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ከARRA ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በዛሬው ጉብኝት ላይ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጨምሮ ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተገኝተው ነበር። #UNHCR

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#update

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ህገወጥ የመሬት ወረራ ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ ዛሬ የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል።

በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ ወስኗል።

በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል ተወስኗል።

ይህ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡

ምንጭ ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ዕ/ቤት
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን "ሰዴ ሙጃ ወረዳ" በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ገለፀ።

መነሻውን ከባሕር ዳር ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሲደርስ 200 ሜትር ከሚረዝም ገደል በመግባቱ ነው የ24 ሰዎች ህይወት ያለፈው።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በደብረ ታቦር እና በፈለገሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አብመድ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ካቢኔ ውሳኔ ፦

በአዲስ አበባ ለመምህራን ይከፈል የነበረውን የቤት አበል ከብር 850 ወደ ብር 3,000 እንዲሻሻል ወሰኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድሩ ካሁን በፊት በከተማው ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን 5,000 የመኖርያ ቤት አቅርቦ ነበር።

ለሁሉም መምህራን በፍጥነት ቤት ማዘጋጀት ባለመቻሉ ፤ ለሁሉም መምህራን 3000 የኢት ብር የቤት አበል ክፍያ እንዲከፈላቸው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia