TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በሆሳዕና በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

በሆሳዕና ከተማ በአንድ የገበያ አዳራሽ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ማውደሙን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኤርደዶ አወኖ ዛሬ እንደገለፁት በቀን 05/04/2013 ዓ/ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በርካታ የኤሌክትሮኒክስና የአልባሳት የንግድ ድርጅቶች ከነ ሙሉ ንብረታቸው አውድሟል ።

ለሦስት (3) ተከታታይ ሰዓት የቆየው የእሳት ቃጠሎ የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረገው እርብርብ ወደ ሌሎች ድርጅቶች ሳይዛመት ማጥፋት የተቻለ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ መሆኑንም ኮማንደሩ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የሆሳዕና ከተማ ኮሚኒኬሽን ፣ ፎቶ - Tikvah Family Hossana
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ርእሰ መዲና መቐለ አዲስ ከንቲባ እንደተመደበላት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ተናግረዋል። የመቐለ ከተማ ነዋሪዎችን ፀጥታ እና ደህንነት እንዲጠበቅ እንደሚሰራ ገልጸዋል። በሌላ በኩል በጊዜያዊ አስተዳደሩ ብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን ዶክተር ሙሉ ነጋ አሳውቀዋል። ፓርቲዎቹ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ እንዲሁም የካቢኔ አባል እየሆኑ እንደሆነ…
#Mekelle

የትግራይ ርእሰ መዲና መቐለ ጊዜያዊ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ናቸው።

ጊዜያዊ ከንቲባው የከተማዋ ነዋሪዎችን የልማት እና የጸጥታ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ዛሬ ከኢ.ፕ.ድ. ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ከንቲባው የከተማ የታክሲ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ሌሎች የመስሪያ ቤት አገልግሎቶች በመጀመር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

በከተማይቱ ውስጥ አብዛኛው አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ቦታዎች መከፈታቸውን እና ህዝቡም ከስጋት እየወጣ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ መሆኑን አቶ አታኽልቲ ኃ/ስላሴ አስታውቀዋል።

More : https://telegra.ph/Mekelle-12-15

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#HumanRightsWatch

በሪያድ ስደተኞች የማቆያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አስከፊ በሆነ አያያዝ ውስጥ እንደሚገኙ ሂዩማን ራይትስ ዋች ገለጸ።

ሕጋዊ የሆኑ ሰነዶች ሳይኖራቸው ሥራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ የገቡ እነዚህ ስደተኞች ተይዘው የሚገኙበት ማዕከል የተጨናነቀ ከመሆኑ ባሻገር በጥበቃዎች ማሰቃየት እንዲሁም ድብደባ እንደሚፈጸምባቸውም አመልክቷል።

የማዕከሉ ጥበቃዎች በጎማ በተሸፈነ ብረት በሚፈጸምባቸው ድብደባ ጉዳት እንደሚደርስባቸው የገለጸው ሂማን ራይትስ ዋች፤ በጥቅምት እና ኅዳር ወራት ውስጥ ቢያንስ ሦስት (3) ለሚሆኑ ስደተኞች ሞት ምክንያት መሆኑን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TigraiTV

የትግራይ ቴሌቪዥን በጊዜያዊ የትግራይ ክልል አስተዳደር እየተመራ በቅርብ ቀን መደበኛ ስርጭቱን እንደሚጀምር ዛሬ አሳውቋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ወደአየር መመለሱንም ለመመልከት ችለናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ወደ መቐለ እና ባህር ዳር በረራ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እንዲሁም መቐለ ከተማዎች አቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት እንደገና እንደሚጀምር አሳውቋል።

መንገደኞች በመመዝገብ በረራዎቹን መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,867
• በበሽታው የተያዙ - 300
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,082

አጠቃላይ 117,542 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,813 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 96,307 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

291 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደ መቐለ በረራ ተጀመረ !

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት አቋርጦት የነበረውን በረራ በዛሬው እለት መጀመሩን ኢዜአ አሳውቋል።

ዛሬ ምሽት ከአዲስ አበባ መንገደኞችን የጫነ የመጀመሪያው አውሮፕላን መቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት አርፏል።

መቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የደረሰው አውሮፕላን ሌሎች መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገልጿል።

በቀጣይ አየር መንገዱ በቀን ሁለት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በሱማሌ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የሚንስትሪ ፈተና ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ጀምሯል።

ፈተናውን በሁሴን ጊሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፈተና ጣቢያ በመገኝት ያስጀመሩት የሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ መሀመድ ፈታህ እንደገለፁት ፈተናው ከታህሳስ 7-10 የሚቆይ ሲሆን በፈተናው ላይ 41,889 ተማሪዎች መቀመጣቸውን አስታውቀዋል።

657 የፈተና ጣቢያዎች ዝግጁ መደረጋቸውን የገለፁት ሀላፊው ፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ፈተናው እንደሚሰጥ መናገራቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬ መሰጠት ተጀመረ። #SRTA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ #ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ የአዲስ አ በባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Tigray

አቶ አብርሃ ደስታ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዋና ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

አቶ አብርሃ ደስታ በመቐለ ዩንቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ክፍለ ትምህርት አስተማሪ ነበሩ።

በሌላ በኩል አቶ ሚሊዮን ኣብርሃ የደቡብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተደርገው መሾማቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በአ/አ 11 መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች ታሽጉ !

በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ መጠጥ ቤቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ባለሙያዎች ባደረጉት የድምፅ ልኬት አካባቢ እና ህብረተሰቡ የሚያዉክ ድምጽ ማዉጣታቸዉ በመረጋገጡ የማስተካከል እርምጃ እንዲወሰድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዉ ነበር።

አብዛኛዎቹ መጠጥ ቤቶች ቢያስተካክሉም 11 የሚሆኑት መጠጥ ቤቶች የሚለቁትን የድምጽ መጠን ባለማስተካከላቸዉ እንደታሸጉ የአካባቢ ብክለት ኢንስፔክሽን ቡደን መሪ አቶ ሙላቱ ወሰኑ ተናግረዋል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በአቂቃ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የሚገኙት 11 መጠጥ ቤቶች ከተፈቀደዉ 45 ዴስባል የድምፅ መጠን በላይ አልፍዉ እሰከ 85 ዴሲባል መጠን ሲጠቀሙ መገኝታቸዉ ተረጋግጧል።

በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸዉም ሊያስተካክሉ ባለመቻላቸዉ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ ተወስዶባቸወል።

በዚህም መሰረት፦

- ከዚራ ባርና ሬስቶራንት
- ሰለሞን ጀርመን ሀዉስ
- ፋልከን ላወንጂ
- ሴራኒ ባርና ሬስቶራንት
- አዲናስ ባርና ሬስቶራንት
- ዊንግ ላዉንጂ
- ፎድ ዞን ኤልቢስ ትሮ ባርና ሬስቶራንት
- ሚሚስ አዲስ ባርና ሬስቶራንት
- ሮያል ባርና ሬስቶራንት እንዲሁም ተክላኋይማኖት ግሮሰሪ ታሽገዋል፡፡

ህብረተሰቡ በሚኖርበት አካባቢ ብክለት የሚያደርሱ ተቋማትን በ6713 የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረስ እንደሚችል መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ፦ የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SNNPRS

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከዛሬ ታህሳስ 07 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መሰጠት ተጀመሯል።

ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀን ይሰጣል።

አጠቃላይ 292,769 ተማሪዎች ለፈተናው ተቀምጠዋል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተና የማይሰጥባቸው ጣቢያዎች ቢኖሩም እንደ ጣቢያ በጣቢያቸው አይፈተኑም እንጂ በፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች አቅራቢያ ወዳለው ወደ ሌሎች ፈተና ጣቢያዎች ሄደው እንዲፈተኑ ሁኔታዎች መመቻቸቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ነዋሪው የጦር መሳሪያዎችን እንዲያስረክብ ያሰቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቋል።

በሕጋዊም ሆነ በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች እስከ ማክሰኞ ታኅሳስ 6/2013 ዓ.ም ድረስ መሳሪያቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የጸጥታ አካላት እንዲያስረክቡ መታዘዙን ይታወሳል።

የጦር መሳሪያዎችን ለማስረከብ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደሚሰበሰቡ እና በፍተሻውም ትጥቅ የሚገኝባቸው ግለሰቦች "በሕግ ተጠያቂ ይሆናል" መባሉ አይዘነጋም።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እስካሁን በተደረገው የጦር መሳሪያዎችን መሰብሰብ ሂደት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያዎች መሰብሰባቸውን አሳውቆ መጠኑም በሁሉም አካባቢ የተገኘው የጦር መሳሪያ መረጃ ተጣናቆ ሲያበቃ የሚታወቅ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ BBC
PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ አረፉ !

አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ማረፋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ84 አመት እድሜአቸው ማረፋቸው ታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia