TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
"ሐኪሞች አሰቃቂ የሕይወት-ሞት ውሳኔዎችን እየተጋፈጡ ነው"

ይህ አርዕስተ ዜና የእኛ ሀገር እጣፈንታ እዲሆን አንፈልግም!

(በዶክተር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሙያ)

ህብረተሰባችን በኮሮና ቫይረሱ እየተያዘ ያለው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው /ያላት ወይም በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው/ያላት ናቸዉ እያለ በመዘናጋት የኋልዮሽ ግን ምንጩ ባልታወቀበት የህብረተሰብ አካል በሆኑ ግለለሰቦች እና ለሌላ በሽታ ሆስፒታል የመጡ ላይም እየተገኘ ነው።

እነዚህ ክስተቶች ህዝባችንን ሊያስደነግጡት ይገባል፤ ቫይረሱ በማይታወቅ መንገድ እራሱን እየገለጠ ሳለ የጤና ባለሙያዎችንም ጭምር በድንገት እያጋጠማቸው ነው ያለው።

ካለው የቫይረሱ ክስተት ጋር የህብረተቡ መዘናጋት ተጨምሮ የጤና ባለሙያዎችን ከስራ ገበታቸው እያስነሳና ብሎም ለበሽታው እያጋለጣቸው ነው።

የሚቀጥሉትን ሳምንታት ካልተጠነቀቅን ፣ ከባባድ ምርጫዎችን የምናስተናግድ እንዳንሆን እባካችሁ ጨርሶ አትዘናጉ ፣ አትሰላቹ።

እኛ ለእርሶ በስራችን እንቆይ ፤ እርሶ ለኛ በቤት ይቆዩ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#MoHEthiopia

የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ከ03/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው።

ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ ነው ተብሏል።

አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ መስተዋሉ ተገልጿል ።

በመሆኑም ወጥ በሆነ ጋይድ ላይንና ቼክሊስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል ይጎበኛሉ ድጋፍም ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ይህ ድጋፋዊ ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን ይኖርበታል ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,847 ላቦራቶሪ ምርመራ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ሰማንያ ሰባት (187) ደርሷል።

ዛሬ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 24 ወንድ 1 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ17-65 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የመኖሪያ ቦታቸው አዲስ አበባ የሆኑት 21 ሲሆኑ 2 ደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል (ሃድያና ከምባታ) ፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል (ቦረና ለይቶ ማቆያ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ - 3 ሰዎች

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት - 3 ሰዎች

• የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው - 19 ሰዎች

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 25 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 24 ወንድ 1 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ17-65 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል።

የመኖሪያ ቦታቸው አዲስ አበባ የሆኑት 21 ሲሆኑ 2 ደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል (ሃድያና ከምባታ ዞን) ፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል (ቦረና ለይቶ ማቆያ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን) ይገኛሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጭር መረጃ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር ፦

- ከምባታ ጠምባሮ ዞን በቅርቡ ከሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ተለቆ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች የማፈላለግ እና ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የማስገባት ተግባር ሲያከናውን ቆይቷል።

- ዛሬ በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ በቅርቡ ከሞያሌ አስገዳኝ ለይቶ ማቆያ ወጥቶ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንክኪ ያለው ነው።

- ግለሰቡ ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ወደ አንጋጫ ለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲገባ ተደርጎ ናሙናው ወደ ደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ መያዙ #ተረጋግጧል

- በአሁን ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል። ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች በማፈላለግ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማዕከል የማስገባት ስራ እየተሰራ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AtoAknawKawza

ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የተሰጠ መረጃ፦

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ከከምባታ ጠምባሮና ሐድያ ዞኖች በላፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በደቡብ ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ በተደረገው 59 የላብራቶሪ ምርመራ ነው 2 (ሁለት) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - 22 ዓመት ወጣት ፤ ከሻሾጎ ወረዳ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ፤ በ23/08/2012 ከኬንያ በሞያሌ በኩል ከተመለሰው ታማሚ ጋር ንክኪ #ያለውና አሁን በሆሳዕና ከተማ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ21 ዓመት ወጣት ፤ ከአንጋጫ ወረዳ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #ያለው ፤ በ23/08/2012 ከኬንያ በሞያሌ በኩል ከተመለሰው ታማሚ ጋር ንክኪ ያለውና አሁን በአንጋጫ ለይቶ ማቆያ ያለ።

በአጠቃላይ በክልሉ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ከጤና ሚኒስቴር በተገለጸው መሰረት ቁጥር 4 (አራት) መድረሱን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

(ደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ የፀሃይ ግርዶሽ ይከሰታል!

በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚታይ ሲሆን ክስተቱም ወለጋ፣ ከፊል ጎጃምና ጎንደር፣ በወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ቀኑ #የሚጨልም ይሆናል ተብሏል።

በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ በዕለቱ በከፊል ጨለማ ሊሆን እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰሎሞን በላይ ተናግረዋል።

ግርዶሹ ስድስት ሰዓታት የሚፈጅ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር የፊታችን ሰኔ 14 እሁድ ቀን ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33 የሚቆይ ይሆናል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በትግራይ ክልል 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት የተደረገው የ4 ሰዎች #ፖዘቲቭ ኬዝ ጥዋት በፌደራል ደረጃ በጤና ሚኒስቴር ከተገለፀው ውጭ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ #አረጋግጠውልናል

በትግራይ ክልል ስልተገኙት 4 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የክልሉን ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎዶፋይን አነጋግረን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrRashidAman

በኬንያ 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 632 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 607 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 7 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 197 ደርሷል።

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 29 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በትግራይ ክልል 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በክልሉ ጤና ቢሮ…
የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ፦

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አራት (4) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ28 ዓመት ወጣት ፤ የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ፤ ረዳት ሹፌር

ታማሚ 2 - የ25 ዓመት ወጣት ፤ የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ፤ ረዳት ሹፌር

ታማሚ 3 - የ24 ዓመት ወጣት ፤ የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ፤ ረዳት ሹፌር

ታማሚ 4 - የ33 ዓመት ወጣት ፤ የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ፤ ሹፌር

በአጠቃላይ በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ 608 የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 78 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 78 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 12 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመኖሪያ ቦታቸዉ ፦

- ካርቱም ግዛት 55 ሰዎች
- ጋዳሪፍ 5 ሰዎች
- ሲናር 6 ሰዎች
- ሽማል ሱዳን (ሰሜን ) 2 ሰዎች
- ገርብ ሱዳን 2 ሰዎች
- ሰሜን ኮርዶፋን 1 ሰዉ
- ሰሜን ዳርፎር 1 ሰው

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 930 መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 52 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 92 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩሲያ በአንድ ቀን 11,231 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በሩሲያ 11,231 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 177,160 ደርሷል።

የሩሲያ መንግስት የኮቪድ-19 ስርጭት አነስተኛ በነበረበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እንዳይባባስ ዜጎች የሚባሉትን እንዲያደምጡ #ሲያሳስብ ነበር።

የከተማ ከንቲባዎች በሚዲያ እየወጡ ሁሉም ሰው የጤና ባለሞያዎችን ምክር እንዲተገብር #ሲማፀኑ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrFawziyaAbikar

በሱማሊያ ተጨማሪ 55 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 55 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 928 ደርሷል።

በሌላ በኩል አስራ ዘጠኝ (19) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 106 ደርሷል።

በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 44 ከፍ ብሏል ባለፉት 24 ሰዓት የአምስት (5) ሰው ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ያገገሙ ሰዎች 799 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 44 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 799 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል 213 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 1,133 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በኢትዮጵያ ተጨማሪ 25 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,847 ላቦራቶሪ ምርመራ ሃያ አምስት (25) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ሰማንያ ሰባት (187) ደርሷል። ዛሬ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 24 ወንድ 1 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው…
#AtoTemesgenHaile

በሀዲያ ዞን በኮሮና ቫይረስ መያዙ ስለተረጋገጠው አንድ (1) ሰው ዙሪያ ከሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ኃይሌ የተገኘ አጭር መረጃ ፦

- በዞኑ ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ሆነዋል በሚል ተጠርጥረው በተዘጋጀው አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ከተደረጉት ውስጥ በ2ኛ ዙር ወደ ሀዋሳ የምርመራ ማዕከል ከተላከው የ10 ሰዎች ናሙና ውስጥ ነው አንድ ሰው በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው።

- በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ሲሆን ወደ ደቡብ አፍሪካ ጉዞ ጀምረው ሞያሌ ቆይተው ወደ ዞኑ ከተመለሱና ከነርሱም መካከል በሀላባ ዞን በትራንስፖርት ሲጓዝ ተይዞ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኘው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተረጋገጠው ግለሰብ ጋር የቀጥታ ግንኙነት የነበረው ነው።

- በዞኑ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተረጋገጠው ግለሰብ ጋር በቀጥታም ሆነ በሌላ መንገድ ግንኙነት የነበራቸው 9/ዘጠኝ/ ሰዎች በመለየት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ወደተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል።

- በአጠቃለይ በሀዲያ ዞን 51 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሓጎስ ጎዶፋይ ከደቂቃዎች በፊት የሰጡን አጭር መረጃ ፦

- ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 4 ሰዎች የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

- የረዳቶቹ ዕድሜ 28፣ 25 እና 24 ነው ፤ ሹፌሩ ደግሞ 33 ዓመቱ ነው።

- ታማሚዎቹ ምንም ምልክት የላቸውም።

- ወደ ክልሉ የሚገቡ ሰዎች ላይ ጠንካራ ምርመራ እየተደረገ በመሆኑ ነው ግለሰቦቹ የተገኙት።

- እኚህ አራት (4) ሰዎች ወደ ትግራይ የገቡት ወደ ሚያዚያ 23 አካባቢ ነው።

- በአሁን ሰዓት የጤናቸው ሁኔታ ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ ነው።

- ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ወደለይቶ ማቆያ የማስገባቱ ስራ #ተጠናክሮ ቀጥሏል።

- ዛሬ በክልሉ ጤና ቢሮ #ዘግየት ብሎ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ መግለጫ ከሰጡ በኃላ የተረጋገጠ በመሆኑ ነው (ወደ 7:00 አካባቢ ነው ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠው) ፤ ከ8:00 በኃላ በይፋ መግለጫ ተሰጥቷል።

#TIKVAHETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ዛሬ መደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኃላ በደረሰን አዲስ መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት በተደረገ 85 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በዕለቱ ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 191 ደርሷል።

በትግራይ ክልል ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው አራቱም ኢትዮጵያውያን ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ24-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። አራቱም ታማሚዎች ከጅቡቱ የተመለሱና በመቐለ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ናቸው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 28,445
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 1,928
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 29
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 92
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አዲስ ያገገሙ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 93
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 191

(የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

በደቡብ ሱዳን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 90 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,133 ፣ ሞት 3 ፣ ያገገሙ 799

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 607 ፣ ሞት 29 ፣ ያገገሙ 197

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 928፣ ሞት 44 ፣ ያገገሙ 106

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 930 ፣ ሞት 52 ፣ ያገገሙ 92

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 191 ፣ ሞት 4 ፣ ያገገሙ 93

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 90 ፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 2

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 30

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia