"...በአሁኑ ጊዜ ትግራይ የገጠማት ችግር በዘመኗ ገጥሟት የማያውቅ ችግር ነው" - ኣቶ ኣብርሃ ደስታ (የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ)
በትግራይ ክልል ከተማ ይሁን በገጠር ውስጥ ጦርነት በመካሄዱ የሰብዓዊ ችግሩ ሁሉንም አካባቢ እንዳካለለ ኣቶ ኣብርሃ ደስታ ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ ትግራይ የገጠማት ችግር በዘመኗ ገጥሟት የማያውቅ ችግር ነውም ብለዋል።
ቢሯቸው ባደረገው ዳሰሰ ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።
ኣቶ ኣብርሃ ፥ "..የትግራይ ህዝብ ተፈናቅሏል፤ አብዛኛው ንብረቱ ተዘርፏል፤ ተወስዷል፤ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል፤ አብዛኛው ሰው የአስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል፤ በተደረገው ዳሰሳ 4.5 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል፤ ከዚህም 2.2 ሚሊዮን ህዝብ ምግብ ብቻ ሳይሆን የምግብ መስሪያም የሌለው ሆኗል፤ ስለዚህ አስቸኳይ እርዳታው ሁለንተናዊ ነው" ብለዋል።
እንደ ኣቶ ኣብርሃ ገለፃ በክልሉ አስፈላጊ የእርዳታ ምግብ አለ ነገር ግን ለማጓጓዝ የፀጥታ ስጋት አለ ፤ አሽከርካሪዎች ይሰጋሉ፤ መንግስታዊ መዋቅርም በመፍረሱ እርዳታውን ለማድረስ ኣስቸጋሪ ሆኗል።
"በጦርነቱ ሁሉም ነገር ስለተነካ ረሃብ ተከስቷል፤ በእኛ በኩል እህል አለ ለማጓጓዝ መንግስታዊ መዋቅር ያስፈልጋል፤ እሱም ፈርሷል፤ እርዳታው ወደ ህዝቡ እንዲደርስ አልቻለም ተቸግረናል" ብለዋል አቶ ኣብርሃ።
ቀጣዩን ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-01-22
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 555 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በ24 ሰዓት ውስጥ የሶስት ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 507 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ ከተደረገው ከ1.9 ሚሊዮን በላይ የላብራቶሪ ምርመራ 132,881 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 2,060 ሰዎች ሞተዋል፤ 118,513 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
@tikvahethiopia

#InjibaraUniversity
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ4 ኮሌጆች ስር በሚገኙ 21 ትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸው 525 ወንድ እና 432 ሴት በድምሩ 957 ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ (የመጀመሪያ ዙር) ነው ተማሪዎችን ያስመረቀው።
በ2007 የግንባታ መሰረት ድንጋይ የተጣለው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ነው የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረው።
በዛሬው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተማሪ ወላጆች ፣ ቤተሰቦች፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ፣ አርቲስት ታማኝ በየነ፣ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

#Gondar
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ አካባቢ እያቀረበ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ መጎብኘታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘገበ።
ሚኒስትሩ ጎንደር በመገኘት የብሪታኒያ ተራድኦ ድርጅት ለዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም እና በተመድ የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ ያደረገውን የ10 ሚሊየን ፓውንድ የሰብዓዊ ድጋፍ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ሰብዓዊ ድጋፉ በተፈለገው ቦታ ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል፡፡
ዶሚኒክ ራብ በኬንያና ሱዳን ጉብኝት ሲያደርጉ ነበር የኬንያ እና ሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ትናንት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።
ሚኒስትሩ ትናንት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።
#GondarUniversity
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ኘሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ7000 በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
#WerabeUniversity
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
በ5 ኮሌጆች ስር በሚገኙ በ14 ፕሮግራሞች በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ-629 ሴት- 503 በድምሩ 1,132 ትምህርታቸውን ከተከታሉት ውስጥ 1077 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
#JinkaUniversity
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመርቋል።
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 854 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።
የዛሬዎቹ ተመራቂዎች 501 ወንድ እና 353 ሴት ናቸው።
#DebreMarkosUniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለ12ኛ ዙር ዛሬ ጥር 15 እና ነገ ጥር 16/2013 ዓ/ም በቡሬ እና ዋናው ግቢዎች ያስመርቃል።

ፕ/ር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የበሪሳ ጋዜጣ መስራች ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ በ1960ዎቹ በብቸኝነት በአፋን ኦሮሞ ሲዘጋጅ የነበረውን በሪሳ ጋዜጣን ካቋቋሙት እና በአርታኢነት ካገለገሉ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡
በሪሳ በጊዜው በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የግል ጋዜጣ የነበረ ሲሆን በደርግ መንግስት ከተወረሰ በኋላም ብቸኛው በቋንቋው የሚታተም ጋዜጣ ነበር፡፡
የሂሳብና የፊዚክስ መምህሩ ፕሮፌሰር ማህዲ ሀሚድ ሙዴ የአፋን ኦሮሞ መዝገበ ቃላት፣ የበሪሳ ግጥሞች፣ የበሪሳ ደብዳቤዎችን እና ሌሎች መፅሀፍትን ለንባብ አብቅተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን ኑሯቸውን ውጭ ሃገር አድርገው ቆይተዋል፡፡
ባደረባቸው የልብ ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቢቆዩም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ~ ኤፍ ቢ ሲ

በኳታር ዶሃ የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የሕንጻ ግንባታ በይፋ ጀመረች።
በኳታር ዶሃ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የሕንጻ ግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ እንደምትገኝ በዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቃል።
በአሁኑ ወቅት የመሬት ቁፋሮ ሥራው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የሕንጻ ግንባታውን ለማከናወን ቤተ ክርስቲያኗ እና #አል_ኻሊጅ_የግንባታ_ተቋራጭ_ድርጅት በትላንትናው እለት በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ፣ የሃንጋሪ አምባሳደር በርናባስ ፎዶር እና ሕዝበ ክርስቲያኑ በተገኙበት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ቤተ ክርስቲያኗ ይህንን ሕንጻ መገንባት እንድትችል ድጋፍ ላደረጉት የኳታር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ፣ ለኢትዮጵያ እና ለሃንጋሪ ኤምባሲዎች፣ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እና ሌሎች ተባባሪ ተቋማት ምስጋናዋን አቅርባለች።
አምባሳደር ሳሚያ እና የሃንጋሪው አቻቸው በበኩላቸው ቤተ ክርስቲያኗ የራሷን ሕንጻ ለመገንባት ወደ ተግባር በመሸጋገሯ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አምባሳደሮቹ የሕንጻ ግንባታውን ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የሃንጋሪው አምባሳደር በርናባስ ፎዶር የሕንጻ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ የገለጹ ሲሆን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑም በጉልበት፣ በጸሎት እና በፋይናንስ የሚችለውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በ537 ስኩየር ሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን ፣ አጠቃላይ የግንባታ ወጪውም 13.5 ሚሊዮን የቀጠር ሪያል እንደሚወስድ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል።
ምንጭ፦ ዶሃ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን (የኢትጵያ ኤምባሲ-ዶሃ)

ከመተከል ተፈናቃዮች የተመለመሉ ሚሊሻዎች እንዲደራጁ መወሰኑን አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ !
ከመተከል ከተፈናቀሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተመለመሉ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ማኅበረሰቡን በዘላቂነት ከጥቃት መከላከል የሚያስችል አደረጃጀት እንዲፈጠር መወሰኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።
አቶ ደመቀ ይህን ያሉት ከመተከል የተፈናቀሉ እና በቻግኒ ራንች በተባለ መጠለያ ጣቢያ ከተጠለሉ ተጎጂዎች ጋር ውይይት ባደረጉት ወቅት ነው።
የአካባቢውን ሰላም በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ እና ከማኅበረሰቡ ጋር እርቅ የማካሄድ ሥራ እንደሚሠራም መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። ~ AlAiN
@tikvahethiopiaBOT

#MadaWalabuUniversity
በዛሬው ዕለት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።
ዛሬ ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁት መካከል መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል።
ዩኒቨርሲቲው ኮሮናን በመከላከል በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ሁለት ሺህ 324 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል። ~ ENA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia