TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በማዳጋስካር ተጨማሪ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 213 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ስድስት(6) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 192 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ትላንት ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገሙን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 107 ደርሰዋል።

#ProffesorHantaVololontiana

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1,481 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ 48 ሰዎች ሞተዋል።

- በኢራን ዛሬ መስጊዶች በጊዜያዊነት ተከፍተው ሌሎችም እንቅስቃሴ ላይ የተጣሉ ገደቦች እየተነሱ እንደሚቀጥሉ ተገልጻል - #BBC

- በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከUK በልጧል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 10,899 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 232,243 ደርሰዋል።

- የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል።

- የቻይናዋ ዉሃን ከተማ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ነዋሪዋን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልታደርግ ዕቅድ እያዘጋጀች መሆኑ ተነግሯል - #BBC

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 176 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26,920 ደርሷል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ትላንት ብቻ 627 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 32,692 ደርሷል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ82,000 በላይ ሆኗል።

- በኳታር በአንድ ቀን 1,526 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 25,149 ደርሷል።

- በሳዑዲ አረቢያ በ24 ሰዓት 1,911 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 9 ሰዎች ሞተዋል።

- በቻይና ትላንት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል ፤ በደቡብ ኮሪያ ደግሞ 27 ሰዎች ተይዘዋል እንዲሁም 2 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrFawziyaAbikar

በሱማሊያ በአንድ ቀን 81 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 81 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,170 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አምስት (5) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሰው ህይወት አለማለፉን ከሱማሊያ ጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ መግለጫ ተረድተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 194 ደረሱ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ከ193 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መካከል 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቋል ፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 194 ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
1 ሺህ የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ተባለ!

(በቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት)

የዓለም ጤና ድርጅት በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው #በአፍሪካ ውስጥ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ብሏል።

ድርጅቱ በተጨማሪም የአፍሪካ መንግሥታት ለነርሶች እና ዶክተሮች የመከላከያ ቁሳቁሶች እንዲያሟሉ ጥሪ አቅርቧል።

ከኮሮና ቫይረስ ህሙማን ጋር ንክኪ የሚኖራቸው የህክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚከላከሉበት የህክምና ቁሳቁሶችን መሟላታቸውን መንግሥታት እርግጠኛ መሆን አንዳለባቸውም አፅንኦት ሰጥቷል።

በተለይም ከህሙማኑ ምራቅ ናሙና ጋር ንክኪ ያላቸው የላብራቶሪ ሰራተኞችም ሆኑ ዶክተሮች ደረጃውን የጠበቀ መከላከያ ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል።

ከዚህም ውስጥ በውስጡ መተንፈሻ የተገጠመለት ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ጭምብል እና ቶሎ ቶሎ መቀየር የሚችሉ ጋወኖች ይገኙበታል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 1,661፣ ሞት 80፣ ያገገሙ 173

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,256፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 886

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,170፣ ሞት 52 ፣ ያገገሙ 126

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 715፣ ሞት 36 ፣ ያገገሙ 259

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 261 ፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 106

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 194 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 38

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 12 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,661 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 80 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 173 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸዉ ተገልጿል።

* የሱዳን ጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓት ሪፖርት ከእኩለ ለሊት በኃላ እየቀረበ በመሆኑ ከላይ (የኢትዮጵያና አጎራባች ሀገራት የኮቪድ-19 መረጃ) በዛሬው ሪፖርት #ተስተካክሏል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እራሴን እጠብቃለሁ፤ ሀኪሜን አግዛለሁ!

(ዶክተር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሙያ)

እንሆ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሀገራችን ከገባ ሁለት ወራትን አስቆጥሯል ፤ ለአንዳንዶች በሁለት ወር ውስጥ የተያዘው ሰው ቁጥር አናሳ ሊመስል ይችላል፤ ነገሩ ግን እንደዛ አይደለም።

ባለፈው ሣምንት ብቻ 104 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ስናይ ፤ ቫይረሱ መጀመሪያ ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ 105 ሰዎች ለመያዝ የፈጀበት ጊዜ 36 ቀናት ነበሩ።

የኮሮና ቫይረስ የስርጭት መጠኑን ያን ያህል ሰዎች ለመያዝ የፈጀበትን ጊዜ በ5 እጥፍ ፍጥነት አሳንሶታል ማለት ነው። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ቫይረሱ የሚገኝባቸውም ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። ይህም ሣምንቱን ከሌሎቹ ሳምንታት የከፋ አድርጎት አልፏል።

እያየነው እንዳለው በአጎራባች ሀገሮችም ላይ ሆነ በአህጉሪቱ ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችም ሆነ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር #እያሻቀበ ነው።

ክብርት ሚንስትሯ እንዳሉት 'መራራቅ፣ መታጠብ ፣ መቆየት ፣ መሸፈን' የሚሉ አራቱ የኮቪድ-19 “መ” ህጎችን መተግበር ደግሞ ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ የጥንቃቄ አማራጭ ነው።

ስለዚህ እራስን መጠበቅ ፣ ሌላውን መጠበቅ ነውና ፤ እባካችሁ ጆሮዎቻችንን ማንቂያውን ደውል ይስማ!

እርስ በእርሳችን እንጠባበቅ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 4,354,545 ደርሷል ፤ ከእነዚህ መካከል 1,609,611 ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ፤ 293,033 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EPHI

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አሐዛዊ መረጃ!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በላብራቶሪ ምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እድሜ ፦

• ከ5 ዓመት በታች - 1

• ከ5-14 ዓመት - 7

• ከ15-24 ዓመት - 91

• ከ25-34 ዓመት - 75

• ከ35-44 ዓመት - 43

• ከ45-59 ዓመት - 26

• ከ60 ዓመት በላይ - 18

በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው 261 ሰዎች ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Mauritius

በሞሪሽየስ አክቲቭ ኬዝ 0 ሆኗል!

በሞሪሺየስ አዲስ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዘ ሰው ሳይገኝ 15 ቀናት ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አሳውቋል።

በሀገሪቱ ውስጥ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት 332 ሰዎች መካከል 10 ሰዎች ሲሞቱ የተቀሩት (322) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በቅርቡ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ 220 የሚደርሱ ዜጎች በልይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

በአዲስ አበባ ሁለተኛ ዙር በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ መጀመሩን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ አሳውቀዋል።

አሰሳው ህብረተሰቡን ማስተማር እና የተገኙ መረጃዎችን በፍጥነት በማስተላለፍ በሽታውን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል፡፡

ለተጀመረው በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት አሰሳ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር ማድረግ እንዳለበትም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በዜጎች ዘንድ ፍቃደኛ ያለመሆን ፣ ቤት ዘግቶ የመጥፋት እና መልክቶችን መጨመርን ጨምሮ ሌሎች ያለመተባበር ችግሮች እንደተስተዋሉ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,650 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 263 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው 24 እና 33 ዓመት የሆኑ ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው አንደኛው የትግራይ ክልል ነዋሪና የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ሲሆን ሁለተኛው ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 2

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 0

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 0

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስምንት (108) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በማዳጋስካር ተጨማሪ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ!

በማዳጋስካር በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ነው፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 212 ደርሰዋል።

#ProffesorHantaVololontiana

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SENEGAL

ሴኔጋል በኮቪድ-19 ምክንያት በውጭ ሃገራት የሞቱ ዜጎቿን አስከሬን መቀበል ጀመረች ፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የትኛውም አስከሬን ወደ ሃገሯ እንዳይገባ ከልክላ የነበረችው ሴኔጋል ክልከላዋን አንስታለች - #AlAin

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 900 ደረሱ!

የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ውስጥ 14 ሰዎች ማገገማቸውን ሪፖርት አድርጓል።

በሌላ በኩል 331 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አሳውቋል።

በጅቡቲ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,268 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት 1,516 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 737 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 22 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 281 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፖሊስ የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም እና የታሰሩትም ሊለቀቁ ይገባል!

(የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን)

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች በፖሊስ እየታሰሩ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ በሚዲያዎች የወጡ ዘገባዎችንና ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚከተለውን ብለዋል ፦

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል አስፈላጊ የጤና መመርያ ሲሆን ሕብረተሰቡም ሊከተለው የሚገባ ነው፡፡

በእርግጥም የአስቸኳይ ጊዜ ደንቡ ማንኛውም ሰው እንደ ገበያ ቦታዎች፥ ሱቆች ፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ባሉ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች እና በሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸውና የአካል መራራቅን መጠበቅ በማይቻልባቸው አካባቢዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡

ከዚህ ውጪ ግን በየትኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች ላይ ሁሉ የሚደረግ የዘፈቀደ እስር ከህግ ውጭ ከመሆኑም በላይ ለነገሩ ሁኔታ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ እና የታለመለትን አላማ የሚቃረን በመሆኑ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፣ በዚህ ሁኔታ የታሰሩ ሰዎችም በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በትላንትናው ዕለት በኬንያ 4 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት መሞታቸውን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አሳውቋል ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 40 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖሊስ የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም እና የታሰሩትም ሊለቀቁ ይገባል! (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን) በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች በፖሊስ እየታሰሩ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ በሚዲያዎች የወጡ ዘገባዎችንና ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚከተለውን ብለዋል ፦ …
ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ታስረዋል!

(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተላላፉ ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎች የአፍና የአፍንጫ መከለያ ባለመጠቀማቸው ለእስር መዳረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንደተናገሩት የታሳሩ ሰዎች ምን እርምጃ ይወሰድባቸዋል የሚለውን በቀጣይ ማብራሪያ እንሰጣለን ብለዋል፡፡

ህግ አስከባሪ የፖሊስ አባላት እራሳቸው የፊት መሸፈኛ ሳያደርጉ እና ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል ፣ ለምን ሆኑ ተብለው ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት ኮማንደር ፋሲካ ለእነሱም አንደ ህዝቡ የግንዛቤ ትምህርት ይሰጣል ተላልፎ የሚገኝ የፖሊስ አባል ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

እየወሰድን ባለው እርምጃ ከህዝቡ #ድጋፍ እያገኘን ነው ፣ እየታሰሩ ያሉትም ብዙ ህዝብ ከሚበዛባቸው አካባቢዎች የተያዙ ናቸውም ብለዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia