TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
''ኮቪድ-19 በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል''-ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል መግለፃቸውን BBC አስነብቧል።

ዶክተር ቴድሮስ በጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከ2 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይሎች ተመረቁ!

በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይሎች የምረቃ ስነ ስርዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከናውኗል፤ ዛሬ የተመረቁት የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቁጥር 1000 እንደሚጠጉ ተነግሯል።

ተመራቂዎቹ ለአስራ ሁለት (12) ቀናት የተሰጣቸውን ስልጠና ተከታትለው ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር የተገኘው መረጃ ያሳያል ፤ ስልጠናው ቴክኒካዊ ጉዳዩችን ያካተተ አለመሆኑም ተገልጿል።

ስልጠናው የደቡብ ክልል አካባቢዎች ተመድበው ሲሰሩ የቆዩት የልዩ ኃይል አባላት ፤ በሲዳማ ክልል ካለው ህብረተሰብ ሲቀላቀሉ በሚኖራቸው መስተጋብር ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፊሊጶስ ኖሆም ስልጠናውን በሚመለከተት ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ የተናገሩት ፦

"የልዩ ኃይል አባላቱ ከዚህ በፊት በደቡብ ክልል ውስጥ ስር ነው ሲሰሩ የነበሩት። አሁን የወሰዱት ስልጠና የሲዳማ ተወላጆች ሆነው ወደ ሲዳማ ክልል ሲመጡ የሲዳማ ተወላጅነታቸውን ብቻ ይዘው እንዳይመጡ፣ የተለየ መዋቅር እንደሆነ እና በህዝቦች አንድነት ላይና በአመለካከት ላይ ነው ስልጠና የወሰዱት"

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም ከአዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጋር በትላንትናው ዕለት የስራ ርክክብ አድርገዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ፕ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው መሾማቸውና በምትካቸው የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ መሾማቸው ይታወሳል @MinistryoSHE

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ይደረጋል! የሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ውይይት ሊያደርጉ መሆናቸውን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ዘግቧል። በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በሚካሄደው ውይይት ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።  በነገው ውይይት ሶስት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚያቀርቡ…
#UPDATE

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ከ ኢትዮጵያ የምስረታ ዘመን እስከ ስርአቶች ዝርጋታ ታሪካዊ - ጥናታዊ የመነሻ ሃሳብ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አማካይነት ቀርቦ በፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይት እየተካሄደበት እንደሚገኝ ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(የኢትዮጵየ ንግድ ባንክ)

የኮንዶሚኒየም ብድር ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ!

የኮሮና ወረርሽኝ የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኮንዶሚኒየም ብድር ተበዳሪዎች የ3 ወር (ከሚያዝያ 2012 እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም) የወርሃዊ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ይህ የእፎይታ ጊዜ በሰኔ 2012 ዓ/ም የተጠናቀቀ ስለሆነ የባንኩ ደንበኞች ክፍያቸውን ከ ሀምሌ ወር 2012 ዓ/ም ጀምሮ መክፈል መጀመር እንዳለባቸው ባንኩ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለአስራ አራተኛ (14) ዙር ያሰለጠናቸው ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ አስመርቋል።

ኮሌጁ በከፍተኛ ስልታዊ አመራር ካስመረቃቸው ዘጠና ስልጣኞች አስራ ስምንቱ ከአምስት የጎረቤት ሀገር የመጡ ናቸው።

በዛሬው የምረቃ ስነ ስርዓት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሃመድ ተገኝተው እንደነበር ከመከላከያ ሰራዊት ገፅ ገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrHirutKassaw

የሻደይ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት በማይዳሰሱ ቅርስነት የመመዝገብ ጉዳይ በሚቀጥለው አመት በዩኔስኮ ድምጽ እንደሚሰጥበትና እንደሚመዘገቡ እንደሚጠበቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለአልዓይን ተናግርዋል።

የዘንድሮ አሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ በዓላት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ እየተከበሩ አይደለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ስፖርታዊ ጉዳዮችን መከታተያ ገፅ : @tikvahethsport
"ሃኪምን ለቤት አስቀምጦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከል አይቻልም፤ ሃኪምን ከቤት አስቀምጦ የዜጎችን ጤንነት መጠበቅ አይቻልም!" - በ2012 ተመርቀው ቋሚ ቅጥር ያልፈፀሙ ጠቅላላ ሃኪሞች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
FDRE Defense Force.pdf
599.5 KB
የመከላከያ ሚኒስቴር ቀጥሎ በተመለከቱት ልዩ ልዩ ሙያዎች የሠራዊት አባላትን መመልመል ይፈልጋል !

- መደበኛ ሰራዊት
- ሎጂስቲክስ ሞያዎች
- ፋይናንስ ዘርፍ
- በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስር ላሉ ሞያዎች
- ኮማንዶ

ማስታወቂያውን በማንበብ እሰከ ነሀሴ 30 ቀን 2012 ድረስ ብቻ በየአቅራቢያችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OLF #BALDERAS

ዛሬ "በብሄራዊ መግባባት" ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባካሄዱት ውይይት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጥሪ እንዳልተደረገለት አሳውቋል።

ፓርቲው ዛሬ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ሊያደርጉ ነው መባሉ የሰማው ከሚዲያ እንደሆነና ከዚህ ባለፈ ለድርጅቱ የቀረበ ጥሪ የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" እያካሄደ ያለው ውይይት ሁሉን አሳታፊ አይደለም ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

Via @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እኔ እያለሁ ወገኔ አይራብም"

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፣ ዛውያ ቲቪ ኸይር ፈላጊ ፣ ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት ፣ ተአውን እድር ፣ ፍልውሃ ቶፊቅ መስጂድ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፋቸውን አድርገዋል።

ምንጭ፦ የስልጢ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 16/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 535 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በአፋር ፦
- 800 በቫይረሱ የተያዙ
- 198 ያገገሙ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 742 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 93 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሐረሪ ፦
- 789 በቫይረሱ የተያዙ
- 16 ሞት
- 187 ያገገሙ

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 375 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5,441 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 325 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 62 ከምስራቅ ሸዋ
- 56 ከጉጂ
- 46 ከለገጣፎ ከተማ
- 37 ከአዳማ ከተማ
- 27 ከምስራቅ ሀረርጌ
- 12 ከገላን ከተማ
- 10 ከምዕራብ አርሲ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 4,468 በቫይረሱ የተያዙ
- 41 ሞት
- 1,384 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 391 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 14 ከዳምቤ (አጋሎ) ወረዳ
- 1 ከፓዌ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ከተማ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ39 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,776 የላብራቶሪ ምርመራ 1,368 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ25 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 567 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 39,033 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 662 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,480 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia