TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጁ እንደሚሆን የአ/አ ምክትል ከንቲባ አረጋገጡ!

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጁ እንደሚሆን በዛሬው ጉብኝታቸው ማረጋገጫ እንዳገኙ ገልፀዋል።

"የተለያዩ አካላትን በጥምረት ያሳተፈው ይህ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት ወቅቱን ባማከለ መንገድ ለበዓሉ ዝግጁ እንደሚሆን በማወቄም ተደስቻለሁ" ሲሉ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 4/2013 ዓ/ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነባሮቹን የ10 ፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የሁለት መቶ ብር ኖትን ወደ ሥራ ታስገባለች።

የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል።

የብር ኖቶቹን ለምን መቀየር አስፈለገ ?

- መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ፣

- ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ፣

- ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ ለማስቀረት ፣

እርምጃው የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም እንደሚያግዝ ከPMO ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል። የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት ይተገበራል።

በገንዘብ ቅያሬው ሂደት ውስጥ የጸጥታ አስከባሪ አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ ተብሏል።

ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።

የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ያስታወቁትን የግብይት ገንዘብ ዓይነቶች ለውጥን በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንደሌለ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር (Ethiopian Bankers Association) ለአል ዓይን አስታወቀ፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ቀርበውልናል ያሉት የማህበሩ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ግርማ “በይፋ የደረሰን ነገር የለም፡፡ የተሟላ መረጃም እያገኘን አይደለም፣ ስለፋይዳና ተጽዕኖው ልንናገርም አንችልም” ሲሉ ገልጸዋል።

የብር ለውጡን በተመለከተ በዚህ ሳምንት ሊሰጡ የሚችሉት መግለጫ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

https://telegra.ph/AlAin-09-14

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ የታተሙት የብር ኖቶች አይነት፣ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች እና ምስሎች ፦

ተከታታይ ቁጥሮች ፦

የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ።

ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦

የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው።

ጎርባጣ መስመሮች ፦

የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል።

ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደህንነት መጠበቂያ ምልክት።

የደህንነት መጠበቂያ ክር ፦

የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE ፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተፅፎ ይገኛል።

የውሃ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል።

ትይዩ ምልክት ፦

የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘብ በስተኃላው ካለው ተመሳሳይ ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ።

ፈሎረሰንስ ምልክት ፦

አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፍሎረሰንት ምልክት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አጫጭር መረጃዎች ፦

- አሁን በገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል።

- አሮጌው የብር ኖት በአዲሱ ብር በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ ይውላሉ።

- ገንዘቡን የመቀየር ሂደቱ ከዛሬ ጀምሮ ይጀመራል። አብዛኛው የመቀየር ስራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ይሰራል።

- በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ዝግጅት ተደርጓል።

- ለአዲሱ የገንዘብ ህትመት 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።

- በጎረቤት ሀገራት የሚገኝ የኢትዮጵያ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባ መከላከያ ሰራዊት ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል።

- የግል ባንኮች ሀሰተኛ የብር ኖቶችን እንዳይቀበሉና ይህንን በሚያደርጉ ላይ ባንኩን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሲሠሩ የቆዩት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ፣ ከቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ።

ከመስከረም 4/2013 ዓ/ም ጀምሮ አቶ ኃይለየሱስ ኃላፊነት ያለባቸው ውሳኔዎችን ከማስተላለፍ የታገዱ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት አዲስ ብድር እንዳይፈቅዱ ፣ የተፈቀደ ብድር ካለ እንዳይለቀቅ መታገዱን የሪፖርተር ጋዜጣ መረጃ ያሳያል።

በአቶ ኃይለየሱስ ምትክ የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ዋና የኢኮኖሚ ባለሙያና ምክትል ገዥ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) እንደሚሾሙ ከልማት ባንክ የቦርድ አባላት ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አጫጭር መረጃዎች ፦ - አሁን በገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል። - አሮጌው የብር ኖት በአዲሱ ብር በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ ይውላሉ። - ገንዘቡን የመቀየር ሂደቱ ከዛሬ ጀምሮ ይጀመራል። አብዛኛው የመቀየር ስራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ይሰራል። - በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ…
"ከ100 ሺህ ብር በላይ ያላቸው ሰዎች በ1 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲቀይሩ/እንዲለውጡ ይጠበቃል። ትንንሽ ገንዘብ ያላቸው ከአንድ ወር በላይ የሚወስደው ጊዜ ከአንድ ወር በተጨማሪ ሌላ አንድ ወር / አንድ ወር ተኩል ከወሰደ እንደሁኔታው አይተን እንወስናለን። ዞሮ ዞሮ ሁሉም ስራ እስከ ሶስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።" - ዶ/ር ይናገር ደሴ (የብሄራዊ ባንክ ገዥ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ገብረየሱስ ብርሃነ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት አድርጎ ሾሟቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከግንቦት 28/2005 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ከነገ መስከረም 5/2013 ዓ/ም ጀምሮ ኃላፊነቱ እንደተነሳላቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሟል!

አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ለስርጭት ዘግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አዲሱን የብር ኖት በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የብር ኖት ቅያሬውን ለማከናወን ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

አዲሱን የብር ኖት ለማሳተም 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ውጭ መደረጉንም ገልጸው፤ በሁሉም ክልሎች በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

የብር ቅያሬው በውክልና የማይከናወን በመሆኑ መታወቂያ በመያዝ ባለቤቱ ብቻ ማከናወን ይኖርበታል ብለዋል።

ከአጎራባች አገራት የሚገባን ህገ ወጥ የሆነ ገንዘብ ለመቆጣጠር በድንበር አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑን ዶክተር ይናገር መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ ሆነ!

ዛሬ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛው ክልላዊ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል።

ከአጠቃላዩ 190 የክልሉ ምክር ቤት ወንበሮች 189ኙ በህወሓት የተያዙ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በምክር ቤቱ አንድ (1) ወንበር አግኝቷል፡፡

ባይቶና በአንድ ወንበር ምክር ቤት የገባ ፓርቲ ሆኗል፡፡

ምንጭ፦ ሚሊዮን ኃይለስላሴ (DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia