TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የኮቪድ-19 ምልክቶችን በምናሳይበት ጊዜ በጤና ተቋም ህክምና የማግኘት ጥቅሞች ፦

በዶ/ር መክብብ ካሳ (COVID-19 RRT)

1.ምርመራ በማድረግ ትክክለኛ ህመማችን ምን እንደሆነ ለማወቅና ተገቢውን ህክምና ለማግኘት።

2. ምናልባት ቫይረሱ ከተገኘብን ተጨማሪ ምርመራዎች በማድረግ ያስከተለብንን ጉዳቶች(Complications)አውቆ ተጨማሪ ህክምና ለማድረግ እና የሰውነት አካላቶቻችን እንዳይጎዱ(organ damage) አንዳያስከትል በአጭሩ ለመግታት።

3. በቫይረሱ ተይዣለሁ በሚል ምክንያት ሊከሰት የሚችል የአእምሮ ጭንቀት በባለሙያዎች እገዛ ለመቀነስ፡፡

4. ቅርብ የሆነ ክትትል ስለሚደረግሎት ቶሎ ከህመምዎ ለማገገም ይረዳዎታል፡፡

5. ከጤና ተቋማትም ሆነ ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያዎች ባለመሸሽዎ ቤተሰብዎን፣ ማህበረሰቡን እንዲሁም የጤና ስርአቱ ላይ ወደፊት ሊፈጠር የሚችል ጫናን ይቀንሳሉ፡፡

- አጠራጣሪ ምልክቶች ሲያጋጥሞት ካሉበት ሆነው ይደውሉ!

- ኮቪድ-19ን በፍራቻ ሳይሆን በእውቀት አናሸንፈው!

#TIKVAH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን ለመፍጠር እንጂ በስፋት ለማምረት አቅም የላትም” - ፕሮፌሰር ጆን ቤል

ዩናይትድ ኪንግደም ኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] ለመከላከል የሚያስችል የክትባት መጠን ለማምረት አቅም እንደሌላት ነገር ግን ክትባቱን ለመፍጠር “አመቺ ቦታ” መሆኗን የአገሪቱ መንግሥት ግብረ ኃይል አባል ፕሮፌሰር ጆን ቤል ተናግረዋል።

በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማምረት ይቻል እንደሆነ የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ በሰጡት መልስ ላይ ጥያቄው መሆን ያለበት ውጤታማ ይሆናል ወይ ነው ካሉ በኋላ “እስከ ግንቦት ድረስ ሊገኝ አይችልም” ሲሉ ወቅቱ ገና መሆኑን አመልክተዋል።

"ዋናው ጉዳይ ተገቢው #ሙከራ መደረጉ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ክትባትን በተመለከተ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑ በጣሙን አስፈላጊው ነገር ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ቤል ተናግረዋል።

"ነገር ግን በግንቦት ወር አጋማሽ ወይም መጨረሻ ላይ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ማስረጃ ማግኘት #ከቻልን ሥራው የሚጀመር ይመስለኛል። ከዚያም ነሐሴ አጋማሽ ላይ ፍጻሜን ያገኛል” ሲሉ አመልክተዋል።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመገበያያ ቦታ ጥንቃቄ በማድረግ ግብይት ይፈፅሙ!

(በጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)

በግብይት ሰፍራዎች ከፍተኛ የሰው መጨናነቅ ይፈጠራል ይህ ደግሞ ለወረርሸኙ ሰርጭት በእጅጉ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
በመሆኑም በግብይት ሰፍራዎች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገባያየዩች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገበያየዩና ጥንቃቄ ባለው መልኩ ግብይት እንዲፈፀም ሰምሪት ቢሰጥ ከፍተኛ አጋዥ ይሆናሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን ተጨማሪ ሀያ ስድስት (26) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዣቸው ተሰምቷል። ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎችም ሞተዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 92 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ወደ 12 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 396 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 111 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ11 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ፤ ከጅቡቲ የመጠና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 3 - የ15 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- የኮሮና በሽታን ቅድመ መከላከል እና በሽታው አስከፊ ደረጃ ላይ ከደረሰ አቅመ ደካሞች በረሀብ እንዳይጎዱ ጎሀጽዮን ከተማ የተማሩ ልጆች 'የወረጃርሶ ልጆች በሚል የቴሌግራም ቻናል' በመሰባሰብ ለወገን የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- በደቡብ ክልል የሀላባ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ጀምዓ ለ250 አቅም ለሌላቸው ምስኪኖች ለረመዳን መያዣ የሚሆን የአስቤዛ ድጋፍ አድርገዋል። በድጋፉም የተለያዩ እህል፣ ዘይት እና የመሳሰሉትን ለምግብነት የሚውሉ ድጋፎችን አድርገዋል::

- በጅማ ከተማ ሸዋበር መስጅድ የወጣቶች ጀመዓ ለ33 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ድጋፍ አድርጓል። የወጣት ጀመዓው ከበጎ አድራጊዎችና ከአባላቱ ያሰባሰበውን አስቤዛ ጎዳና ለወደቁ እና አቅም ላነሳቸው ቤተሰቦች አድርሷል።

- በአዲስ አበባ ሳሪስ ሷሊህ መስጂድ የሚገኘው ነሲሀቱል አማ የልማትናመረዳጃ ተቋም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት የሚከሰተውን ማህበራዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ታላቁ የረመዳን ወር መቃረቡን ተከትሎ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘው ሸኪህና ህንፃ ለሱቅ እና ለቢሮ አገልግሎት ለተከራዩት በሙሉ የ2 ወር ክፍያ ነፃ ማድረጉን አሳውቆናል። በብር ቢተመን 1,711,746 ይደርሳል #P1

- የጅማ ሆሊላንድ ሆቴል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ሆቴሉን ለጅማ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል። በተጨማሪ የሆቴሉ ባለቤት 'ተሰማ ገበያ' የንግድ ህንፃ ላይ ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎች የ2 ወር ኪራይ ነፃ አድርገዋል #P & #P4

- የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በሀገራችን እዳይስፋፋ ለሚደረገው ጥረት ካፍደም ትሬዲንግ /ቃሊቲ / ከህዝብ ከመንግሥት እዲሁም ከተከራይ ደንበኞቻችን ጎን በመቆም ድርጅቱ ለ170 የህንፃው ተከራይ ደምበኞች የ2 ወር 50% ( ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ) ቅናሽ አድርጓል፤ በተጨማሪም ከህንፃው ተከራይ ደንበኞች ፣ ከድርጅቱ ሰራተኞች ጋር በመሆን አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችን ለአንድ ወር የሚሆን የምግብና የንፅህና ግባቶችን ድጋፍ ያረግን መሆኑን አሳውቆናል #P5

- ቢሾፍቱ የሚገኘው ፒራሚድ ሆቴል እና ሪዞርት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ሁለንተናዊ ጫና በመረዳት እገዛ ለሚያስፋጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ አሳውቆናል #P6

- የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በዩኒቨርስቲ አካባቢ በሚገኙ የተቸገሩ ህብረተሰብ (100)አንድ መቶ አባወራዎች )የዱቄት፤ ዘይት ፤የእጅ መታጠቢያ ሻምፖ እና በዩኒቨርስቲው የተመረተ ሳኒታይዘር እገዛ አድረገዋል ። እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሰርተዋል #P7

- ከዚህ ቀደም ካሳ ግራንድ ሞል ቅናሽ ማድረጉን አሳውቀናችሁ ነበር፤ ደብዳቤውን ልኮልናል #P2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ኮድ-2 የቤት ተሽከርካሪዎች ከዛሬ እለተ ሰኞ ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በሰሌዳ ቁጥር ሙሉና ጎዶሎነት በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡

ለጤና እና ፋርማሲ ባለሙያዎች ፣ ለሚዲያ አካላት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ስምሪት መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እየታየ የይለፍ ወረቀት እየተሰጣቸው እንደሆነ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል፡፡

በአዋጁ መሰረት የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ መንቀሳቀስ የሚችሉ ሲሆን የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ማክሰኞ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እሁድ እለት ደግሞ ሁሉም ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸዋል።

ምንጭ፡- አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትኩረትና ጥንቃቄ ለታዳጊዎች እና ወጣቶች!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

በኢትዮጲያ ኮሮና ቫይረስ በሽታ [ኮቪድ -19] የታዳጊዎች እና ወጣቶች ቁጥራቸው ከወትሮ እየጨመረ እንደሆነ የሚወጡት ሪፖርቶች ያሳያሉ።

ቀደም ሲልም የብዙኃኖች መላምት ወጣቶችን እንደማይዝ እና በእድሜ የገፉትን አረጋውያንን እንደሚያጠቃ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳተ መረጃ መሰራጨቱ ይታወቃል። ሆኖም ግን ቫይረሱ ታዳጊ ልጆች ሳይቀሩ እየተያዙ ስለሆነ ወላጆች ልጆቻቸውን ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።

ሚዲያውም ለታዳጊዎች በሚገባቸው መልኩ ማስተማር ይገባቸዋል። በዛሬው ዕለትም ከድሬደዋ ከተማ የ11 ዓመት የ15 ዓመት የ18 ዓመት ልጆች መያዛቸውን ተሰምቷል።

ስለዚህ ልጆች የወላጆች ክትትል እና ድጋፍ ከሌላቸው በቀላሉ ተጠቂ መሆናቸው ስለማይቀር ይታሰብበት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,953
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 396
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 3
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 90
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 16
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 111

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UAE

በUAE ተጨማሪ 484 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7,265 ደርሰዋል።

እንዲሁም ባልፉት 24 ሰዓት ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር አርባ ሶስት (43) ደርሷል።

76 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,329 መድረሱም ሪፖርት ተድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወላጆች ከመደበኛ ክፍያ ከ50 እስከ 75 በመቶ እንዲከፍሉ ተጠየቀ!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ትምህርት ቤቶችን በተመለከት ከ50 እስከ 75 በመቶ የሚሆን ክፍያ እንዲከፍሉ የውሳኔ ሀሳብ አቀረበ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገው በክፍያ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዲወስኑ የሚፈቅድ ሲሆን ትምህርት ቤቶችም በኤሌክትሮኒክ መንገድ ለተማሪዎች ትምህርት እንዲያገኙ ያዝዛል፡፡

ወቅታዊ ችግርን በመተሳሰብና በመተጋገዝ ማለፍ እንደሚገባ ያሳሰበው ትምህርት ሚኒስቴር የግል ትምህርት ቤቶች የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ ክፍያ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ያሳሰበ ሲሆን ሚኒስቴሩ የተማሪዎች የትምህርት ክፍያን በተመለከተ የወላጆች ኮሚቴና የትምህርት ቤቶች መሪዎች እየተመካከሩ እንዲወስኑ አመላክቷል፡፡

ወላጆች በረዥም ጊዜ እንዲከፍሉ፣ አቅማቸው ያልፈቀደ በግማሽ እንዲከፍሉና ምንም መክፈል የማይችሉም ነጻ እንዲደረጉ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

(አዲስ ልሳን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia