ራይሌ ሀሙድ የኦብነግ ሊቀመንበር ሆነው ተሹመዋል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አዲስ ሊቀመንበር መሾሙን "አል ዐይን ኒውስ" ዘግቧል።
ለረጅም ጊዜ በሊቀመንበርነት ያገለገሉት አብዲራህማን መሀዲን አሁን ላይ በአዲስ ሊቀመንበር መተካታቸውን ነው ዜና ማሰራጫው የገለፀው።
በዚህም መሰረት ራይሌ ሀሙድ አዲሱ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው ተሸመዋል፡፡
ቀደም ሲል የኦብነግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ከ10 በላይ የሚሆኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በገዛ ፈቃዳቻ ከኃላፊነት ተነስተዋል፡፡ (አል ዓይን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

አጫጭር የኮቪድ-19 መረጃዎች ፦
- በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ዳግም መጨመር እያሳየ ይገኛል። ባለፉት ቀናት 558 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በትላንትናው ዕለት 124 ኬዝ የተመዘገበ ሲሆን 117ቱ ከሀገር ውስጥ ናቸው።
- እስራኤል ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሚሆኑ ወጣቶችን ኮቪድ ክትባት መስጠት መጀመሯን ቢቢሲ አስነብቧል። ለነዚህ ወጣቶች ክትባቱ እንዲሰጠት የሆነው የማትሪክ ፈተና ሊቀመጡ ስለሆነ ነው። እስራኤል 9 ሚሊዮን ከሚሆነው ሕዝቧ ውስጥ ሩብ ያህሉ የመጀመርያውን የክትባት ጠብታ ወስዷል። የክትባቱ አይነትም ፋይዘር ሰራሹ መሆኑ ታውቋል።
- ሜክሲኮ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ወደ 150 ሺህ እየተጠጉ ነው። ባለፉት 5 ቀናት ውስጥ 7,836 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።
- የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ-19 መያቸውን አሳውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ ቀላል ምልክት እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸው እንደማገግም “ብሩህ ተስፋ አለኝ” ማለታቸውን አል ዓይን ዘግቧል።
- ኤሜሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት ያጣቻቸው ዜጎች ቁጥር ወደ 430 ሺህ እየተጠጋ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 1,844 ሰዎች ሞተዋል፤ ቁጥር ባለፉት 5 ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው።
- የቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦታማን ጀራንዲ በኮሮና ተይዘዋል። ሚኒስትሩ ”ምንምእንኳን ጥንቃቄ አድርጌ ሁሉንም የጥንቃቄ መመሪያዎች ብከተልም በተደረገልኝ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶብኛል” ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ ምልክቱ እየታየባቸው መሆኑንና ሰዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ መጠበቅ እንዳለባቸው እንዳሳሰቡ አል ዓይን ዘግቧል።
@tikvahethiopia

ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ።
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ በሀራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክእስር ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መስማማታቸውን ገለፁ።
ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በታንዛኒያ ይገኛሉ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በህገ ወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጠው የገቡ ኢትዮጵያወያን እስረኞች እንደሚገኙ በመግለፅ እስረኞችን ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።
በነፃ ከእስር ይፈታሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሀገራቸው ግንባታ ይሳተፋሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያውያኑን ዛሬ ከፈለጉ ወደ ሀገራቸው መሄድ ይችላሉ ሲሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ከእስር ለሚለቀቁት የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንደሌለ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ሊስመርቅ ነው።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከ4,500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ጥር 18/2013 ዓ/ም በዓባያ ካምፓስ ሁለገብ ስታዲዬም እንዲሁም ጥር 20/2013 ዓ/ም የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎችን በሳውላ ካምፓስ ያስመርቃል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ/የቀድሞ ምሩቃን/ፕሬዝደንት፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የጋሞ ዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ይገኛሉ፡፡
መረጃውን ያደረሰን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

#EthiopiaNISS
የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር የሞከሩ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ፡፡
ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡
አገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ስጋት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,473
• በበሽታው የተያዙ - 365
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 783
አጠቃላይ 134,132 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,071 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 120,199 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
231 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው የእሳት አደጋ...
ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
አደጋው "ትዊንስ ኬ" በተባለ ብሎክ ላይ ባለ የዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ነበር የደረሰው።
በግቢው ውስጥ ውሃ ባለመኖሩ አደጋውን ለመቆጣጠር አክብዶት እንደነበር በስፍራው የነበሩ የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ምሽት አሳውቋል ፤ ሟቹ የአንዲት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የሆነ የዘጠኝ አመት ልጅ ነው።
በተማሪዎች ህይወት ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ግምጃ ቤቱ ውስጥ ባሉ ንብረቶች ላይ ግን ጉዳት ደርሷል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል፤ ፖሊስ የምርመራ ስራ እየሰራ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ውጤቱን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
PHOTO : Tikvah Family DDU ፣ DireDawa University
@tikvahethiopiaBOT @tikvah

ለበጎፈቃደኞች የቀረበ ጥሪ ፦
የ "እኛ ለእኛ በጎፈቃደኞች" ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከተለያዩ ሀገሮች የሚመለሱ ዜጎችን የመቀበል ሥራዎችን ላለፉት ሰባት ወራት ሲያስተባብርና ድጋፍ ሲሰጥ ቆይቷል።
በቅርቡም በርካታ ከስደት ተመላሽ ዜጎች ወደ ሀገር ለመመለስ ዝግጅት ላይ ናቸው።
በመሆኑም ከዚህ ቀደም የነበረውን ተግባር ማጠናከርና ዜጎቻችን ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የተለያዩ እገዛዎችን የሚያስተባብሩ በጎፈቃደኞችን መመልመል ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ጥሩ ተነሳሽነት ያላችሁ ፤ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆነ፤ በጎፈቃድ አገልግሎቱ ለመሳተፍ ፍላጎቱና አቅሙ ያላችሁ በሙሉ በፎርሙ የሰፈሩትን መረጃዎች በማንበብና ቅጹን በመሙላት መሳተፍ ትችላላችሁ ተብሏል።
https://forms.gle/5ZyCzPEMshG14WbR9
@tikvahethiopia @tikvagethiopiabot

"...የእኔና የምወክለው መንግስት ትኩረት አሁን ባለው የጦርነቱ ማግስት ሁኔታ ላይ ነው።" - ተሰናባቹ አምባሳደር ማይክ ሬይነር
ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር ትላንት በአሜሪካ ኤምባሲ ከተመረጡ ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
በቆይታቸውም በትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ጨምሮ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ተነስተዋል።
ተሰናባቹ አምባሳደር ሀገራቸው በትግራይ ክልል ጦርነት የተሳተፉትን ሁለት ወገኖች ለያይታ እንደምትመለከት ተናግረዋል።
ማይክ ሬይነር ፥ "በጦርነቱ የተሳተፉትን ሁለት ወገኖች በእኩል ደረጃ እንደማንመለከት ከመጀመሪያውም ግልፅ አድርገናል። አንደኛው የሀገሩን የግዛት አንድነት እና የህዝቦቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት የፌዴራል መንግስት ሌላኛው ደግሞ ህገወጥ በሆነ የትጥቅ አመፅ የተሳተፈ ነበር" ብለዋል።
ይህም ሆኖ ግን ጦርነት ምንጊዜም ጥሩ ውጤት እንደሌለው ነው የገለፁት።
"የጦርነት ማግስት ሁሌም የጠራ ሆኖ አያውቅም፤ ሁል ጊዜ የተመሰቃቀለ ማግስት ነው የሚኖረው እንዳለመታደል ሆኖ አሁን ያለነው እዚያ ደረጃ ላይ ነው፤ እንደአሜሪካም ትኩረታችን ያ ነው። በተለይ የሰዎች መብት እና ደህንነት መከበሩን ማረጋገጥ ፣ ሰብዓዊ ፍላጎቶቻቸው መሟላቱን ማረጋገጥ፣ አሁን ከሆነው በላይ ችግሩ አከባቢያዊ እንዳይሆን፣ ያ በሆነበት አካባቢ ችግሩ እንዲያበቃ ማድረግ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።
አሜሪካ ከጦርነቱ በኃላ በትግራይ ክልል እየታዩ ያሉ ችግሮች እንደሚያሳስባት ተሰናባቹ አምባሳደር አሳውቀዋል።
"ማንኛውም መንግስት በትጥቅ ከተደገፈ አመፅ እራሱን የመከላከል መብት እና ግዴታ አለበት በዚህ ነጥብ ላይ ግልፅ መሆን ፈልጋለሁ ፥ የእኔና የምወክለው መንግስት ትኩረት አሁን ባለው የጦርነቱ ማግስት ሁኔታ ላይ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ እየተራዘመ የመጣው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት፣ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ፆታዊ ጥቃቶች፣ በየቦታው የሚፈፀሙ የተለያዩ ነገሮችን በተመለከተ እዚያ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ተጠያቂነት አለመኖር ነው።"
በተለይም ደግሞ የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴው ሊፋጠን እንደሚገባ ነው አምባሳደር ሬይነር ያሳሰቡት።
አምባሳደሩ ፥ "ከ3 ወራት በኃላም ሰብዓዊ ድጋፍ እጅግ ተጋላጭ ወደሆኑ አካባቢዎች በበቂ ሁኔታ ሲደርስ እያየን አይደለም። የኢትዮጵያም ሆኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በስቃይ ላይ ላሉ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ በአስቸኳይ ሙሉ እድል ሊሰጣቸው ይገባል።" ሲሉ ተናግረዋል።
አምባሳደሩ በትላንትናው ማብራሪያቸው በትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ስላሏቸው የኤርትራ ወታደሮችም ጠቅሰው አልፈዋል።
ማይክ ሬይነር ፥ "በትግራይ ክልል ያሉ የኤርትራ ወታደሮች እንቅስቃሴ እያሳሰበን ቀጥሏል። ይህ በፍጥነት እንዲያበቃ ጥሪ ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
አክለውም፥ "ግድያዎችን፣ የፆታ ጥቃቶችን፣ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በየመለከቱ ተጨባጭነት ባላቸው ሪፖርቶች ላይ በትግራይ እንደዚሁም መተከልን በመሳሰሉ ሌሎች ቦታዎች ገለልተኛ ማጣራት እንዲደረግ እንጠይቃለን" ብለዋል።
አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ስለመገኘታቸው በተደጋጋሚ ቢገልፁም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ሲያስተባብል ነው የቆየው።
Via ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ

በየሳምንቱ 1,000 ዜጎች ወደ ሀገር ሊመለሱ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በየሳምንቱ 1000 ተመላሾች ወደ አገር እንደሚገቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አስታውቋል።
በመንግስት በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት የተመላሾች ቁጥርም ይጨምራልም ሲል ገልጿል።
ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን በስፋት ወደ አገር የመመለስ ስራ መጀመሩንም አስታውሷል።
ጅዳ ሹሜሲ የህገወጥ ስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ የመጀመርያዎቹ 296 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱም ይጠበቃል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ። የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ በሀራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክእስር ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መስማማታቸውን ገለፁ። ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በታንዛኒያ ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ…
ታንዛንያ ለ1 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ስደተኞች ምሕረት አድርጋለች።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትላንትናው ዕለት በታንዛንያ የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ታንዛንያ 1 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንደምትመልስ ገልጻለች።
የታንዛንያ ፕሬዝዳነት ማጉፉሊ፤ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅን ባስተናገዱበት በትናንትናው ዕለት፤ "በሁለቱ አገራት መካከል ካለው ወዳጅነት የተነሳ [ኢትዮጵያውያን እስረኞች] በነጻ ወደ አገራቸው እንዲሄዱ መፍቀዳችንን ነግሬያቸዋለሁ" ብለዋል።
በታንዛንያ እስር ቤቶች ውስጥ ለሰባት ዓመት ያህል የቆዩ እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።
ማጉፉሊ አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዙፍ አየር መንገድ መሆኑን በመጥቀስ፤ 260 ሰው የመጫን አቅም ያለው ድሪም ላይነር አውሮፕላን በሁለት በረራ ከአንድ ኤር ባስ ጋር ተጨምሮ እስረኞቹን በአንድ ጊዜ ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚቻል ገልፀዋል።
"ዛሬ እንኳን የታሰረ እስረኛ ቢኖር ሁሉንም ለመውሰድ እስከመጣችሁ ድረስ እንዲለቀቅ እፈቅዳለሁ፤ ይህ ደግሞ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ማሳያ ነው" ብለዋል።
በታህሳስ ወር በዳሬ ሰላም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በታንዛኒያ 4 ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ባደረገው ጉብኝት ቁጥራቸው 1100 የሆኑ ኢትዮጵያውያን ታስረው ማግኘቱን ገልጾ ነበር።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በታንዛንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከ3100 በላይ ዜጎችን ከእስር አስፈትቶ ወደ አገር ቤት መመለሱንም ገልጿል። ~ BBC