TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 245 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,709 የላብራቶሪ ምርመራ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,915 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 172 ወንድ እና 73 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 241 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አራቱ (4) የውጭ ሀገር ዜጋ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 190 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 17 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 16 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 15 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል እንዲሁም 3 ሰዎች ከአማራ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት አስራ ሰባት (17) ሰዎች (16 ከአዲስ አበባና 1 ከደቡብ ክልል ትላንት በክልሉ ሪፖርት የተደረገ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 47 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት (7) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 47 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ75 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

3. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

4. የ29 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

5. የ48 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት።

6. የ85 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

7. የ21 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 2 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 3 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 4 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌላቸው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠው አራቱ (4) ሰዎች ይርጋለም ህክምና ማዕከል እንዲቆዩ ተደርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰባት (107) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 182 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው አስራ አምስት (15) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከአስራ አምስቱ (15) መካከል አስሩ (10) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ ሶስት (3) ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው እንዲሁም ሁለት (2) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስልሳ ሰባት (167) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 246 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በዛሬው ዕለት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- አንድ (1) ሰው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልና አንድ (1) ሰው በደሴ ከተማ በሚገኘው የግል የህክምና ማዕከል አገልግሎት ለማግኘት በሄዱበት ወቅት ናሙና ሲወሰድላቸው ኮቪድ-19 የተገኘባቸው።

- አንድ (1) ሰው ደግሞ በጎንደር ጎሃ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላት የነበረች ሴት ናት።

ከፆታ አኳያ ሲታዩ አንድ (1) ወንድ እና ሁለት (2) ሴቶች ሲሆኑ ከ22 እስከ 60 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 167 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 686 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 17 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

- 3 ሰዎች ከምሥራቅ ሐረርጌ፥የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ (ሁለቱ ወደ ሱማሊያ፣ አንድ ሰው ጅቡቲ) ያላቸው።

- 1 ሰው (የ24 ዓመት ወጣት) ከባሌ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ከማህበረሰቡ የተገኘ።

- 1 ሰው (የ27 ዓመት ወጣት) ከምስራቅ ባሌ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

- 1 ሰው ከጅማ (የ42 ዓመት ወንድ)፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ (ጅቡቲ) ያለው።

- 1 ሰው ከጅማ ዞን (የ74 ዓመት አዛውንት)፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 2 ሰዎች ከምዕራብ ሸዋ፤ሁለቱም ሴቶች ናቸው፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።

- 2 ሰዎች ከቡራዩ (1 ወንድ እና 1 ሴት) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 1 ሰው ምዕራብ ሐረርጌ (የ25 ዓመት ወጣት)፤የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ (ጅቡቲ) ያለው።

- 2 ሰዎች ከሆለታ (1 ወንድ እና 1 ሴት) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 1 ሰው ከሱሉልታ (የ30 ዓመት ወጣት)፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

- 1 ሰው ከሰሜን ሸዋ (የ40 ዓመት ዕድሜ ያለው ወንድ)፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

- አንዲት የ22 ዓመት ወጣት ሴት መኖሪያዋ እየተጣራ ይገኛል፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ከማህበረሰቡ የተገኘች።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከኮቪድ-19 ጉዳዮች ውጭ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethmagazine መከታተል ትችላላችሁ!

ትክክለኛው የ @tikvahethmagazine ገፅ ከ 220,000 በላይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያሉበት ነው።
#ATTENTION

በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2,000 አለፈ!

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 5/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 2,136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 190 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ዩሉም። 14 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 176 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ዘጠና (190) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 6 ሰዎች
• ቦሌ - 85 ሰዎች
• ጉለሌ - 5 ሰዎች
• ልደታ - 10 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 22 ሰዎች
• የካ - 7 ሰዎች
• አራዳ - 16 ሰዎች
• ቂርቆስ - 22 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 13 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 2 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,136 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 496 ሰዎች
• ቦሌ - 375 ሰዎች
• ጉለሌ - 256 ሰዎች
• ልደታ - 218 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 199 ሰዎች
• የካ - 121 ሰዎች
• አራዳ - 110 ሰዎች
• ቂርቆስ - 110 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 108 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 68 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 75 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SRHB

በሱማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ አስራ ስድስት (216) ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው 122 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከአስራ ስድስቱ (16) መካከል አስራ አራቱ (14) ከደዋሌ ለይቶ ማቆያ ሲሆኑ ሁሉም (ወደ ጅቡቲ) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ሁለቱ (2) ሰዎች ደግሞ ከጅግጅጋ ናቸው ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የላቸውም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ያመለጠው የኮቪድ-19 ታማሚ ተያዘ!

አዲስ አበባ ናሙና ሰጥቶ ኮቪድ-19 እንደተገኘበት ተነግሮት አምልጦ ደብረብርሃን ከገባ በኃላ ስልኩን አጥፍቶ ለመሰወር የሞከረው ግለሰብ በጸጥታ አካላት እና የጤና ባለሞያዎች ክትትል ጫጫ ከተማ ላይ ተይዟል ፤ ከእርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው 13 ግለሰቦች ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተገልጿል #MORE : https://telegra.ph/D-06-12

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#TIGRAY

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ የስራ ዘመን 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ወር ተኩል (75 ቀን) እንዲቀጥል ወስኗል።

@tikvahmagbot @tikvahethmagazine
ኮቪድ-19 በሜክሲኮ እና ብራዚል!

በሜክሲኮ እና ብራዚል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ (ኮቪድ-19) የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ በእጅጉ እየጨመረ ይገኛል።

በአጠቃላይ በብራዚል እስካሁን 41,058 ሰዎች በሜክሲኮ ደግሞ 15,357 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

በሌላ በኩል በሁለቱ ሀገራት በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር በድምሩ 934,833 (ብራዚል 805,649 ሰዎች እና ሜክሲኮ 129,184 ሰዎች) ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
አመለጡ ስለሚባሉ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ጉዳይ...

በተደጋጋሚ ቫይረሱ እያለባቸው ከ አንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ አምልጠው ስለሚያዙ እና ከለይቶ ማቆያ ስለሚጠፉ ሰዎች ሁላችንም እየሰማን ነው።

ይህ እየሆነ ያለው ስለበሽታው፣ ስለወረርሽኙ ያለን ግንዛቤ እጅግ በጣም አናሳ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህ በሽታ ህይወታችንን ሊያሳጣን ፣ በኛ ትንሽ ስህተት የምንወዳቸውን ሁሉ ከጎናችን ሊነጥቀን እንደሚችል አልገባንም።

ምርምራ ተደርጎላቸው ወጤታቸውን የሚጠብቁ ሰዎች አሉ እኚህ ሰዎች ምርመራ የሚደረግላቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው ነው ስለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።

ያወቅነውን በማሳወቅ የበሽታውን አደገኝነት በማስተማር የሁላችንም ድርሻ ትልቅ ቢሆንም ሚዲያዎች ግን የተለየ ድርሻቸውን መወጣት ይገባቸዋል።

ማስተማር! ማሳወቅ! ማስገንዘብ! ማስረዳት! ከሚዲያዎች በእጅጉ ይጠበቃል። በተለያዩ አጀንዳዎች የተጠመዱ ዋና ዋና ሚዲያዎችና የማህበራዊ ሚዲያዎች እነሱ ነቅተው ሰዎችን ማንቃት አለባቸው።

በሀገራችን የኮቪድ-19 ጉዳይ ሪፖርት ከወጣ በኃላ ግፋ ቢል የ2 እና 3 ሰዓት አጀንዳ ብቻ እየሆነ ነው። ይህ ሁኔታ በኃላ እንድናዝንና እንዲቆጨን የሚያደርግ ነው።

ይህ በሽታው እጅግ እየተስፋፋና የሁላችንንም ቤት እያንኳኳ ነው። የጤና ተቋማት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እየገቡ ነው ፣ የጤና ባለሞያዎች ለቫይረሱ እየተጋለጡ ነው ፣ በአጠቃላይ ልንወጣ የማንችለው መከራ ውስጥ እየገባን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአንድ ሰው ጥንቃቄ የብዙዎችን ህይወት ይታደጋል!

የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች ውጤቱ እስኪደረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደረጉ የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ከዚህ ቀደም ከየክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በነበሩን ቆይታዎች ተገልጾልናል።

አንድ ሰው ተጋላጭ ነው ተብሎ ከታሰብ እና ከሌሎች በተለየ መልኩ ምርመራ ከተደረገለት በሚችለው አቅም ሁሉ ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለወገኑ ሲል ሊጠነቅቅ ይገባል።

እንዳንዶች ስልክ እንደሚያጠፉ ፣ ያሉበትን ቦታ እና ከተማ እንደሚደብቁ ከሚመለከታቸው አካላት ተገልጾልናል። ይህ የአንድ ሰው የጤና ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ሁላችንም ልንረዳው ይገባል።

የጤና ባለሞያዎች ካላቸው ውድ ጊዜ ቀንሰው ከሚሰጡት ግንዛቤ በተጨማሪ 24 ሰዓት ሙሉ በተለያዩ አጀንዳዎች ተጠምደው የሚውሉት የሀገራችን ሚዲያዎች ኃላፊነታቸው በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።

በሌላ በኩል 'ከለይቶ ማቆያ' የሚያመልጡ አካላት እንዳሉ ይታወቃል ፤ ይህ ጉዳይ መንግስት በእጅጉ ሊሰራበት የሚገባው ነው። በየለይቶ ማቆያዎቹ ያሉ ችግሮች ሊፈተሹ እና በተቻለ መጠን አቅም በፈቀደ መፈታት ይኖርባቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የሟቾች ቁጥር ከ700 አለፈ!

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 21,615 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ703 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 7,242 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ይለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia