#የኮማንዶ_አባላት_ተሳትፎ!
በራያ ግንባር ተሰልፎ ያለው የኮማንዶ ኃይል ኮንክሪት ምሽጎች እና አስቸጋሪ ተራራማ ቦታዎችን በመስበር ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ በልዩ ዘመቻዎች ሃይል የኮማንዶ አዛዥ የሆኑት ኮ/ል ከማል በሪሱ ገልጸዋል።
ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ቆርጦ በመግባት ፤ የታፈነ ወገንን በማስለቀቅ እና በቀጥታ ውጊያዎች ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት የኮማንዶ አባላት የላቀ ጀግንነት መፈፀማቸውን እና እየፈፀሙም እንደሚገኙ ኮ/ል ከማል ገልፀዋል።
ቀደም ሲልም በሁመራ ግንባር ቅርቅር በተባለው ቦታ የተያዘውን ስትራቴጂክ ቦታ በማስለቀቅ እና የህውሓት ቡድን ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንፃር ምቹ የሆኑትን የመሬት ግፆችን እንዳይጠቀባቸው በማድረግ አንጻር ትልቅ ስራ መሰራቱን ኮሎኔል ከማል ተናግረዋል።
* መረጃውን የላከልን በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#ማስታወሻ
* በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።
* በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግፅ ለገፅ ትምህርት በግል ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28 ይጀምራል።
* በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
* በሌሎች ክልሎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደየ ክልሎቹ ዝግጁነት ከታህሳስ 1 እስከ ታህሳስ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል።
* የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መንግስት የፀጥታ ጉዳዮችን እንዳረጋገጠ ይሰጣል።

አጫጭር መረጃዎች ፦
1. መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከተማን ለመቆጣጠር የወታደራዊ ዘመቻውን ጀምሯል ፤ ዛሬ ከረፋድ 4:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ዙሪያ የከባድ መሳሪያ ድምጽና ፍንዳታዎች መሰማት እንደጀመሩ ቢቢሲ፣ አልጀዚራና ሮይተርስ ዘግበዋል።
2. የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ደብረጽዮን ለሮይተርስ በጽሁፍ መልዕክት መቐለ ላይ "የከባድ መሳሪያ ድብደባ" እየተካሄደ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
3. የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም የሀገር መከላከያ ሰላማዊ ሰዎች የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት አይፈጽምም ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
"በመቐለ ከተማም ሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደኅንነት የፌደራል መንግሥቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ ይቀጥላል" በማለት ሰራዊቱ ለሰላማዊ ሰዎች ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
4. የፌዴራል የህብረት ስራ ኤጀንሲ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደትግራይ ለማሰረጨት ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን አሳውቋል።
5. ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን የሸሹ ዜጎቻችን ቁጥር ከ43 ሺህ አልፏል።
6. ፍሊፖ ግራንዲ (ከUNHCR) ትላንት በምስራቃዊ ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን የተደዱ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።
አብዛኞቹ ስደተኞች ውጊያው ከቆመና ፣ ደህንነታቸው የሚጠበቅ ከሆነ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን ገልፀዋል።
ህዳር 19/2013

#FederalPoliceCommission
ዛሬ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በመሆን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም "አገር አፍራሽ መረጃ" ያሰራጫሉ ባላቸው ግለሰቦች እንዲሁም በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን አሳውቋል።
* የስም ዝርዝራቸው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በመሆን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም "አገር አፍራሽ መረጃ" ያሰራጫሉ ባላቸው ግለሰቦች እንዲሁም በ27 ወታደራዊ ሹማምንት ላይ የመያዣ ትዕዘዝ መውጣቱን አሳውቋል።
* የስም ዝርዝራቸው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከተማ መግባቱን አሳውቀዋል።
በተካሄደው ዘመቻ ላይ ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ሳይሆኑ ፣ ከተሞችና ቅርሶች ሳይጎዱ መቐለ ለመግባት መቻሉን ነው የገለፁት።
ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ሕዝብ በህግ ከሚፈለጉት "የህወሓት ቡድን አባላት" ጋር እንዳልሆነ በተግባር አስመስክሯል ብሏል።
* ማምሻውን ያሰራጩት መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

#BREAKING
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሠራዊት መቐለን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል።

የመከላከያ ሰራዊት መቐለን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯል።
ሰራዊቱ ከ7 ሺህ በላይ የሰሜን እዝ አባላትን ነጻ አውጥቷል።
የሰሜን እዝ ማዘዣን ተቆጣጥሯል።
በህግ የሚፈለጉ የህወሃት ቡድን አባላትን እያደነ ይገኛል።
የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም የሆኑት ጀነራል ብርሀኑ ጁላ የሠራዊቱን ድሎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,406
• በበሽታው የተያዙ - 492
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 744
አጠቃላይ 108,930 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,695 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 68,250 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
309 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#UPDATE
በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁ ተገለፀ።
ጠ/ሚ ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ “በትግራይ ክልል ስናካሂድ የነበረው የህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን እና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ” ብለዋል።
“ቀጣይ ትኩረታችን ክልሉን መልሶ መገንባት እና ለሰብአዊ ድጋፎችን መድረስ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።
በዚሁ ጊዜም የፌደራል ፖሊስ 'በህግ የሚፈለጉ' ወንጀለኛ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራ መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#FDREDefenseForce
ጦርነቱ ማብቃቱን ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አሳውቁ።
ከዚህ በኃላ የተበታተነ ፣ ተቆርጦ የቀረ ፣ ያመለጠ፣ የተደበቀ ኃይል የመለቃቀምና ወደ ህግ የማቅረብ ስራ ነው የሚቀረው ብለዋል።
ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ፥ የህወሓት ቡድን የመጨረሻው ምሽጉ በመደርመሱ እና በሰራዊቱ እጅ በመግባቱ "ወሳኙ ጦርነት" አልቋል ብለዋል።
በውጊያ ደረጃ የሚገለፅ ተልዕኮ የለንም ሲሉም አሳውቀዋል።
በቀጣይ ሰራዊቱ ከፖሊስ ጋር በመሆን ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረቡን ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ጄኔራሉ ብርሃኑ ጁላ ፥ "በህግ የሚፈለጉትን አካላት የገቡበት ገብተን እንለቅማቸዋለን፣ በሰላም እጅ የሚሰጥ ካለ ወደ ፍርድ እናቀርባቸዋለን ፤ እጅ አልሰጥም ብሎ የሚገዳደረውን እንጨርሰዋለን" ሲሉ ዝተዋል።

የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለጸ !
በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
#MoSHE ከአንድ (1) ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን 3 የትምህርት ሴሜስተር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ለኢቲቪ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
#MoSHE ከአንድ (1) ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን 3 የትምህርት ሴሜስተር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ለኢቲቪ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
1. የመከላከያ ሰራዊት የመቐለ ኤርፖርት ፣ የክልሉን አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዲሁም ቁልፍ የሆኑ ህዝባዊ እና ሌሎች ተቋማትን በዋናነት መቆጣጠሩን ዶክተር አብይ አህመድ ገልፀዋል።
2. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ለሮይተርስ ጦራቸው ከመቐለ አካባቢ መልቀቁን ጠቁመዋል ፤ በፍልሚያው ግን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ዶክተር ደብረፅዮን "የእራስን እድል የመወሰን መብታችንን ለመከላከል ወራሪዎችን እስከ መጨረሻው እንታገላቸዋለን" ነው ያሉት።
3. ትላንት ምሽት ኤርትራ አስመራ ከተማ 6 የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱን በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጿል። ኤርትራን በሚመለከት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት 'ህወሓት' ወደ ኤርትራ ለሶስተኛ ጊዜ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን ገልፀዋል።
4. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጡ አሳውቋል።
5. በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የተጠናቀቀውን የህግ ማስከበር ዘመቻን አስመልክቶና በቀጣይ ሁኔታ ላይ ከጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በመቐለ ከተማ መግለጫ እንደሚሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ገልፀዋል።
3ኛው ምዕራፍ የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል ተጠናቆ አሁን ላይ ወደ መልሶ ማደራጀት መገባቱን ሌ/ጄኔራሉ እንደገለፁት አብመድ ዘግቧል።
6. የUNHCR ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀዋል። "ሆኖም ግን በቀን ከ5 መቶ እስከ 6 መቶ የተፈናቃዮች ቁጥር ትንሽ የሚባል አይደለም" ብለዋል።
በሌላ በኩል በሱዳን የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመርዳት የሱዳን መንግሥት $147 ሚሊየን እንዲያስፈልገው መግለፃቸውን SBS አስነብቧል።
ህዳር 20/2013 ዓ/ም