TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ የተመረቀው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መመርመሪያ ኪት ማምረቻ ፋብሪካ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ስራ ለሰሩት ዶ/ር አርከበ እቁባይ ምስጋና አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም ተስፋ የጣለበት የኦክስፎርድ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ክትባት ምርምር እንዲቆም ተደረገ። የመጨረሻ የክሊኒካል ሙከራ ላይ የነበረው እና ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የቆየው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ከመድሃኒት አምራቹ አስትራዜኔካ ኩባንያ ጋር እያበለጸጉት የነበረው የኮሮና ክትባት ነበር። ምርምሩ ለጊዜው ባለበት ይቁም ተብሏል። ምክንያቱ ደግሞ የክትባት ቅንጣቱን የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ…
#UPDATE

ከጥቂት ቀናት በፊት ተቋርጦ የነበረው አስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እየሰሩት ያለው ዓለም ተስፋ የጣለበት የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ዳግም ሊጀመር መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

የክትባት ሙከራው እንዲቆም የተደረገው በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ አንድ የሙከራው ተሳታፊ ላይ የጎንዮሽ ችግር በመታየቱ ነበር።

ባሳለፍነው ማክሰኞ አስትራዜኔካ፤ ምርምሩ እንዲቆም የተደረገው በሙከራው ተሳታፊ ላይ የታየው የጤና ችግር ከክትባቱ ጋር ይያያዝ ፤ አይያያዝ እንደሆነ ለመፈተሽ እንደሆነ ተናግሯል።

ይሁን እንጅ ትላንት ቅዳሜ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የክትባቱን ሙከራ መቀጠል እንደሚቻል አስታውቋል።

ምርምሩ ተሳታፊ ያጋጠማቸው ጤና እክል በተመለከተ ሚስጢር ለመጠበቅ ሲባል እንደማይገልፅ የተነገረ ቢሆንም ኒው ዮርክ ታይምስ በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የሚገኙት የሙከራው በጎፈቃደኛው በአንድ በኩል ያለው የአከርካሬ አጥንታቸው ላይ ያሉ ነርቮች መቆጣት እንዳጋጠማቸው ዘግቧል።

Via BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 የፊልድ ሆስፒታል በዛሬው እለት በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡ ሆስፒታሉ ከባድ የኮቪድ ምልክቶች ለሚያሳዩ ህመምተኞች ህክምና የሚሰጥ ሲሆን አቅማችንን የሚያሻሽሉ በቂ የህክምና መሳሪያዎችም እንዲሟሉም አድርገናል። ሆስፒታሉ በቀጣይ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ለአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጪ የህክምና ቡድኖች ስልጠናን ይሰጣል፡፡" - ዶክተር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤት ለቤት እየዞረች ትምህርት የምታስተምረው ቱርካዊቷ መምህርት!

(BBC)

በምስራቃዊ ቱርክ በምትገኘው ቫን ግዛት የምትገኝ ጋምዜ አርስላን የተባለች መምህርት በበይነ መረብ ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ተማሪዎች ቤት ለቤት እየዞረች ትምህርት ትሰጣለች።

"በትምህርት ቤታችን ውስጥ ኢንተርኔት አለ ነገር ግን በዚያ ማስተማር እልቻልንም። ምክንያቱም በርካታ ወላጆች በቤት ውስጥ ኢንተርኔት የላቸውም" በማለት ሃበርቱርክ ለተባለው የዜና ወኪል ተናግራለች።

"ነጭ ሰሌዳዬን ይዤ ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እየሄድኩ አስተምራለሁ" በማለት የምትናገረው ጋምዜ በቫን ቱስባ ግዛት ውስጥ ያሉ መንደሮችንም ማካለል አለባት።

በየቀኑም ማስተማር ፣ የቤት ስራቸውን በአግባቡ ሰርተው እንደሆነ መቆጣጠርና መከታተል ከዚያም በተጨማሪ አካላዊ ርቀታቸውንና ንፅህናቸውን በጠበቀ መልኩ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዲከናወንም ዋናው ኃላፊነት የሷ ነው።

የጋምዜ አርስላን መልካም ተግባር ከተሰማ በኋላ በርካቶች እያሞገሷትና እያወደሷት ይገኛሉ። የተለያዩ ሚዲያ ቀልብንም መሳብ ችላለች። 'ኢንተርኔት ላይኖር ይችላል ግን መምህርት ጋምዜ አለች' በሚልም በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ፕሮግራም ተሰርቶላት ነበር ፤ የአካባቢው ባለስልጣናትም አመስግነዋታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር ከ1,000 አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,162 የላብራቶሪ ምርመራ 413 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 490 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 64,301 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,013 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 24,983 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

አፋር የመንግስትን እና የህዝብን አስቸኳይ ድጋፍ እና እርዳታ ይሻሉ!

ይህን ከባድ የተፈጥሮ አደጋ በቸልታ የሚታለፍ አይደለም።

አፋር የሃገራችን ዳርድንበር ለዘመናት እየጠብቁ የቆዩ ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በእኩልነት እና በክብር ተቀብለው የሚያስተናግዱ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ጋር ተካፍለው መብላት ህይወታቸው የሆነ የኢትዮጵያ ውድ ህዝቦች ናቸው።

እነዚህ ወገኖቻችን ባጋጠማቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ከ200 ሺህ ህዝብ በላይ ተፈናቅሎ የመንግስትን እና የህዝብን ድጋፍ እየጠበቁ ነው።

ሰብዓዊነት ሁሉም ሊሰማው ይገባል። አንድ አካላችን ሲታመም ሁሉም አካላችን እንደሚታመም ሁሉ የአፋር ወገኖቻችን ጉዳት እና ህመም እኛንም ሊያመን ይገባል።

በሌላ በኩል ፦

ጣና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩ የተነሳ ውሃው ተመልሶ በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን እያጥለቀለቀ ይገኛል።

በዚሁ ምክንያት እስካሁን ድረስ በደንቢያ ወረዳ ከ600 በላይ ሰው እንደተፈናቀለ መረጃ የደረሰኝ ሲሆን ፎገራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች፤ ሊቦ ከምከም ወረዳ ደግሞ አራት ቀበሌዎች በውሃ ተጥለቅልቀዋል።

የውሃው መጠን አሁን ካለው በላይ ጨምሮ ጉዳት እንዳይደርስ ሕዝቡ ከአካባቢው እንዲነሳና ወደ ደረቅ ቦታ እንዲሰፍር ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ክትትል ሊያደርጉ ይገባል።

(ኢስታዝ አቡበክር አህመድ፣ መልካሙ ሹምዬ ኮከብ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጁ እንደሚሆን የአ/አ ምክትል ከንቲባ አረጋገጡ!

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጁ እንደሚሆን በዛሬው ጉብኝታቸው ማረጋገጫ እንዳገኙ ገልፀዋል።

"የተለያዩ አካላትን በጥምረት ያሳተፈው ይህ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ትልቅ ፕሮጀክት ወቅቱን ባማከለ መንገድ ለበዓሉ ዝግጁ እንደሚሆን በማወቄም ተደስቻለሁ" ሲሉ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስከረም 4/2013 ዓ/ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነባሮቹን የ10 ፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የሁለት መቶ ብር ኖትን ወደ ሥራ ታስገባለች።

የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል።

የብር ኖቶቹን ለምን መቀየር አስፈለገ ?

- መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ፣

- ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ፣

- ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ ለማስቀረት ፣

እርምጃው የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም እንደሚያግዝ ከPMO ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል። የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት ይተገበራል።

በገንዘብ ቅያሬው ሂደት ውስጥ የጸጥታ አስከባሪ አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ ተብሏል።

ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።

የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ያስታወቁትን የግብይት ገንዘብ ዓይነቶች ለውጥን በተመለከተ የደረሰው መረጃ እንደሌለ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር (Ethiopian Bankers Association) ለአል ዓይን አስታወቀ፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ቀርበውልናል ያሉት የማህበሩ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ግርማ “በይፋ የደረሰን ነገር የለም፡፡ የተሟላ መረጃም እያገኘን አይደለም፣ ስለፋይዳና ተጽዕኖው ልንናገርም አንችልም” ሲሉ ገልጸዋል።

የብር ለውጡን በተመለከተ በዚህ ሳምንት ሊሰጡ የሚችሉት መግለጫ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

https://telegra.ph/AlAin-09-14

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ የታተሙት የብር ኖቶች አይነት፣ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች እና ምስሎች ፦

ተከታታይ ቁጥሮች ፦

የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ።

ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦

የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው።

ጎርባጣ መስመሮች ፦

የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል።

ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደህንነት መጠበቂያ ምልክት።

የደህንነት መጠበቂያ ክር ፦

የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥ NBE ፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተፅፎ ይገኛል።

የውሃ ምልክት ፦

ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልክት ይታያል።

ትይዩ ምልክት ፦

የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘብ በስተኃላው ካለው ተመሳሳይ ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ።

ፈሎረሰንስ ምልክት ፦

አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፍሎረሰንት ምልክት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia