ኦነግ 6 አመራሮቹን ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፣ አቶ ቶሌራ አዳባና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮቹን #ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል፡፡
በእግዱ ተካተዋል የተባሉ አመራሮች ነሐሴ 4 ቀን የድርጅቱ አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫ በሂልተን ሆቴል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳዎድ ኢብሳ በበኩላቸው የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
ከዚህም አስቀድሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ በኀላ በተነሱ ጉዳዮችና ልዩነቶች ላይ የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲያጣራ መወሰኑን አመራሮቹ ገልጸው ነበር።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#ATTENTION
ነቀምቴ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2,272 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ መቶ ስምንት (108) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከነዚህ መካከል፦
- 27 ከአዳማ
- 20 ከነቀምቴ
- 16 ከሞጆ
- 12 ከቢሾፍቱ
- 7 ከቡራዩ ይገኙበታል።
በኦሮሚያ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ በመሆኑ ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ለመቆጣጠር ፈተናው እንዳይበረታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የእነ አቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ውሎ!
ዛሬ በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክሮች ግማሾቹ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ግማሾቹ ደግሞ በዝግ ችሎት እንዲመሰክሩ ብይን መሥጠቱን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳውቌል።
እነ አቶ እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ከዚህ በኋላ የክርክሩ አካል መሆን እንደማይፈልጉ ስለዚህም በሁሉም ስምምነት ጠበቆቻቸውን #ማሰናበታቸውን ፣ ከዚህ በኃላ በግዳጅ ካላቀረቡን በስተቀር አንከራከርም ፣ አንቀርብምም ማለታቸውን ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።
ፍረድ ቤቱ ምስክሮችን በነሃሴ 8/2012 ዓ/ም እንዲቀርቡ አዟል።

ነሃሴ 6/2012 ዓ/ም - ወላይታ ዞን!
ዛሬ በወላይታ ዞን ወረዳዎች እና የተለያዩ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የወላይታ ዞን ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
ሰልፈኞቹ ፥ 'የታሱሩት የዞኑ መሪዎች ይፈቱ፣ ያለ ህዝብ ፍላጎት ከኃላፊነታቸው ሊነሱ አይገባም፣ በንፁሃን ላይ የተፈፀመውም ግድያ እናወግዛለን፣ የሰው ህይወት ያጠፉ ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ' ሲሉ ጠይቀዋል።
በቦዲቲ፣ በዴሳ፣ ጉኑኖ መንገዶች ተዘግተው እንደነበር የሰዎችም እንቅስቃሴ ተገቶ መቆየቱን አባላቶቻችን ገልፀዋል።
ዛሬም መስሪያ ቤቶች ፣ባንኮች ዝግ ሆነው ውለዋል፤ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ፣ እንዲሁም የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።
ዛሬ ከሰዓት ከሰሞኑን የነበረው ውጥረት እየረገበ በነበረባት ወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና ኮሌጅ አከባቢ የሰው ህይወት ማለፉና ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል ከሰሞኑን በቁጥጥር ስር የዋሉት የዞኑ አመራሮች ፣ ምሩናን እና አክቲቪስቶች ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል ፤ ሂደቱ ለሚዲያዎች ዝግ እንደነበር ተነግሯል።

#UPDATE
የዓለም ጤና ድርጅት ሩሲያ ስራ ላይ ለማዋል ያዘጋጀችው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ውጤታማነትና ትክክለኛነት ላይ ከሩሲያ ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ ከሩሲያ የጤና ዘርፍ ባለሥልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ በቅርበት እየተነጋገረ እንደሚገኝ ገልጿል።
በሩሲያ የተዘጋጀው ክትባት ለክትባት ዝግጅት የሚያስፈልጉ ሁሉም መስፈርቶች ማሟላቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ታሪክ ገጃሳሬቪክ በጄኔቫ መናገራቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ኢቢሲ ዘግቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ነሃሴ 6/2012 ዓ/ም - ወላይታ ዞን! ዛሬ በወላይታ ዞን ወረዳዎች እና የተለያዩ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የወላይታ ዞን ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። ሰልፈኞቹ ፥ 'የታሱሩት የዞኑ መሪዎች ይፈቱ፣ ያለ ህዝብ ፍላጎት ከኃላፊነታቸው ሊነሱ አይገባም፣ በንፁሃን ላይ የተፈፀመውም ግድያ እናወግዛለን፣ የሰው ህይወት ያጠፉ ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ' ሲሉ ጠይቀዋል። በቦዲቲ፣ በዴሳ፣ ጉኑኖ…
ችሎት!
ዛሬ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዎላይታ ህዝብ አመራሮች፣ ምሁራንና አክቲቪስቶች ለፍርድ ቤቱ ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ብይን ለመስጠት ለነገ 9:00 ተቀጥረዋል።
Via Hailemichael T Lemma / Elias Meseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዎላይታ ህዝብ አመራሮች፣ ምሁራንና አክቲቪስቶች ለፍርድ ቤቱ ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ብይን ለመስጠት ለነገ 9:00 ተቀጥረዋል።
Via Hailemichael T Lemma / Elias Meseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 943 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,540 የላብራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 338 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 25,118 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 463 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,034 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,540 የላብራቶሪ ምርመራ 943 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 338 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 25,118 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 463 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,034 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 216 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- 1 ከመተከል ዞን ጉባ ወረዳ
- 2 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ
#Harari
በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 670 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት ሰዎችም ህይወት አልፏል።
አጠቃላይ በሀረሪ ፦
- 366 በቫይረሱ የተያዙ
- 14 ሞት
- 78 ያገገሙ
#Tigray
በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 586 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ትላንት 39 ሰዎች አገግመዋል።
አጠቃላይ በትግራይ ፦
- 1,252 በቫይረሱ የተያዙ
- 10 ሞት
- 697 ያገገሙ
#DireDawa
በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 250 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 10 ከጅቡቲ ተመላሾች በለይቶ ማቆያ የነበሩ ሲሆኑ፤ 26 ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,086 የላብራቶሪ ምርመራ 70 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከነዚህ መካከል
- 25 ከባህር ዳር
- 13 ከምዕራብ ጎንደር ዞን
- 12 ከሰሜን ሸዋ ዞን
- 7 ከደ/ጎንዳር ዞን
- 6 ከሰ/ወሎ ዞን
- 3 ከምስ/ጎጃም ዞን
- 3 ከደሴ ከተማ
- 1 ከማዕ/ጎንድር
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 6 ሰዎች ከሀዋሳ ይገኙበታል።
#CARD #TIKVAH

በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 943 ሰዎች መካከል 612 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው።
ከፍተኛ ኬዝ ከተመዘገበባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ክፍለ ከተማዎች መካከል አራዳ (124)፣ ቦሌ (84)፣ ጉለሌ (80) በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪ በ24 ሰዓት በሀገሪቱ ከተመዘገበው ሃያ ሶስት የሟቾች ቁጥር 18 ከአዲስ አበባ ከተማ ናቸው ፤ 13 ሰዎች ከአስክሬን ምርመራና 5 ሰዎች ከጤና ተቋም መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት !
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 76,587 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
ከኤርትራ ውጭ በ6ቱ ሀገራት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የ1,904 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል ፤ በአጠቃላይ 40,210 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ወደ ሀገራችን ከገባበት ጊዜ አንስቶ ተቋርጦ የቆየው 'አገልግሎትና ድርጅትን የማስተዋወቂያ' መድረክ ከዛሬ ጀምሮ ክፍት ተደርጓል።
ለምትሰሩት ስራ 'ህጋዊ ፍቃድ' ያላችሁ ድርጅቶችና ተቋማት ብቻ የቲክቫህ የማስታወቂያ ደንቦችን አክብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ከሆናችሁ በ @tikvahadvertisement የድርጅታችሁን ስም በመላክ ፓኬጁን ማግኘት እንዲሁም ቦታ ማሲያዝ ትችላላችሁ።
MORE : 0919743630

በደቡብ አፍሪካ እስካሁን በትንሹ 10 ኢትዮጵያውያን ሞተዋል!
በደቡብ አፍሪካ እስካሁን ከ10 የማያንሱ #ኢትዮጵያውያን በኮቪድ-19 መሞታቸውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ፀሃፊ አቶ ፋኖስ ሃይሌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ጁሃንስበርግ ፣ ሊንፖፖ፣ ማፑማላንጋ እንዲሁም ዌስተርን ኬፕ ኢትዮጵያውያን ከሞቱባቸው አካባቢዎች ይጠቀሳሉ።
አስክሬናቸውን ወደ ሀገር ቤት መላክ ስለማይፈቅድ የሁሉም ቀብር ስነስርዓት በዛው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተፈፅሟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ አፍሪካ እስካሁን ከ10 የማያንሱ #ኢትዮጵያውያን በኮቪድ-19 መሞታቸውን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ፀሃፊ አቶ ፋኖስ ሃይሌ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ጁሃንስበርግ ፣ ሊንፖፖ፣ ማፑማላንጋ እንዲሁም ዌስተርን ኬፕ ኢትዮጵያውያን ከሞቱባቸው አካባቢዎች ይጠቀሳሉ።
አስክሬናቸውን ወደ ሀገር ቤት መላክ ስለማይፈቅድ የሁሉም ቀብር ስነስርዓት በዛው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተፈፅሟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity
በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን በመከላከል ስራ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ላለፈው ዶ/ር ፍሳሃየ አለምሰገድ ትላንት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
ለዶክተር ፍስሃየ አለምሰገድ በተዘጋጀው በዚሁ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በzoom ንግግር አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም እናቱም በzoom ንግግር ማድረጋቸውን የዶክተር ፍሳሃየ የቅርብ ወዳጅ አሳውቀውናል።
በነገራችን ላይ ዶክተር ፍሳሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት ፣ በተመራማሪነትና በሙያ እማካሪነት ከ1994 ዓ/ም እስከ 2011 ዓ/ም አገልግለዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB

ዛሬ (ነሃሴ 7/2012 ዓ/ም) በወላይታ ዞን ወረዳዎች እና የተለያዩ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ እንደነበር የወላይታ ዞን ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
ሰልፈኞቹ ፥ 'የታሱሩት የዞኑ መሪዎች ይፈቱ፣ ያለ ህዝብ ፍላጎት ከኃላፊነታቸው ሊነሱ አይገባም፣ በንፁሃን ላይ የተፈፀመውም ግድያ እናወግዛለን፣ የሰው ህይወት ያጠፉ ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ' ሲሉ እየጠየቁ ናቸው።
በወላይታ ዞን ከተሞች ዛሬም የንግድ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አልተጀመረም፤ ባንክ ቤቶች፣ መስሪያ ቤቶች ዝግ ናቸው። የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎትም እንደተዘጋ ነው። ባለፉት ቀናት በወላይታ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በትንሹ ከ25 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዓለማየሁ ባውዲ ዛሬ በetv ቀርበው መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄ ለመፍታት ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ ባለበት ወቅት ጉዳዩ ወደ ግጭት እንዲያመራ አድርጎ የሕዝብን ጥያቄ መቀልበስ ትክክል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
በአንዳንድ አመራሮች አካባቢ በሕገ-ወጥ መንገድ የተጀመረው ሥራ ሀገርን እና የሕዝቦችን አንድነት የሚጎዳ መሆኑ ታውቆ እርምጃ የተወሰደ እንደሆነ ሕዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲሉ አስታውቀዋል።
የሕዝቡ ጥያቄ ፍፁም የማይቀለበስ ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊው ፣ "ጥያቄችሁ ሊቀለበስ ነው፤ ተነሱ እና ታገሉ" እያሉ ከሚቀሰቅሱ ወገኖች ህዝቡ ራሱን መጠበቅ ይገባዋል ሲሉ አሳስበዋል።
PHOTO : Social Media

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ቀን 143 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ እየጨመረ ይገኛል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 2,051 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ ሶስት (143) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከነዚህ መካከል፦
- 31 ከነቀምቴ
- 22 ከሰበታ
- 16 ከአዳማ
- 13 ከቢሾፍቱ
- 12 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 10 ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል።
በድጋሚ ነቀምቴ፣ሰበታ፣ ቢሾፍቱ ፣ሞጆ፣ አዳማ በሌሎችም የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውስጥ የምትኖሩ ነዋሪዎች እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በዚህ አጋጣሚ መልዕክት እናስተላልፋለን።