TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ባህር ዳር ምን ተፈጠረ ?

ዛሬ ምሽት ከ5:00 በኃላ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ፍንዳታ እና የተኩስ ልውውጥ ነበር።

መኮድ አካባቢ 2 የቦንብ ፍንዳታዎች ነበሩ። ከፍንዳታዎቹ በኃላ የተኩስ ልውውጥ ነበር።

የፀጥታ ኃይሎች ወደ ስፍራው ደርሰው ተቆጣጥረውታል።

አንድ ስማቸው በይፋ ያልተገለፀ የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፥ "ብዙም ችግር የለም፤ ወዲያው ተቆጣጥረነዋል፣ አካባቢው ተረጋግቷል ፤ ስለጉዳዩ ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ መገለጫ ፦

"የተከበራችሁ የክልላችን ህዝቦች አሁን ምሽት ላይ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ የተፈጠረ ፍንዳታ የነበረ ቢሆንም ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በከተማችን የተለየ የመብራተ መቆራረጥ አልተፈጠረም፡፡ ከተማችን በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡

ፍንዳታው ከጁንታው ቡድን የአጥፍቶ ጠፊነት የሽብር ተግባር ጋር ስለመገናኘት አለመገናኘቱ መረጃዎቹ በሚመለከተው አካል በመጣራት ላይ ነው።

ጉዳዩ ተጣርቶ እንዳለቀ እናሳውቃለን፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጎንደር ፦

የአማራ ክልል መንግስት በጎንደር አዘዞ አካባቢ ከ5:00 በኃላ ልክ የባህር ዳሩን አይነት ፍንዳታ መፈፀሙን አሳውቋል።

በአሁን ሰዓት ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ ገልጿል።

የክልሉ መንግስት ሁሉም ህብረተሰብ ተረጋግቶ አካባቢውን እና እራሱን እንዲጠብቅ በጥብቅ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አማራ ክልል ፖሊስ ፦

የአማራ ክልል ፖሊስ በባህር ዳር ከተማ (መኮድ) እና ጎንደር ከተማ (አዘዞ) አካባቢ ፍንዳታዎች ተከስቶ እንደነበር እና አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ እንደቆመ አረጋግጧል።

የፍንዳታውን መንስኤ ፣ ያደረሰውን አካል ማንነት እና የደረሰ ጉዳት ካለ ሙሉ መረጃው በመጣራት ላይ ስለሚገኝ ለህዝብ ይገለፃል ተብሏል።

ህዝቡ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚናፈሱ ተጨባጭ ባልሆኑ መረጃዎች መሸበር እንደማይገባውም መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ ፦

ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር #ሮኬት ተተኩሷል።

በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የህወሓት ቡድን በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ ሞክሯል ብሏል የፌዴራል መንግስት።

ይህም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን ዐቅሙን እየሞከረ መሆኑን ያመለክታል ሲል ገልጿል።

ዝርዝሩን መርማሪ ቡድን ተመድቦ እያጣራው ሲሆን በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopiap
#ATTENTION

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ያምፕ ቀበሌ" የታጠቁ ኃይሎች በነዋሪው ላይ ተኩስ መክፈታቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

በአሁን ሰዓትም በከተማው አካባቢ 'የተኩስ ድምፅ' እንዳለ ገልፀዋል።

በቂ የሆነ የፀጥታ ኃይል የለም ፤ የሚመለከተው አካል ይህን መልዕክት ተመልክቶ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፦

የፕሬዜዳንታዊ ምርጫው የሁሉም ግዛቶች ውጤት ታውቋል።

ጆ ባይደን አጠቃላይ 306 የውክልና ድምጽ ሲያገኙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 232 ድምፅ አግኝተዋል።

ባይደን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል።

ከአጠቃላይ 538 ድምጽ ምርጫውን ለማሸነፍ 270 እና ከዚያ በላይ ድምጽ ነው የሚያስፈልገው።

ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት እስካሁን ሽንፈታቸውን አልተቀበሉም።

በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ የመራጮች ድምጽ በድጋሚ እንዲቆጠር በመጠየቅ ክስ መስርተዋል።

ይህ ጉዳይ በብዙዎች ከመተቸቱ ባለፈ የፓርቲያቸውን ሰዎች ለሁለት መክፈሉን CNN ዘግቧል።

Via AlAin News/CNN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ ፦ ትናንት ምሽት ወደ ባሕርዳር እና ጎንደር #ሮኬት ተተኩሷል። በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። የህወሓት ቡድን በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ ሞክሯል ብሏል የፌዴራል መንግስት። ይህም ከመሞቱ በፊት የመጨረሻውን ዐቅሙን እየሞከረ መሆኑን ያመለክታል ሲል ገልጿል። ዝርዝሩን መርማሪ ቡድን ተመድቦ እያጣራው ሲሆን በቀጣይ…
#UPDATE

'ህወሓት' ትላንት ምሽት በጎንደር እና ባህር ዳር ለተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በትግራይ አከባቢዎች ለተካሄደው የአየር ድብደባ የተሰጠ አፀፋዊ ምላሽ ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው፥ "የሚሳኤል ጥቃቱ ያነጣጠረው በባህርዳርና ጎንደር ከተማ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ነው" ሲሉ ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ያምፕ ቀበሌ" የታጠቁ ኃይሎች በነዋሪው ላይ ተኩስ መክፈታቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። በአሁን ሰዓትም በከተማው አካባቢ 'የተኩስ ድምፅ' እንዳለ ገልፀዋል። በቂ የሆነ የፀጥታ ኃይል የለም ፤ የሚመለከተው አካል ይህን መልዕክት ተመልክቶ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ ቀርቧል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፥ "የሕውሓት ቅጥረኛ ቡድን በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ባደረሰው ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት አለፈ" ሲል አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ፥ በሕወሓት የሚደገፈው የጥፋት ቡድን ከትናንት በፊት ጀምሮ በውብግሽ ፣ ያምፕ እንዲሁም ቂዶህ ቀበሌዎች ውስጥ ባደረሰው ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት አልፏል ብላል።

በተጨማሪም የጥፋት ኃይሎች ከወምበራ - ቡለን - ድባጤ - ቻግኒ በሚወስደው መስመር ሲንቀሳቀስ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አስቁመው በንፀሃን ተሳፋሪዎች ላይ ዝግናኝ የሆነ ጥቃት አድርሰዋል ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሀገሪቱ አሁን ባለችበት የፀጥታ ሁኔታ በምንም አይነት ምክንያት "ርችት መተኮስ" የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን መልዕክት በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን አስታውቋል።

@tikvahethhiopiaBot @tikvahethiopia
ከእስር የተፈቱት ፖለቲከኞች ፦

ለአራት ወራት ገደማ በእስር ላይ የቆዩ ሁለት አነግ መካከለኛ አመራሮች እያንዳንዳቸው የ20 ሺህ ብር ዋስትና ተፈተዋል።

ዛሬ ከእስር የተፈቱት የኦነግ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ ለሚ ቤኛ እና በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ድርጅታዊ ጉዳዩች ኃላፊ አቶ ዳዊት አብደታ ናቸው።

ከሁለቱ አመራሮች ጋር አብሮ ክስ የቀረበበት አቶ ደምሴ በንቲ የተባለ የኦነግ አባልም በ10 ሺህ ብር ዋስትና በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቋል።

በሌላ በኩል ፦

እንደ አዲስ አበባው ባልደራስ የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማ ደረጃ ለማታገል የተቋቋመው ድሬዳዋ አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ መስራች ከ4 ወራት እስር በኋላ ተፈተዋል።

የድሬዳዋ ነዋሪዎች አንድነት ፓርቲ የተሰኘው ፓርቲ መስራች አቶ ሲሳይ አየለ የታሰረው በፌስቡክ ገጻቸው ካወጣው መረጃ ጋር በተያያዘ ነበር።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ፣ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የአልሸባብ እና አይኤስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ'

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸው 14 የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለሚዲያዎች ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ አሳውቋል።

ህዳር 5/2013 ዓ/ም

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ ጉዳት ደረሰ'

አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት 'ቦንብ' በእጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

* በዚህ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈነዳው የእጅ ቦንብ በአንድ የ13 ዓመት ህፃን ላይ ከፍተኛ እንዲሁም በ4 ህፃናት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

* በጉዳዩ ዙሪያ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን ዝርዝር መረጃ አሰራጭቷል ፤ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,343
• በበሽታው የተያዙ - 564
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 104

አጠቃላይ 102,321 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,565 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,675 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

321 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

የቢቢሲው ጋዜጠኛ ሞውሊድ ሃጂ አብዲ ኤርትራ አስመራ ከተማ ምሽቱን በ3 ሚሳኤል መመታቷን ገልጿል።

ጋዜጠኛው የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር እና አስመራ ኤርፖርቱ አቅራቢ ጥቃት ሳይደርስ እንዳልቀረ ፅፏል።

ኤርትራን አስመልክተው የሚዘግቡ ሚዲያዎችም "አስመራ" ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱ ፤ በኃላም ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እንደነበር ዘግበዋል።

* የኤርትራ መንግስት ይፋዊ መረጃ እስካሁን አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ ፦

ታማኝ የሆኑ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ዛሬ በአስመራ ከተማ 3 ፍንዳታዎች መሰማታቸውን እንደገለፁ ጋዜጠኛ ሳራ ክሬታ አሳውቃለች።

አንደኛው ፍንዳታ የተሰማው ኤርፖርቱ አቅራቢያ ነው።

* የኤርትራ መንግስት ይፋዊ መረጃ እስካሁን አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ'

"ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል።

በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም።

* የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia